Oct 17, 2013

የትግራይ ምሁራን ይህንን እያያችሁና እየታዘባችሁ ዝም ማለታቸሁ ለምን ይሆን?

Posted on  

አማራና ኢትዮጵያዊነት፤ በጠላትም በወገንም እስከ ሞት!
በገ/ክርስቶስ ዓባይ(አቶ በገ/ክርስቶስ ዓባይ ታዋቂ የትግራይ ተወላጅ ናቸው!)
የአማራው ሕዝብ ባህልና አስተዳደግ መተኪያ ከሌላት ከአገሩ ከኢትዮጵያና፤ ጥላና ከለላ በመሆን እነርሱን ለመታደግ ሕወቱን ሳይሳሳ ሲገብርላቸው ለቆዮት ኢትዮጵያውያን ወገኖቹ ፤ ከፍተኛ ክብርና ፍቅር እንዲያድርበት ሆኖ በዓለማዊውም ሆነ በመንፈሣዊው አስተሳሰብ ተቃኝቶ ያደገ፤ የዳበረና፤ በጠነከረ አለት ላይ እንደታነጸ ግንብ በቀላሉ የማይሸረሸር መሆኑን በተግባር እያረጋገጠ ይገኛል።
ለመሆኑ ወያኔ አማራን ለምን ጠላው?
ወያኔ ከምንወደውና ከምናፈቅረው ከትግራይ ወገናችን በመውጣቱ በጣም ያሳዝናል። ግን ደግሞ “ቆማጣን ቆማጣ ካላሉት ገብቶ ይፈተፍታል” እንደሚባለው ወያኔን እራሡ ባወጣው ስም ወያኔ፤ ወይም ደግሞ የበግ ለምድ ለብሦ በበጎች መካከል እንደተገኘ ቀበሮ ኢሕአዴግ፤ ብለን መጥራቱ የክብር ካባ ማልበስ ስለሚሆን በሚመጥነው ስም መጥራቱ ተገቢ ይመስለኛል። ይኸውም የከሃዲ ባንዳ ዘር ስብስብ ለመሆኑ አንድና ሁለት የሌለው እውነት ስለሆነ ደቂቀ ባንዳ መባል አለበት።
ከአሁን ቀደምም ቢሆን ካሣ ምርጫ ወይም ሕዝብ ባወጣላቸው ስም በዝብዝ ካሣ እኰ ለጠላት ባማበር አፄ ቴዎድሮስን በመክዳት፤ የንግሊዙን ጦር አዝማች ጄኔራል ናፒርን እየመሩ እስከመቅደላ ድረስ ያደረሱ መሆናቸው ይታወቃል። አማራው ይህንን ታሪክ በሚገባ ያውቃል፤ ይሁን እንጂ በጎሣ ግጭት የማታ ማታ የምትጎዳው አገራችን ኢትዮጵያ ስለሆነች እንዲህ ያለውን አስነዋሪ የክህደት ታሪክ በመተው ደግ ደጉን ብቻ ለልጆቹ እያስተማረ ይገኛል።
ምክንያቱም እንደ ራሥ አሉላ አባ ነጋና አው አሎም ያሉ ታማኝ ኢትዮጵያውያንም ስላሉ “ከተልባ ጋር የተገኘህ ሰሊጥ አብረህ ተወቀጥ” እንዳይሆን የጅምላ ፍረጃውን አማራው ስለማይቀበል ሁሉንም ለአገር አንድነት በሚጠቅምና ክብርን በማይነካ መልኩ በጥንቃቄ መዝግቦ ይዞታል።
እንደሚታወቀው አማራው ቀደም ባሉት መንግሥታትም ቢሆን የተመቸው ዜጋ አልነበረም። የውጭ ጠላት በመጣ ቁጥር ክተት ሥራዊት እየተባለ በራሱ ስንቅና ትጥቅ በባዶ እግሩ በመዝመት የአገሩን ዳር ድንበርና ወገኖቹን ከውጭ ወራሪ ጠላትና ከባርያ ፈንጋይ የዓረብ ነጋዴዎች ሲከላከልና ሲጠብቅ መኖሩን ታሪክ ምስክር ነው።
አማራ ለአገሩ መንግሥትም ሆነ ለወገኑ ታማኝ፤ ከመሆኑ የተነሳ ለውጭ ጠላት ፈጽሞ የማይመችና የማይታለል በመሆኑ ይኸው አገራችን ኢትዮጵያ ዳር ድንበሯ ሳይደፈር አሁን ላለው ትውልድ እንድትደርስ ከፍተኛውን አስተዋጽዖ ያደረገ ኩሩና ጀግና ሕዝብ መሆኑን አይደለም ኢትዮጵያዊ፤ የዓለም ሕዝብ ያውቀዋል።
አሁን አጭበርብሮ በሥልጣን ላይ የሚገኘው ከሐዲ የባንዳ ዘር ስብስብ ጀግና ነኝ ሲል አላፈረም። ሐቁ ግን አሁንም ቢሆን የባንዳው ዘር የአገሪቱን መሣሪያ እንኳ ታጥቆ እያለ ቢሆን አማራው የፈራ መስሎት ከሆነ የባንዳው ዘርና ፍርፋሪ ለቃሚዎቹ ውሾች ተሳስተዋል እላለሁ። እርግጥ ከአሁንም በፊትም ሆነ በአሁኑ ሰዓት አማራው ሦስትን ነገር ይፈራል።
አንደኛውና የመጀመሪያው ለብዙ ምዕተ ዓመታት አያት ቅድመ አያቶቹ ያቆዩአት ኢትዮጵያ በጠላት ሤራ የተነሣ እንዳትበታተን ይጠነቀቃል።
ሁለተኛው ደግሞ የሚወደውንና የሚያከብረውን የትግራይ ሕዝብ ላለማስቀየም ከዛሬ ነገ ይሻላል በማለት “ላም እሣት ወለደች እንዳትልሰው ፈጃት እንዳትተወው ልጇ ሆነባት “ የተባለው ዓይነት ሆኖበት እንጂ ፈርቶ ወይም ኃይል የሌለው ሆኖ አይደለም።
ሦስተኛው ደግሞ አማራ በፈሪሃ እግዚአብሔርነቱም ይታወቃል። የእናቱ ልጅ ወንድሙ እንኳ ቢሆን ከሌላ ሰው ጋር ተጣልቶ ቢያየው ያስታርቅ እንደሆን እንጂ ለወንድሙ አድልቶ ሌላውን ሰው ለመጉዳት አይደፍርም። ምክንያቱም ሰማይና ምድርን የፈጠረ አምላክን ስለሚፈራ። በዚህም ለጊዜው እየተጎዳ ቢገኝም ነገ ግን ምላሹን ከሚያመልከው ፈጣሪ እንደሚያገኘው አያጠራጥርም።
የከሃዲ ደቂቀ ባንዳዎች ዋና ጠርናፊ ሟቹ መለስ ዜናዊ ልክ የዛሬ ዓመት ገደማ የፋሲካ በዓል አካባቢ፤ በጉራ ፋርዳ ይኖሩ የነበሩትን አማርኛ ቋንቋ ተናጋሪ ኢትዮጵያውያንን እንዲፈናቀሉ ሲያደርጉ ለራሳቸው ግን አንድ ሺህ ዓመት የሚኖሩ ይመስሉ ነበር።
ፓርላማ ላይ በትዕቢት ተወጥረው ጠረጴዛ እየደበደቡ ምድር አልበቃቸው ብሎ እንደነበር አይዘነጋም ።ዛሬ ግን በሕይወት የሉም ሁለት ሜትር በማትሞላ ጠባብ ጉድጓድ ውስጥ ተወስነው ቀርተዋል። የተከሉት መርዝ ግን አሁንም ገና አልጠወለገም።
ውቃቢያቸውን የተላበሱት መብራህቱ ገ/ሕይወት (በረከት ስምዖን) ከመጋረጃ በስተጀርባ በመሆን የሙት መንፈስ እየጠሩ፤ በአሻንጉሊሊታቸው ኃ/ማርያም ደሣለኝ አማካኝነት እኩይ ተግባራቸውን እያስፈጸሙ ይገኛሉ።
እዚህ ላይ መነሣት የሚገባው ዓቢይ ጉዳይ አለ፤ ይኸውም አቶ በረከት የአማራው ድርጅት የብአዴን ድርጅት፤ የወያኔ የበላይ ክንፍ ኃላፊ መሆናቸው ይነገራል። ነገር ግን ቆሜልሃለሁ የሚሉት የአማራ ሕዝብ በገዛ ሀገሩ እንዲህ በሕገወጥ መልክ ሀብትና ንብረቱን እየተቀማ ሲሳደድና ሲንገላታ፤ ሌላው ቢቀር ከሞራል አኳያ እንኳ ህሊናቸውን አይሰቀጥጣቸውም? የእርሳቸው ልጆችስ? የአሰፉ ልጆች ስለሆኑ ምንም አይድል? “የማትረባ ፍየል ዘጠኝ ትወልዳለች ልጆቿም ያልቃሉ እሷም ትሞታለች” እንደተባለው ይሆናል ብለው ይሆን? ግምታቸውን እውን ያድርግላቸው።
ወያኔ የውጭ ዜጋ ቢሆን ኖሮ እሱን አያድርገኝ፤ በየደረሰበት ዋጋው እየተሰጠው በወጣበት ይቀር ነበር እንጂ፤ እንዲህ እነሱ እንደፈለጉ ሲፏልሉ፤ አማራው አማርኛ ቋንቋ በመናገሩ ብቻ በሰላም ከየሚኖርበት፤ በድካሙ ያፈራውን ህብትና ንብረቱን በመንግሥት አካላት እየተቀማ ሲባረር ዝም አይልም ነበር። አዎ! መንግሥት ይለወጣል፤ ፖሊሲም ይቀየራል፤ ታዲያ ለሚያልፍ ቀን ሲል የሚወዳትን አገርና ወገኑን እኔ ከሞትኩ ሠርዶ አይብቀል አንዳሉት የባንዳ ልጆች አስተሳሰብ ቢሆንማ ኖሮ ያሳያቸው ነበር። ሡሪውም፤ ጀግንነቱም ወኔውም በደም ሥር ውስጥ ያለ መሆኑን ባንዶች የተገነዘቡት አይመስልም።
ገና ከመጀመሪያው ወያኔ ወገን ባይሆንና ወይም ተንኮሉ በግልጽ ቢታወቅ ኖሮ እንኳን ኢትዮጵያን መቆጣጠር ይቅርና ተከዜን መሻገር አይችልም ነበር። አሁንም ጊዜ ይለወጣል የሰውም ልብ እንዲሁ ይቀየራል ያን ጊዜ ወዮ!
ከሐዲ የባንዳዎች ስብስብና ፍርፋሪ ለቃሚ ውሾቻቸው፤ አማራውን ባትነካኩት ጥሩ ነው ሌላው ቀርቶ ለራሣችሁና ለልጆቻችሁ ስትሉ ባታሠቃዩት መልካም ነው። ያለበልዚያ ይህ ሕዝብ መሣሪያ የለውም ብላችሁ እንደዜጋ ሳይሆን እንደእንስሣ የምታዩት ከሆነ መሣሪያው እኮ ጠመንጃና ጥይት ብቻ አይደለም። ሐቅን ለያዘ ሰው ልብ ብቻ በቂ ነው። መሥሪያውማ ዙሪያ ገባው ሁሉ መሣሪያ መሆኑን ልትገነዘቡ ይገባል።
የአማራው ሕዝብ ግን ለአገሩና ለወገኑ ሲል፤ ንብረቱን እየተቀማ፤ ለረጅም ጊዜ ከኖረበት ቀዬ እንዲፈናቀል ሲደረግ አንገቱን ደፍቶ ለአገርና ለወገን ሲል መከራውን በትዕግሥት እየተቀበለ ይገኛል።
ምን ዓይነት አርቆ አስተዋይነት ነው? ምን ዓይነትስ ሆደ ሠፊነት ነው? ምን ዓይነት ታማኝነት ነው ?እጅግ በጣም ይገርማል! ይደንቃል።
በተለይ የትግራይ ምሁራን ይህንን እያያችሁና እየታዘባችሁ ዝም ማለታቸሁ ለምን ይሆን?
የአማራው መንገላታት ፤መሰደድ፤ በፍርድ መጓደል ከሚኖርበት ቅየው መፈናቀል፤ እውነት እናንተን ጤናና ሰላም ይሰጣችኋል? በእንደዚህ ያለ ወሳኝ ወቅት ላይ፤ እንኳን ወገን ለወገኑ ለባዕድም ቢሆን በሰብዓዊነት እንኳ ድምጽ ሊሆንለት በተገባ ነበር።
ምናልባት በጥቅም ተይዛችሁ እንኳ ቢሆን ሌላው ቀርቶ የዓለም አቀፍ መብቶች እንዲከበሩላቸው ብታደርጉ፤ ለራሳችሁና ለልጆቻችሁ እንዳደረጋችሁ ልትቆጥሩት በተገባ ነበር። ያለበለዚያማ ፈጽሞ ለማይቀረው ለውጥ ተዘጋጁ። የምትሠሩትን የምታውቁ አይደላችሁም።
ዛሬ በአማራው ላይ የምትፈጽሙት ሤራ ነገ እኰ ወደናንተም እንደሚቀሰር ረሳችሁት እንዴ? እንደዚህ ያለውን ተግባር የምትደግፉ ከሆነ ትግሬም ከተከዜ ማዶ እንጂ ወንዙን መሻገር የለበትም መባሉን ዘንግታችሁት ከሆነ እኔ ላስታውሳችሁ።
ወንድነቱንና ጀግንነቱን እንኳ ለአማራው ማንም ሊያስተምረው አይችልም። የአማራውን ትዕግስት እንደ ፍርሃት ቆጥራችሁ ከሆነም ትሳስታችኋል። እንኳን አሁን ቀደም ሲል ኰሎሎኔል መንግሥቱ ኃይለ ማርያም እንኳ በአንድ ወቅት ወያኔን አስመልክቶ ሲናገሩ “ ድንጋይ ቢወድቅብን ይሰብረናል፤ ብንወድቅበትም ይሰብረናል” ማለታቸው ይታወሳል። ምሁራን ናችሁና የዚህን ፈሊጣዊ አባባል ትርጉም ታጡታላችሁ የሚል ጥርጥር ባይኖረኝም፤ ገድለንም የምንጎዳው እኛ ሞተንም የምንጎዳው እኛ ማለታቸው ነበር። በዚያም ሆነ በዚህ የወገን የእርስ በእርስ ግጭት ዞሮ ዞሮ የሚጎዳው የአገራችንን ዕድገትና ልማት፤ እንዲሁም ሕዝባችንን በቀላሉ ሊጠገን ከማይችል ማኅበራዊና ሥነ ልቦናዊ ቀውስ ውስጥ መክተት ይሆናል ማለታቸው ነበር።
የአማራውም ሕዝብ እንዲህ የሚሠቃየውና እንደከብት አንገቱን በስለት የሚታረደው ለአገሩ አንድነትና ኅልውና ስለሚቆረቆርና፤ ችግሩ የጥርስ ደም ሆኖበት፤ ይህ የስቃይ ዘመን ያጥር ዘንድ ፈጣሪውን እየለመነ ይገኛል። የፖለቲካ ሀሁ የማያውቁ፤ ኢትዮጵያዊ መሆናቸውን እንጂ አማርኛ ቋንቋ ከመናገር ውጭ አማራ መሆናቸውን እንኳ የማያውቁ ንፁሕ ኢትዮጵያውያን በወራሪ ደቂቀ ባንዶች ስብስብ ቀጭን ትዕዛዝ ሲንገላቱና ሲሠቃዩ እያያችሁ ዓይኔን ግንባር ያድርገው፤ የዝሆን ጆሮ ይስጠኝ የምትሉ ከሆነ ነገ ከተጠያቂነት በፍጹም አታመልጡም።
ወዮ የትግሬ ምሁራን የሆናችሁ ሁሉ፤ አሁን ያለው የከሐዲ ባንዳ ስብስብ፤ ዘራፊ ሥርዓት በዚሁ ይቀጥላል ብላችሁ የምታስቡ ከሆነ ተሳስታችኋል። ሐቁን መረዳት ተስኗችሁ ከሆነ እንኳን እየዘረፉና እየቀሙ መኖር ይቅርና በወያኔ ሥርዓት እንደ እንጉዳይ የፈሉ ሚሊየነሮችና ባለቪላ ቱጃሮች፤ እንዲሁም ያለፉበትንና ያልደከሙበትን ውድ መኪና የሚያሽከረክሩ ሁሉ በአገር ውስጥ ብቻ ሳይሆን በውጭ አገር ሳይቀር በተለያዬ ዘመድና ጓደኛ ስም እንኳ የተቀመጠ ያለአግባብ ከሕዝብ የተዘረፈ ገንዘብ ሁሉ እንደሚመለስ አትጠራጠሩ። እናንተም የሚጠብቃቸሁ ፍትህ ስለሚሆን እንደየተግባራችሁ የየሥራችሁን ማግኘታችሁ አይቀርም። ስለዚህ ከአሁኑ ወደ ኅሊናችሁ ተመልሳችሁ ከተገፋው ሕዝብ ጎን ልትቆሙ ይገባል።

No comments:

Post a Comment