Mar 17, 2013

አማረ አረጋዊ እሳት መሞቅ ምንድን ነዉ??? በአሁኑ ጊዜ በአገር ውስጥም በውጭ አገርም በሥልጣን ላይ ያለውን መንግሥት የሚጠሉና የሚቃወሙ ኃይሎች አሉ፡፡ በፓርቲ፣ በቡድንና በግለሰብ ደረጃ፡፡ እነዚህን መጠጋት መዋሃድ አብሮ መስራት ይሆን ???


ምንም ቢበርደው ቅቤ እሳት አይሞቅም!   አማረ አረጋዊ


ቅቤዉ ማን ነዉ???  TPLF ይሆን?

እሳት መሞቅ ምንድን ነዉ???  በአሁኑ ጊዜ በአገር ውስጥም በውጭ አገርም በሥልጣን ላይ ያለውን መንግሥት የሚጠሉና የሚቃወሙ ኃይሎች አሉ፡፡ በፓርቲ፣ በቡድንና በግለሰብ ደረጃ፡፡አማረ አረጋዊ ከተናገረዉ  እነዚህን መጠጋት መዋሃድ አብሮ መስራት በኢሳት ቃለመጠየቅ ማድረግን ይሆን?
ብርዱስ ምንድን ነዉ??? አሁን TPLF  ያጋጠመዉ ችግር ይሆን?  

እንደ ግለሰብም፣ እንደ ቡድንም፣ እንደ ድርጅትም፣ እንደ ሕዝብም፣ እንደ አገርም ምን ጊዜም ችግር ያጋጥመናል፡፡ ለምን ችግር አጋጠመ ብሎ መደናገጥ ፋይዳ የለውም፡፡ ችግሩን አውቆ ለመፍትሔው መረባረብና መታገል እንጂ፡፡
ግን! ነገር ግን! መፍትሔ ስናፈላልግ ችግሩን የሚፈታ እንጂ በመፍትሔ ስም የባሰ ችግርና ጥፋት የሚያስከትል ዕርምጃ እንዳንወስድ ወይም እንዳንወስን መጠንቀቅ አለብን፡፡ ቅቤ ቢበርደው መፍትሔው እሳት መሞቅ አይሆንምና፡፡

በአሁኑ ጊዜ በአገር ውስጥም በውጭ አገርም በሥልጣን ላይ ያለውን መንግሥት የሚጠሉና የሚቃወሙ ኃይሎች አሉ፡፡ በፓርቲ፣ በቡድንና በግለሰብ ደረጃ፡፡ ለምን መንግሥትንና ገዥውን ፓርቲ ትጠላላችሁ፣ ትቃወማላችሁ የሚል ጥያቄ አይነሳባቸውም፡፡ በሰላማዊና በሕጋዊ መንገድ እስከተንቀሳቀሱ ድረስ መቃወም ሕገ መንግሥታዊ መብታቸው ነውና፡፡ እንዲያውም እባካችሁ ተጠናክራችሁ ተቃወሙ እንላለን እንጂ ለምን ትቃወማላችሁ አንልም፡፡

ግን! ነገር ግን! የምንለው ነገር አለ፡፡ እባካችሁ ተቃወምን ብላችሁ ራሳችሁን፣ አገርንና ሕዝብን ለጠላትና ለአደጋ የሚዳርግ መስመር አትከተሉ፤ ውሳኔ አትወስኑ፤ ዕርምጃ አትውሰዱ እንላለን፡፡ ምንም ቢበርደው ቅቤ እሳት አይሞቅም፡፡ እሳት መሞቅ ከብርድ የሚከላከል ቢመስልም ከቅቤ ባህርይ አንፃር ሲታይ ግን እሳት ከብርድ የሚያድን ሳይሆን በማቅለጥ የቅቤን ህልውና ያሳጣል፡፡

በመቃወም ስም የሃይማኖት ቅራኔን ማባባስ፣ በመቃወም ስም የብሔር ብሔረሰቦች ቅራኔን ማፋፋም፣ በመቃወም ስም የጠላት መሣሪያ መሆን፣ በመቃወም ስም ኢትዮጵያን በማዳከም መሳቂያና መሳለቂያ ማድረግ የሚቃወመውን ኃይል የሚያጠናክረው ሳይሆን የሚያቀልጠው ነው፡፡ በረደኝ ብሎ እሳት የሚሞቅ ቅቤ እንደሚቀልጥ ሁሉ፡፡

ኢሕአዴግ አራት አባል ድርጅቶችን ያቀፈ ነው፡፡ በእያንዳንዱ አባል ድርጅት ውስጥና በአራቱ ድርጅቶች መካከል የሐሳብ ልዩነት ሊኖርና ሊፈጠር ይችላል፡፡ ለምን ልዩነት ታየ? ለምን ልዩነት ተፈጠረ? ተብሎ አይጠየቅም፡፡ የሐሳብ ልዩነት የትም ያለ ነው፡፡ ሕገ መንግሥታዊ መብት ነው፡፡ ከዚያ አልፎም አንድ ፖለቲካ ድርጅት ውስጥ በመሆን በዓላማ አንድ ቢኮንም፣ ዓላማውን ለማሳካት የሚሻለው መንገድ ይህ ነው የለም ያኛው ነው ብሎ መከራከርና መለያየት ያለ ነው፡፡ ከሌለ ይገርማል እንጂ መኖሩ ጤናማ ነው፡፡

ግን! ነገር ግን! በተፈጠረው ልዩነት፣ መራራቅና አለመግባባት ሕገ መንግሥታዊ፣ ሰላማዊ፣ ሕጋዊ፣ ዴሞክራሲያዊና ትክክለኛ የፓርቲ ውስጥ የትግል ዘዴ ከመከተል ይልቅ ያዙኝ ልቀቁኝ ከተባለ፣ መጠቃቃት እንደ ዘዴ ከተወሰደ፣ መኮራረፍ እንደ አማራጭ ጥቅም ላይ ከዋለ፣ ውስጥ ለውስጥ የስም ማጥፋትና የኔትወርኪንግ እንቅስቃሴ ከተጀመረ ፓርቲውን፣ መንግሥትንና አገርን ለአደጋ የሚዳርግ ይሆናል፡፡ ከብርድ ለመዳን ብሎ እሳት ሞቆ ቀልጦ የሚቀር ቅቤ መሆንን ያስከትላል፡፡

በግሉ ዘርፍና በሲቪል ማኅበረሰቡ ውስጥ የሚንቀሳቀሱ አካላትና ድርጅቶችም በተወሰነ ጊዜ የተወሰነ ችግር ሊያጋጥማቸው 
ይችላል፤ ያለ ነው፡፡ የግብር አከፋፈል ችግር ሊያጋጥም ይችላል፡፡ ከደንበኞች ጋር ውል ተዋውሎ ውሉን ለመፈጸም ችግር ውስጥ ሊገባ ይችላል፡፡ ገንዘብ ሊያጥር ይችላል፡፡ ተጠያቂነትና መከሰስ ሊከተል ይችላል፡፡ ይህንን በሕጋዊና ሥርዓት ባለው መንገድ ለመፍታት የድርሻን መጫወት እንጂ፣ ተጨማሪ ወንጀል ብፈጽም መፍትሔ ይሆናል፣ ጉቦ ብሰጥ ይሰረዝልኛል፣ ከአገር ብጠፋ የት ያገኙኛል እየተባለ አኩኩሉ ጨዋታ ውስጥ የሚገባ ከሆነ መጨረሻው  በሕግም፣ በመንግሥትም በወንጀል ተፈላጊ ሆኖ መቅለጥና ተዋርዶ መጥፋት እንጂ መፍትሔ አይሆንም፡፡ የበረደው ቅቤ እሳት ቢሞቅ መፍትሔ አያገኝምና፡፡

እያነሳነው ያለው ቁም ነገር ግልጽ ነው፡፡ ችግር የትም ምንጊዜም ያጋጥማል፡፡ አፈታት ላይ ግን በሳል፣ አስተዋይ፣ ሕጋዊና ሰላማዊ ዕርምጃ ያስፈልጋል፡፡ መፍትሔ እናገኛለን ብለን ወደባሰ ችግርና ጥፋት እንዳንገባ እንጠንቀቅ ነው፡፡ ይህ ሁላችንንም የሚመለከት ቢሆንም በመንግሥትና በገዥው ፓርቲ ሲመጣ ግን የበለጠ ልዩ ጥንቃቄ ያስፈልጋል፡፡

በአሁኑ ጊዜ የውጭ ምንዛሪ ችግር አለ፡፡ የገንዘብ እንቅስቃሴ ዝግመት አለ፡፡ መቀዝቀዝ አለ፡፡ የብድርና የዕርዳታ ማነስም አለ፡፡ በአንፃሩ የዕቅዳችንና ፕሮጀክታችን ግዝፈትና አስቸኳይነት አለ፡፡ መሮጥ የምንፈልገው ርቀት አለ፡፡ አላስሮጥ የሚል እንቅፋትም አለ፡፡ አፈታት ላይ እንጠንቀቅ ነው፡፡ መንግሥት የውጭ ምንዛሪ ችግር አለ ሲባል የለም ‹‹በሽበሽ›› ነው እያለ ከሚመልስ ይልቅ፣ ረጋና ኮራ ብሎ ችግሩን እያጠናና እያመነ መፍትሔ ይስጥ ነው፡፡ አለበለዚያ የኋላ ኋላ ችግሩ የማንሸከመው ይሆናል፡፡

በኢትዮጵያ ላይ የሚያነጣጥሩ ጥላቻዎች ካልተጠበቁ ወገኖች ባልተጠበቁ ክብደቶች እየተወረወሩብን ናቸው፡፡ ችግር የለም የአፍ ወለምታ ነው፣ ወይም ችግር የለም የግለሰብ አስተያየት ነው እያልን የምንጓዝ ከሆነ የሚቆጨን ሁኔታ ውስጥ ልንገባ እንችላለን፡፡ በተለይም ኢሕአዴግ አሁን ወደ ጉባዔ ሊገባ ነው፡፡ ራሱን የሚገመግምበት መድረክ ነው፡፡ ምርጫ የሚያካሄድበት ወቅት ነው፡፡ አቋሞችን ይፋ የሚያደርግበት መድረክ ነው፡፡ ወይ ተጠናክሮ ሊወጣ ወይ ችግሩን ሳያይ ቀርቶ ተዳክሞ ሊንገዳገድ የሚችልበት መንታ መንገድ ላይ ነው፡፡

ራሱም የሚፈልገው ሕዝብም የሚመኘው ተጠናክሮ መውጣቱንና ችግር መፍታቱን ነው፡፡ ነገሩ ግን ቀላል አይደለም፡፡ በአባላት መካከል የአመለካከት ልዩነት ይኖራል፡፡ የሥልጣን ፈላጊነት ባህርይ ሊከሰት ይችላል፡፡ የኔትወርኪንግ መጠላለፍ ሊከሰት ይችላል፡፡ እነዚህ ግን በቀላሉ የሚፈቱ ችግሮች አይደሉም፡፡ በሳል፣ ኃላፊነት የሚሰማውና ሕዝቡን የሚያገለግል ወገን ይህን ለመፍታት አያስቸግረውም፡፡ ብዙ ችግር እየፈታ የመጣ ነውና፡፡

ግን! ነገር ግን! በኃላፊነት፣ በሕዝባዊነት፣ በዴሞክራሲያዊነት፣ በሕጋዊነትና በሕዝባዊ የአደራ መንፈስ የማይጓዝና የማይሠራ ወገን የበላይነት ከያዘ የተጀመረው ሁሉ ተበላሽቶ ከመራመድ ወደ መንሸራተት ሊያመራ ይችላል፡፡

ችግር አለ አያስደንግጠን፡፡ መፍትሔው ላይ ግን እንረባረብ፡፡ እንዳንሳሳት እንጠንቀቅ፡፡ እንተባበር አንድ እንሁን በማለት ገዢው ፓርቲና መንግሥት ሊረባረቡ ይገባል፡፡ የተሳሳተ መፍትሔ ሊያስከትል የሚችለው አደጋ ከወዲሁ ሊታይ ይገባል፡፡

ውጤቱ ችግር ፈተው ተጠናክረው አገርንና ሕዝብን አጠናክሩ የሚያስብል እንጂ፣ ‹‹ቅቤ በርዶት እሳት ሞቀ›› ቀለጠ የሚያስብል መሆን የለበትም፡፡

ከእኔ ልጅ ጋር ሐረር ከተማ ውስጥ አራት ሰው በፓሊስ ነዳጅ እየተደፋበት በእሳት ተቃጥሎ ሞቷል” ወ/ሮ ኢትዮጵያ ይልማ



“ልጄ በእሳት ተቃጥላ እንድትሞት ተደርጋ፣ ቤቴን ተነጥቄና ንብረቴ ወድሞ ከሀረር ተባረርኩ” ሲሉ
 አንዲት የ67 አመት ባልቴት በተለይ ለፍኖተ ነጻነት ጋዜጣ አስታወቁ፡፡
ወ/ሮ ኢትዮጵያ ይልማ የሚባሉት እኚሁ እናት የ75 ዓመት አዛውንት የሆኑት ባለቤታቸውም እንደ  እሳቸው ሁሉ ጎዳና ላይ መውደቃቸውን ለፍኖተ ነፃነት ጋዜጣ ዘጋቢ ከዕንባቸው ጋር እየታገሉ አስረድተዋል፡፡
“በሐረር ከተማ ቀበሌ 17 ውስጥ ከ30 ዓመት በላይ ኖሬ፤ ሀብትና ንብረት አድርቼ እኖር ነበር  አሁን ግን በአካባቢው  እንዳልኖር ተደርጌያለሁ” የሚሉት ወ/ሮ ኢትዮጵያ ይልማ “ከ30 ዓመት በላይየኖርኩበትን ቤቴን የወረዳው አስተዳዳሪ እና የወረዳው ፓሊስ አዛዥ አስጠርተው ቤትሽን ለወ/ሮ አኒሳ መሐመድ ሸጠሽ ግቢውን እንድታስረክቢያት አሉኝ፡፡ እኔ ቤቴን የመሸጥ ሐሳብ የለኝም፡፡ ቤቴን ሸጪ የት እወድቃለሁ? አልሸጥም አልኳቸው እንቢ ካልሽ ከአገራችን እናባርራሻለን በገንዘብ አልሸጥም ካልሽ በባዶሽ ተባረሽ ወደ አገርሽ
ትሄጃለሽ አሉኝ፡፡ እኔ ሌላ አገር የለኝም የምሄድበትም ቦታ የለኝም መንግስት ባለበትአገር ቤትሽን ተቀምተሽ ውጪ የሚለኝ የለም ብዬአቸው ተመለስኩኝ” በማለት የችግሩ መነሻ ነው ያሉትን ጉዳይ ወደኋላ መለስ ብለው ያስረዳሉ፡
 ጎስቋላዋ የ67 ዓመት ባልቴት በመቀጠልም “በማግስቱ እኔ ቡና አፍልቼ፣ ባለቤቴም ጫማውን
 አውልቆ ፍራሽ ላይ አረፍ ብሎአል፤አንድ ፓሊስ በሩን በሰደፍ እና በእርግጫመቶት በሩን በረገደው፡፡
ምንድነው? ብለንስንወጣ ከ30 በላይ ፓሊሶች ቤታችንንከበውታል፡፡ ይህች ናት፡፡ ነይ ውጭ!
ብሎለሁለት ሶስት ሆነው ጎተቱኝ፡፡ እባካችሁ ምን አደረኩ ብዬ ስለምናቸው አንቺ ለህግ አልገዛ
 ያልሽ አመጸኛ ነሽ! ወንጀለኛ ነሽ እያሉ መሬት ለመሬት ጎተቱኝ፡፡ እባካችሁ ምንም የሰራሁት
ወንጀል የለም ብዬ ጮኩኝ፡ ፡ ጎረቤት ተሰበሰበ ምንድነው ብሎ ጠየቀ ማንም ምላሽ አልሰጠም”
የሚሉት ወ/ሮ ኢትዮጵያ ይልማ ሟች ልጃቸውን በሀዘን ተውጠው እያስታወሱ ይቀጥላሉ “ልጄ
 ባል አግብታ የምትኖረው ሌላ ቦታ ነው፡፡ ቀን ቀን ምግብ እየሰራች ትሸጣለች ፓሊሶች እናትሽን
 ከበው እየደበደቡ ናቸው ብሎ ጎረቤት ሲደውልላት ሮጣ መጣች፡፡ ደርሳ ምን አድርጋ ነው ብላ
ብትጠይቅ ቤቱን አስረክቢ ስትባል እንቢ ብላ ነው አሏት፡ ፡ የተወለድንበትና ያደግንበትን ቤት
ከህግ ውጭ እንዴት እንነጠቃለን ብላ ስትጮህጥላው ሄዱ” በማለት በለቅሶ ያስረዳሉ፡፡
ወ/ሮ ኢትዮጵያ ይልማ በመቀጠልም “ያንለቱኑ ማታ ልጄ ምግብ የምትሸጥበት ቦታ
ሁለት ሰዎች ተመጋቢ መስለው ከገቡ በኋላ (ረመዳን የተባለ ፓሊስና እንዳለ ግርማ የተባለ ወጣት)
ቤቱን አስረክቡስትባሉ አናስረክብም የምትሉት ለምንድነውብለው ረመዳን ልብሷና ሰውነቷ ላይ
ጋዝሲደፋባት እንዳለ ግርማ የተባለው ላይተርለኩሶ አቃጥለዋታል፡፡ ሳትሞት ሆስፒታልደርሳ ነበር፡፡
 በማግስቱ አዲስ አበባ አምጥቼ ላሳክም መኪና ተከራይቼ ይዤ ስወጣ ፓሊስ እዚህ ትታከም እንጂ
 ከሐረር አትወጣም ብሎ ከለከለኝ፡፡ እኔም ገንዘብ ካለኝ እንኳን አዲስ አበባ አሜርካን ወስጄ ባሳክም
ለምን እከለከላለሁ ብዬ ብጮህ ባለቅስ ማንም ሊደርስልኝ አልቻለም፡፡ ልጄ ህክምና አጥታ ሞተች፡፡”
ብለዋል፡፡
ባልቴቷ ከልጃቸው ሞት በኋላ የደረሰባቸውን በምሬት ያወጋሉ “እኔንም ከቤቴ አስወጥተው ቦታውን ሺጭላት
ላሏት ሴት ሰጧት፡ ፡ አሁን ቦታዬ ላይ ፎቅ እየተገነባ ነው፡፡ እኔና ባለቤቴ ግን ጎዳና ተጣልን፡፡
የአካባቢው ህብረተሰብ አዋጥቶ የሰጠኝን 3ሺ ብር እንድፓሊስና አንድ ደላላ መጥተው ነጠቁኝ፡፡
ሐረር ውስጥ አደሬ ወይም ኦሮሞ ካልሆንክ አቤት የሚባልበት ቦታ የለም፡፡ አማራ ነው ከተባለ ሁሉም
 ባለስልጣን በደረሰበት ግፍና ስቃይ ይስቅበታል፡፡ በደርግ ጊዜ የሐረር ፓሊስ አዛዥ ትግሬ ነበር፤
የማረሚያ ቤትአዛዥም ትግሬ ነው፡፡ የከፍተኛ ፍርድቤት ዳኛ ትግሬ ነው፡፡ ለምን ትግሬ ሆነያለ አንድም
 ሰው የለም፡፡ ዛሬ በሀረርበየትኛውም መስሪያ ቤት አማራ ባለስልጣንየለም፡፡ ባለቤቴ ኦሮሞ ነው፡፡
ልጆቼም ኦሮሞ ናቸው፡፡ እኔ አማራ በመሆኔ ብቻ ይህ ሁሉ ጉዳት ተፈጸመብን፡፡” የሚሉ ወይዘሮዋ
የተፈፀመባቸው የሰብአዊ መብት ጥሰት ዘራቸውን መሰረት ያደረገ መሆኑን ያስረዳሉ፡፡ አክለውም
 “አዲስ አበባ መጥቼ ለእንባ ጠባቃ ተቋም አመለከትኩኝ፡፡
ፌደራል እንባጠባቂ ተቋም እንዴት እንዲህ ይፈጸማል ብለው ይዘውኝ ሐረር ተመለሱ፡፡ የቤቴካሳ
 እንዲከፈለኝ ተወሰነልኝ፡፡ የክልሉ ባለስልጣናትም እሺ ይፈጸምሎታል ብለው ቃል ገቡልኝ፡፡
እንባ ጠባቂዎቹ ወደ አዲስ አበባ ተመልሱ፡፡ እነሱ ከተመለሱ በኋላ ግን ምንም መፍትሄ አልሰጡኝም፡፡
 በድጋሚ አዲስ አበባ መጥቼ ለእንባ ጠባቂ ተቋም ባመለክት እነሱም ውሳኔያቸውን እንደ አጀማመራቸው ሊያስፈጽሙልኝ አልቻሉም፡ ፡ ጉዳዬንም ለመስማት ፍቃደኛ አልሆኑም፡፡ ” በማለት የበደላቸውን
ስፋት ለፍኖተ ነፃነት ዘጋቢ በዝርዝር አስረድተዋል፡፡
“ዛሬ እኔ አዲስ አበባ ላይ ባለቤቴ ደግሞሐረር ላይ ጎዳና ላይ ነን፡፡ መፍትሔ ማግኘት አልቻልኩም”
 ሲሉ ተስፋ መቁረጥና ምሬት ተሞልተው በለቅሶ የመንግስት ያለህ ... የህዝብ ያለህ በማለት
ጥያቄቸውን ያቀርባሉ፡፡
 የወ/ሮ ኢትዮጵያ ይልማን ጉዳይ አስመልክቶ የፌደራሉ እንባ ጠባቂ ተቋም ለሐረሪ ክልላዊ
መንግስት ጸጥታ ቢሮ የጻፈውን ደብዳቤ እንደተመለከትነው ደብዳቤው ከዚህ በፊት ስለጉዳዩ
ተጠይቆ መልስ አለመስጠቱን በማስታወስ አሁን በድጋሚ በ 15 ቀን ውስጥ መልስ እንዲሰጥ ያለበለዚያ
 በህግ በተሰጠው ስልጣን መሰረት አስፈላጊውን እርምጃ እንደሚወስድ የሚገልጽ ነው፡፡ ሆኖም
 የእምባ ጠባቂ ተቋም ውሳኔ ባልቴቷንና ባለቤታቸውን ከጎዳና ተዳዳሪነት የሚታደግ አልሆነም፡፡
በጉዳዩ ላይ የፊደራል እንባ ጠባቂ ተቋም አስተያየት እንዲሰጥበት ወደ ተቋሙ ህዝብ ግንኙነት
ክፍል በማምረት ባለሙያዎችንም አነጋግረን ነበር፡፡ በቅድሚያ ያነጋገርናቸው የህዝብ ግንኙነት
ባለሞያ ጉዳዩን ከስሙንና በእጃችን ያለውን መረጃ ከተመለከቱ በኃላ ወደ ሌላው የህዝብ ግኑኝነት
ባለሙያ መሩን፡፡እሳቸውም በተመሳሳይ ሁኔታ ማስረጃችንን ከተመለከቱ በኃላ ይህንን ጉዳይ
የሚያውቁት ዋና አማካሪው አቶ ቀነአ ሶና ናቸው፡፤ እሳቸውን አነጋግሩ አሉን፡፡ አቶ ቀነአን በወቅቱ
ማግኘት አላቻልንም፡ ፡ በሌላ ጊዜ ተመልሰን ቢሮአቸው ያሉትን የተቋሙን ሰራተኛ አቶ ቀነአን እንደምንፈልግ አስረዳናቸው፤ አቶ ቀነአን ወደ መስክ ወጥተዋል፡፡ ሰሞኑን ቢሮ አይገቡም አሉን፡ ፡ በዚህ ምክንያት
የፌደራሉን እንባ ጠባቂ ተቋም አስተያየት ማካተት አልቻልንም፡፡ ጉዳዩ ተከቷል ወደ ተባለለት ወረዳ
ፖሊስ ደወልን የሐኪም ወረዳ ፖሊስ ወንጀል መከላከል ሀላፊ የሆኑትን ሳጂን ተሾመ  ሰይፉን አግኝተናቸዋል፡፡
 ወ/ሮ ኢትዮጵያ ይልማ ደረሰብኝ የሚሉትን በደል ወቅቱን ጠቅሰንም አስረድተናቸዋል፡፡ ሆኖም
 ሳጂን ተሾመ ሲመልሱ ‹‹እኛ ፖሊሶች በየሁለት ዓመቱ እንቀያየራለን፡፡ አሁን በዚህ ወረዳ ያለነው
 ከሁለት ዓመት ወዲህ ተዛውረን የመጣን ነን፡፡ ስለዚህ ጉዳይ የሚያውቅ ሰው የለም፡፡ በአሁኑ ወቅት
 በወረዳችን ሮመዳን የሚባል ፖሊስ የለም፡፡ ምናልባት የወረዳው መስተዳድር የሚያውቁት ነገር ካለ
 እነሱን ብትጠይቁ ይላል፡፡›› በማለት መልሰውልናል፡፡ በአሁኑ ጊዜ ያሉትን የወረዳውን አስተዳዳሪ
አቶ ኢስማኤልንም ስለጉዳዩ ጠይቀን በሰጡን መልስ ‹‹እኔ በቅርብ ጊዜ ነው የመጣሁት ስለዚህ
ጉዳይ የማውቀው ነገር የለም፡፡ የሚያውቁት ነገር ካለ ከእኔ በፊት የነበሩትን ጠይቋቸው›› ብለውናል፡፡
ከእሳቸው በፊት የወረዳው አስተዳዳሪ የነበሩትን አቶ ጀማል አህመድን አፈላልገን ጠየቅናቸው፡፡
 “እኔ ድርጊቱ ተፈፀመ በምትለኝ ወቅት እዚያ ወረዳ አልሄድኩም፡፡ ስለዚህ ጉዳይ የማውቀው ነገር የለም፡፡
 ከእኔ በፊት የነበረውን ሰው አፈላልጋችሁ ጠይቁ ብለውናል፡፡” ከእሳቸው በፊት የነበሩትን አስተዳዳሪ
 ማንነትና አድራሻ ማግኘት ባለመቻላችን ዜናውን በተገቢው ሁኔታ ሚዛናዊ ማድረግ አልቻልንም፡፡ 

ያርበኛ ልጀች ግራዚያኒን በመቃወም የተቃውሞ ሰልፉ በቅስቀሳ ላይ እያሉ በባንዳ ልጆች እየተለቀሙ ታሰሩ




ዛሬ ከጠዋቱ 3 ሰዓት ለኢትዮጵያ ተቆርቋሪ 
የግል ተነሳሽነት ማህበር፤ ሰማያዊ ፓርቲ እና ባለራዕ ወጣቶች ማህበር በጋራ በመሆን“ለፋሽስቱ የጦር ወንጀለኛ ለማርሻል ግራዚያኒ ክብር መስጠት የአባቶቻችን መስዋዕትነት ማራከስ ነው” በሚል የተጠራውን ሰልፍ አምባገኑ የኢህአዴግ መንግስት በርካታ የፌደራል ፖሊስ፣ የደህንነት አባላትን እና የአዲስ አበባ ፖሊሶችን በማሰማራት ሲበትን፤ የተቋማቱን ከፍተኛ አመራሮች፤ ታዋቂ ግለሰቦች እና በርካታ ወጣቶች ጨምሮ ቢያንስ 34 ሰዎች አስሯል የታሳሪዎች ቁጥር አሁንም በመጨመር ላይ ነው፡፡
እንዲሁም በትላንትናው እለት ለተቃውሞ ሰልፉ የቅስቀሳ ስራ ሲሰሩ ከነበሩት ውስጥ2 የሰማያዊ ፓርቲ የስራ አስፈጻሚ አባላትን እንዲሁም የባለራዕይ ወጣቶች የስራ አስፈጻሚ አባላትን ጨምሮ 8 ሰዎችን አስረዋል፡፡





በአሁኑ ሰአት በእስር ላይ የሚገኙት እና ስማቸው የተገኘ

1. ዶ/ር ያዕቆብ ኃ/ማርያም
2. አቶ ታዲዎስ ታንቱ
3. አቶ ይልቃል ጌትነት (የሰማያዊ ሊቀመንበር)
4. ስለሺ ፈይሳ (የሰማያዊ ም/ሊቀመንበር)
5. ይድነቃቸው ከበደ (የሰማያዊ የህግ ጉዳይ ሀላፊ)
6. ሀና ዋለልኝ (የሰማያዊ የሴቶች ጉዳይ ሀላፊ)
7. ጌታነህ ባልቻ (የሰማያዊ የድርጅት ጉዳይ ሀላፊ)
8. ብርሀኑ ተክለያሬድ (የባለራዕይ ወጣቶች ተ/ምክትል ሊቀመንበር)
9. ያሬድ አማረ (የባለራዕይ ወጣቶች ማህበር ጸሀፊ)
10. ኤልሳቤጥ ወሰኔ
11. ሰለሞን ወዳጅ
12. ወይንሸት ንጉሴ
13. እየሩሳሌም ተስፋው
14. ለገሰ ማሞ
15. ትዕግስት ተገኝ
16. አማኑኤል ጊዲና
17. አለማየሁ ዘለቀ
18. አገኘሁ አሰገድ
19. ሻሚል ከድር
20. አሸብር ኪያር
21. ጌታቸው ሽፈራው
22. ግሩም አበራ
23. አቤል ሙሉ
24. ዩሀንስ ጌታቸው
25. ስማቸው ተበጀ
26. ፍቃዱ ወንዳፍራው
27. ባህረን እሸቱ
28. ሄኖክ መሀመድ
29. እንቢበል ሰርጓለም
30. አለማየሁ በቀለ
31. ዩናስ
32. የመኪናው ሹፌር
33. ዮዲት አገዘ
34. ጥላዬ ታረቀኝ

ለህወሓት ማእከላዊ ኮሚቴ ስልጣን የነብር ጭራ ሆናባቸዋለች

ትናንት የህወሓት ማእከላዊ ኮሚቴ ኣባላትና ተሰሚነት ያላቸው የፓርቲው ሰዎች በከፍተኛ ንትርክ የታጀበ ስብሰባ ማድረጋቸው ጠቅሼ ነበር። የስብሰባው ኣጀንዳም ለሚቀጥለው የፓርቲው ድርጅታዊ ጉባኤ ስብሰባ ኣጀንዳ መያዝ (ና ማስያዝ) ሲሆን እንደዉጤትም ብዙ እንዳልተስማሙ ተገልፀዋል።

በስብሰባው መግባባት ካልቻሉበት ነጥብ ኣንዱ “የመተካካት መርህ” ነው። “መተካካት” መኖር እንዳለበትና በጉባኤው ከሚተገበሩ ኣንዱ እንደሆነ ብዙ ልዩነት የለም። በመተካካት ኣፈፃፀም ላይ ግን የከረረ ልዩነት (ጠብ ያስከተለ) ኣለ። እስካሁንም ኣልተግባቡም።

የልዩነቱ ነጥብ፣ “በህወሓት ማእከላዊ ኮሚቴ የመተካካት ኣፈፃፀም በምን መስፈርት ይተግበር? በትግል ቆይታ፣ (የህወሓት ነባር ታጋዮች ይወገዱ ወይስ ይቀጥሉ?) በዕድሜ፣ በብቃት ወይስ በስልጣን ረዥም ግዜ በመቆየት ?” የሚሉ ነጥቦች ሊያግባቧቸው ኣልቻሉም። 

ኣብዛኞቹ የማእከላዊ ኮሚቴ ኣባላት፣ ‘መተካካት በወጣትና ሽማግሌ (በዕድሜ) መሆን የለበትም’ ብለው ይከራከራሉ። በስልጣን የመቆየት ፍላጎት ኣላቸው። እያንዳንዱ የማ/ኮሚቴ ኣባል ከስልጣኑ (ከሓላፊነቱ) ሊወገድ እንደሚችል በመስጋት የየራሱ ተወካይ (ጥቅም ኣስከባሪ) ወደ ኮሚቴው ለማስመረጥ ተዘጋጅተዋል። 

ለምሳሌ ቴድሮስ ሓጎስ (ከጀነራል ሰዓረ መኮነን ጋር በመመካከር)፣ ኣልጋ ወራሹ ዶክተር ክንደያ ገበረሂወት (የኣሁኑ የመቀሌ ዩኒቨርስቲ ተጠባባቂ ፕረዚደንት) መሆኑ ኣሳውቀዋል። ተክለወይኒ ኣሰፋ (የማረት ዳይሬክተር) ታጋይ በላይ ገበረዮውሃንስ እንዲመረጥለት መልምለዋል። ጌታቸው ረዳ (በጠቅላይ ሚኒስተር ቢሮ የህዝብ ግንኙነት ….. ምናምን ? ሓላፊ) ከኣዲስ ኣበባ በመጡ ሰዎች ለማእከላዊ ኮሚቴ ኣባልነት ታጭተዋል። ባጭሩ የማእከላዊ ኮሚቴ ኣባላት (ከጉባኤው በፊት) እየተመረጡ ናቸው። እርስበርስ መግባባት የለም እንጂ።

እያንዳንዱ የማእከላዊ ኮሚቴ ኣባል የራሱ ደጋፊዎች ለማፍራትና ለመመረጥ ጥረት እያደረገ ይገኛል። ዶር ቴድሮስ ኣድሓኖም (ከነ ኪሮስ ቢተው፣ ኣባይ ፀሃየና ሌሎች) የሽምጋይነት ሚና ይጫወታል። 

ፀጋይ በርሀና ኣርከበ ዕቁባይ በተለያዩ ኣከባቢዎች (ካፌዎች፣ መጠጥ ቤቶች, Coffee House …) እየተዘዋወሩ የህዝቡ ስሜት (በህወሓት ያለው ግምት) እየፈተሹ ሲሆን በብዙ መቶዎች የሚቆጠሩ ሲቪል የለበሱ የደህንነት ሰዎች፣ የፖሊስና መከላከያ ሰላዮች (እንዲሁም ፈጥኖ) የህዝቡንና የኣባላቱ መንፈስ እንዲያጠኑ ታዝዘዋል። ፀጋይ በርሀ ከትግራይ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ዘኣማኑኤል ለገሰ (ወደ ሻምበል) ጋር በመሆን ስላልታወቀ ጉዳይ በተደጋጋሚ ለብቻቸው እንደሚነጋገሩ የዓይን እማኞች ጠቁመዋል።

የነ ኣባይ ወልዱ ቡድን ግን ያላቸው የክልል ስልጣን ተጠቅመው እስከ ቀበሌ ወርደው ድጋፍ ለማሰባሰብ ሞክረዋል።

የመቀሌ ዩኒቨርስቲ የህወሓት ኣባላት በመተካካቱ ኣፈፃፀም ተስፋ ቆርጠዋል።

እኔም እላለሁኝ፣

በሙስና በበሰበሰ ስርዓት የመተካካት መርህ ዉጤት ኣያመጣም። ምክንያቱም መሪዎቹ በሙስና ከተዘፈቁ ብቁና ለውጥ ሊያመጣ የሚችል ተተኪ ወጣት የመመረጥ ዕድሉ ኣነስተኛ ነው። ወጣት ተተኪዎቹ ማነው የሚመርጣቸው? ኣለቆቻቸው ናቸው (ገምግመው የሚያቀርብዋቸው)። ሲመለምሉ ታድያ ለነሱ ታማኝ ሁኖ ያገለገለ፣ ሙስና ሲበሉ የማያጋልጣቸው (ወይም የተባበራቸው ……. ኣብሮ ሙስና የበላ ቢሆን ይመረጣል ምክንያቱም በኋላ እንዳያሳስራቸው)፣ የነሱ ዘመድ የሆነ (እንደማይጥላቸው የሚተማመኑበት)፣ ባጭሩ የራሳቸው ኣምሳያ ተክተው ይሄዳሉ (ተተኪዎች የመመልመል ስልጣን ስለተሰጣቸው)።

ስለዚ መተካካት እንኳ ቢደረግ (ዘሮ ዘሮ ከእጃቸው ስለማይወጣ) ስርዓቱ የሚፈለገው የመልካም ኣስተዳደርና የኢኮኖሚ ልማት ማስመዝገብ ኣይቻለውም። ለውጥ ለማምጣት መጀመርያ ሙስና ማጥፋት ኣለባቸው፤ ሙስና ካጠፉ ደግሞ ገዢው ፓርቲ ጠፋ ማለት ነው። ምክንያቱም ፓርቲው የተገነባ በሙስና ነው። ግንቡ ከፈረሰ ፓርቲው ወደቀ። 

ወይ ሙስና!

አበራ ደስታ

Mar 16, 2013

ኢትዮጵያዊቷ በሶርያ ያሳለፈችውን ስቃይ

*የወንድ ልጅ ብልት ቆርጠው “ተጫወችበት” ይላሉ— *ቦንብ ታጥቀሽ ራስሽን አፈንጂ ተብዬ ነበር —- *አፍሪካውያንን በኤሌክትሪክ ማቃጠል የተሰጠኝ የሥራ ኃላፊነት ነበር— *ውሃ ስንጠይቅ ሽንታቸውን ነበር የሚሰጡን …እላያችን ላይ ይሸናሉ … ከአማርኛ ይልቅ አረብኛ መናገር ይቀናታል፡፡ የምትናገረው በቁጭት፣ በእልህና በፍርሃት ስሜት ነው፡፡ ከአራት ዓመት በፊት ለሥራ ወደ ሶሪያ የተጓዘችው ሃረግ (ሜሪ)፤ በሶርያ ከጦርነቱ መጀመር ጋር ተያይዞ ያሳለፈችውን መከራና ስቃይ በአንደበቷ ትናገራለች – አንዳንዴ በሰመመን፣ ሌላ ጊዜ በመንገሽገሽ፡፡ ከሶሪያ በሱዳን በኩል አድርጋ ወደ ኢትዮጵያ በገባች በአምስተኛ ቀኗ ከጋዜጠኛ አበባየሁ ገበያው ጋር ያደረገችውን ቃለምልልስ ከዚህ በታች አቅርበነዋል፡፡ በሶርያ በምን ሥራ ላይ ነበር የተሰማራሽው? በ2009 ዓ.ም ወደ ሶርያ የሄድኩት በአውሮፕላን ነበር፡፡ እንደሌሎች ሴት እህቶቼ የቤት ውስጥ ሥራ ሳይሆን እርሻ ላይ ነበር ሥራ ያገኘሁት፡፡ ሥራዬ የወይራ ፍሬ መልቀም እንዲሁም ሙዝ፣ ትፋህ፣ አትክልትና ፍራፍሬ መኮትኮት፣ ማጨድ፣ ወዘተ ነበር፡፡ አንድ አመት ሙሉ ብቻዬን ነው የሠራሁት፡፡ ሴት ነሽ— እንዴት የእርሻ ሥራን ልትመርጪ ቻልሽ? በመጀመሪያም ወደ ሶሪያ ስሄድ ሰው ቤት እንደምቀጠር አልነበረም የተነገረኝ፡፡ እዚያ ስደርስም ወደ ገጠር ነው የተላኩት፡፡ በእርግጥ ግብርናውን ወድጄው ነበር፡፡ ግን የምኖርበት ሰውዬ በጣም አስቸገረኝ፡፡ የተቀጠርኩበት ቤት እናትና ልጅ ነበሩ፡፡ ልጁ ትልቅ ሰው ቢሆንም የአእምሮ ዘገምተኛ ነበር፡፡ እናቱ አሮጊት ናት፡፡ ልጅዬው በተደጋጋሚ ይዝትብኝ ነበር፡፡ አብረሽኝ ካልተኛሽ እያለ ያስጨንቀኛል፡፡ ምን ልበልሽ… በጣም ያሳቅቀኝ ነበር፡፡ እና ስራዬን ሰርቼ ወደ ቤት መመለስ እንደ ጦር ነበር የምፈራው፡፡ ይመታኛል፣ ይጎትተኛል፣ ይጎነትለኛል … አንድ ዓመት ሙሉ በእነዚህ ሰዎች ቤት በስቃይ ቆየሁ ፡፡ ምን ያህል ነበር የሚከፈልሽ? ከዚህ ስሄድ 125 ዶላር እንደሚከፈለኝ ነበር የተነገረኝ፡፡ እዛ ስደርስ ግን መቶ ዶላር ሆነ፡፡ እንዲያም ሆኖ አንድ ዓመት ሙሉ የሰራሁበትን ገንዘብ ከሰዎቹ አልተቀበልኩም፡፡ በቃ ጠፍቼ ነው … የሄድኩት፡፡ በየወሩ አልነበረም ደሞዝ፡፡ አንድ ዓመት ከስድስት ወር ከሰራሽ በኋላ ነው የሚከፍሉሽ፡፡ እንዴት ጠፋሽ? በእርሻው ቦታ ላይ ስሰራ ጎረቤታችን የሆነ አንድ መልካም ሰው ሁልጊዜ ሁኔታዬን ያይ ነበር፡፡ አንድ ቀን አናገረኝ፡፡ እኔም የሚደርስብኝን በደል ሁሉ አጫወትኩት፡፡ እዚህ ሰውዬ ቤት ስቀጠር ህፃን ልጅ አለው ተብዬ ነበር … ይመስለኛል ለሰውዬው ማረጋጊያና ስሜት መወጫ ነው የወሰዱኝ፡፡ እኔ ከሄድኩ በኋላ እናቱን ሌላ አገር ልኳቸው እኔ ብቻ ከእርሱ ጋር ቀረሁ፤ ለሦስት ወር ሁለታችን ብቻ ነበር፡፡ በየጊዜው ይደበድበኝ ነበር፡፡ በተደጋጋሚ በስለት አስፈራርቶ ደፍሮኛል፤ እ..ከዛ በጣም ታመምኩኝ፣ አርግዤ ነበር፡፡ ‹‹ፔሬዴ ቀርቷል፤ ሃኪም ቤት ውሰደኝ አሊያም ወደ አገሬ ላከኝ›› አልኩት፡፡ ‹‹እገልሻለሁ›› አለኝ፡፡ ስንት ቀን እየፈራሁ ዛፍ ላይ ወጥቼ ‹‹አልወርድም›› እለው ነበር፡፡ … ይሄን ሁሉ ይመለከት ነበር – ያ ጎረቤታችን ሰውዬ፡፡ በኋላ ‹‹ከተማ ወስጄሽ የውጪ ዜጎች ቤት ትቀጠሪያለሽ›› አለኝ፡፡ ጎረቤትሽ ማርገዝሽን ያውቅ ነበር? አውቋል፡፡ ወደ ከተማ ሊወስደኝ የተነሳሳው እኮ ይህንንም ሚስጢር አጫውቼው ነው፡፡ ከዚያም ‹‹ማርሊዬስ›› የሚባል ክርስቲያን አረቦች የሚሄዱበት ቤተክርስትያን ወስዶ ጣለኝ፡፡ እዚያ ችግሬን ነገርኳቸው – ለቤ/ክርስቲያኑ ቄስ፡፡ ሀሙስ፣ አርብና ቅዳሜ ለሦስት ቀን ቤተክርስትያን ውስጥ አሳደሩኝ፡፡ “እሁድ ነው ኢትዮጵያውያኖች የሚመጡት፤ ከእነርሱ ጋር ትገናኛለሽ” አሉኝ፡፡ እሁድ ዕለት ኢትዮጵያውያኖች መጡ – ብዙ ናቸው፡፡ የደረሰብኝን በሙሉ አጫወትኳቸው፡፡ ቅዳሴ እንኳን ሳያልቅ ነው ይዘውኝ ወደ ቤታቸው የሄዱት፡፡ አንድ እንደ ትልቅ እህቴ የማያት ሴት ነበረች … ለእሷ ምስጢሬን ሁሉ አጫወትኳት፡፡፡ ‹‹ምንም ችግር የለም›› አለችና ሃኪም ቤት ሄድን፡፡ አስመረመረችኝ —–የሁለት ወር ተኩል እርጉዝ ነሽ ተባልኩ፡፡ እዛ አገር ማስወረድ ክልክል ነው፡፡ እርጉዝ ከሆንሽ ወደ አገርሽ አይልኩሽም፡፡ ከተወለደ በኋላ ልጁን ነጥቀው ነው አንቺን ወደ አገርሽ የሚሰዱሽ፡፡ በጣም አስቸጋሪ ህይወት ነው፡፡ ብወልደውም ልጄን አይሰጡኝም፤ ለማስወረድ ደግሞ ገንዘብ አልነበረኝም … እስከ አምስት መቶ ዶላር ያስፈልጋል ፡፡ ያቺ እንደ ትልቅ እህቴ የማያት ልጅ የምታውቀውን ሰው አነጋግራልኝ፣ እሱ ረዳኝና ፅንሱን አቋረጥኩ፡፡ ልጆች በእስር ቤት ወልደው የሚያሳድጉ ኢትዮጵያውያኖች አሉ ይባላል … በርካታ ኢትዮጵያውያኖች፣ ኤርትራውያኖችም … አሉ፡፡ እኔ ፅንሱን ካቋረጥኩ በኋላ … ሁለት ሳምንት … እቤቷ አረፍኩ፡፡ ምናልባት ሰውዬውም የሚያፈላልገኝ ከሆነ በሚል … ሁለት ሳምንት ሙሉ ከቤት አልወጣሁም፡፡ ከሌሎች ኢትዮጵያውያኖች ጋር ተገናኘሽ … ደማስቆ ውስጥ ያሉ ኢትዮጵያውያኖች በሙሉ እርስ በርስ ይተዋወቃሉ፡፡ በሳምንት አንድ ቀን እሁድ እሁድ አንድ ላይ እንውላለን፣ ቡና ይፈላል፣ ተሰብስቦ እረፍት መውሰድ፣ መዝናናት የተለመደ ነው፡፡ ሴቶቹ ሰው ቤት ነው የሚሠሩት፡፡ ወንዶቹ ግን አይቀመጡም— እዛ አገር የሚሄዱበት ምክንያት በቱርክ አድርገው ወደ ሌላ አገር ለመሻገር ነው፡፡ አንቺ ከዛ በኋላ ሌላ ሥራ አገኘሽ ወይስ—– ራሴ አማርጬ ሰው ቤት ተቀጠርኩ፡፡ ቋንቋ ስለማውቅ ችግር አልገጠመኝም፡፡ አሮጊትና ሽማግሌ ባልና ሚስቶች ቤት ተቀጥሬ መሥራት ጀመርኩ ፡፡ ይኸኛውስ ቤት ተስማማሽ? ምን ያህል ይከፈልሽ ነበር? መጀመሪያ ስገባ መቶ ሃምሳ ዶላር ነበር፡፡ በኋላ ሁለት መቶ ሃያ አምስት ዶላር ሆነልኝ፡፡ አሮጊቷ ከተኛችበት አትነሳም፡፡ 85 ዓመቷ ነበር — እሷን አንስቼ አጥባለሁ፡፡ ፓምፐርስ (የሽንትና የሰገራ መቀበያ) እቀይርላታለሁ፡፡ … መርፌ አወጋግ ልጃቸው አሰልጥናኝ — መርፌ እወጋቸው ነበር፡፡ እንደ ልጃቸው ነበር የሚያዩኝ፡፡ ልጆቻቸው ዩኤን ነው የሚሠሩት፡፡ የመጀመርያው ቤት ፓስፖርቴን ትቼው ስለወጣሁ እዛ ተመዝግቤ በዚያ ወረቀት ነበር የምጠቀመው፡፡ አሮጊቷ የዛሬ ዓመት ሞተች፡፡ ከዛ ሽማግሌው ልክ እንደ ሚስቱ ሆነ፡፡ እሱን ሳነሳ ስጥል … (95 ዓመቱ ነበር፡፡) ግን በጣም ጥሩ ሰዎች ነበሩ፡፡ የቤቱ ሃላፊ እኔ ነበርኩ፡፡ በጣም ሀብታሞች ናቸው፡፡ መኪና አስመጪና ላኪ ነበሩ፡፡ ሴቷ ልጅ ነበረች የቤተሰቦቿን ሀብት የምታስተዳድረው፡፡ ምን ያህል ጊዜ ሰራሽ? አራት ዓመት ከ6 ወር አብሬአቸው ነበርኩ፡፡ ጦርነቱ ሲጀመር ሃብታሞች ስለሆኑ ሁሉን ነገር ትተውት ወጡ፡፡ በመሃል እኔ ቀረሁ፡፡ ልጅቷ ፓስፖርት ልታወጣልኝ በጣም ደክማልኛለች፤ ግን አልተሳካም፡፡ እና ቤቱን ለእኔ ጥለው ወደ ቤሩት ተሳፈሩ፡፡ አካባቢው በጣም አስቀያሚ ነበር፡፡ አሸባሪዎች እንደፈለጉ የሚገቡበት የሚወጡበት ቦታ ነበር፡፡ እዚያ መኖር እንደማልችል አውቄዋለሁ፡፡ የነበርኩባቸዉ ሰዎች ደግሞ ክርስቲያኖች ነበሩ፡፡ አሸባሪዎች ይፈልጓቸዉ ነበር፡፡ ያንን ትልቅ ቤት ጥለውልኝ ብቻዬን ተሸክሜው ስለቀረሁ ተጨነቅሁ … መወሰን ነበረብኝ፡፡ በርካታ ቤተክርስያኖች ተቃጥለዋል፡፡ ፈርሰዋል፡፡ የሚሸሸው ክርስቲያኑ ነው፡፡ ፓስፖርት ያለው ይሸሻል፡፡ ፓስፖርት ኖሮት ብር የሌለው ኢትዮጵያዊ አለ—ሁሉም መሸሽ ነው፡፡ እስር ቤት መግባትም አለ፡፡ እኔም እጣ ፋንታዬ ይሄው ሆነ፡፡ በእስር ቤት ውስጥ .. የነበረውን ሁኔታ ንገሪኝ? እስር ቤት አንድ ወር ተቀመጥኩ፡፡ እስር ቤት እኮ የገባሁት ልመጣ አካባቢ ነው ከዛ በፊት በአሸባሪዎች እጅ ወድቄ ስንት ነገር ደርሶብኛል..በአሁኑ ሰዓት በጣም በረዶ ነው፡፡ እስር ቤት አትበይው … ‹‹የምድር ጀሃነም›› ነው፡፡ እዚህ ካዛንቺስ ሆነሽ ፍንዳታ ከተሰማ ተነስተሽ መገናኛ ድረስ ነው የምትሮጪው፡፡ ትራንስፖርት የለም፣ ከተያዙ መያዝ ነው፤ የሚሞተውም ይሞታል፡፡ አሁን እኔ በወጣሁበት ሰዓት ከተማው ላይ ብዙም ጦርነት አልነበረም፡፡ ዳር ዳሩ ላይ ነበር፡፡ እኔ ደግሞ እንደ አቃቂ ባለ ከከተማው ዳር ነበር የምኖረው፡፡ ከደማስቆ ራቅ ይላል፡፡ በጣም ብዙ ኢትዮጵያውያን ሴቶች በሴተኛ አዳሪነት ይሠራሉ የሚባለው እውነት ነው? ወደው አይደለም ሴተኛ አዳሪ የሚሆኑት፡፡ ፓስፖርት የላቸውም፤ ሊቀጠሩ ሲሄዱ ፓስፖርት ይጠየቃሉ፡፡ ቀጣሪዋ ‹‹አልፈግሽም›› ብላ ልታባርራት ትችላለች ፡፡ መኖር፣ መብላት ስላለባቸው የግድ ለእንደዚህ ዓይነት ህይወት ይዳረጋሉ፤ እዚያ ደግሞ የኢትዮጵያ ቆንስላ የለም፤ ኤርትራውያን እንኳ ቆንስላ አላቸው፡፡ ኤርትራዊ ላይ አንድ ችግር ቢደርስበት ቆንስላው ወደተከራየው ቤቱ ይወስዳቸዋል፡፡ ኢትዮጵያውያን በጣም የሚያሳዝን ነው ኑሯቸው ፡፡ አሁን እንኳን ወደ አገራቸው መምጣት አቅቷቸው በየሜዳው ወድቀዋል፡፡ በጦርነቱ ቤቱ ሁሉ እየፈረሰ ነው፡፡ ተከራይተው የሚኖሩት ንብረታቸውን ማውጣት አልቻሉም፡፡ የሴቶች ህይወት … በቃ ይሄው ነው፡፡ ወደው አይደለም የገቡበት —- ኢትዮጵያውያኖች ያ ባህል ኖሯቸው አይደለም፤ በችግር ነው፤ አማራጭ በማጣት፡፡ እስር ቤት ከመጣልሽ በፊት..በአሸባሪዎች እጅ ወደቅሽ? በጣም አሰቃቂ ነው … በአሸባሪዎች እጅ ላይ ወደቅሁኝ፡፡ /ሰውነቷ ይንቀጠቀጣል፣ ለደቂቃዎች በዝምታ ቆየች፤ አይኖቿ እንባ አቀረሩ …) አየሽ ሰውነቴን … (ትከሻዋ አካባቢ እያሳየችኝ … የተቃጠለ ገላ …) ምንድን ነው? ሲጋራ ተርኩሰውብኝ ነው … … አሸባሪዎቹ ናቸው እንዲህ ያደረጉኝ— የት ነው የወሰዱሽ? ቢሄዱት የማያልቅ ምድር ቤት (Underground) አላቸው፡፡ ውስጥ ለውስጥ ተቆፍሮ … የቀለጠ ከተማ ነው፡፡ በአንድ አቅጣጫ ብቻ እንዳይመስልሽ … ወደ አምስትና ከዛም በላይ አቅጣጫ መግቢያ መውጭያ ያለው ነው … የታሰሩ ሰዎች የሚሰቃዩበት፣ የጦር መሳሪያ በየዓይነቱ በብዛት ያለበት … ኑሯቸውም እዛው ነው? አዎ፡፡ ሴቶችም ወንዶችም አሉ፡፡ ብዙ ጊዜ አሸባሪዎቹ አይወልዱም፡፡ ከወለዱ ግን የልጆቻቸው አስተዳደግ አሰቃቂ ነው፡፡ በፊት ለፊታቸው አንገት በቢላዋ እየተቀላ፤ እጅና ጣት እየተቆረጠ … ያንን እያዩ ነው የሚያድጉት፡፡ ወንዶችን በፊንጢጣቸው … ኤሌክትሪክ ይልኩባቸዋል፡፡ ሴቶችን ህፃናቱ ፊት ይደፍራሉ፡፡ … የ3 እና የ5 ዓመት ህፃናት እንዲያዩ እንዲለማመዱ ይገፋፏቸዋል፡፡ የአሸባሪዎቹ ሚስቶች እዚያው አሉ፡፡ እነርሱም ሰውን ያሰቃያሉ፡፡ ሴትን ሴት፤ ወንድን ወንድ ነው የሚያሰቃየው፡፡ ሚስቱ ካሰቃየችኝ በኋላ ‹‹አምጫት›› ብሎ ይደፍረኛል፡፡ ሱዳኖች፣ ናይጄሪያዎች፣ ሴኔጋሎች … ብዙ የአፍሪካ ዜጐች ነበሩ – የሚሰቃዩ፡፡ የተለያየ አደንዛዥ ዕፅ ይሰጡናል፤ በመርፌ የሚወጋ፣ የሚጨስ፣ የሚሸተት … በግዴታ ነበር፡፡ ከዚያ መጋረፍ ነው … ወንዶቹ ብልት ላይና ምላሳቸው ጫፍ ላይ ኤሌክትሪክ ያደርጉባቸዋል፡፡ እኔን … ቦንብ ታጥቀሽ ራስሽን ታጠፊያለሽ ብለውኝ ነበር፡፡ ‹‹ላ … ላ›› አልኳቸው፡፡ ከዛ … የደረሰብኝን ስቃይ … (ረጅም ትንፋሽ) እስቲ የደረሰብሽን ንገሪኝ … … በቃ ተይው ይቅር … (ለመሄድ ተነስታ ተመልሳ በማቅማማት ተቀመጠች) አይዞሽ ንገሪኝ … ስታወሪው ይሻልሻል … ለመናገር ይከብዳል፡፡ የወንድ ልጅን ብልት ቆርጠው አምጥተው “ተጫወችበት” ይላሉ— በጣም … አስቀያሚ ነው … ተይኝ ባክሽ … በተደጋጋሚ ስትደፈሪ እርግዝና አልተፈጠረም? ሃሃ … (ሳቅ) የሚሰጡኝ መድሃኒትስ … አምፒሲሊን ይሁን … ምን ይሁን አላውቅም ግን ይሰጡኝ ነበር … ስለዚህ እርግዝና የለም፡፡ ስቃይ ሲበዛብሽ … ምንም አትይም … ቁጣ ወይ ደግሞ … “በቃ ራሴን አፈነዳለሁ” አልኳቸው:: ውይ ሳልነግርሽ … ምግብ የለም፣ ውሃ በምንጠይቅ ሰዓት ሽንታቸውን ነበር የሚሰጡን … ሲያሰኛቸው በገላችን ላይ ይሸናሉ፡፡ ትንሽ ውሃ በተለያዩ ማደንዘዣ ዕፆች ቀላቅለው ጠጡ ይሉናል ፡፡ ያን ከሰጡኝ በኋላ የሚያደርሱብኝ ስቃይ አይታወቀኝም … እና “አፈነዳለሁ” ብዬ ተስማማሁ … ወጥቼ ልሙት … አንድ ኢትዮጵያዊ ይህንን እንዳዳረገች ሁሉም ይወቅ ብዬ ወሰንኩ፡፡ ከእንግዲህ ምን ቀረኝ … ብሬን ንብረቴን ወስደውታል፡፡ አማርኛ የማወራው— ችግሬን የማስረዳው ሰው እንኳን የለም፡፡ እንዲህ እናድርግ ምናምን ብላችሁ ከሌሎቹ ጋር አትማከሩም ነበር? እኔ ከሴቶች ጋር ሳይሆን ከወንዶች ጋር ነበር ይበልጥ የምቀራረበው፡፡ ናይጀሪያኖች፣ ሱዳኖች … ሱዳኖች በእኔ ስቃይ በጣም ተጐድተዋል … ስጮህ ይሳቀቁ ነበር፡፡ በእነሱ ፊት ይገናኙኝ ነበር፡፡ አፍሪካውያኖችን በኤሌክትሪክ አቃጥይ ይሉኝ ነበር፡፡ “ሂጅና አቃጥያቸው”፤ “ሽንትሽን ሽኝባቸው…” እባላለሁ፡፡ እነሱ ጋ ስደርስ በጣም አለቅስ ነበር፡፡ ጣታቸውን … እግራቸውን ይቆርጡባቸዋል፡፡ … ህክምና የለ፤ ደማቸው እየፈሰሰ ነው የሚውሉት … አቃተኝ (ረጅም ትንፋሽ) ምን ያህል ነበሩ? አስራ ሶስት፡፡ ከሞቱት ሌላ ማለቴ ነው—- (ደረትዋን ደጋግማ በእጅዋ ትይዛለች) አቤት …ሽታው በልብሴ …በሠራ አካላቴ ጠረኑ ሁሉ..ይመጣብኛል፡፡ ናይጀራዊው ጋ ሄጄ የታዘዝኩትን ስነግረው ..በአረብኛ ‹‹..አድርጊው..ካላደረግሽው አትወጪም፤ እኛንም አታድኝንም..አድርጊው..ለኩሽኝ..›› አለኝ፡፡ አልቻልኩም፤ የመጀመሪያ የጨካኝነት ልምምድ ነበር፡፡ አለቀስኩኝ፡፡ በብዛት ኮኬን እወስድ ነበር፡፡ ስትለኩሺያቸው ቆመው ያዩሽ ነበር? አዎ.. ደስ ይላቸዋል፡፡ .ናይጀሪያዊውን እየለኮስኩት ሳለ “ጭኔ ላይ የምታያት የበር ቁልፍ ናት፡፡ እቺን ይዘሽ መውጣት ትችያለሽ” አለኝ፡፡ እሱን እየለኮስኩ ቁልፉን ወሰድኩት፡፡ አረቡ እያየን አልነበረም፡፡ ናይጄሪያዊው ቁልፉን ከየት አገኘው? ከየት እንዳገኘው መጠየቅም አልፈለኩም፤ ጊዜውም አልነበረኝም፡፡ ማውራት አንችልም ነበር፤ ከናይጀሪያዊው ጋር ልንግባባ የምንችለው በአረብኛ ቋንቋ ብቻ ነው፡፡ በንግግርሽ ውስጥ እንግሊዝኛ ከሰሙ …ጉድሽ ነው፡፡ የተለየ ቋንቋ እንድትናገሪ አይፈቀድልሽም፡፡ (ንግግርዋን አቋርጣ) ይቅር በለኝ— አሰቃየኋቸው፡፡ በኤሌክትሪክ ከለኮስኳቸው በኋላ ስላለቀስኩ ..‹‹ለምን ታለቅሻለሽ›› ብለው አሰቃዩኝ፡፡ ‹‹የገነት ፓስፓርት›› የሚሉት አለ፡፡ የገነት ፓስፖርት … ሰው ገድለው ገነት የሚገቡበት ፓስፖርት፡፡ የራሳቸው የቡድን ፓስፖርት ነው፡፡ ‹‹ነፍስ አጠፋለሁ›› ብዬ ስነሳ ፓስፖርት ተሰራልኝ፡፡ ፓስፖርቱ ምን አለው? ምንም፡፡ የእኔ ስምና የቤተሰቤ ስም ዝርዝር አለው፡፡ አረንጓዴ ነው፡፡ ፎቶ የለውም፡፡ ስትገልጪው ይሄ ብቻ ነው የያዘው መረጃ፡፡ “የገነት ፓስፖርት” ይላል ፅሁፉ፡፡ ፓስፖርቴ ተሰራልኝ፡፡ እላዬ ላይ ቦንብ ካጠመዱልኝ በኋላ የገነት መግቢያ ፓስፓርቴም፣ አብሮ ይታተምልኛል፡፡ ፓስፖርቴ ተሰራ፤ አብሬያቸው እሰግድ ነበር፤ ቁራን እንዴት እንደሚቀራ አስተማሩኝ፡፡ “የዛሬ 15 ቀን ወደ ገነት መሄጃሽ ነው ማረፍ አለብሽ” ብለው ነገሩኝ… እረፍቱ የት ነው …? ‹‹የምድር እረፍት›› ነው የሚሉት፡፡ 15 ቀኑን የሟች ሬሳ በተጠራቀመበት … (ፀጥ አለች) … ሰውነታቸው የተቆራረጠ ሰዎች በብዛት ተገድለው በተጣሉበት … ከነበርንበት ወደ አንድ ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ … ሬሳ ውስጥ … ከሙታን ጋር፡፡ ጨካኝ … እንድትሆኝ ነው … እዚያ የጉድጓድ መውጫ በር አለ … ያ … ናይጄሪያዊ የሰጠኝ ቁልፍ መውጫ ነው … እሱ እኮ ከታሰረ ሁለት ዓመቱ ነው … ጦርነቱ ሲጀምር የተያዘ ነው፡፡ እረፍት እንደሚወስዱኝ ሁሉ ያውቃል፡፡ … በዚያ አሰቃቂና ዘግናኝ ቦታ በአጋጣሚ ህይወቱ ያላለፈ ትኩስ ቁስለኛ … (የገደሉት መስሏቸው ትተውት የሄዱት) አገኘሁ፡፡ ለመሞት ጥቂት ደቂቃዎች ነበር የቀረው፡፡ የእረፍቱ ቦታ….. ሱሪ እና አሮጌ ነገር አለበሱኝ፤ ሬሳው ውስጥ ተቀመጥኩ፡፡ … እፀልይ ነበር … ቁልፉን እንዴት ይዘሽው ገባሽ? በማህፀኔ ውስጥ ደብቄ … በምኔም ልደብቅ አልችልም ነበር፡፡ ስፀልይ ሰውየውም ቀና አለ … እጅግ ያሳዝናል … ሰውነቱ ሁሉ የተጠባበሰ ነው … ተበለሻሽቷል፡፡ ይህ ሰው እንደተጋደመ “ሬሳዎቹን … ገለል ገለል አድርገሽ ውጪ” ብሎ አሳየኝ … የደረጃ መወጣጫ … አለው … እሱ ሲወጣ አስፓልት ይገኛል፡፡ እየመጡ አያዩሽም ነበር? በፍፁም አያዩኝም … 15 ቀን ካረፍኩ በኋላ መጥተው ይወስዱኛል … ብቅ ብለው ግን አያዩኝም፡፡ ከዛ ሰው ጋር ተግባባሁ፤ ውሃ … ሲለኝ ሽንቴን ሸንቼ ሰጠሁት፡፡ ህይወቱን ለትንሽ አተረፍኩት፡፡ … በሌሊት በሩን ከፈትን … ተሸክሜ … አወጣሁና ጣልኩት፡፡ እነሱ ለሊት ለሊት ስራ አይሰሩም፡፡ ስራቸው ቀን ነው፡፡ በግርግር ጫጫታ ባለበት ሰዓት እንጂ … ጨለማ ተገን አድርገው እንኳን ሰውን አይደበድቡም፡፡ ቢያስተጋባ ቢሰማብን ብለው ስለሚያስቡ ይፈራሉ፡፡ ሌሊት መጠጣት ነው ሥራቸው፡፡ የቆሻሻ ቱቦ … ስር ለስር … የትና የት የሚደርስ— ውስጥ ለውስጥ የሚያስኬድ መንገድ መሰለሽ … እንደ ምንም ደረጃውን ተሸክሜው … እየጎተትኩት … ወጥተን ያ ናይጄሪያዊ በሰጠኝ የበለዘ ቁልፍ … ከፈትኩት … ስወጣ አስፓልት ላይ ነው የወጣሁት፡፡ ቅርብ ነው ለከተማው፡፡ ምሽት ላይ ነበር፤ ማንም ዝር አይልም፡፡ ‹‹ስምርዬ›› የሚባል ቦታ አለ፡፡ እንደ አውቶብስ ተራ ዓይነት ነው፡፡ አስፓልቱ ላይ ከወጣን በኋላ … ተሸክሜ ያወጣሁት ሰው … የተወሰነ ቦታ ድረስ እየጎተትኩት ከተማ አካባቢ ስንደርስ አደባባይ ላይ ጥዬው ሄድኩ፡፡ ከወጣሁ በኋላ ደክሞኛል … አሞኛል፡፡ ኢትዮጵያኖችን መጠጋት አልቻልኩም፡፡ ለምን? በጣም አስቀያሚ ሁኔታ ላይ ነበርኩ፡፡ ሀሺሽ ጠጥቻለሁ፣ ጠረኔ በጣም መጥፎ ነው፤ ፀባዬ ከፍቷል፡፡ በዛ ሰዓት የሄድኩት ቤተክርስቲያን ነው፡፡ ፀለይኩ … አለቀስኩ … የት እንደምሄድ አላውቅም፡፡ … ሁሉ ነገር ብርቅ ሆኖብኛል፡፡ መንገድ ላይ ስዘዋወር አንድ ኢትዮጵያዊ አገኘሁ፡፡ ሳናግረው “ሰምተናል ሰምተናል” አለኝ፡፡ ምኑን? አንዲት ኢትዮጵያዊ ተይዛለች መባሉን፡፡ ማን እንደሆነች ግን አላወቅንም ነበር፡፡ በአሸባሪዎች እጅ ወደቀች ሲባል ሰምተናል – አለኝ፡፡ በአገሪቱ ላይ ስልክ የሚባል የለም … አጋጣሚ ሆኖ በነጋታው ወደ ካናዳ የሚሳፈር ልጅ ነበር፤ በጣም አዘነ፡፡ ከዛ ጉድጓድ ከወጣሁ በኋላ ግን በጣም ፈራሁ … የሚያየኝ ሰው ሁሉ የሚያውቀኝ የሚከተለኝ… የሚገለኝ ይመስለኝ ነበር፡፡ ቀን ቀን ስታያቸው ኖሮማል ሰው ስለሚመስሉ፤ ለብሰው ዘንጠው ስለሆነ የሚወጡት … አንድ ሰው አስተውሎ ካየኝ ከእነርሱ መካከል አንዱ ይመስለኝ ነበር፡፡ በአጋጣሚ በዛን ወቅት ደግሞ በዊግ ቁጥርጥር ተሰርቻለሁ … በፀጉሬ ይለዩኛል ብዬ እሰጋም ነበር፡፡ “እባክህ ከአንድ ሱናዳዊና ናይጄሪያዊ የተሰጠኝ መልዕክት አለ … ስማቸው እገሌ ይባላል … ሂጂና ያሉበትን ቦታ ተናገሪ ስላሉኝ እዛ ውሰደኝ” አልኩት፡፡ ናይጄሪያዎች በጣም ጎበዞች ናቸው … እንዴት እንደሚወጣ … ያውቃሉ —-ጥበበኞች ናቸው እና ይሄን ልንገር አልኩት፡፡ የተባለው ቦታ ወሰደኝ፡፡ … ነገርኳቸው፡፡ ተላቀስን — ቁልፍ ሰጥቶ ያስወጣኝ የናይጄርያው ወንድም “ኢሾ” ይባላል፡፡ ምን ማድረግ እንዳለብን አወራን፡፡ ቦታው እንደዚህ ዓይነት ቦታ ነው፤ ቁልፉም ይሄው … ‹‹ስጪያቸው እነርሱ ምን ማድረግ እንዳለባቸው ያውቃሉ ነው ያለኝ” አልኩት፡፡ ቁልፉ ላይ … ሌላ መልዕክት አለው? እንዴ … እንዴት አወቅሽ? — ቁልፉ ሰፋ ያለ ነው.. በላዩ ላይ በራሳቸው ቋንቋ ፅፈውበታል … ሰጠኋቸውና አወጣጤን ነገርኩት፡፡ አለቀሱ፤ በህይወት የለም ብለው ደምድመው ነበር፡፡ (እንባዋን እየጠረገች) አንድ ኢትዮጵያዊ ከአንድ ሱዳናዊ ጋር አገናኘኝ፡፡ በጣም ባለውለታዬ ነው– እንደ ነገ ወደ ካናዳ በረራ ነበረው— ለእኔ ሲል ቀኑን አራዘመ … በሃሺሽና በተለያዩ ሱሶች የተበከለው ደሜ … ባህሪዬን አስከፍቶት ስለነበረ መርዙ ከደሜ እስኪወጣ ድረስ ተቸገርኩ፡፡ ስለዚህ … አስመረመረኝ … ከሰው ጋር ትንሽ ትራቅና ትቀመጥ ተባለ … መድሃኒት ተሰጠኝ፡፡ ያ ያስተዋወቀኝ ያልኩሽ ሰው በሱዳን አድርጌ ወደ ኢትዮጵያ እንድመጣ ነገሮችን ያመቻችልኝ ጀመር፡፡ ሌላ ዳዊት ባህሩ የሚባል ኢትዮጵያዊ (እዛ የሚኖር የአሜሪካ ዜግነት ያለው) … የቻልኩትን ሁሉ እረዳታለሁ … ፓስፖርቷንም በማውቀው ሰው አወጣላታለሁ አለ፡፡ የምንኖረው አንድ አፓርታማ ላይ ነው፡፡ እኔን ይዞ ሲወጣ ሲገባ ያየ ሰው በትኩረት ያየኝ ነበር፡፡ ስወጣ ከእግር ጥፍሬ እስከ ራስ ፀጉሬ ተከናንቤ ነበር የምወጣው፡፡ እዛ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ደግሞ አይከናነቡም፡፡ ‹‹አሸባሪ ናት፤ ጥቁር ናት ግን ተከናንባ ነው የምናያት ፈራናት›› ብለው አስጠቆሙኝና እስር ቤት ገባሁ፡፡ የዩኤን ወረቀት ነበረኝ፡፡ የደረሰብኝን ነገር ሁሉ አጫወትኳቸው፡፡ እስር ቤት ውስጥ ስገባ ለእኔ እረፍት ነበር፤ አልተጐዳሁም፡፡ ከእስር ቤት ውጪ ያሉ ኢትዮጵያውያን በየሜዳውና በየመናፈሻው ወዳድቀው ተወንጫፊና፣ ተፈንጣሪ መሳሪያ እየወደቀባቸው ይሞታሉ፡፡ እኔ በቅርብ የማውቃት ልጅ የሞተች አለች፡፡ እኔ እዚህ ስመጣ … አሁንም የሚያስለቅሰኝ እዛ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ሁኔታ ነው … ቢያንስ መቶ ኢትዮጵያውያንን ማምጣት ቢቻል

Mar 14, 2013

የስለላ ተግባርን ቀዳሚ አጀንዳ ያደረገው የወያኔ አገዛዝ የግንቦት7 ንቅናቄን መሰለሉ ተጋለጠ

March 14, 2013 | Filed underአማርኛ ዜናና መግለጫ | Posted by admin

ኢትዮጵያዊያንን አፍኖና ረግጦ አንድ ለአምስት በተሰኘ አደረጃጀት እስከቤተሰብ የወረደ የስለላ ተግባርን እየፈጸመ ያለው ዘረኛ የወያኔ አገዛዝ የግንቦት 7 ንቅናቄን መረጃ ለማግኘት ከፍተኛ የሆነ የስለላ ተግባር ሲፈጽም እንደቆየ ተቀማጭነቱ አውሮፓ የሆነ አንድ አለማቀፍ የሶፍት ዌር ኩባንያ አጋለጠ።
የወምበዴዎች ጥርቅም የሆነው የወያኔ አገዛዝ በስሩ ለዚሁ ተግባር ያቋቋመው ኢትዮ ቴሌኮም ፊን ሰፓይ በመባል የሚታወቀውን ሶፍትዌር በመጠቀም የግንቦት 7 ለፍትህ፣ ለነጻነትና ለዲሞክራሲ መረጃዎችን ሲሰልል መገኘቱን ያጋለጡት ሞርጋን ማርኩዊስ ቦሪ፣ ቢል ማርዛክ ፣ ክላውዲዮ ጋርኔሪ እና ጆን ስኮት በመባል የሚታወቁ ባለሙያዎች ሬይላተን ሲትዝን ላብ በተባለ ዌብሳይት ላይ ባወጡት ጽሑፍ  ነው።
እነኝሁ ባለሙያዎች ፊን ስፓይ የግንቦት 7ትን መሪዎች ፎቶግራፍ ወደ ኮምፒዩተር ተጠቃሚዎች በመላክ መረጃዎችን ለኢትዮጵያ መንግስት ባለስልጣናት ለማቀበል መሞከሩን የገለጹ ሲሆን የግንቦት ሰባት ንቅናቄ ኢንተለጀንስ በበኩሉ ፣ የወያኔው አፋኝ አገዛዝ ከድርጅቱ መረጃዎችን ለመውሰድ ተደጋጋሚ ሙከራ ሲያደርግ እንደነበር መረጃዎች እንዳሉት አስታውቋል።
የድርጂቱ መረጃዎች ወደ አፋኙ አገዛዝ እጅ አለመግባታቸውን ያረጋገጠው የግንቦት ሰባት ንቅናቄ  ድርጅቱ በስልጣን ላይ ካለው ዘረኛና አፋኝ የወያኔ አገዛዝ ጋር ከፍተኛ የሳይበር ጦርነት ሲያድረግ እንደነበር ም ታውቋል።
ፊን ስፓይ  ወንጀለኞችን ለመያዝ ተብሎ የፍትህና የደህንነት ሰራተኞች እንዲጠቀሙበት በሚል መነሻ የተመረተ መሆኑ የሚታወቅ ሲሆን፣ እንደወያኔ አገዛዝ ያሉ አፋኝ መንግስታት  ሶፍትዌሩን ተቃዋሚዎቻቸውን በስፋት ይጠቀሙበታል።