ምንም ቢበርደው ቅቤ እሳት አይሞቅም! አማረ አረጋዊ
ቅቤዉ ማን ነዉ??? TPLF ይሆን?
እሳት መሞቅ ምንድን ነዉ??? በአሁኑ ጊዜ በአገር ውስጥም በውጭ አገርም በሥልጣን ላይ ያለውን መንግሥት የሚጠሉና የሚቃወሙ ኃይሎች አሉ፡፡ በፓርቲ፣ በቡድንና በግለሰብ ደረጃ፡፡አማረ አረጋዊ ከተናገረዉ እነዚህን መጠጋት መዋሃድ አብሮ መስራት በኢሳት ቃለመጠየቅ ማድረግን ይሆን?

ብርዱስ ምንድን ነዉ??? አሁን TPLF ያጋጠመዉ ችግር ይሆን?
እንደ ግለሰብም፣ እንደ ቡድንም፣ እንደ ድርጅትም፣ እንደ ሕዝብም፣ እንደ አገርም ምን ጊዜም ችግር ያጋጥመናል፡፡ ለምን ችግር አጋጠመ ብሎ መደናገጥ ፋይዳ የለውም፡፡ ችግሩን አውቆ ለመፍትሔው መረባረብና መታገል እንጂ፡፡
ግን! ነገር ግን! መፍትሔ ስናፈላልግ ችግሩን የሚፈታ እንጂ በመፍትሔ ስም የባሰ ችግርና ጥፋት የሚያስከትል ዕርምጃ እንዳንወስድ ወይም እንዳንወስን መጠንቀቅ አለብን፡፡ ቅቤ ቢበርደው መፍትሔው እሳት መሞቅ አይሆንምና፡፡
በአሁኑ ጊዜ በአገር ውስጥም በውጭ አገርም በሥልጣን ላይ ያለውን መንግሥት የሚጠሉና የሚቃወሙ ኃይሎች አሉ፡፡ በፓርቲ፣ በቡድንና በግለሰብ ደረጃ፡፡ ለምን መንግሥትንና ገዥውን ፓርቲ ትጠላላችሁ፣ ትቃወማላችሁ የሚል ጥያቄ አይነሳባቸውም፡፡ በሰላማዊና በሕጋዊ መንገድ እስከተንቀሳቀሱ ድረስ መቃወም ሕገ መንግሥታዊ መብታቸው ነውና፡፡ እንዲያውም እባካችሁ ተጠናክራችሁ ተቃወሙ እንላለን እንጂ ለምን ትቃወማላችሁ አንልም፡፡
ግን! ነገር ግን! የምንለው ነገር አለ፡፡ እባካችሁ ተቃወምን ብላችሁ ራሳችሁን፣ አገርንና ሕዝብን ለጠላትና ለአደጋ የሚዳርግ መስመር አትከተሉ፤ ውሳኔ አትወስኑ፤ ዕርምጃ አትውሰዱ እንላለን፡፡ ምንም ቢበርደው ቅቤ እሳት አይሞቅም፡፡ እሳት መሞቅ ከብርድ የሚከላከል ቢመስልም ከቅቤ ባህርይ አንፃር ሲታይ ግን እሳት ከብርድ የሚያድን ሳይሆን በማቅለጥ የቅቤን ህልውና ያሳጣል፡፡
በመቃወም ስም የሃይማኖት ቅራኔን ማባባስ፣ በመቃወም ስም የብሔር ብሔረሰቦች ቅራኔን ማፋፋም፣ በመቃወም ስም የጠላት መሣሪያ መሆን፣ በመቃወም ስም ኢትዮጵያን በማዳከም መሳቂያና መሳለቂያ ማድረግ የሚቃወመውን ኃይል የሚያጠናክረው ሳይሆን የሚያቀልጠው ነው፡፡ በረደኝ ብሎ እሳት የሚሞቅ ቅቤ እንደሚቀልጥ ሁሉ፡፡
ኢሕአዴግ አራት አባል ድርጅቶችን ያቀፈ ነው፡፡ በእያንዳንዱ አባል ድርጅት ውስጥና በአራቱ ድርጅቶች መካከል የሐሳብ ልዩነት ሊኖርና ሊፈጠር ይችላል፡፡ ለምን ልዩነት ታየ? ለምን ልዩነት ተፈጠረ? ተብሎ አይጠየቅም፡፡ የሐሳብ ልዩነት የትም ያለ ነው፡፡ ሕገ መንግሥታዊ መብት ነው፡፡ ከዚያ አልፎም አንድ ፖለቲካ ድርጅት ውስጥ በመሆን በዓላማ አንድ ቢኮንም፣ ዓላማውን ለማሳካት የሚሻለው መንገድ ይህ ነው የለም ያኛው ነው ብሎ መከራከርና መለያየት ያለ ነው፡፡ ከሌለ ይገርማል እንጂ መኖሩ ጤናማ ነው፡፡
ግን! ነገር ግን! በተፈጠረው ልዩነት፣ መራራቅና አለመግባባት ሕገ መንግሥታዊ፣ ሰላማዊ፣ ሕጋዊ፣ ዴሞክራሲያዊና ትክክለኛ የፓርቲ ውስጥ የትግል ዘዴ ከመከተል ይልቅ ያዙኝ ልቀቁኝ ከተባለ፣ መጠቃቃት እንደ ዘዴ ከተወሰደ፣ መኮራረፍ እንደ አማራጭ ጥቅም ላይ ከዋለ፣ ውስጥ ለውስጥ የስም ማጥፋትና የኔትወርኪንግ እንቅስቃሴ ከተጀመረ ፓርቲውን፣ መንግሥትንና አገርን ለአደጋ የሚዳርግ ይሆናል፡፡ ከብርድ ለመዳን ብሎ እሳት ሞቆ ቀልጦ የሚቀር ቅቤ መሆንን ያስከትላል፡፡
በግሉ ዘርፍና በሲቪል ማኅበረሰቡ ውስጥ የሚንቀሳቀሱ አካላትና ድርጅቶችም በተወሰነ ጊዜ የተወሰነ ችግር ሊያጋጥማቸው

ይችላል፤ ያለ ነው፡፡ የግብር አከፋፈል ችግር ሊያጋጥም ይችላል፡፡ ከደንበኞች ጋር ውል ተዋውሎ ውሉን ለመፈጸም ችግር ውስጥ ሊገባ ይችላል፡፡ ገንዘብ ሊያጥር ይችላል፡፡ ተጠያቂነትና መከሰስ ሊከተል ይችላል፡፡ ይህንን በሕጋዊና ሥርዓት ባለው መንገድ ለመፍታት የድርሻን መጫወት እንጂ፣ ተጨማሪ ወንጀል ብፈጽም መፍትሔ ይሆናል፣ ጉቦ ብሰጥ ይሰረዝልኛል፣ ከአገር ብጠፋ የት ያገኙኛል እየተባለ አኩኩሉ ጨዋታ ውስጥ የሚገባ ከሆነ መጨረሻው በሕግም፣ በመንግሥትም በወንጀል ተፈላጊ ሆኖ መቅለጥና ተዋርዶ መጥፋት እንጂ መፍትሔ አይሆንም፡፡ የበረደው ቅቤ እሳት ቢሞቅ መፍትሔ አያገኝምና፡፡
እያነሳነው ያለው ቁም ነገር ግልጽ ነው፡፡ ችግር የትም ምንጊዜም ያጋጥማል፡፡ አፈታት ላይ ግን በሳል፣ አስተዋይ፣ ሕጋዊና ሰላማዊ ዕርምጃ ያስፈልጋል፡፡ መፍትሔ እናገኛለን ብለን ወደባሰ ችግርና ጥፋት እንዳንገባ እንጠንቀቅ ነው፡፡ ይህ ሁላችንንም የሚመለከት ቢሆንም በመንግሥትና በገዥው ፓርቲ ሲመጣ ግን የበለጠ ልዩ ጥንቃቄ ያስፈልጋል፡፡
በአሁኑ ጊዜ የውጭ ምንዛሪ ችግር አለ፡፡ የገንዘብ እንቅስቃሴ ዝግመት አለ፡፡ መቀዝቀዝ አለ፡፡ የብድርና የዕርዳታ ማነስም አለ፡፡ በአንፃሩ የዕቅዳችንና ፕሮጀክታችን ግዝፈትና አስቸኳይነት አለ፡፡ መሮጥ የምንፈልገው ርቀት አለ፡፡ አላስሮጥ የሚል እንቅፋትም አለ፡፡ አፈታት ላይ እንጠንቀቅ ነው፡፡ መንግሥት የውጭ ምንዛሪ ችግር አለ ሲባል የለም ‹‹በሽበሽ›› ነው እያለ ከሚመልስ ይልቅ፣ ረጋና ኮራ ብሎ ችግሩን እያጠናና እያመነ መፍትሔ ይስጥ ነው፡፡ አለበለዚያ የኋላ ኋላ ችግሩ የማንሸከመው ይሆናል፡፡
በኢትዮጵያ ላይ የሚያነጣጥሩ ጥላቻዎች ካልተጠበቁ ወገኖች ባልተጠበቁ ክብደቶች እየተወረወሩብን ናቸው፡፡ ችግር የለም የአፍ ወለምታ ነው፣ ወይም ችግር የለም የግለሰብ አስተያየት ነው እያልን የምንጓዝ ከሆነ የሚቆጨን ሁኔታ ውስጥ ልንገባ እንችላለን፡፡ በተለይም ኢሕአዴግ አሁን ወደ ጉባዔ ሊገባ ነው፡፡ ራሱን የሚገመግምበት መድረክ ነው፡፡ ምርጫ የሚያካሄድበት ወቅት ነው፡፡ አቋሞችን ይፋ የሚያደርግበት መድረክ ነው፡፡ ወይ ተጠናክሮ ሊወጣ ወይ ችግሩን ሳያይ ቀርቶ ተዳክሞ ሊንገዳገድ የሚችልበት መንታ መንገድ ላይ ነው፡፡
ራሱም የሚፈልገው ሕዝብም የሚመኘው ተጠናክሮ መውጣቱንና ችግር መፍታቱን ነው፡፡ ነገሩ ግን ቀላል አይደለም፡፡ በአባላት መካከል የአመለካከት ልዩነት ይኖራል፡፡ የሥልጣን ፈላጊነት ባህርይ ሊከሰት ይችላል፡፡ የኔትወርኪንግ መጠላለፍ ሊከሰት ይችላል፡፡ እነዚህ ግን በቀላሉ የሚፈቱ ችግሮች አይደሉም፡፡ በሳል፣ ኃላፊነት የሚሰማውና ሕዝቡን የሚያገለግል ወገን ይህን ለመፍታት አያስቸግረውም፡፡ ብዙ ችግር እየፈታ የመጣ ነውና፡፡
ግን! ነገር ግን! በኃላፊነት፣ በሕዝባዊነት፣ በዴሞክራሲያዊነት፣ በሕጋዊነትና በሕዝባዊ የአደራ መንፈስ የማይጓዝና የማይሠራ ወገን የበላይነት ከያዘ የተጀመረው ሁሉ ተበላሽቶ ከመራመድ ወደ መንሸራተት ሊያመራ ይችላል፡፡
ችግር አለ አያስደንግጠን፡፡ መፍትሔው ላይ ግን እንረባረብ፡፡ እንዳንሳሳት እንጠንቀቅ፡፡ እንተባበር አንድ እንሁን በማለት ገዢው ፓርቲና መንግሥት ሊረባረቡ ይገባል፡፡ የተሳሳተ መፍትሔ ሊያስከትል የሚችለው አደጋ ከወዲሁ ሊታይ ይገባል፡፡
ውጤቱ ችግር ፈተው ተጠናክረው አገርንና ሕዝብን አጠናክሩ የሚያስብል እንጂ፣ ‹‹ቅቤ በርዶት እሳት ሞቀ›› ቀለጠ የሚያስብል መሆን የለበትም፡፡

No comments:
Post a Comment