Jul 31, 2013

በቤተክርስትያን አስተዳደርነት ተሰግስገዉ ያሉት የትግራይ ነጻ አዉጭ ተወካዮች ምእመኑን ማገልገል አልቻሉበትም!!!

የአንድነት ከፍተኛ አመራር የህይወት ታሪክ እንዳይነበብ የቤተክርስቲያኗ አስተዳዳሪዎች የትግራይ ነጻ አዉጭ ተወካዮች ከለከሉ

Ato-Girma-w-senbetJuly 30, 2013
ፍኖተ ነፃነት
የአንድነት ፓርቲ ብሔራዊ ም/ቤት አባል የነበሩት አቶ ግርማ ወ/ሰንበት የቀብር ስነስርዓት ላይ የህይወት ታሪካቸው እንዳይነበብ የፈለገህይወት አቡነ ገ/መንፈስቅዱስ ቤ/ክ አስተዳደር ከለከለ፡፡
ዛሬ ሐምሌ 23 ቀን 2005 ዓ.ም ከቀኑ 6 ሰዓት የአንድነት ፓርቲ ስራ አስፈፃሚ አባላትና ደጋፊዎች እንዲሁም ወዳጅ ዘመድ ወዳጅ በተገኘበት የቀብር ስነስርዓታቸው ተፈፅሟል፡፡ የቀብር ስነስርዓታቸው ላይ የህይወት ታሪካቸውን የአንድነት ፓርቲ አመራሮች ለማንበብ ሲዘጋጁ የሳሪስ ፈለገ ህይወት አቡነ ገብረመንፈስ ቅዱስ ገዳም አስተዳዳሪዎች ከልክለዋል፡፡
አስተዳዳሪዎቹ የሰጡት ምክንያት አቶ ግርማ የህይወት ታሪካቸው እንዳይነበብ ተናዘዋል የሚል የሐሰት መረጃ የህይወት ታሪካቸው እንዳይነበብ ከመከልከል አልፈው የፖለቲካ ተሳትፏቸው የሌለበትን የህይወት ታሪክ እንዲነበብ አድርገዋል፡፡ በሁኔታው ቅር የተሰኙት የአንድነት ፓርቲ አመራሮች ይህንን ህገወጥ ድርጊት መሆኑን በመግለፅ የአቶ ግርማ የህይወት ታሪክ ከቀብር ስነስርዓት በኋላ በዛው በቤተክርስቲያና አውደምህረት ላይ በአንድነት ፓርቲ የብሔራዊ ምክር ቤት ሰብሳቢ አቶ ዘካሪያስ የማነብርሃን ተነቧል፡፡