Oct 20, 2013

በመከላከያ ሰራዊት ውስጥ ውጥረት አይሏል::

ሌ/ጄ ሳሞራ የኑስ በሜ/ጄ ዮሃንስ ገብረመስቀል ለመተካት የሚደረገው ሩጫ ተቃውሞ ገጥሞታል::
ከፍተኛ ጄኔራሎች ምስጢራዊ ስብሰባዎችን አብዝተዋል::የምስጢራዊ ስብሰባ ቃለ ጉባዬ የምትይዝ የሆነችው የአንድ ከፍተኛ ጄነራል ጸሃፊ ትክዳ ወይም ትገደል አልታወቀም::ለሜ/ጄ ዮሃንስ ethiopian_troops_pickupገብረመስቀል የተሰጠው የሌ/ጄ ማእረግ የታሰበው ሌ/ጄ ሳሞራን ይተካሉ ተብለው ለነበሩት ለሜ/ጄ አበባው ታደሰ የነበረ ቢሆንም በምን ምክንያት እንደተዘዋወረ አልታወቀም::
በሰሜን እዝ እና በምስራቅ እዝ የተከሰተው የሰራዊቱ ህገመንግስታዊ ጥያቄ እና የጥቅማ ጥቅም አቤቱታ በመላው ሃገሪቱ ተስፋፍቶ በከተማ እና በሌሎች የእዝ መምሪያዎችም መቀጠሉን የውስጥ አዋቂ ምንጮች ጠቁመዋል::በተለያዩ ጊዜያት እየተንከባለለ የመጣው ይህ የሰራዊቱ አቤቱታ እጅግ አደገኛ አዝማሚያ እያሳየ ሲሆን በዘረኝነት ላይ የተመሰረተ አስተዳደር እንዲወገድ እና ህገመንግስታዊ መብቶች እንዲከበሩ ጥያቄዎች ገፍተው መምጣታቸው ሲታወቅ ከፍተኛ የሕወሓት ጄኔራሎች በየቀኑ ካለማቋረጥ ምስጢራዊ ስብሰባዎችን እያደረጉ ከመሆኑም በላይ ከየእዙ የሚመጣላቸው ሪፖርት መፍታት የሚቻልበትን ጉዳይ እየተወያየኡ መሆኑ ተጠቁሟል::
ሰራዊቱ በኑሮ ውድነት እና በተቃዋሚዎች ህገመንግስታዊ መብቶች ላይ ያነሳው ጥያቄ አዛዦቹን ያስደነገጠ ከመሆኑም በላይ በአንድ ብሄር ላይ የተመሰረተ አስተዳደር እስከመቼ የሚለውም ጥያቄ መመለስ አለበት በሚል የእግር እሳት እየሆነባቸው ነው:: በቅርቡ ከስልጣን ይነሳል የሚባለው ሌ/ጄ ሳሞራ የኑስን በሜ/ጄ ዮሃንስ ገብረመስቀል ለመተካት የሚደረገውን ጥረት የብኣዴን ታጋይ መኮንኖች የተቃወሙት ሲሆን እኛም ከማንም ያላነሰ የታገልን ስለሆነ ለቦታው ብቁ የሆነ ሰው ብኣዴን እያለው ለምን እንዲህ ይደረጋል የሚል ጥያቄ አንስተዋል::
ከፓርቲ አጣብቂኝ ያልተላቀቀው የመከላከያ ሰራዊቱ የበላይ አመራር ህገመንግስታዊ መዋቅር እንዲይዝ ለማድረግ ምንም አይነት ስራ አለመሰራቱ በሰራዊቱ አዳዲስ መኮንኖች ዘንድ አቤቱታ ቢያስነሳም ጄኔራሎቹ የሚያደርጉት ምስጢራዊ ስብሰባ እንዴት መፍታት ሳይሆን ማክሸፍ እንደሚቻላቸው እየመከሩ ሲሆን አዳዲስ ወታደራዊ ደህንነቶችን በየእዙ አስርጎ በማስገባት እንዲሁም የሰራዊቱን አቤቱታ ያስተባብራሉ የሚባሉትን በስራ ምክንያት በየማእዘኑ በመበተን ለመስራት የታቀደ ሲሆን የአበታተኑን ሁኔታ በማስጠናት ላይ መሆናቸው ታውቋል:: በተጨማሪ የሚደርስባቸውን ጥቃት ለመከላከል ይረዳቸው ዘንድ ኮማንዶዎችን እና ንቁ የደህንነት ጠባቂዎችን ለራሳቸው እና ለቤተሰቦቻቸው ለመመደብ ተነጋግረዋል::
መከላከያ ሚኒስቴር ውስጥ ምዽር ጦር መምሪያ እንዲሁም ደብረዘይት እና አስፈላጊም ሲሆን በመኖሪአ ቤቶቻቸው የሚያደርጉትን ስብሰባ ቃለጉባዬ የምትይዘው የአንድ ጄኔራል ጸሃፊ ከድታ ይሁን ተገድላ ሳይታወቅ ካለፈው ሳምንት ጀምራ በስራ ገበታዋ ላይ ያልተገኘች እና የት እንዳለች የማይታወቅ ሲሆን ስልኳም መዘጋቱን ምንጮቹ አያይዘው ጠቁመዋል::
ምንሊክ ሳልሳዊ

Oct 17, 2013

የትግራይ ምሁራን ይህንን እያያችሁና እየታዘባችሁ ዝም ማለታቸሁ ለምን ይሆን?

Posted on  

አማራና ኢትዮጵያዊነት፤ በጠላትም በወገንም እስከ ሞት!
በገ/ክርስቶስ ዓባይ(አቶ በገ/ክርስቶስ ዓባይ ታዋቂ የትግራይ ተወላጅ ናቸው!)
የአማራው ሕዝብ ባህልና አስተዳደግ መተኪያ ከሌላት ከአገሩ ከኢትዮጵያና፤ ጥላና ከለላ በመሆን እነርሱን ለመታደግ ሕወቱን ሳይሳሳ ሲገብርላቸው ለቆዮት ኢትዮጵያውያን ወገኖቹ ፤ ከፍተኛ ክብርና ፍቅር እንዲያድርበት ሆኖ በዓለማዊውም ሆነ በመንፈሣዊው አስተሳሰብ ተቃኝቶ ያደገ፤ የዳበረና፤ በጠነከረ አለት ላይ እንደታነጸ ግንብ በቀላሉ የማይሸረሸር መሆኑን በተግባር እያረጋገጠ ይገኛል።
ለመሆኑ ወያኔ አማራን ለምን ጠላው?
ወያኔ ከምንወደውና ከምናፈቅረው ከትግራይ ወገናችን በመውጣቱ በጣም ያሳዝናል። ግን ደግሞ “ቆማጣን ቆማጣ ካላሉት ገብቶ ይፈተፍታል” እንደሚባለው ወያኔን እራሡ ባወጣው ስም ወያኔ፤ ወይም ደግሞ የበግ ለምድ ለብሦ በበጎች መካከል እንደተገኘ ቀበሮ ኢሕአዴግ፤ ብለን መጥራቱ የክብር ካባ ማልበስ ስለሚሆን በሚመጥነው ስም መጥራቱ ተገቢ ይመስለኛል። ይኸውም የከሃዲ ባንዳ ዘር ስብስብ ለመሆኑ አንድና ሁለት የሌለው እውነት ስለሆነ ደቂቀ ባንዳ መባል አለበት።
ከአሁን ቀደምም ቢሆን ካሣ ምርጫ ወይም ሕዝብ ባወጣላቸው ስም በዝብዝ ካሣ እኰ ለጠላት ባማበር አፄ ቴዎድሮስን በመክዳት፤ የንግሊዙን ጦር አዝማች ጄኔራል ናፒርን እየመሩ እስከመቅደላ ድረስ ያደረሱ መሆናቸው ይታወቃል። አማራው ይህንን ታሪክ በሚገባ ያውቃል፤ ይሁን እንጂ በጎሣ ግጭት የማታ ማታ የምትጎዳው አገራችን ኢትዮጵያ ስለሆነች እንዲህ ያለውን አስነዋሪ የክህደት ታሪክ በመተው ደግ ደጉን ብቻ ለልጆቹ እያስተማረ ይገኛል።
ምክንያቱም እንደ ራሥ አሉላ አባ ነጋና አው አሎም ያሉ ታማኝ ኢትዮጵያውያንም ስላሉ “ከተልባ ጋር የተገኘህ ሰሊጥ አብረህ ተወቀጥ” እንዳይሆን የጅምላ ፍረጃውን አማራው ስለማይቀበል ሁሉንም ለአገር አንድነት በሚጠቅምና ክብርን በማይነካ መልኩ በጥንቃቄ መዝግቦ ይዞታል።
እንደሚታወቀው አማራው ቀደም ባሉት መንግሥታትም ቢሆን የተመቸው ዜጋ አልነበረም። የውጭ ጠላት በመጣ ቁጥር ክተት ሥራዊት እየተባለ በራሱ ስንቅና ትጥቅ በባዶ እግሩ በመዝመት የአገሩን ዳር ድንበርና ወገኖቹን ከውጭ ወራሪ ጠላትና ከባርያ ፈንጋይ የዓረብ ነጋዴዎች ሲከላከልና ሲጠብቅ መኖሩን ታሪክ ምስክር ነው።
አማራ ለአገሩ መንግሥትም ሆነ ለወገኑ ታማኝ፤ ከመሆኑ የተነሳ ለውጭ ጠላት ፈጽሞ የማይመችና የማይታለል በመሆኑ ይኸው አገራችን ኢትዮጵያ ዳር ድንበሯ ሳይደፈር አሁን ላለው ትውልድ እንድትደርስ ከፍተኛውን አስተዋጽዖ ያደረገ ኩሩና ጀግና ሕዝብ መሆኑን አይደለም ኢትዮጵያዊ፤ የዓለም ሕዝብ ያውቀዋል።
አሁን አጭበርብሮ በሥልጣን ላይ የሚገኘው ከሐዲ የባንዳ ዘር ስብስብ ጀግና ነኝ ሲል አላፈረም። ሐቁ ግን አሁንም ቢሆን የባንዳው ዘር የአገሪቱን መሣሪያ እንኳ ታጥቆ እያለ ቢሆን አማራው የፈራ መስሎት ከሆነ የባንዳው ዘርና ፍርፋሪ ለቃሚዎቹ ውሾች ተሳስተዋል እላለሁ። እርግጥ ከአሁንም በፊትም ሆነ በአሁኑ ሰዓት አማራው ሦስትን ነገር ይፈራል።
አንደኛውና የመጀመሪያው ለብዙ ምዕተ ዓመታት አያት ቅድመ አያቶቹ ያቆዩአት ኢትዮጵያ በጠላት ሤራ የተነሣ እንዳትበታተን ይጠነቀቃል።
ሁለተኛው ደግሞ የሚወደውንና የሚያከብረውን የትግራይ ሕዝብ ላለማስቀየም ከዛሬ ነገ ይሻላል በማለት “ላም እሣት ወለደች እንዳትልሰው ፈጃት እንዳትተወው ልጇ ሆነባት “ የተባለው ዓይነት ሆኖበት እንጂ ፈርቶ ወይም ኃይል የሌለው ሆኖ አይደለም።
ሦስተኛው ደግሞ አማራ በፈሪሃ እግዚአብሔርነቱም ይታወቃል። የእናቱ ልጅ ወንድሙ እንኳ ቢሆን ከሌላ ሰው ጋር ተጣልቶ ቢያየው ያስታርቅ እንደሆን እንጂ ለወንድሙ አድልቶ ሌላውን ሰው ለመጉዳት አይደፍርም። ምክንያቱም ሰማይና ምድርን የፈጠረ አምላክን ስለሚፈራ። በዚህም ለጊዜው እየተጎዳ ቢገኝም ነገ ግን ምላሹን ከሚያመልከው ፈጣሪ እንደሚያገኘው አያጠራጥርም።
የከሃዲ ደቂቀ ባንዳዎች ዋና ጠርናፊ ሟቹ መለስ ዜናዊ ልክ የዛሬ ዓመት ገደማ የፋሲካ በዓል አካባቢ፤ በጉራ ፋርዳ ይኖሩ የነበሩትን አማርኛ ቋንቋ ተናጋሪ ኢትዮጵያውያንን እንዲፈናቀሉ ሲያደርጉ ለራሳቸው ግን አንድ ሺህ ዓመት የሚኖሩ ይመስሉ ነበር።
ፓርላማ ላይ በትዕቢት ተወጥረው ጠረጴዛ እየደበደቡ ምድር አልበቃቸው ብሎ እንደነበር አይዘነጋም ።ዛሬ ግን በሕይወት የሉም ሁለት ሜትር በማትሞላ ጠባብ ጉድጓድ ውስጥ ተወስነው ቀርተዋል። የተከሉት መርዝ ግን አሁንም ገና አልጠወለገም።
ውቃቢያቸውን የተላበሱት መብራህቱ ገ/ሕይወት (በረከት ስምዖን) ከመጋረጃ በስተጀርባ በመሆን የሙት መንፈስ እየጠሩ፤ በአሻንጉሊሊታቸው ኃ/ማርያም ደሣለኝ አማካኝነት እኩይ ተግባራቸውን እያስፈጸሙ ይገኛሉ።
እዚህ ላይ መነሣት የሚገባው ዓቢይ ጉዳይ አለ፤ ይኸውም አቶ በረከት የአማራው ድርጅት የብአዴን ድርጅት፤ የወያኔ የበላይ ክንፍ ኃላፊ መሆናቸው ይነገራል። ነገር ግን ቆሜልሃለሁ የሚሉት የአማራ ሕዝብ በገዛ ሀገሩ እንዲህ በሕገወጥ መልክ ሀብትና ንብረቱን እየተቀማ ሲሳደድና ሲንገላታ፤ ሌላው ቢቀር ከሞራል አኳያ እንኳ ህሊናቸውን አይሰቀጥጣቸውም? የእርሳቸው ልጆችስ? የአሰፉ ልጆች ስለሆኑ ምንም አይድል? “የማትረባ ፍየል ዘጠኝ ትወልዳለች ልጆቿም ያልቃሉ እሷም ትሞታለች” እንደተባለው ይሆናል ብለው ይሆን? ግምታቸውን እውን ያድርግላቸው።
ወያኔ የውጭ ዜጋ ቢሆን ኖሮ እሱን አያድርገኝ፤ በየደረሰበት ዋጋው እየተሰጠው በወጣበት ይቀር ነበር እንጂ፤ እንዲህ እነሱ እንደፈለጉ ሲፏልሉ፤ አማራው አማርኛ ቋንቋ በመናገሩ ብቻ በሰላም ከየሚኖርበት፤ በድካሙ ያፈራውን ህብትና ንብረቱን በመንግሥት አካላት እየተቀማ ሲባረር ዝም አይልም ነበር። አዎ! መንግሥት ይለወጣል፤ ፖሊሲም ይቀየራል፤ ታዲያ ለሚያልፍ ቀን ሲል የሚወዳትን አገርና ወገኑን እኔ ከሞትኩ ሠርዶ አይብቀል አንዳሉት የባንዳ ልጆች አስተሳሰብ ቢሆንማ ኖሮ ያሳያቸው ነበር። ሡሪውም፤ ጀግንነቱም ወኔውም በደም ሥር ውስጥ ያለ መሆኑን ባንዶች የተገነዘቡት አይመስልም።
ገና ከመጀመሪያው ወያኔ ወገን ባይሆንና ወይም ተንኮሉ በግልጽ ቢታወቅ ኖሮ እንኳን ኢትዮጵያን መቆጣጠር ይቅርና ተከዜን መሻገር አይችልም ነበር። አሁንም ጊዜ ይለወጣል የሰውም ልብ እንዲሁ ይቀየራል ያን ጊዜ ወዮ!
ከሐዲ የባንዳዎች ስብስብና ፍርፋሪ ለቃሚ ውሾቻቸው፤ አማራውን ባትነካኩት ጥሩ ነው ሌላው ቀርቶ ለራሣችሁና ለልጆቻችሁ ስትሉ ባታሠቃዩት መልካም ነው። ያለበልዚያ ይህ ሕዝብ መሣሪያ የለውም ብላችሁ እንደዜጋ ሳይሆን እንደእንስሣ የምታዩት ከሆነ መሣሪያው እኮ ጠመንጃና ጥይት ብቻ አይደለም። ሐቅን ለያዘ ሰው ልብ ብቻ በቂ ነው። መሥሪያውማ ዙሪያ ገባው ሁሉ መሣሪያ መሆኑን ልትገነዘቡ ይገባል።
የአማራው ሕዝብ ግን ለአገሩና ለወገኑ ሲል፤ ንብረቱን እየተቀማ፤ ለረጅም ጊዜ ከኖረበት ቀዬ እንዲፈናቀል ሲደረግ አንገቱን ደፍቶ ለአገርና ለወገን ሲል መከራውን በትዕግሥት እየተቀበለ ይገኛል።
ምን ዓይነት አርቆ አስተዋይነት ነው? ምን ዓይነትስ ሆደ ሠፊነት ነው? ምን ዓይነት ታማኝነት ነው ?እጅግ በጣም ይገርማል! ይደንቃል።
በተለይ የትግራይ ምሁራን ይህንን እያያችሁና እየታዘባችሁ ዝም ማለታቸሁ ለምን ይሆን?
የአማራው መንገላታት ፤መሰደድ፤ በፍርድ መጓደል ከሚኖርበት ቅየው መፈናቀል፤ እውነት እናንተን ጤናና ሰላም ይሰጣችኋል? በእንደዚህ ያለ ወሳኝ ወቅት ላይ፤ እንኳን ወገን ለወገኑ ለባዕድም ቢሆን በሰብዓዊነት እንኳ ድምጽ ሊሆንለት በተገባ ነበር።
ምናልባት በጥቅም ተይዛችሁ እንኳ ቢሆን ሌላው ቀርቶ የዓለም አቀፍ መብቶች እንዲከበሩላቸው ብታደርጉ፤ ለራሳችሁና ለልጆቻችሁ እንዳደረጋችሁ ልትቆጥሩት በተገባ ነበር። ያለበለዚያማ ፈጽሞ ለማይቀረው ለውጥ ተዘጋጁ። የምትሠሩትን የምታውቁ አይደላችሁም።
ዛሬ በአማራው ላይ የምትፈጽሙት ሤራ ነገ እኰ ወደናንተም እንደሚቀሰር ረሳችሁት እንዴ? እንደዚህ ያለውን ተግባር የምትደግፉ ከሆነ ትግሬም ከተከዜ ማዶ እንጂ ወንዙን መሻገር የለበትም መባሉን ዘንግታችሁት ከሆነ እኔ ላስታውሳችሁ።
ወንድነቱንና ጀግንነቱን እንኳ ለአማራው ማንም ሊያስተምረው አይችልም። የአማራውን ትዕግስት እንደ ፍርሃት ቆጥራችሁ ከሆነም ትሳስታችኋል። እንኳን አሁን ቀደም ሲል ኰሎሎኔል መንግሥቱ ኃይለ ማርያም እንኳ በአንድ ወቅት ወያኔን አስመልክቶ ሲናገሩ “ ድንጋይ ቢወድቅብን ይሰብረናል፤ ብንወድቅበትም ይሰብረናል” ማለታቸው ይታወሳል። ምሁራን ናችሁና የዚህን ፈሊጣዊ አባባል ትርጉም ታጡታላችሁ የሚል ጥርጥር ባይኖረኝም፤ ገድለንም የምንጎዳው እኛ ሞተንም የምንጎዳው እኛ ማለታቸው ነበር። በዚያም ሆነ በዚህ የወገን የእርስ በእርስ ግጭት ዞሮ ዞሮ የሚጎዳው የአገራችንን ዕድገትና ልማት፤ እንዲሁም ሕዝባችንን በቀላሉ ሊጠገን ከማይችል ማኅበራዊና ሥነ ልቦናዊ ቀውስ ውስጥ መክተት ይሆናል ማለታቸው ነበር።
የአማራውም ሕዝብ እንዲህ የሚሠቃየውና እንደከብት አንገቱን በስለት የሚታረደው ለአገሩ አንድነትና ኅልውና ስለሚቆረቆርና፤ ችግሩ የጥርስ ደም ሆኖበት፤ ይህ የስቃይ ዘመን ያጥር ዘንድ ፈጣሪውን እየለመነ ይገኛል። የፖለቲካ ሀሁ የማያውቁ፤ ኢትዮጵያዊ መሆናቸውን እንጂ አማርኛ ቋንቋ ከመናገር ውጭ አማራ መሆናቸውን እንኳ የማያውቁ ንፁሕ ኢትዮጵያውያን በወራሪ ደቂቀ ባንዶች ስብስብ ቀጭን ትዕዛዝ ሲንገላቱና ሲሠቃዩ እያያችሁ ዓይኔን ግንባር ያድርገው፤ የዝሆን ጆሮ ይስጠኝ የምትሉ ከሆነ ነገ ከተጠያቂነት በፍጹም አታመልጡም።
ወዮ የትግሬ ምሁራን የሆናችሁ ሁሉ፤ አሁን ያለው የከሐዲ ባንዳ ስብስብ፤ ዘራፊ ሥርዓት በዚሁ ይቀጥላል ብላችሁ የምታስቡ ከሆነ ተሳስታችኋል። ሐቁን መረዳት ተስኗችሁ ከሆነ እንኳን እየዘረፉና እየቀሙ መኖር ይቅርና በወያኔ ሥርዓት እንደ እንጉዳይ የፈሉ ሚሊየነሮችና ባለቪላ ቱጃሮች፤ እንዲሁም ያለፉበትንና ያልደከሙበትን ውድ መኪና የሚያሽከረክሩ ሁሉ በአገር ውስጥ ብቻ ሳይሆን በውጭ አገር ሳይቀር በተለያዬ ዘመድና ጓደኛ ስም እንኳ የተቀመጠ ያለአግባብ ከሕዝብ የተዘረፈ ገንዘብ ሁሉ እንደሚመለስ አትጠራጠሩ። እናንተም የሚጠብቃቸሁ ፍትህ ስለሚሆን እንደየተግባራችሁ የየሥራችሁን ማግኘታችሁ አይቀርም። ስለዚህ ከአሁኑ ወደ ኅሊናችሁ ተመልሳችሁ ከተገፋው ሕዝብ ጎን ልትቆሙ ይገባል።

Sep 25, 2013

A Journalist kidnapped, Threatened, and Beaten by Intelligence and Security Agents in Ethiopia



By Betre Yacob.

Bisrat Woldemichael The Ethiopian journalist Bisrat Woldemichael was kidnapped, threatened, humiliated, and beaten by the Ethiopian intelligence and security agents on 28 August, 2013. He has reported this incident today to journalists.
Bisrat reported that the dreadful incident took place at Gotera, a place in the capital Addis Ababa as he was walking home from work. He said he was victimized for exercising his right to free expression in conjunction with the related right to press freedom.
Bisrat Woldemichael works for a magazine, Ebony, as Editor in Chief, and writes political articles on different Ethiopian private press outlets. He also blogs at  www.addismedia.wordpress.com andwww.ethiopiahot.wordpress.com. The journalist is known for his outspoken articles focused on the poor governance and pervasive human right violation, which are turning the oldest East African nation, Ethiopia, into a hell.
Violence against journalists is a common practice in Ethiopia, a country generally regarded as one of the most dangerous places to be a journalist. According to Amnesty International, during the past three years only, over 100 prominent journalists were brutally prosecuted on fabricated charges, and too many others were also subjected to harassment, intimidation, and other violence.
“It was 3:30 AM in the evening, and I was returning home from my workplace. 4 people came to me and said: ‘we need to ask you some questions. Two of them were dressed in black and their faces were almost covered with their caps”, Bisrat said, while narrating his ordeal to journalists.
“I first didn’t understand what was going on. I realized that I was in danger just when one of them put a knife on my stomach”, he noted.  “When I saw the knife, I asked them: ‘Who are you? What do you need? But none of them gave me an answer, instead they warned me just to keep walking forward,” he explained.
“I didn’t do anything but followed them, because I was surrounded, and the guy also clearly told me he would stab me with the knife if I tried to challenge them. In addition, one of them had a gun”, Bisrat said.
From there Bisrat was taken to a place far away from the main road. The place he was taken to was quite dark and out of public sight.
“As soon as we reached there they told me they were disappointed at my articles I had recently written, particularly at the one which dealt about the wealth of the late Prime Minister Meles Zenawi ”, Bisrat said.
“They said: ‘Who are you to count the wealth of Meles Zenawi? Who are you to write about his family’s wealth?  You have passed the red line!’ ” he explained.
The journalist said that the kidnappers violently interrogated him at length, for almost one hour, and threatened him to stop writing.
 “They said: ‘here we are giving you a last warning. If you write any more for any media (or if you keep blogging), the consequence will be worse for you. If you need your life, stop wiring. Remember!  It is a last warning’ ”, Bisrat explained.
The journalist said that this was not the end of the drama but the beginning. “They also insulted and humiliated me, and finally began to beat me.
Right after the incident, Bisrat was able to go to a nearby police station, to report the case. But, according to him, having heard the case, the police officers simply gave him an appointment for the coming mooring and let him go. Bisrat said that it took him several days to get the case registered.
“They are Watching Me”
Bisrat Woldemichael Bisrat said since the day he experienced the violence he has been under surveillance. “Few days ago, I saw them following me behind”, he explained adding “I know they are watching me very closely.”
But, in the face of such grave threats, Bisrat, a journalist who is committed to freedom of speech, has continued doing his job with courage. He continues writing about the political crisis, poor governance, and human right violation worsening in Ethiopia.
“I don’t have a choice. I am a journalist. There is nothing to do except writing what I see, hear, and feel.” Bisrat explained. He again and again made clear that no threats and tortures would make him stop writing
The paper Tigers
Article 19 of the Universal Declaration of Human Rights, guarantees the right to freedom of expression saying that: “Everyone has the right to freedom of opinion and expression; this right includes freedom to hold opinions without interference and to seek, receive and impart information and ideas through any media regardless of frontiers. Likewise, the International Covenant on Civil and Political Rights (ICCPR), which Ethiopia ratified in 1993, and the African Charter on Human and Peoples’ Rights guarantee the right in a very clear way. They even impose formal legal obligations on state parties to insure this fundamental right is protected.
But, sadly, even in the presence of all these legal documents, Enjoyment of press freedom and freedom of expression still continue to be a far cry for Ethiopian journalists and bloggers as they experience violence while doing their job. They are harassed, threatened, humiliated, and arbitrary jailed.

Sep 24, 2013

The Fake ‘Amharas’ – To milk “Lamie Bora – ላሜ ቦራ”

September 22, 2013

Wondimu Mekonnen, London
Recently, someone one visited Britain from home on business tour and entertained us with an amusing story of Lamie Bora, the fictional character in the children’s stoy. Woyyane officials call us, Diaspora Lamie Bora (ላሜ ቦራ)።Are we really that “milka-cow?”Woyane officials call us, Diaspora Lamie Bora
I am sure everyone who went to school in Ethiopia at my age knows the children story of Lamie Bora. Lamie Bora is a very touching story. The story goes like this. A dying mother entrusts her two children unto a cow, called “Lamie Bora.”Just before she died, she sung to the cow: “Lamie Bora! Lamie Bora! I leave my children’s wellbeing to you” (ላሜ ቦራ! ላሜ ቦራ! የልጆቼን ነገር አደራ). After a while the children’s father remarried another woman, whoturned out to be acruel stepmother. Every time she denied them food, the two children would go to Lamie Bora and sing “Lame bora! Lamie Bora! Don’t forget Mammie’s plea (ላሜ ቦራ! ላሜ ቦራ የእማምዬን አደራ!)Then Lamie bora would let the children suckle directly from the tits on her breast. Lamie Bora is supposed never to stop giving milk all year round.
This story is now retold among Woyyane agents referring to Diaspora as Lamie Bora, for the simple reason that whenever Woyyane runs out foreign currency it runs to the Diaspora – a cow full of milk all the year round. Every year, Woyyane officials fly to London, Washington and other major cities of the world, where exiled Ethiopians live in abundance with the hope of harvesting cash from the unsuspecting Diaspora – the cash cow. Their embassies have been instructed to implement the design for the purpose using various tactics. One such means is the Millennium Dum, (sorry I meant Dam), development associations, “Investors” and the recent 40/60 formula to own a house in Ethiopia! Recently, one of our church clergy renegades went for it, but fell out with the guys doing the business on some procedural grounds.
A good way of milking the milka-cow is to organise the Lamie Bora’s along their ethnic blood lines – such as the ‘Amhara’ Development Association, the Guragea Development Association, etc. This time, it is the ‘Amhara’ Lamie Bora’s turn to be milked in Queens capital city. The fake ‘Amhara’s (ቁጩ አማሮች)[1]are used as tools for the purpose. You rarely find any ‘Amhara’ among their leaders. Their organisation, The ‘Amhara’ National Democratic Movement (ANDM) was found in November 1980 in Tigray, at a place known as Tekrarwuha. The mission of ANDM – It’s all about shutting down the ‘Amhara’ threat. ANDM was the favoured puppet organization. They leadership was made up of various ethnic groups, but ‘Amhara’! They were then and are now actually predominantly Woyyanes disguised as Amaras. They are all fake-fake-fake to the root third rated ‘Amharas’. Take for Example, Bereket Simon. He is a Shabbo-banda whose mother and father hail from Eritrea.  Hilawi Yosef is either a Tigre or a Shabo-Banda like Bereket, but has no drop of ‘Amhara’ blood in him. Tefera Walwa is a Gimira. Well at least Gimira sounds like ‘Amhara’. The only ‘Amhara’ thing in Addisu Legesse is his name. He is an Oromo from Harar. Did you know who Tamirat Layne was before he became Tamirat Layne? His real name was Getachew Mamo Waqkenie. Go and figure out that. Tadesse Tinqishu, regardless of his beautiful name, is a Tigre? Is Kassu Ilalla sound ‘Amhara’? Give me a break! All the ethnic based organisations, except the TPLF were formed using the same formula. Their extensions in the Diaspora are called “development associations” followed by the appropriate suffixes. The “associations” are kind of support groups for the “forged” ethnic groups.
Coming back to the Lamie Bora story, the fake ‘Amharas’ in London are organised under “‘Amhara’ Development Association – UK”. Do you want to see, who they are exactly, from their 2011 fund raising event? http://www.youtube.com/watch?v=8fmeHCLPgpU. Those of you who reside in London should be able to tell who is who in that video. The majority are Tigres, followed by Jamaicans and then some hod-aders like Yalew Kebede. Gondares have yet to tell us about the ethnic background of Yalew Kebede. Could he be another fake ‘Amhara’ like Bereket from Gondar?
This year, Lamie Bora – Diaspora is planned to be milked on 28 September 2013 at the Ethiopian Embassy. The entrance fee is free. Why not invite ourselves to the abundant food and drink? Oh, one more thing. Where are they advertising their event? Not of course mainstream websites, but Tigrai Online. This is yet another proof that this is another Woyyane organisation camouflaged as ‘Amhara’s! See for yourself.http://www.tigraionline.com/’Amhara’-ada-event-uk.html
 The forged Amaras are disgusting who trade in the name of ‘Amhara’ to milk the Diaspora, to fill in the never quenching thirst of Woyyane for hard currency. It looks like its recent attempt to milk Lamie Bora did not work at fund raising events for the millennium dam, so they are punishing their Ambassadors for failing to trap Lamie Bora – the milka-cow. Many lost their jobs this week. May be the 40/60 formula for owning a house in Addis might attract some fools to sacrifice their hard earned currency. The idea is the Diaspora would pay 40% down payment in hard currency. The 60% would be lent in birr by the TPLF. Don’t you even think of owning the land on which the house is going to be built. It belongs to the TPLF. Whenever the TPLF wants the land, it will ask you to carry away your bricks and mortars as the land is needed by the landlord to be sold to foreign investors!
The Diaspora has to cease being treated like Lamie Bora. It has to distance itself from these corrupt and human rights abusers. Whenever one needs to do business with the TPLF, it is that person’s morale obligation to remember prisoners like Reyyot Alemu, Andualem Arage, Eskinder Nega, Nathnael Mekonen, Kinfemichael Debebe, Yohannes Terefe, Shambel Yeshewas Yehunealem and Andualem Ayalew, tens of thousands of members of the Oromo ethnic group and the illegally imprisoned Muslim leaders.
The Woyyane is a No. 1 corrupt regime in Africa. One would better avoid dealing with Woyyane at all levels unless that person wants to be milked dry. One can invest his/her money elsewhere, where a good return is expected without risk of being fleeced. The least, if you don’t want to invest, just drink your own milk rather than giving it to the Woyyane. Even some cows have become smarter and drinking their own milk rather than giving it away. Don’t you believe me? Watch the next clip!
Good for you, cow! Well done! You are much better than some Ethiopians that are regularly milked dry by the Woyyane!

ግንቦት ሰባት የኤርትራ ድጋፍ እንዳለው አስታወቀ -ቪኦኤ

v o A/  ፖለቲካ

በ ሰሎሞን አባተ – ቪኦኤ

“የወያኔን መንግሥት ከሥልጣን ማስወገድ ዋነኛው አጀንዳዬ ነው” የሚለው ግንቦት 7 የፍትሕ፣ የነፃነትና የዴሞክራሲ በኤርትራ ምድር እንደሚንቀሣቀስና ከኤርትራ መንግሥትም እገዛ እንደሚያገኝ አስታወቀ፡፡
ድርጅቱ ዋሽንግተን ዲሲና በአካባቢው ለሚገኙ ኢትዮጵያዊያን ትናንት ባዘጋጀው የውይይት መድረክ ላይ እያከናወንኩ ነው ስለሚላቸው እንቅስቃሴዎች መሪዎቹ ማብራሪያና ለቀረቡላቸው ጥያቄዎችም መልስ ሰጥተዋል፡፡
ዝርዝር ዘገባውን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡

ከለውጡ በኋላስ? (ተመስገን ደሳለኝ)


 ኢህአዴግ ወደ መጨረሻው ምዕራፍ (በውስጥም በውጪም ተግዳሮቶች) መገፋቱን በሚያመላክቱ የፖለቲካ አጀንዳዎች ላይ የሚያጠነጥን አንድ ፅሁፍ (‹የአብዮቱ የምፅዓት ቀን ምልክቶች›› በሚል ርዕስ) አቅርቤ እንደነበር ይታወሳል፤ ይዘቱም በመጪዎቹ ወራት ወይም ዓመት ስርዓቱ ‹ምርጫ› አሊያም ‹ህዝባዊ›  እምቢተኝነት ከሚያመጣው ‹ማዕበል› (እንደበረከት ስምዖን አገላለፅ ‹ናዳን በሚገታ ሩጫ›) የማምለጥ ዕድሉ የጠበበ መሆኑን የሚያመላክት ነው፤ ይሁንና አንድ አብዮት ታላቅ (ውጤታማ) ሊባል የሚችለው አምባገነን ስርዓትን በመቀየሩ ብቻ ስላልሆነ (ሥር-ነቀል ለውጥ የሚፈጥር አብዮት ዋጋ የሚኖረው የዲሞክራሲ ተቋማትን መሰረት መጣል ሲችል ነውና) በቀጣይ መፃኢ ዕድሉ ላይ መነጋገሩ አስፈላጊ ነው ብዬ አስባለሁ፡፡
በዚህ ፅሁፍህ ተጠየቅም ‹ከስርዓቱ ለውጥ በኋላ፣ ማን ነው አማራጩ?› የሚለው ጥያቄ ትኩረት ይደረግበት ዘንድ አመላክታለሁ፡፡ ምክንያቱም በጠለፉ መንገድ ከቀሩ አብዮቶች ታሪክ ተምረን፣ ‹መጥነን ካልደቆስን› የሚከፈለውን ዋጋ በብላሽ የሚያስቀር አሳዛኝ ሁናቴ ሊፈጠር ይችላልና (ቭላድሚር ኤሊች ሌኒን ‹‹አብዮት፣ ለአብዮት ብቻ ሲባል መካሄድ የለበትም›› እንዲል፣ ከኢህአዴግ መገላገሉ መልካም ቢሆንም፣ የአገላጋዩን ማቀፊያ ከወዲሁ መምረጡ ወይም የምንጠይቀውን ማወቁ ብልህነት ነው)
አማራጩ ተወልዷልን? ከኢህአዴግ በኋላ የሚተካው አማራጭ ተዘጋጅቷል? …ይህንን ቀዳዳ አስቀድሞ መድፈኑን አስቸኳይ ያደረገው፣ ለውጡ የሚመጣበት መንገድ ‹ከህዝባዊ እምቢተኝነት› ይሆናል የሚለው ቅደመ-ግምት ነው፡፡ ከታዓማኒና በዕኩል አሳታፊ ምርጫ የሚነሳ ሽግግር (‹ሕዝብ የሚፈልገውን ያውቃልና ውሳኔው መከበር አለበት› ከሚለው የዲሞክራሲ ፅንሰ-ሃሳብ በመነሳት) አሳሳቢነቱ ከአደባባይ ተቃውሞ የሚመነጨውን ያህል አይደለም፤ ስለዚህም ከስጋት ነፃ መሆን የሚቻለው በሰላማዊ መንገድ ለመታገል መሰረታቸውን ሀገር ቤት አድርገው በህግ የተመዘገቡ የፖለቲካ ድርጅቶች የቤት ስራቸውን ሰርተው ዝግጁ ሆነው ሲጠብቁ ብቻ ነው፡፡ ይህ ግን የድርጅቶቹን ቁጥር ከሰማኒያ በላይ ከማሻቀብ ያለፈ አስተዋፅኦ የሌላቸውን አሰስ-ገሰስ ‹ፓርቲ›ዎች በሙሉ እንደሚመለከት ተደርጎ መወሰድ የለበትም፡፡ ነፍስ ይማርና በ‹‹ልዕልና ጋዜጣ›› እልፍ አእላፍ ችግሮቹን ማረም ከቻለ መድረክ ተስፋ ሊጣልበት ይችላል ብዬ እንደማስብ መፃፌን አስታውሳለሁ፡፡ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ደግሞ የመድረክ አሰላለፍ ሊቀየር በማጋደሉ (ከአንድነት ጋ አብሮ መቀጠሉ ማጠራጠሩ) እና ሰማያዊ ፓርቲ አዎንታዊ እንቅስቃሴ ከማድረጉ አኳያ ተፎካካሪ ሊሆን የሚችልበት ዕድል በመፍጠሩ፣ በአጀንዳው ላይ ማካትቱን ተገቢ ሆኖ አግኝቸዋለሁ፡፡ ይሁንና ሌሎች ፓርቲዎችን እዚህ ጋ ያላነሳሁበት፣ ከላይ ከጠቀስኩት በተጨማሪ ሶስት ምክንያቶች አሉኝ፤ ቅቡልነትን ማጣት፣ እንቅስቃሴ አልባ መሆን እና በገዥው ፓርቲ ስፖንሰርነት መተንፈስ የሚሉ፡፡ መድረክየስድስት ፓርቲዎች ስብስብ ነው፤ በምርጫ ሁለት ሺህ ሁለት (ምንም እንኳ ከአንድ የምክር ቤት ወንበር በላይ ባይሳካለትም) ከሁሉም ተቀናቃኞች በላይ ጐልቶ መውጣት ችሎ እንደነበር ይታወሳል፡፡ የአምስተኛውን ዙር ሀገር አቀፍ ምርጫም ተስፋ አድርጎ ለመጠበቁ ማሳያዎቹ፡- አንድም ስብስቡ ዛሬም ህላዊ መሆኑ፣ ሁለትም ለበርካታ አባላቱና ደጋፊዎቹ ወደ ‹ግንባር ተሻጋገሩ› ግፊት ምላሽ መስጠት መቻሉ ነው፡፡ በምስረታው ዋዜማና ማግስት ብዙ የተነገረለት መድረክ እርስ በእርሱ (በአንድ ጠርዝ-የአንድነት አመራሮች፤ በሌላኛው-ኦፌኮ እና ኢሶዴፓ) የፈጠረው ውዝግብ በዙሪያው ለተሰለፉ አባላትና ደጋፊዎች ተስፋ አስቆራጭ ነው፡፡ ለግንባሩ ቅርብ የሆነ ወዳጄ የችግሩን መጦዝ የገለፀው ‹‹ሁለቱ ጎራዎች በስብሰባ ወቅት ‹በውሃ ቀጠነ› ለፀብ ሲገባበዙ የሚያይ እና ለስድብ የሚጠቀሙባቸውን ቃላት የሚሰማ በአንድ ግንባር የተሰለፉ ናቸው ብሎ ከሚያምን ‹ግመል በመርፌ ቀዳዳ መሽሎኩን› ቢቀበል ይቀለዋል›› በሚል ምፀት ነው፡፡ አደጋውን የከፋ የሚያደርገው ደግሞ ኩነቶቹ ከመለዘብ ይልቅ መባባሳቸው ይመስለኛል፡፡ በመሬት ያለው እውነታ ይህ ቢሆንም፣ ፓርቲው በ2005 ዓ.ም ወርሃ መጋቢት ወደ ‹ግንባር› መሻገሩን ከማብሰሩም በላይ፣ ‹‹የኢትዮጵያን ወቅታዊና መሰረታዊ ችግሮች የመፍቻ አጋጣሚዎች›› በሚል ርዕስ ይፋ ባደረገው ባለአራት ገፅ ‹ማኔፌስቶ›፣ የሀገሪቱን ችግር በሙሉ በአራት ክፍል ቀንብቦ ካስቀመጠ በኋላ፣ ጉዳዩን ፈረንጅኛው ‹የሲኒ ማዕበል› እንደሚለው አድርጎ በማለፍ የ‹ደግፉኝ› ጥሪውን እንዲህ ሲል አስተላልፏል፡-‹‹ይህንን ፀረ-ህዝብና ፀረ-ሀገር የሆነውን ኢህአዴጋዊ ስርዓት በሰላማዊ አግባብ በምታደርገው ብርቱ ትግልህ መለወጥ እንደምትችል ካለፈው የትግል ተሞክሮህ ሆነ የአለም ህዝቦች ለነፃነት፣ ለዕኩልነትና ለፍትህ ብሎም ለዴሞክራሲያዊ ስርዓት እውን መሆን ከሚያደርጓቸው እንቅስቃሴዎችና ከሚያስመዘግቧቸውም ድሎች ትገነዘባለህ፡፡ ስለሆነም መድረክ ይህንን ክቡር ትግልህን በመምራት ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝለስልጣን ባለቤትነት እንድትበቃ በፅናትህ ከጎንህ ሆኖ ለመታገለ መወሰኑን ተገንዝበህ ከምንጊዜም በላይ ሁለንተናዊ ድጋፍህን እንድትሰጥ ጥሪያችንን በከፍተኛ አክብሮትና በአንተም ላይ ባለን ሙሉ እምነት እናስተላልፋለን፡፡›› በግሌ መድረክ ራሱ በሁለት ምክንያቶች እምነት ሊጣልበት የሚችል አልመስለኝም፡፡ የመጀመሪያው ከአንድነት ጋር የገባበት ድምፅ የለሽ ውዝግብ ከዕለት ወደ እለት እያደገ መሄዱ ነው፤ አዲሱ የዶክተር መረራ ጉዲና መጽሐፍም ቅራኔውን ቢያሳፋው አይገርምም፤ ዶ/ሩ ስለ2002ቱ ምርጫ ባወሳበት ምዕራፍ ‹‹የ1997ቱ የቅንጅት ወራሽ ነው ብለን የተማመንበት አንድነት እውነተኛ ወራሽ ለመሆን በጣም ብዙ እንደሚቀረው ተረዳው›› ያለበት ግምገማ እና ‹‹ያልገባኝና የሚከነክነኝ አንድነት ኦሮሚያ ላይ በብዛት ያወዳደራቸው ኦህዴድ ያሰማራቸው ወሮበሎች ነበሩ›› ፍረጃው ‹ትችት›ን በቅንነት ለመቀበል ልምድ ከሌለው የሀገሪቱ ፖለቲካ አንጻር አቧራ ማስነሳቱ አይቀሬ ለመሆኑ መገመቱ አይከብድም፡፡ ይህ እንግዲህ አንድነትን የአማራ (የከተማ ልሂቃን) ተወካይ የሚያደረገውን ወቀሳ ሳይጨመር ነው (እዚህ ጋ የሚነሳው አስቂኙ ጉዳይ ወቀሳውን የሚሰነዝሩት አባል ፓርቲዎች አንድነት የብሔር ድርጅት ቢሆን ይበልጥ ተጠቃሚ ከመሆናቸው በተጨማሪ ለአብዛኛው ችግሮቻቸው በቀላሉ መፍትሄ የመስጠቱ ጉዳይ ሲታሰብ ነው) ሁለተኛው መድረኩ ከለውጡ በኋላ ሀገር ለመምራት የሚያስችል የጠራ የፖለቲካ አመለካከት አለመከተሉ ነው፤ በውስጡ ያሉ ፓርቲዎች ቢያንስ ሁለት የተለያዩ ፕሮግራም የሚያራምዱ መሆናቸው ይታወቃል፡፡ የአንድነትን እና የኦፌኮን ፕሮግራም ብንወስድ የችግሩን ግዝፈት ያሳየናል፤ አንድነት መልካ ምድር ላይ ስለተመሰረተ ፌደራሊዝም አስተዳደር ጠቀሜታ ሲያብራራ፤ የኦፌኮ ባለስድስት ገፅ ፕሮግራም ደግሞ በማንነት ላይ ስለተመሰረተ ፌደራሊዝም ይሰብካል፡፡ በግልባጩ ውድሀት ይፈፅሙ እንዳይባል ደግሞ የእነ ዶ/ር መረራ ‹ከተዋህድን ኦሮሞ ተውጦ ይጠፋል› ስጋት ጋሬጣ ነው፡፡ አንዳንድ የአመራር አባላቱ ‹‹ዓላማችን ቅድሚያ ዴሞክራሲያዊ ተቋማትን መገንባት ነው›› የሚል መከራከሪያ ሲያቀርቡ ቢደመጡም፣ ከዚህ በኩል ከሚነሳው ተግዳሮት በቀላሉ የሚመለጥ አይመስለኝም (በነገራችን ላይ መድረኩ በወቅታዊው ቁመና ‹ግንባር› ለመመስረት የሚያስችለውን መስፈርት ሟሟላቱ ራሱ አጠራጣሪ ነው) አንድነትየአንድነት ተግዳሮት ወደ መድረክ ከመግባት ጋ ተያይዞ የመጣ ነው (ከጠዋቱ ሰማያዊ ፓርቲን የመሰረቱት ወጣቶች ከድርጅቱ ለመውጣት አንዱ ምክንያታቸው ይህ እንደሆነ ይታወሳል)፤ ትብብሩን ‹ያልተባረከ ጋብቻ› የሚያስብለው ደግሞ የዛሬ አራት ዓመት ‹ወደ መድረክ ካልገባን ትግሉን እናደናቅፋለን› ሲሉ የነበሩ አንዳንድ የአንድነት አመራሮች የውዝግቡ ተሳፊ መሆናቸውን ስንመለከት ነው፤ መተነኳኮሱ በ2002ቱ ምርጫ ማግስት የተጀመረ ቢሆንም፣ ባለፈው ዓመት ወደ መጦዝ ተሸጋግሯል፡፡ በተለይም አንድነት ‹‹የሚሊዮኖች ድምፅ ንቅናቄ›› በሚል መርህ ያካሄደው የሶስት ወር ዘመቻ መድረክን አለማካተቱ የሚያስተላልፈው መልዕክት ግልፅ ነው፡፡ በ‹‹ፀረ- ሽብር›› አዋጁ ላይ (ኢህአዴግንና ኢዴፓን ጨምሮ) በተደረገው ክርክርም አንድነት እና መድረክ በተለያዩ ሰዎች ተወክለው መቅረባቸው ግንኙነቱን እንደ ቀድሞ ለማየት አስቸጋሪ አድርጎታል፡፡ ይህም ሆኖ አንድነት በራሱ የተሻለ ፓርቲ ሆኖ ሊወጣ የሚችልበት ዕድል አለው፡፡ ምሁራዊ ስብስቡም ሆነ የኢኮኖሚ አቅሙ (የዲያስፖራ ድጋፉ) አንፃራዊ ጥንካሬ እንዲያገኝ ረድቶታል፤ ርዕዮተ-ዓለሙንም ከተቀናቃኝ ፓርቲዎች በጠበቀ መልኩ ማዘጋጀቱ ለቅቡልነቱ አስተዋፅኦ ሊያደርግለት ይችላል፤ ከመኢአድ ጋር የጀመረውን ውህደት (‹የአማራ ተወካይ› የሚለውን ፍረጃ ቢያጠናክረውም)  ከዳር ካደረሰ ደግሞ ከአቻዎቹ ጋ ያለው ልዩነት በእጅጉ መስፋቱ አይቀሬ ነው (መኢአድ የፈራረሰው ከአናት ነውና ግዙፍ መዋቅሩ ‹እረኛ አልባ› በመሆኑ፣ አንድነት በውህደት ስም ቢሰበስበው በከፍተኛ ደረጃ ይጠቅመዋል) የወል-መንገድበቀጣይ የተሻለ አማራጭ ሆኖ ለመገኘት መድረክና አንድነት መቻቻላቸው ወሳኝ ነው፡፡ ይሁንና ኩነቱን በታዛቢነት መመልከት የመረጡት የአረና ሰዎቸ በግንባሩ ቢሮ ሰላም ለማውረድ የአስታራቂነት ሚና ቢጫወቱ ጠቃሚነቱ ለእነርሱም ነው፡፡ አንድነቶችም፣ በመድረክ ስም እዚህ ድረስ ለመጓዝ የከፈሉት ዋጋ ብላሽ ከሆነ ማንንም አያተርፍም፡፡ በአናቱም ወቅታዊው የኢትዮጵያ ፖለቲካ አስገዳጅ መሆኑ መረሳት የለበትም፡፡ ምክንያቱም አንድነት የሰበሰባቸው ልሂቃኖችም ሆኑ በሀገሪቱ የተለያዩ ከተሞች ያነበረው መዋቅር (ጥንካሬው ላይ ያለኝ ጥርጣሬ እንደተጠበቀ ሆኖ) ቅድሚያ ለብሔር ፖለቲካ ከሚሰጡ አካባቢዎች በ‹መድረክ ባርኔጣ› በሚገኝ ድጋፍ (ድምፅ)  ካልታገዘ በቀር አየር ላይ ተንጠልጥሎ ከመቅረት አይታደገውም፡፡ የመድረክ ተግዳሮትም ተመሳሳይ ነው፤ በፖለቲካው ላይ ውጤት የሚያዛባ ተፅዕኖ ማሳረፍ የሚቻላቸውንና አንድነት የራሱ ያደረጋቸውን ከተሜዎች ‹ቡራኬ› ሳይቀበል ወደ ውድድር መግባቱ ‹ውሃ በወንፊት…› አይነት ሊሆንበት ይችላል፡፡ የመድረክንና የአንድነትን የወል ቀዳዳ መዘርዘሩን እዚሁ ገትቼ፣ የተሻለ ጥንካሬና የመግባባት መንፈስ ለማስረፅ በቅድሚያ የችግሮቻቸውን መንስኤ ለይተው ማወቅ አለባቸው ብዬ ስለማስብ፣ በግሌ ‹ያለመግባባቱ መነሻ› ከምላቸው ዋና ጉዳዮች ሶስቱን በአዲስ መስመር እጠቅሳለሁ፡፡  የፕሮግራም መጋጨት ያመጣው ጣጣ አንዱ ነው፤ ይኸውም የፀቡ የቡድን አባቶች የ‹ሕብረ ብሔር› እና የ‹ክልል› ፖለቲካ አቀንቃኝነት፣ ሁሉም አባል ፓርቲዎች መድረኩን ሲፈጥሩ የየራሳቸውን ፕሮግራም እንደያዙ መሆኑ፣ ጥቂት የማይባሉ ልዩነታቸውን ሳይፈቱ ‹በይደር› ማስቀመጣቸው… እንደ ማሳያ ይጠቀሳሉ፡፡ ይህ ሁኔታም የእርስ በእርስ መተማማን እንዳይኖራቸው ያደረገ ይመስለኛል (ከዚህ አኳያም ለመፍትሄው ቅድሚያ ከልሰጡ በመድረክ በኩል ‹መጪው ጊዜ ብሩህ ይሆናል› ብሎ መጠበቅ ‹የዋህ› ሊያስብል ይችላል) የጫናው ተፅእኖ ደግሞ በሁለቱም በኩል (በአንድነትና በብሄር ድርጅቶቹ) ከሚከተሉት የፖለቲካ አመለካከት አንፃር ወደ ስልጣን የመምጣቱ አጋጣሚ ቢፈጠር፣ የታገሉለትን ስርዓት ማንበሩ ፍፁም አዳጋች መሆኑን በማስታወስ ነው፤ አንድነቶች ፓርቲያቸው ከመድረክ እንዲወጣ ይጎተጉታሉ፤ ብሔር ተኮሮቹ ደግሞ ‹አንድነት የነፍጠኛውን ስርዓት የሚመለስ በመሆኑ፣ ወይ ወደ ብሄር ድርጅት ራሱን ይቀየር፣ አሊያም ፕሮግራሙን ይከልስ› የሚለው ሙግታቸው በአሳማኝ ሁኔታ መፍትሄ አለማግኘቱ ራሱን የቻለ ሌላ ትግል ከሚፈልግ አጀንዳ ጋ አላትሟቸዋል፡፡ አንድነት በሚያራምደው የሊብራል ዲሞክራሲ እና አብዛኛው የመድረክ አባል ድርጅቶች በሚከተሉት የሶሻል ዲሞክራሲ መካከል ያለውን ልዩነት የማሰታረቅ ስራ አለመሰራቱ ነው፡፡ ‹‹የአንድነት ፓርቲ ስትራቴጂና የአምስት ዓመት ዕቅድ›› በሚል ርዕስ 246 ገፅ ይዞ በታተመው መፅሀፍ ላይ ‹‹አንድነት የሚመሰረትበት ርዕዮተ-ዓለም ሊበራሊዝም ሆኖ በማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ፖሊሲዎች የሶሻል ዲሞክራሲን ጠቃሚ ገፅታዎች ይወስዳል›› የሚለው አንቀፅ ቢጤን ለመልካም ግንኙነት መደላድል መሆን ይችላል (በነገራችን ላይ ‹እንዲህ የችግር ቋት ተሸክመው ስለምን በጋራ ለመስራት ተስማሙ?› የሚል ጥያቄ መነሳቱ አይቀርምና ግምቴን ላስቀምጥ፤ የብሔር ድርጅቶቹን እስትንፋስ የሚቆጣጠሩት ፕ/ር በየነ ጴጥሮስ እና ዶ/ር መረራ ጉዲና ምርጫ 97ን ከሁለት አቅጣጫ ገምግመው ከደረሱበት ድምዳሜ ጋ የሚያያዝ ይመስለኛል፤ ይኸውም ‹አንድነት፣ የቅንጅት ወራሽ ነው› የሚለው የተሳሳተው ትንተና አንዱ ሲሆን፣ ሁለተኛው በዛው ምርጫ ተቀማጭነታቸው አውሮፓና አሜሪካ ከሆኑ አስራ ሁለት ፓርቲዎች ጋር መስርተውት የነበረው ‹‹ህብረት››፣ ፓርላማ በመግባታቸው፣ ከውግዘት ጋር እንዲባረሩ በማድረጉ ያሳደረባቸው መገለል ሊሆን ይችላል፤ በአንድነት በኩል ደግሞ ‹የመድረኩመሀንዲስ› ተደርገው የተወሰዱት ዶ/ር ነጋሶና አቶ ስዬ አብርሃ አንድነትን ለመቀላቀል ወደ መድረክ መግባትን እንደ መደራደሪያ በማቅረባቸው ሲሆን፣ ሌላኛው ደግሞ ዛሬም ያልተሸነፈው የ‹ተባበሩ ወይም ተሰባበሩ› ግልብ ግፊት ነው ብዬ አስባለሁ፤ የዚህ ድምር ውጤትም ከነርዕዮተ-ዓለም እና የፕሮግራም ልዩነት ወደ መድረኩ አምጥቷቸው አይን የሚገባ ሥራ እንዳይሰሩ አግዷቸዋል) የመድረክ አባል ድርጅቶች መተዳደሪያ ደንብን አለማክበር ‹የፖለቲካ ብልጠት› በማድረጋቸው፣ ለራሳቸው ተጨማሪ የመናተረኪያ አጀንዳ ፈጥረዋል፡፡ ይህ አይነቱ ስርዓት አልበኝነት በጋራም በተናጥልም ተፈፅሟል፡፡ አንድነትን ጨምሮ የመድረኩ ስራ አስፈፃሚ ደጋግሞ ከመርሁ ሲያፈነግጥ ታይቷል፤ ለምሳሌ በደንቡ ላይ መሻሻል ያለበትን አንቀፅ የሚወስነውም ሆነ ከፍተኛው ስልጣን የጠቅላላ ጉባዔው መሆኑ በግልፅ ተቀምጦ ሳለ፣ ጉባዔው ከተሰበሰበባቸው በአንዱ ዕለት ‹የመድረኩ ሊቀ-መንበረ በዙር ከሚሆን፣ በብቃት ይሁን›፤ እንዲሁም ‹አዲስ ፓርቲ በአባልነት የምንቀበልበት መንገድ መሻሻል አለበት› የሚሉ አቋሞች ላይ ቢደርስም፣ ስራ አስፈፃሚው ቃል በቃል ‹ይህንን አሰራር ጉባኤው ሊቀይረው አይችልም› ሲል ውድቅ ያደረገበትን አጋጣሚ መጥቀስ ይቻላል፡፡ በተናጥል አንድነት፣ ኦፌኮ እና ኢሶዴፓ በአንቀፅ 21 ‹የአባል ድርጅቶች ግዴታ› በሚል ርዕስ ስር የተቀመጡትን፡- ‹ከአፍራሽና ተቃራኒ ከሆኑ እንቅስቃሴዎች መቆጠብ›፣ ‹በአባላት መካከል አለመተማመን ከሚፈጥሩ ማናቸውም ተግባር መቆጠብ›፣ ‹የግንባሩን አቋም የሚፃረር አቋም ያለማራመድ› እና መሰል ደንቦችን ደጋግመው በአደባባይ ሲጥሱ ታይተዋል፤ ይህ አይነቱ ስርዓተ-አልበኝነት መፍትሄ ሳያገኝ የተሻለና ጠንካራ ሆኖ መውጣቱ አዳጋች ይመስለኛል፡፡ ሰማያዊሰማያዊ ፓርቲ አዲስ በመሆኑ ለወቀሳ መቸኮሉ አግባብ እንዳልሆነ ቢሰማኝም፣ ፓርቲው እያሳየ ካለው ፈጣን እንቅስቃሴ አኳያ፣ በፍጥነቶቹ መካከል የሚፈጥራቸውን ድክመቶቹን ቢያሻሽል ጠቀሜታው ለሀገር ስለሆነ የግል አስታየየት መስጠቱን አስፈላጊ ሆኖ አግኝቸዋለሁ፡፡ የሰማያዊ ዋናው ድክመት ከ‹ግንፍሌ ፓርቲ›ነት አልፎ የመሄድ ፍላጎት ያለው አለመምሰሉ ነው (ጽ/ቤቱ አራት ኪሎ /ግንፍሌ/ አካባቢ ይገኛል)፡፡ ከአዲስ አበባ ውጪ ለመንቀሳቀስ ሲሞክር አይታይም፤ በሌሎቸ የሀገሪቱ ከተሞች የተከፈተ ተጨማሪ ቢሮ ካለ፣ ከምስረታው በኋላ የአባላቱ ቁጥር ምን ያህል እንደደረሰ፣ እና መሰል መረጃዎችን ለማግኘት ወደ ፓርቲው ጽ/ቤት ሄዶ የነበረው የመፅሄቱ ሪፖርተር ‹እንዴት እንደምትጠቀሙበት ስለማናውቅ አንናገርም› በሚል ክልከላ በመመለሱ ስለወቅታዊው ቁመና እዚህ ጋ መጥቀስ አልተቻለም (ከዚህ ውጪ ሊቀ-መንበሩ ይልቃል ጌትነት ከ‹ሰንደቅ› ጋዜጣ ጋር ባደረገው ቃለ-መጠይቅ ‹‹ባለፉት 40 ዓመታት ከመጣው የፓርቲዎችጥንካሬ ይልቅ፣ በአንድ ዓመት ውስጥ ሰማያዊ ፓርቲ ብቻውን አምጥጦታል›› ያለው ሀረግ ስህተት ቢሆንም፣ አንድም በሂደት የሚታረም፣ሁለትም የአፍ ወለምታ፣ ሶስትም ከልምድ ማነስ የሚያጋጥም በመሆኑ ‹ፀጉር መንጨቱ› ፓርቲው ፍርሃትን ለመስበር ከሚያደርገው እንቅስቃሴ አኳያ ገንቢ አይደለምና አልፈዋለሁ፡፡) ‹እምነት ጨምሩልን› ‹ለውጥ! ለውጥ!› የሚል ድምፅ በመላ ሀገሪቱ የበረከተው የ‹ቡርዣ› ወይም ‹አድሀሪ› አብዮትን በመናፈቅ አይደለም፤ እንዲህ አይነት አብዮት፣ ከሰው ለውጥ በቀር ሕዝባዊ ጠቀሜታ የለውማና፡፡ የደርግም ሆነ የኢህአዴግ ‹አብዮት› የዚህ አምሳያ በመሆኑ ነው፣ ዛሬም ዘመን ተጋሪዎቼ ‹ፋኖ ተሰማራ!› ከማለት ነፃ ያልወጡት፡፡ ‹ሶስተኛው አብዮት› የማይሸነፍ እና የማይንበረከክ እንዲሆንልን ከምንመኘው በላይ ወደ ‹መፈንቅለ-መንግስት›ነት እንዳይቀየር መጠንቀቁንም ግዴታ ያደረገው ጠንካራ ፓርቲና የነቃ ማህበረሰብ ያለመኖሩ ስጋት ነው፡ ፡ ይህ ደግሞ ከወዲሁ ከአማራጩ ኃይል ጎን መቆም ይቻል ዘንድ ‹እምነት ጨምሩልን!› (ሀገር የመረከብ አቅማቸውን አሳዩን?) እንድንልአስገድዷል (‹ጀግናው› ኢህአዴግ ወደ ማይቀረው ሽንፈት መንገዱን ከጀመረ ጥቂት ክረምቶች በማለፋቸው፣ ከለውጡ በኋላ የሚመጣው ኃይል ሁለንታው የተቃና መሆኑን ማስመስከር አለበት) መድረክ፣ አንድነት እና ሰማያዊ ወደራሳቸው ይመለከቱ ዘንድ ከሞላ ጎደል የወል ‹ክፍተቶች› ወይም ‹ድክመቶች› የምላቸውን ሶስት ጉዳዮች ከዚህ ቀጥሎ እጠቅሳለሁ፡፡ ሃሳብ-አልባፓርቲዎቹ በምስረታቸው ዘመን ቅድሚያ የሚሰጡት ለምርጫ ቦርድ የእውቅና ሰርተፍኬት እና ‹ተቃዋሚ ድርጅት› ተብለው ለመጠራት በመሆኑ አንድም የሀገሪቱን አንኳር ችግሮች አጥንተው መፍትሄ በመያዝ አልተዘጋጁም፤ ሁለትም ከነባር ድርጅቶች ድክመትና ጥንካሬ ተምረው አልመጡም፤ በዚህም የሚፈልጉትን ሳያወቁ እና የተለየ አማራጭ ሳይይዙ ወደ ፖለቲካው ገብተዋል ወደሚል ጠርዝ እየገፋን ነው፤ ጠንካራና የተፍታታ የፖለቲካ ፕሮግራም የላቸውም፤ በንፅፅር ‹‹አንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ›› የተሻለ ፕሮግራም ለመቅረፅ ከመሞከሩ ውጪ፣ የመንግስቱ ስልጣን ‹ገጭ-ቋ› ቢል ‹አማራጭ ሊሆኑ ይችላሉ› የሚባሉት ፓርቲዎች ‹እያሾፉ ነው› በሚል ችላ ካልተባሉ በቀር ‹ፕሮግራሜ› ብለው ያቀረቡትን ለተመለከተ ምን ያህል ሃሳብ አልባ እንደሆኑ ለመረዳት አይቸገርም፡፡ የሆነው ሆኖ ይህንን ፅሁፍ ሳዘጋጅ የነበረኝ አመለካከት ስለመድረክና አንድነት የፖለቲካ ፕሮግራም ደካማነት ከዚህ ቀደም ስለጠቀስኩ፣ ዛሬ ሰማያዊ ፓርቲን ብቻ አንስተን ብንነጋገር ይሻላል የሚል ነበር፤ ይሁንና የድርጅቱን ፕሮግራም ካነበብኩ በኋላ ግን ምንም ማውራት እንደማይቻል ተረዳው (ያውም ያየሁት ወረቀት ‹ፕሮግራም› ተብሎ ሊጠራ ከቻለ ማለት ነው)፡፡ ፓርቲው ለስልጣን የመብቃት ዕድልካገኘ፣ ለዘመናት ሲንከባለልና ሲደራረብ የመጣውን ዘርፈ ብዙ የሀገሪቷን ችግር የሚፈታው ‹‹የሰማያዊ ፓርቲ ፕሮግራም›› በማለት ርዕስ ባዘጋጀው ባለአስራ አምስት ገፅ ወረቀት ነው፡፡ መቼም በዚህ ፕሮግራም ‹ከሌሎች የተሻልኩ ነኝ-ምረጡኝ› የማለቱ ድፍረት ግራ አጋቢ ይመስለኛል፤ ምናልባት ‹የፖለቲካ ሳይንስ ምሁሩ ዶ/ር መረራ ጉዲና ካዘጋጀው አራት ገፅ ፕሮግራም፣ የእኛ የበለጠ ነው› የሚል መከራከሪያ ካልቀረበ፡፡ ስለርዕዮተ-ዓለሙም ቢሆን ‹ለዘብተኛ ሌብራሊዝም› ከማለት ያለፈ ያብራራልን ጉዳይ የለም (በዚህ በኩል ኢዴፓ ከሁሉም በተሻለ የተብራራና የጠበቀ ፕሮግራም አለው፤ ግና! ለአንድ ፓርቲ ከምንም በላይ አስፈላጊ የሆነውን ‹ታአማኒነት› አፍርሷልና ፕሮግራሙ ጠቀመ አልጠቀመ ፋይዳ አለው ማለት አይቻልም) በተቀረ ያለ ርዕዮተ-ዓለም ፓርቲ መስርቶ፣ ‹ሀገሬን፣ ሀገሬን…› ማለቱን ከቀረርቶ ለይቶ መረዳት ይቸግራል፡፡ መድረክ፣ አንድነት እና ሰማያዊ አሁንም ጊዜውም ዕድሉም አላቸውና ስልጣን ቢይዙ በዋና ዋና ሀገራዊ አጀንዳዎች፣ በፖሊሲዎች፣ በማህበራዊ ፍትህ እና መሰል ጉዳዮች ላይ ያላችውን የመፍትሄ ሃሳብ እና የተሻለ አማራጭ በትክክል ተንትነው ማዘጋጀቱን ቢያስቀድሙ መልካም ይመስለኛል፡፡ ቅንጅት ለአንድነትና ለዲሞክራሲ በ1997 ዓ.ም ‹‹የምርጫ ማኒፌስቶ›› ብሎ ያዘጋጀው ሰነድ እንኳ ከ130 ገፅ በላይ የፈጀ እንደነበር የቅርብ ጊዜ ትውስታችን ነው፡፡ እናም ፓርቲዎቹ ‹ፕሮግራሜ› የሚሉትንም ሆነ፣ ከተራራ የገዘፈ ችግሮቻችንን በደቃቃ ግምገማ ለማብራራት መዳከሩን አርቀው በመስቀል ወደ ቁም-ነገሩ ቢያዘንብሉ ጠቀሜታው ለራሳቸው ነው፤ ‹የትም ፍጪው…› መረሳት አለበት፤ ለፖለቲካ ፓርቲ ሃሳብ ከምንም በላይ ወሳኝ ነው፡፡ ዳሩስ! በሰላማዊ መንገድ ለመታገል የተዘጋጀ ፓርቲ፣ የሚሸጥ ርዕዮተ-ዓለም ካላዘጋጀ በቀር ወታደራዊ ድርጅት አይደለምና ‹በኃይል ተጠቅሜ ፍላጎቴን አሳካለሁ› ሊል አይችልም፡፡ እውነት እውነት እላችኋለውም በዚህ በኩል ቀድሞ የነቃ፣ እርሱ አትራፊ ነው፤ ረቢው እንዳለውም ‹ላለው ይጨመርለታል›ና፡፡ ምሁር አልባየተፎካካሪ ድርጅቶች ሌላኛው ክፍተት ምሁራንን /ሙያተኞችን/ አለማቀፍ እንደሆነ ተደጋግሞ ቢነገርም፣ ዛሬም በዚህ በኩል የተሰራ ሥራ የለም፡፡ ይህንን ቀዳዳ ለመድፈን አመራሩና አባለቱ ከጽ/ቤት በመውጣት መቀስቀስ፣ ማሳመን፣ ማግባባት… አለባቸው ብዬ አስባለሁ፤ መቼም በሁሉም ዘርፍ ‹እኔ ብቻ ነኝ የማውቀው› ግብዝነትን የወረሱት ነፍሱን ይማረውና ከአቶ መለስ ይመስለኛል፤ ይህ አይነቱ አመለካከት ግን ወንዝ አያሻግርም፡፡ በርግጥ ‹ፖለቲካና ኮረንቲ…› በሚባልበት አገር፣ በደፍረት፣ ድርጅት እስከመመስረት መድረስ ትልቅ ታሪክ ቢሆንም፣ ጠንካራ መሆን ካልተቻለ ዞሮ ዞሮ ያው ክሽፈት ነው፡፡ አደባባዩም እንደቀድሞ ‹ድንጋይ ዳቦ ነው› ብለው ለሚከራከሩ አፈ-ጮማ ፖለቲከኞች ቦታ የሌለው መሆኑ ግልፅ ይመስለኛል፡፡ በተለያየ ሙያ የሰለጠኑ ምሁራኖችን ወደ ፓርቲያችሁ ለመሳብ መደላደሉን አመቻቹ፤ ፍርሃት መሰበር እንዳለበት አሳምኗቸው፤ አንኳኩ፤ ከልከፈቱም ደጋግሙት፡፡ የሴራ ፖለቲካሌላው ድርጅቶቹ የሚጠነክሩት፡- ከሴራ፣ ከስርቻ ስር ፖለቲካ፣ ከጠልፎ መጣል ጨዋታ፣ ከአፍቅሮተ-ስልጣን አና ከመሳሰሉት ነፃ ሲሆኑ ነው፡፡ በአናቱም የጥናትና ምርምር ዘርፍ መሰል እያቋቋሙ እውቀትና መረጃን ወደላይም ወደታችም በማሰራጨት አመራሩንና አባላትን ማብቃት፣ እንዲሁም ግልፅነትን በመተግበር፣ የ‹ጀርባ ፖለቲካ›ን ማዳካም ይቻላል፡፡ ይህ ሲሆን ነው ኩነቶችን ከመበለጥና ያለመበለጥ፤ ከመሸነፍና ያለመሸነፍ አኳያ ብቻ የማየቱ አባዜ የሚለወጠው፡፡ ከእዚህ ሁሉ ስንክሳር በላይ ደግሞ በምሬቷ ብዛትበአማራጩ ኃይል ላይ ተስፋ የጣለች ሀገር መኖሯም ከእያንዳንዷ እንቅስቃሴ ጋ መታወስ ይኖርበታል፡፡ በመጨረሻም-የአልባራዲ መንገድሀገሪቱ ካለችበት ወሳኝና ታሪካው ወቅት አኳያ ቢያንስ በመንግስት ጥቁር መዝገብ ስማቸው ያልሰፈረ፣ እውቀትና አቅም ያላቸው፣ በየትኛውም ሀገር የሚገኙ ኢትዮጵያውያን በራሳቸው መንገድ ወደ ሀገራቸው ገብተው ትግሉን ማገዝ የሀገሪቱ ወቅታዊ ሁናቴ የሚያስገድደው ነው፡፡ በተለይም በእንዲህ አይነት ጉዳዮች ከትምህርትም ሆነ ከመስክ ልምድ ያካበቱ ወንድምና እህቶች የግብፃዊውን መሀመድ አልባራዲ መንገድ ቢከተሉ፣ አንድም ሁኔታዎች ከቁጥጥር እንዳይወጡ ማገዝ ይችላሉ፤ ሁለትም አብዮቱን ከሽንፈትና ቅልበሳይታደጋሉ፡

በኮንዶሚኒየም ቤቶች ሺያጭ ሥም ስደተኛውን የወያኔ ጭሰኛ ለማድረግ የተጀመረው እንቅስቃሴ ይከሽፋል::

ወያኔ እንደ ድርጅት የሚፈልገውን የፖለቲካ ጥቅም የሚያስገኝለት እስከመሰለው ድረስ በህዝብና በአገር ላይ የማይፈጽማቸው ምንም አይነት እኩይ ተግባሮች እንደማይኖሩ በተግባር ያስመሰከረ ድርጅት ነው::
ለአብነት ያህል ለመጥቀስ ፤
  1. ድርጅቱ ገና ትግራይ በረሃ ውስጥ ትግል ላይ በነበረበት ወቅት የትግራይን ወጣቶች ከትምህርት ገበታቸው እያነቀ በመውሰድ አላማውን በግልጽ ላልተረዱትና ላላመኑበት ጦርነት ማግዶአቸዋል:: በዚህም የተነሳ ወያኔ እራሱ ይፋ ባደረገው አሃዝ ብቻ ቁጥራቸው 60 ሺህ የሆኑ ለጋ ወጣቶች ላለፉት 22 አመታት የህዝባችንን ስቃይና መከራ እያራዘመ ያለውን የድርጅቱን መሪዎች ሥልጣን ላይ አውጥቶ ለማንገስ ከፍተኛ የህይወት መስዋዕትነት ከፍለዋል ::
  2. የአገራችንን ክብርና መልካም ገጽታ እስከዛሬ አበላሽቶ ባለፈው በዚያ አስከፊ የ1977ቱ ድርቅ ወቅት ለትግራይ ተጎጂዎች ከአለም አቀፍ ለጋሾች የተበረከተውን የነፍስ አድን እህል በሱዳን በኩል ወደውጭ አሳልፎ በመቸብቸብ መሪዎቹና ተከታዮቻቸው ለተንደላቀቀ ኑሮ ሲበቁ በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ ህጻናት፤ አሮጊቶችና አዛውንቶች እንደቅጠል እንዲረግፉ ምክንያት ሆኖአል::
  3. የትግራይ ህዝብ ተማሮ በመንግሥት ላይ እንዲያምጽ ለመቀስቀስ በደሃው አቅማችን የተገነቡ ትምህርት ቤቶችን፤ የህክምን አገልግሎት መስጫ ተቋሞችን ፤ ድልድዮችንና ሌሎች መሠረተ ልማቶችን በፈንጂና በመድፍ ከማውደም አልፎ የተሳሳተ መረጃ ለደርግ በመስጠት ቁጥራቸው በውል ያልታወቀ ህዝብ ለገበያ እንደወጣ ሃውዜን ከተማ ላይ በጠራራ ጸሃይ እንዲጨፈጨፍ አድርጎአል::
  4. የደርግ አገዛዝ ከተወገደ ቦኋላ ሥልጣን ላይ ለመደላደል የሚያስችል ድጋፍ ለመሸመት ሲባል የአገራችንን ሉአላዊ ጥቅም ለባዕድ አሳልፎ የሰጠ በርካታ ግልጽና ድብቅ ውሎችን ከ3ኛ አካላት ጋር ፈጽሞአል :: ከውሎቹ አንዱ የህዝባችንን ትኩረት ለማስለወጥ ካለፈው 2 አመት ጀምሮ በሰፊው እየተዘመረለት የሚገኘው የአባይ ወንዝን የመጠቀም መብታችንን የሚጻረር እንደነበረ ጉልህ ማስረጃ አለ::
  5. በሚሊዮን የሚጠጋ ህዝባችንን ከቀያቸው በማፈናቀል ለም መሬታችንንና ድንግል የተፈጥሮ ሃብታችንን ለህንድ ፡ ለቻይናና ለአረብ ከበርቴዎች በመቸብቸብ በገዛ አገራችን የባዕድ አሽከር እንዲንሆን ፈርዶብናል::
  6. በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ሴት እህቶቻችን ለባርነት ሥራ ወደ አረብ አገር በመላክ ከፍተኛ ሰቆቃ እንድፈጸምባቸው በማድረግ ብሄራዊ ክብራችንን ኩራታችንን የሚያጎድፍ ተግባር ፈጽሞአል::
  7. በሙስናና ዘረፋ የተጨማለቀ ሥርዓት በማቋቋም አብዛኛው ህዝባችን ከወለል በታች ወደወረደ የድህነት አረንቋ ውስጥ ገብቶ የቁም ስቃይ እንዲቀበል አድርጎአል::
  8. መብታቸውን ለማስከበር በጠየቁ ወገኖቻችን ላይ እስከ አፍንጫው የታጠቀ ጦር በማዝመት በርካቶችን አስጨፍጭፎአል፤ ከቤት ንብረታቸው አፈናቅሎአል ፤ ለእስርና ለስደት ዳርጎአቸዋል:: ወዘተ
ወያኔ ይህንንና ግዝፈታቸው ከዚህ የከበዱ በርካታ ሰቆቃዎችን በአገርና በወገን ላይ እየፈጸመ የአገዛዝ ዘመኑን ሊያራዝም የቻለው፤
  1. ህዝባችን በዘር ፤ በቋንቋና በሃይማኖት ተከፋፍሎ እርስ በርሱ እንዳይተማመንና የጎሪጥ እንድተያይ ሌት ተቀን ተንኮል በመሸረቡ
  2. የጦር ሃይል ፤ የፖሊስ ሠራዊት፤ የደህንነትና ሌሎች የኢኮኖሚና ማህበራዊ አገልግሎት መስጫ ተቋሞች በሙሉ ከአንድ አካባቢ በተሰባሰቡ የጥቅም ተጋሪዎች ቁጥጥር ሥር እንዲወድቅ ተደርጎ እሺ ያለውን በጥቅም እምቢ ያለውን ደግሞ በጠመንጃ ሃይል ጸጥ ለጥ ለማድረግ በመመኮሩ፤
  3. ከራሳቸው የግል ሚቾትና ቅንጦት አሻግረው በወገንና በአገር ላይ እየተፈጸመ ያለውን ሰቆቃ ማየት የማይፈልጉ ወይም የማይችሉ ተፈጥሮአዊ ባህሪያቸው “ እኔ ከሞትኩ ሠርዶ አይብቀል “ ካለቺው እንስሳ የማይለይ ሆዳሞች ከተለያየ የህበረሰተሰብ ክፍል ተመልምለው ከአገዛዙ ዙሪያ በሎሌነት ለመሰለፍ በመቻላቸው እንደሆነ ይታወቃል::
በሌላ አገላለጽ ወያኔ የአገዛዝ እድሜውን ለማራዘም የፈጸመውና እየፈጸመ ያለው ቀደም ሲል ፋሽስት ጣሊያን የአገራችንን ህዝብ በባርነት ለመግዛት አድርጋው ከነበረው ቅስም ሰባሪ እርምጃዎች በባህሪም ሆነ በአይነት አንድ መሆኑ ግልጽ ነው:: ለመብቱና ለነጻነቱ ቀናዕ የሆነው የኢትዮጵያ ህዝብ ግን ትናንት ለጣሊያን መደለያዎች ተታሎ ወይም የሃይል እርምጃ ተንበርክኮ ነጻነቱን አስነጥቆ ለመኖር እንዳልፈቀደ ሁሉ ዛሬም ከአገሩ የሰሜን ክፍል የበቀሉ ባንዳዎች በጉልበታቸውም ሆነ ሌሎች መሸንገያዎች የሚያደርጉትን አሜን ብሎ እስከወዲያኛው ለመገዛት ፈቃደኛ አለመሆኑን በሚያደርገው ተቃውሞ እየገለጸ ነው::
ይህንን ሃቅ የተረዳው ወያኔ የጭቆና ክንዱን ለማፈርጠም የሚያስፈልገውን ገንዘብ በስደት ውጭ አገር ከሚኖረው ኢትዮጵያዊ ለመሰብሰብና የተቃውሞ እንቅስቃሴውን ለማዳከም በኮንዶሚኒየም ቤት ሽያጭ ሥም አዲስ እቅድና ስልት ነድፍ መንቀሳቀስ ጀምሮአል::
ብቸኛው የፓርላማ ተወካይ የሆኑት አቶ ግርማ ሠፉ በቅርቡ ከኢሳት ሬዲዮ ጋር ባደረጉት ቃለመጠይቅ እንዳረጋገጡት ወያኔ በስደት ለሚኖረው ኢትዮጵያዊ የነደፈው የኮንዶሚኒየም ቤት ሺያጭ ዋና አላማ አገር ቤት ውስጥ እየተፏፏመ የመጣውን ህዝባዊ ተቃውሞ ለመምታት በተለያዩ የምዕራብ አገሮች ከፍ ብለው እየተደመጡ ያሉትን ድምጾች አሰቀድሞ ለማዳከም በመፈለጉ እንደሆነ አያጠራጥርም::
ምንም እንኳን ለራሳቸው ማንነትና ስብእና ክብር የሌላቸው አንዳንድ ዜጎች “የአባትህ ቤት ሲዘረፍ አብረህ ዝረፍ” በሚል ፈሊጥ በዚህ የወያኔ ወጥመድ ውስጥ ለመውደቅ ውር ውር እያሉና በየአገሩ የሚገኘውን የወያኔ ኤምባሲ በር ማንኳኳት የጀመሩ መኖራቸው ባይካድም አንድ ወቅት ላይ ግር ግር ፈጥሮ ወዲያው እንደተጨናገፈው የአባይ ቦንድ ሺያጭ የታሰበውን ያህል ውጠት እንደማያስገኝ በእርግጠኝነት መናገር ይቻላል::
ግንቦት 7 የፍትህ የነጻነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ በስደት የሚኖረው ሁሉም ኢትዮጵያዊ አገሩንና ወገኖቹን ጠልቶ ሳይሆን የተሰደደው ለዘመናት የዘለቀው ኢፍትሃዊነት የፈጠረው ኋላ ቀርነትና ድህነት አገሩ ላይ ለመኖር ያለውን ምኞትና ተስፋ አጨልሞበት አለያም በፖለቲካ ችግር ምክንያት ህይወቱን ለማቆየት ተገዶ ነው ብሎ ያምናል::
በዚህም የተነሳ ማንኛውም ስደተኛ ስደት የሚያስከትለውን ማህበራዊና ሥነ ልቦናዊ ቀውሶች ተቋቁሞ አንድ ቀን አገሬ ገብቼ ከወገኖቼ ጋር በሠላም እኖርበታለሁ ብሎ ያጠራቀማትን ጥሪት በከፍተኛ ንቅዘትና ሙሰኝነት ወደ መጨረሻው ታሪካዊ ሞቱ እየወረደ ያለውን የወያኔ ሥርዓት ተማምኖ በማውጣት ቦኋላ እንዳይጸጸት ወገናዊ ምክሩን ይለግሳል::
ወያኔ ለዲያስፖራው ያዘጋጀው የኮንዶሚኒዬም ቤቶች ሺያጭ የፖለቲካ ድጋፍ ለማግኘት የታለም የከተማና የገጠር ህዝባችንን የወያኔ ጭሰኛ ያደረገ የአገር ውስጥ ፖሊሲ አካል ነው:: ከ7 አመት በፊት ኮንዶሚኒዬም ቤት ለማግኘት ለተመዘገቡ 800 ሺህ የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች ያልተዳረሰ ቤት እንዴትና በምን ስሌት ነው በሰው አገር ያውም በአንጻራዊ ምቾት ለምንኖር ዜጎች የታሰበልን ብሎ እራስን መጠየቅ ከትዝብትና ከታሪክ ተወቃሽነት የሚያድን ተግባር ነው ::
ሃብት በተትረፈረፈበትና የሚበላ የሚጠጣ ነገር ከሰው ተርፎ ቆሻሻ ገንዳ ውስጥ በሚጣልበት አሜሪካና አውሮጳ ለምንኖር ዜጎች ከሚስኪኑ ህዝባችን ጉሮሮ በተነጥቀ ገንዘብ ቤተመንሥት ውስጥ ተዘጋጅቶ የተላከ ምግብና መጠጥ ለመደለያነት ሲያጓጉዝ የኖረ መንግሥት አሁን ደግሞ በኮንዶሚኒየም ቤት ሥም ቢመጣብን ጥፋቱ የሱ ሳይሆን የእኛ ለክብራችንና ለነጻነታችን ዋጋ የማንሰጥ ስግብግቦች መሆኑን ምን ጊዜም መዘንጋት የለበትም::
ግንቦት 7 የፍትህ የነጻነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ በስደት ውጭ አገር የሚኖር ማንኛውም አገር ወዳድ ኢትዮጵያዊ ወያኔ በኮንዶሚኒዬም ቤት ሽያጭ ሥም ትግሉን ለማዳከም የዘረጋውን ይህንን የተንኮል ሴራ እንዲያከሽፍ ወገናዊ ሃላፊነት እንዳለበት ያስገነዝባል::
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ !