Dec 2, 2013

ኡ ኡ - የመግባባት ያለህ!!

ግርማ ሠይፉ ማሩ
girmaseifu32@yahoo.com

ኢትዮጵያዊያን በተለያየ ፓርቲ አባል ሆንን ማለት ላለመግባባት ቃልኪንዳን ያሰርን እስኪመስል ድረስ መላቅድሳችን  የጠፋብን ይመስለኛል፡፡ ለምሳሌ የመለስን ራዕይ እናሳካለን በሚለው ዙሪያ መስማማት ላይጠበቅብን ይችላል፡፡ እንጋባባ  ሲባል ደግሞ አንድ እንሁን ማለታችን አይደለም፡፡
ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማሪያም እንደሚሉት ከፋብሪካ እንደወጣ  ሳሙና አንድ መሆን የህይወትን ቅመም ያሳጣል ብቻ ሳይሆን ለስው ልጅ ተፈጥሮውም አይደለም፡፡ በቤት ውስጥ እንኳን  አንድ ዓይነት መሆን ለጫወታም አይመችም፡፡ ከኢህአዴግ ጋር ለመግባባት ብሎ እናስቀጥላለን የሚሉትን የሟች ጠቅላይ ሚኒስትር ራዕይ ማወቅ የሚፈልግ አንድ ቅን ሰው ቢገኝ ይህ የሚባለውን ራዕይ በግልፅ ከየትም አያገኝም፡፡ እርግጠኛ ሆኜ የምነግራችሁ የመጀመሪያ ደረጃ ተማሪዎች፣ የወጣትና የሴት ሊግ አባላት፣ የሀርብቶ አደርና  የሌሎችም መሰል ስብሰባዎች መሪ መፈክሮች ስለ መለስ ራዕይ የሚያወሩ ቢሆንም አንድም ተመሳሳይ የሆነ አጭር  ሀረፍተ ነገርየመለስ ራዕይ ይህ ነውብሎ የሚያስረዳችሁ አታገኙም፡፡ አሁን ደግሞ የመለስ አሰተምሮ የሚል ፈሊጥ መጥቶዋል፡፡  ለእኔ ራዕይ የሚባለው በረጅም ጊዜ ለመድረስ ያሰብንበት ግብ (የተለወጠ ደረጃ) ሲሆን እዚያ ግብ ለመድረስ ግን ብዙ የምናደርጋቸው ተግባራዊ  እንቅስቃሴዎች መኖር ይኖርባቸዋል፡፡ የእነዚህ ተግባራት ድምር ነው በእርግጥ ካስብንበት የሚያደርሰን፡፡ ራዕይ ያለ ትክክለኛ ተግባር የተሳሳተ ጅምር ከመሆን አያልፍም (Vision without proper action is a false start)፡፡ ስለዚህ ዛሬራዕይ”  እናሰቀጥላለን ከሚሉ የጅምላ መፈክሮች ወጥትን መቀጠል የሌለባቸውን የተሳሳቱ ተግባሮችን እያነሳን መወያየት ተገቢ መሰለኝ፡፡  መግባባት ያለብን ነው ብዬ ስለማምን፡፡ ከነዚህ የተሳሳቱ ተግባሮች አንዱ በተለያዩ ደረጃ ያሉ ሞዴል/አርሃያ ያላቸውን ሰዎች ያለማመስገን ሲሆን የሚከፋው ደግሞ እነዚህን ሰዎች  እየተከታተሉ አንገት የማስደፋት ተግባር ነው፡፡ ባለ ራዕይ መሪዎች ይህን አያደርጉም፤ ይልቁንም እነዚህ ሰዎች እንዲበራከቱ እና ለጋራ  ራዕይ ሌሎችን እንዲያስልፉ ያበረታታሉ፣ አርሃያም ይሆናሉ፡፡ ኢህአዴግ ከዚህ አንፃር ባህሪው እንዴት ነው የሚታየው የሚል ነገር በሃሳቤ መጣና ብንወያይበት እና ለመግባባት መንገድ የሚከፍት ከሆነ ብዬ ! ! ማላት ፈለግሁ፡፡ መጮኽ፡፡ ለዚህ ጩኸት መነሻ የሆኑኝ በአጭሩ የሚከተሉት ናቸው፡፡ ቅርቡ አሜሪካን ያለ አንድ ወዳጃችን (ግርማ ጌታቸው ካሣ የሚባል) በሳውዲ ጉዳት ስለደረሰባቸው ዜጎቻችን የተሰማውን መልዕክት  ሲያስተላልፍ የኢህአዴግ ባለስልጣናትን በጅምላ ክፉና ጭራቅ አድርጎ መሳል ተገቢ አለመሆኑን አበክሮ አንስቶ ከእነ ሽመልስ ከማል  ዓይነት አደገኞች ኢህአዴግንም ቢሆን መጠበቅ እንደሚያስፈልግ እና እንደ ዶክተር ቴዎድሮስ አድሃኖም ዓይነቶችን ደግሞ ማወደስ  እንደሚያስፈልግ ጠቆም አድርጎ ነበር፡፡ የዚህ መልዕክት በጎ መሆን የሚያጠራጥር አይደለም፡፡ ይህ ፅሁፍ በደረሰኝ ዕለት ምሽት ደግሞ  እንዲሁ በኢህአዴግ ሰፈር በደግ ስለሚነሳ ታታሪ ታጋይ እና የኢህአዴግ ሹመኛ የሆነ አቶ ሀይለሥላሴ ቢሆን የሚባል በዓለማችን ከጦር  መሳሪያ ቀጥሎ አደገኛ ሙስና ውስጥ ለውስጥ የሚስራበትን የሕክምና መሳሪያዎችና መድሐኒት የሚቆጣጠር መስሪያ ቤት እየመራ በክፉ  ሰሙ የማይነሳ ሰው መሆኑን ሰዎች ነገሩኝ፣ በስራ አጋጣሚ ግለሰቡን ስለማውቀው የሚሉትን ለማመን ብዙ አልተቸገርኩም፡፡ በዚያው ሰሞን በእድሜ ልክ እስር ነገር ግን ከህሊና ዕዳ ነፃ የሆነው ወንድማችን አንዱዓለም አራጌ በጻፈው መፅሃፍ ደግሞ ወደ 1997 ምርጫ ወስዶ አቶ አርከበ ዕቁባይ በአዲስ አበባ ምርጫ ያለመመረጣቸው አንዳንዴ ፍርዳችን ፍርደ ገምድልና የጅምላ እንደሆነ ጠቅሶ  አስነበበን፡፡ የሚገርማችሁ 1997 ምርጫ ቀደም ብሎ ሟቹ ጠቅላይ ሚኒስትር ኤች.አይ./ኤድስን በሚመለከት ምንም ቃል  በማይሉበት ወቅት አቶ አርከብ ዕቁባይ እራሳቸው ኤች.አይ. ተመርምረው በአዲስ አበባ አስደናቂ የመሪነት ሚና ሲጫወቱ ይህን እንደ  ተምሳሌት ተደርጎ ቸርልችል ጎዳና ጫፍ ላይ ከአራዳ ሕንፃ ግርጌ ትልቅ ቢል ቦርድ እና በብዙ የሚቆጠሩ ፖስተሮችን እንዲታተሙ  ተደርጎ ነበር፡፡ በማግስቱ ቢል ቦርዱ ወደቀ ተብሎ ተነሳና ምን ተፈጠረ ሲባል ሟቹ ጠቅላይ ሚኒስትርየምን እዩኝ እዩኝ ነውብለው  እንዲነሳ ትዕዛዝ እንደሰጡ ሰማን፡፡ በይፋ የተሰጠ ትዕዛዝ ስለአልነበረ በሚያስደንቅ ፍጥነት ፖስተሩን እንዳይሰበሰብ አድርገን በማስራጨት አቶ አርከበን ኤች.አይ./ኤድስን አስመልክቶ የሚያደርጉትን የመሪነት ሚና በመላው ሀገሪቱ እንዲስራጭ ተደረገ፡፡ ሟቹ ቢወዱትም  ባይወዱትም ጥሩ ውጤት አመጣና ውሎ አድሮ እራሳቸው ተመርምረውእዩልኝ ስሙልኝለማለት አበቃቸው፡፡ አንዱን አንገት አስደፍቶ  እራሰን ቀና ቀና ማድግ ተገቢ ባለመሆኑ ላይ ሁላችንም መግባባት ያለብን ጉዳይ ይመስለኛል፡፡ ከላይ እንደመግቢያ ያነሳሁትን ሃሳብ ያነሳሁት በኢህአዴግ ፖለቲካ ውስጥ በጎ ምግባር ያላቸው እና የተግባቦት ችግር የሌለባቸው ሰዎች  እንዳሉ እሙን ነው፡፡ እነዚህን ሰዎች አንሰቶ በበጎ ምግባራቸው ተገቢውን ቦታ መስጠት አስፈላጊ እንደሆነ ከልቤ አምናለሁ፣ ለነዚህም  ሰዎች በበጎ ሰራቸው እንዲቀጥሉበት ስንቅ ሊሆናቸው እነደሚችል ምንም ጥርጥር የለኝም፡፡ አሰፈሪው ነገር ግን ኢህአዴግ በባሕሪው እንደዚህ ዓይነት ሰዎችን እንዴት አድርጎ ነው የሚመዝናቸው የሚለው ነው፡፡ እነኚህ ሰዎች ከእኛ ከሚያገኙት ክብርና ሞገስ በተፃራሪበቁጥጥር ስር ያዋላቸው ፓርቲ እንዳይሞቱ እንዳይድኑ አድርጎ ማኮላሸት ይችልበታል፡፡ ለእነደዚህ ዓይነት ተግባር የሟቹ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሚና ከፍተኛ እንደ ነበር በተግባር የተረጋገጠ ነው፡፡ እንግዲህ ይህ ተግባር መቀጠል አለበት የሚል እምነት የለኝም፡፡ ባለ ራዕዩ  መሪ ካስቀመጡልን መጥፎ ተግባራት አንዱ ነው እና ላለማስቀጠል መግባባት ይኖርብናል፡፡
ግርማ ሰይፉ ማሩ  ምክንያቱ በውል ባይታወቅም/የተለያዩ መላ ምቶች አሉ/ ከአቶ መለስ ዜናዊ ሞት በኋላ በኢህአዴግቾ መንደር መነቃቃት የታየባቸው የኢህአዴግ ሰዎች እንዳሉ ሁላችንም የምንታዘበው መሬት የወረደ ሀቅ ነው፡፡ እነዚህ ሰዎች አንገታቸውን ቀና እንዳያደርጉ ሟቹ ጥላቸውን  አጥልተው ነበር፡፡ አለበለዚያም የሆነ ፍላፃ ይዘው ከጀርባቸው ነበሩ ማለት ይቻላል፡፡ አሁንም ቢሆን እነዚህን ሰዎች በስም እያነሱ ማወደስ በተግባራቸው እንዲገፉበት ማበረታት በተገባ ነበር፡፡ ከኛ በኩል ውዳሴ ካገኙ በዚያ በኩል መጥረቢያ የሚሳልላቸው ከሆነ ከጥቅሙ ጉዳቱ  ስለሚያመዝን ለጊዜው ስማቸውን አለማንሳት ተገቢ ይመስለኛል፡፡ እነሱም ይህን ይረዱታል፡፡ በእኔ እምነት አቶ ኃይለማሪያም ደሰለኝ  ማስቀጠል ከሌለባቸው ተግባሮች አንዱ በእንዲህ ዓይነት ሰዎች ላይ የሚመሩት ፓርቲ መጥረቢያ መሳሉን እንዲያቆም ማድረግ  ይመስለኛል፡፡ ለእርሳቸውም ለሌሎች ተተኪ መሪዎችም ከህዝብ በጅምላ ለፓርቲ ከሚሰጥ ድጋፍ በተጨማሪ ለግለሰቦች በአስተዋፅኦ  ደረጃቸው የሚመሰገኑበትና የሚጠየቁበት ስርዓት ፓርቲውንም ቢሆን ይጠቅመዋ እንጂ አይጎዳውም፡፡ ቀና የሚሉትን እየተከተሉ አንገት  ማስደፋት መቆም ይኖርበታል፡፡ ተግባባን!! ኢሕአዴግ ማሸማቀቅ የሚፈልገው ግለሰቦችን ብቻ ሳይሆን የፈለገ ቀን የተወሰኑ የህብረተሰብ ክፍል ብሎ በጅምላ ህዝቡን ሊሆን ይችላል፡ እንደምታስታውሱት በቅርቡ በተደረገው የፕሬዝደንት ለውጥ ኢህአዴግ የህዝብን አስተያየት ለመስማት ደንታ አልነበረውም፡፡ ይልቁንም ለማሳሳት ተግቶ የሰራ ይመስለኛል፡፡ ፓርቲው ለዕጩነት ያሰባቸውን ጥቂት ሰዎች መደበኛ ባልሆነ መልኩ ይፋ አድርጎ የህዝብን ይሁንታ ቢያዳምጥ ምንም አይጎዳውም ነበር፡፡ መግባባትን ከመፍጠር ውጭ፡፡ ህዝቡን አይደለም ለጥቅምም ይሁን ለመስዋዕትነት የተሰለፉ  አባላቶቹን ባይተዋር አድርጎ ስራውን አጠናቀቀ፡፡ ይህ ብቻ አይደለም ኢህአዴግ ሲፈልግ ቡና ነጋዴዎችን፣ ከፈለገ የፋይናንስ ሴክተሩን፣ ባሻው ቀን የሪል እስቴት ሴክተር፣ ከፈለገ በአከራይ ተከራይ፣ ወዘተ ነጥሎ ይመታል፡፡ ዓላማውም አንገት ማስደፋት ነው፡፡ በዚህ በኩል በተቃዋሚ ጎራም ቢሆን የጠራ አቋም አለ ብዬ አላምንም፡፡ ምስጋና ለሚገባው ምስጋና ከመስጠት ይልቅ እየገፉ ከክፋተኞቹ ጎራ ለመቀላቀል ጥረት የሚደረግ ይመስለኛል፡፡ ለዚህ የሚቀርበው አመክንዬም ኢህአዴግን እንደ ስርዓት ነው መቃወም የሚል ነው፡፡ ይህን ስናደርግ ደግሞ ሁሉንም የፓርቲ አባላት በተለይም ከፍተኛ ሹሞች የሚያደርጉትን መቃወም ነው ብሎ የሚያምነው ቁጥር ቀላል  አይደለም፡፡ ይህ አስተሳሰብ ከመቀራረብ ይልቅ መራራቅን፣ ከመተማመን ይልቅ ጥርጣሬን፣ በማስፋት ሀገራችን ለምንላት ኢትዮጵያ እና ለህዝቡ አለን የምንለውን ራዕይ ማሳካት እንዳንችል እርስ በእርስ ተጠላልፈን እንድንቀር እያደረገ ነው፡፡ በእኔ እምነት ለብዙ የኢህአዴግ አባላት በሚፈፅሙት በጎ ምግባር የሚገባቸውን በቸርነት ለማድረግ ዝግጁ መሆን ይጠበቅብናል ከታቀፉበት ፓርቲ ሊወርድባቸው  የሚችለውን ፍላፃ ከግምት ውስጥ በማስገባት ጭምር፡፡ የእኛን ሰፈር ፍላፃ ለመቋቋምም ቢሆን ጥንካሬ ይጠይቃል፡፡ እባካችሁ በፓርቲ  ደረጃ ያሉን ልዩነቶች እንደተጠበቁ ሆነው ግለሰቦች በተናጥል ለሚያደርጉት በጎነት እውቅና ለመስጠት ብንግባባ አንዱን የልዩነት ግንብ  አፈረስን ማለት ነው፡፡ ከዚያም ለመቀራረብ መንገድ እንጀምራለን፡፡ የዛሬ ሁሁታዬ ይህው ነው፡፡


ቸር እንሰንብት!!

Oct 23, 2013

ህወሓቶች ራሳችሁን ከጦርነት ዘመን አታወዳድሩ። የደርግ ዘመን የጦርነት ዘመን ነው

ከአንድ የገጠር ከተማ ወደ መቐለ ስገባ ጓደኞቼ አንድ ወሬ አካፈሉኝ። ወሬው "መንግስቱ ኃይለማርያም 'ከትግራይ ክልል ምንም ዓይነት ግብር ሰብስበን አናውቅም' አለ" የሚል ነው። መንግስቱ ይሄን ነገር ተናግሮት ሊሆን ይችላል ወይ ላይሆን ይችላል። ዋናው ጉዳይ ተናገረው ወይስ አልተናገረውም አይደለም። እውነት ነው ወይ ስህተት?! የሚል ጥያቄም ለግዜው እንተወው።

ግን ደርግ እንዴት ከትግራይ ግብር መሰብሰብ ይችላል? ግብር ለመሰብሰብ'ኮ ባከባቢው መስተዳድር መዘርጋት አለብህ። መስተዳድር ለመዘርጋት ግዛቱ በቁጥጥር ሥር ማዋል አለብህ። ደርግ ትግራይን አልተቆጣጠረም፤ አላስተዳደረም። ደርግ ትግራይን ካላስተዳደረ እንዴት ብሎ ግብር ይሰበስባል?

ደርግ መስከረም (አከባቢ) 1967 ዓም የመንግስትነት ስልጣን ተቆጣጠረ። ከወራት በኋላ (የካቲት 1967 ዓም) ህወሓቶች ጫካ ገቡ። ደርግ ሀገራዊ ስልጣኑ ለመጨበጥ አስተዳደር ለመዘርጋት ተንቀሳቀሰ። ትግራይን ሙሉ በሙሉ ከመቆጣጠሩ በፊት ህወሓቶች ቀላል የማይባል የትግራይ የገጠር ቦታዎች ተቆጣጥረው በእጃቸው አስገቡ። ደርግና ህወሓቶች ትግራይን ለመቆጣጠር ጦርነት ከፈቱ። በሁለቱም ወገኖች የተደረገ ጦርነት ለ17 ዓመታት ዘለቀ። ትግራይ በዛን ግዜ የጦርነት አውድማ ሆነች።

በ17 ዓመቱ የጦርነት ዘመን ገጠር ትግራይ (ሓራ መሬት ትግራይ) በህወሓቶች ቁጥጥር ስር ነበር። የትግራይ ከተሞች ደግሞ በደርግ ስርዓት ቁጥጥር ወደቀ። ስለዚህ "የደርግ ዘመን" ተብሎ የሚታወቀው ግዜ ለትግራይ የጦርነት ዘመን ነበር። እኔ የደርግ ዘመን አልለውም። ምክንያቱም ደርግ ትግራይን ተቆጣጥሮ ማስተዳደር አልቻለም። ስለዚህ ለኔ የደርግ ዘመን ሳይሆን "የጦርነት ዘመን" ነበር።

ስለዚህ ህወሓቶች ራሳችሁን ከጦርነት ዘመን አታወዳድሩ። የደርግ ዘመን የጦርነት ዘመን ነው። 

Oct 20, 2013

በመከላከያ ሰራዊት ውስጥ ውጥረት አይሏል::

ሌ/ጄ ሳሞራ የኑስ በሜ/ጄ ዮሃንስ ገብረመስቀል ለመተካት የሚደረገው ሩጫ ተቃውሞ ገጥሞታል::
ከፍተኛ ጄኔራሎች ምስጢራዊ ስብሰባዎችን አብዝተዋል::የምስጢራዊ ስብሰባ ቃለ ጉባዬ የምትይዝ የሆነችው የአንድ ከፍተኛ ጄነራል ጸሃፊ ትክዳ ወይም ትገደል አልታወቀም::ለሜ/ጄ ዮሃንስ ethiopian_troops_pickupገብረመስቀል የተሰጠው የሌ/ጄ ማእረግ የታሰበው ሌ/ጄ ሳሞራን ይተካሉ ተብለው ለነበሩት ለሜ/ጄ አበባው ታደሰ የነበረ ቢሆንም በምን ምክንያት እንደተዘዋወረ አልታወቀም::
በሰሜን እዝ እና በምስራቅ እዝ የተከሰተው የሰራዊቱ ህገመንግስታዊ ጥያቄ እና የጥቅማ ጥቅም አቤቱታ በመላው ሃገሪቱ ተስፋፍቶ በከተማ እና በሌሎች የእዝ መምሪያዎችም መቀጠሉን የውስጥ አዋቂ ምንጮች ጠቁመዋል::በተለያዩ ጊዜያት እየተንከባለለ የመጣው ይህ የሰራዊቱ አቤቱታ እጅግ አደገኛ አዝማሚያ እያሳየ ሲሆን በዘረኝነት ላይ የተመሰረተ አስተዳደር እንዲወገድ እና ህገመንግስታዊ መብቶች እንዲከበሩ ጥያቄዎች ገፍተው መምጣታቸው ሲታወቅ ከፍተኛ የሕወሓት ጄኔራሎች በየቀኑ ካለማቋረጥ ምስጢራዊ ስብሰባዎችን እያደረጉ ከመሆኑም በላይ ከየእዙ የሚመጣላቸው ሪፖርት መፍታት የሚቻልበትን ጉዳይ እየተወያየኡ መሆኑ ተጠቁሟል::
ሰራዊቱ በኑሮ ውድነት እና በተቃዋሚዎች ህገመንግስታዊ መብቶች ላይ ያነሳው ጥያቄ አዛዦቹን ያስደነገጠ ከመሆኑም በላይ በአንድ ብሄር ላይ የተመሰረተ አስተዳደር እስከመቼ የሚለውም ጥያቄ መመለስ አለበት በሚል የእግር እሳት እየሆነባቸው ነው:: በቅርቡ ከስልጣን ይነሳል የሚባለው ሌ/ጄ ሳሞራ የኑስን በሜ/ጄ ዮሃንስ ገብረመስቀል ለመተካት የሚደረገውን ጥረት የብኣዴን ታጋይ መኮንኖች የተቃወሙት ሲሆን እኛም ከማንም ያላነሰ የታገልን ስለሆነ ለቦታው ብቁ የሆነ ሰው ብኣዴን እያለው ለምን እንዲህ ይደረጋል የሚል ጥያቄ አንስተዋል::
ከፓርቲ አጣብቂኝ ያልተላቀቀው የመከላከያ ሰራዊቱ የበላይ አመራር ህገመንግስታዊ መዋቅር እንዲይዝ ለማድረግ ምንም አይነት ስራ አለመሰራቱ በሰራዊቱ አዳዲስ መኮንኖች ዘንድ አቤቱታ ቢያስነሳም ጄኔራሎቹ የሚያደርጉት ምስጢራዊ ስብሰባ እንዴት መፍታት ሳይሆን ማክሸፍ እንደሚቻላቸው እየመከሩ ሲሆን አዳዲስ ወታደራዊ ደህንነቶችን በየእዙ አስርጎ በማስገባት እንዲሁም የሰራዊቱን አቤቱታ ያስተባብራሉ የሚባሉትን በስራ ምክንያት በየማእዘኑ በመበተን ለመስራት የታቀደ ሲሆን የአበታተኑን ሁኔታ በማስጠናት ላይ መሆናቸው ታውቋል:: በተጨማሪ የሚደርስባቸውን ጥቃት ለመከላከል ይረዳቸው ዘንድ ኮማንዶዎችን እና ንቁ የደህንነት ጠባቂዎችን ለራሳቸው እና ለቤተሰቦቻቸው ለመመደብ ተነጋግረዋል::
መከላከያ ሚኒስቴር ውስጥ ምዽር ጦር መምሪያ እንዲሁም ደብረዘይት እና አስፈላጊም ሲሆን በመኖሪአ ቤቶቻቸው የሚያደርጉትን ስብሰባ ቃለጉባዬ የምትይዘው የአንድ ጄኔራል ጸሃፊ ከድታ ይሁን ተገድላ ሳይታወቅ ካለፈው ሳምንት ጀምራ በስራ ገበታዋ ላይ ያልተገኘች እና የት እንዳለች የማይታወቅ ሲሆን ስልኳም መዘጋቱን ምንጮቹ አያይዘው ጠቁመዋል::
ምንሊክ ሳልሳዊ

Oct 17, 2013

የትግራይ ምሁራን ይህንን እያያችሁና እየታዘባችሁ ዝም ማለታቸሁ ለምን ይሆን?

Posted on  

አማራና ኢትዮጵያዊነት፤ በጠላትም በወገንም እስከ ሞት!
በገ/ክርስቶስ ዓባይ(አቶ በገ/ክርስቶስ ዓባይ ታዋቂ የትግራይ ተወላጅ ናቸው!)
የአማራው ሕዝብ ባህልና አስተዳደግ መተኪያ ከሌላት ከአገሩ ከኢትዮጵያና፤ ጥላና ከለላ በመሆን እነርሱን ለመታደግ ሕወቱን ሳይሳሳ ሲገብርላቸው ለቆዮት ኢትዮጵያውያን ወገኖቹ ፤ ከፍተኛ ክብርና ፍቅር እንዲያድርበት ሆኖ በዓለማዊውም ሆነ በመንፈሣዊው አስተሳሰብ ተቃኝቶ ያደገ፤ የዳበረና፤ በጠነከረ አለት ላይ እንደታነጸ ግንብ በቀላሉ የማይሸረሸር መሆኑን በተግባር እያረጋገጠ ይገኛል።
ለመሆኑ ወያኔ አማራን ለምን ጠላው?
ወያኔ ከምንወደውና ከምናፈቅረው ከትግራይ ወገናችን በመውጣቱ በጣም ያሳዝናል። ግን ደግሞ “ቆማጣን ቆማጣ ካላሉት ገብቶ ይፈተፍታል” እንደሚባለው ወያኔን እራሡ ባወጣው ስም ወያኔ፤ ወይም ደግሞ የበግ ለምድ ለብሦ በበጎች መካከል እንደተገኘ ቀበሮ ኢሕአዴግ፤ ብለን መጥራቱ የክብር ካባ ማልበስ ስለሚሆን በሚመጥነው ስም መጥራቱ ተገቢ ይመስለኛል። ይኸውም የከሃዲ ባንዳ ዘር ስብስብ ለመሆኑ አንድና ሁለት የሌለው እውነት ስለሆነ ደቂቀ ባንዳ መባል አለበት።
ከአሁን ቀደምም ቢሆን ካሣ ምርጫ ወይም ሕዝብ ባወጣላቸው ስም በዝብዝ ካሣ እኰ ለጠላት ባማበር አፄ ቴዎድሮስን በመክዳት፤ የንግሊዙን ጦር አዝማች ጄኔራል ናፒርን እየመሩ እስከመቅደላ ድረስ ያደረሱ መሆናቸው ይታወቃል። አማራው ይህንን ታሪክ በሚገባ ያውቃል፤ ይሁን እንጂ በጎሣ ግጭት የማታ ማታ የምትጎዳው አገራችን ኢትዮጵያ ስለሆነች እንዲህ ያለውን አስነዋሪ የክህደት ታሪክ በመተው ደግ ደጉን ብቻ ለልጆቹ እያስተማረ ይገኛል።
ምክንያቱም እንደ ራሥ አሉላ አባ ነጋና አው አሎም ያሉ ታማኝ ኢትዮጵያውያንም ስላሉ “ከተልባ ጋር የተገኘህ ሰሊጥ አብረህ ተወቀጥ” እንዳይሆን የጅምላ ፍረጃውን አማራው ስለማይቀበል ሁሉንም ለአገር አንድነት በሚጠቅምና ክብርን በማይነካ መልኩ በጥንቃቄ መዝግቦ ይዞታል።
እንደሚታወቀው አማራው ቀደም ባሉት መንግሥታትም ቢሆን የተመቸው ዜጋ አልነበረም። የውጭ ጠላት በመጣ ቁጥር ክተት ሥራዊት እየተባለ በራሱ ስንቅና ትጥቅ በባዶ እግሩ በመዝመት የአገሩን ዳር ድንበርና ወገኖቹን ከውጭ ወራሪ ጠላትና ከባርያ ፈንጋይ የዓረብ ነጋዴዎች ሲከላከልና ሲጠብቅ መኖሩን ታሪክ ምስክር ነው።
አማራ ለአገሩ መንግሥትም ሆነ ለወገኑ ታማኝ፤ ከመሆኑ የተነሳ ለውጭ ጠላት ፈጽሞ የማይመችና የማይታለል በመሆኑ ይኸው አገራችን ኢትዮጵያ ዳር ድንበሯ ሳይደፈር አሁን ላለው ትውልድ እንድትደርስ ከፍተኛውን አስተዋጽዖ ያደረገ ኩሩና ጀግና ሕዝብ መሆኑን አይደለም ኢትዮጵያዊ፤ የዓለም ሕዝብ ያውቀዋል።
አሁን አጭበርብሮ በሥልጣን ላይ የሚገኘው ከሐዲ የባንዳ ዘር ስብስብ ጀግና ነኝ ሲል አላፈረም። ሐቁ ግን አሁንም ቢሆን የባንዳው ዘር የአገሪቱን መሣሪያ እንኳ ታጥቆ እያለ ቢሆን አማራው የፈራ መስሎት ከሆነ የባንዳው ዘርና ፍርፋሪ ለቃሚዎቹ ውሾች ተሳስተዋል እላለሁ። እርግጥ ከአሁንም በፊትም ሆነ በአሁኑ ሰዓት አማራው ሦስትን ነገር ይፈራል።
አንደኛውና የመጀመሪያው ለብዙ ምዕተ ዓመታት አያት ቅድመ አያቶቹ ያቆዩአት ኢትዮጵያ በጠላት ሤራ የተነሣ እንዳትበታተን ይጠነቀቃል።
ሁለተኛው ደግሞ የሚወደውንና የሚያከብረውን የትግራይ ሕዝብ ላለማስቀየም ከዛሬ ነገ ይሻላል በማለት “ላም እሣት ወለደች እንዳትልሰው ፈጃት እንዳትተወው ልጇ ሆነባት “ የተባለው ዓይነት ሆኖበት እንጂ ፈርቶ ወይም ኃይል የሌለው ሆኖ አይደለም።
ሦስተኛው ደግሞ አማራ በፈሪሃ እግዚአብሔርነቱም ይታወቃል። የእናቱ ልጅ ወንድሙ እንኳ ቢሆን ከሌላ ሰው ጋር ተጣልቶ ቢያየው ያስታርቅ እንደሆን እንጂ ለወንድሙ አድልቶ ሌላውን ሰው ለመጉዳት አይደፍርም። ምክንያቱም ሰማይና ምድርን የፈጠረ አምላክን ስለሚፈራ። በዚህም ለጊዜው እየተጎዳ ቢገኝም ነገ ግን ምላሹን ከሚያመልከው ፈጣሪ እንደሚያገኘው አያጠራጥርም።
የከሃዲ ደቂቀ ባንዳዎች ዋና ጠርናፊ ሟቹ መለስ ዜናዊ ልክ የዛሬ ዓመት ገደማ የፋሲካ በዓል አካባቢ፤ በጉራ ፋርዳ ይኖሩ የነበሩትን አማርኛ ቋንቋ ተናጋሪ ኢትዮጵያውያንን እንዲፈናቀሉ ሲያደርጉ ለራሳቸው ግን አንድ ሺህ ዓመት የሚኖሩ ይመስሉ ነበር።
ፓርላማ ላይ በትዕቢት ተወጥረው ጠረጴዛ እየደበደቡ ምድር አልበቃቸው ብሎ እንደነበር አይዘነጋም ።ዛሬ ግን በሕይወት የሉም ሁለት ሜትር በማትሞላ ጠባብ ጉድጓድ ውስጥ ተወስነው ቀርተዋል። የተከሉት መርዝ ግን አሁንም ገና አልጠወለገም።
ውቃቢያቸውን የተላበሱት መብራህቱ ገ/ሕይወት (በረከት ስምዖን) ከመጋረጃ በስተጀርባ በመሆን የሙት መንፈስ እየጠሩ፤ በአሻንጉሊሊታቸው ኃ/ማርያም ደሣለኝ አማካኝነት እኩይ ተግባራቸውን እያስፈጸሙ ይገኛሉ።
እዚህ ላይ መነሣት የሚገባው ዓቢይ ጉዳይ አለ፤ ይኸውም አቶ በረከት የአማራው ድርጅት የብአዴን ድርጅት፤ የወያኔ የበላይ ክንፍ ኃላፊ መሆናቸው ይነገራል። ነገር ግን ቆሜልሃለሁ የሚሉት የአማራ ሕዝብ በገዛ ሀገሩ እንዲህ በሕገወጥ መልክ ሀብትና ንብረቱን እየተቀማ ሲሳደድና ሲንገላታ፤ ሌላው ቢቀር ከሞራል አኳያ እንኳ ህሊናቸውን አይሰቀጥጣቸውም? የእርሳቸው ልጆችስ? የአሰፉ ልጆች ስለሆኑ ምንም አይድል? “የማትረባ ፍየል ዘጠኝ ትወልዳለች ልጆቿም ያልቃሉ እሷም ትሞታለች” እንደተባለው ይሆናል ብለው ይሆን? ግምታቸውን እውን ያድርግላቸው።
ወያኔ የውጭ ዜጋ ቢሆን ኖሮ እሱን አያድርገኝ፤ በየደረሰበት ዋጋው እየተሰጠው በወጣበት ይቀር ነበር እንጂ፤ እንዲህ እነሱ እንደፈለጉ ሲፏልሉ፤ አማራው አማርኛ ቋንቋ በመናገሩ ብቻ በሰላም ከየሚኖርበት፤ በድካሙ ያፈራውን ህብትና ንብረቱን በመንግሥት አካላት እየተቀማ ሲባረር ዝም አይልም ነበር። አዎ! መንግሥት ይለወጣል፤ ፖሊሲም ይቀየራል፤ ታዲያ ለሚያልፍ ቀን ሲል የሚወዳትን አገርና ወገኑን እኔ ከሞትኩ ሠርዶ አይብቀል አንዳሉት የባንዳ ልጆች አስተሳሰብ ቢሆንማ ኖሮ ያሳያቸው ነበር። ሡሪውም፤ ጀግንነቱም ወኔውም በደም ሥር ውስጥ ያለ መሆኑን ባንዶች የተገነዘቡት አይመስልም።
ገና ከመጀመሪያው ወያኔ ወገን ባይሆንና ወይም ተንኮሉ በግልጽ ቢታወቅ ኖሮ እንኳን ኢትዮጵያን መቆጣጠር ይቅርና ተከዜን መሻገር አይችልም ነበር። አሁንም ጊዜ ይለወጣል የሰውም ልብ እንዲሁ ይቀየራል ያን ጊዜ ወዮ!
ከሐዲ የባንዳዎች ስብስብና ፍርፋሪ ለቃሚ ውሾቻቸው፤ አማራውን ባትነካኩት ጥሩ ነው ሌላው ቀርቶ ለራሣችሁና ለልጆቻችሁ ስትሉ ባታሠቃዩት መልካም ነው። ያለበልዚያ ይህ ሕዝብ መሣሪያ የለውም ብላችሁ እንደዜጋ ሳይሆን እንደእንስሣ የምታዩት ከሆነ መሣሪያው እኮ ጠመንጃና ጥይት ብቻ አይደለም። ሐቅን ለያዘ ሰው ልብ ብቻ በቂ ነው። መሥሪያውማ ዙሪያ ገባው ሁሉ መሣሪያ መሆኑን ልትገነዘቡ ይገባል።
የአማራው ሕዝብ ግን ለአገሩና ለወገኑ ሲል፤ ንብረቱን እየተቀማ፤ ለረጅም ጊዜ ከኖረበት ቀዬ እንዲፈናቀል ሲደረግ አንገቱን ደፍቶ ለአገርና ለወገን ሲል መከራውን በትዕግሥት እየተቀበለ ይገኛል።
ምን ዓይነት አርቆ አስተዋይነት ነው? ምን ዓይነትስ ሆደ ሠፊነት ነው? ምን ዓይነት ታማኝነት ነው ?እጅግ በጣም ይገርማል! ይደንቃል።
በተለይ የትግራይ ምሁራን ይህንን እያያችሁና እየታዘባችሁ ዝም ማለታቸሁ ለምን ይሆን?
የአማራው መንገላታት ፤መሰደድ፤ በፍርድ መጓደል ከሚኖርበት ቅየው መፈናቀል፤ እውነት እናንተን ጤናና ሰላም ይሰጣችኋል? በእንደዚህ ያለ ወሳኝ ወቅት ላይ፤ እንኳን ወገን ለወገኑ ለባዕድም ቢሆን በሰብዓዊነት እንኳ ድምጽ ሊሆንለት በተገባ ነበር።
ምናልባት በጥቅም ተይዛችሁ እንኳ ቢሆን ሌላው ቀርቶ የዓለም አቀፍ መብቶች እንዲከበሩላቸው ብታደርጉ፤ ለራሳችሁና ለልጆቻችሁ እንዳደረጋችሁ ልትቆጥሩት በተገባ ነበር። ያለበለዚያማ ፈጽሞ ለማይቀረው ለውጥ ተዘጋጁ። የምትሠሩትን የምታውቁ አይደላችሁም።
ዛሬ በአማራው ላይ የምትፈጽሙት ሤራ ነገ እኰ ወደናንተም እንደሚቀሰር ረሳችሁት እንዴ? እንደዚህ ያለውን ተግባር የምትደግፉ ከሆነ ትግሬም ከተከዜ ማዶ እንጂ ወንዙን መሻገር የለበትም መባሉን ዘንግታችሁት ከሆነ እኔ ላስታውሳችሁ።
ወንድነቱንና ጀግንነቱን እንኳ ለአማራው ማንም ሊያስተምረው አይችልም። የአማራውን ትዕግስት እንደ ፍርሃት ቆጥራችሁ ከሆነም ትሳስታችኋል። እንኳን አሁን ቀደም ሲል ኰሎሎኔል መንግሥቱ ኃይለ ማርያም እንኳ በአንድ ወቅት ወያኔን አስመልክቶ ሲናገሩ “ ድንጋይ ቢወድቅብን ይሰብረናል፤ ብንወድቅበትም ይሰብረናል” ማለታቸው ይታወሳል። ምሁራን ናችሁና የዚህን ፈሊጣዊ አባባል ትርጉም ታጡታላችሁ የሚል ጥርጥር ባይኖረኝም፤ ገድለንም የምንጎዳው እኛ ሞተንም የምንጎዳው እኛ ማለታቸው ነበር። በዚያም ሆነ በዚህ የወገን የእርስ በእርስ ግጭት ዞሮ ዞሮ የሚጎዳው የአገራችንን ዕድገትና ልማት፤ እንዲሁም ሕዝባችንን በቀላሉ ሊጠገን ከማይችል ማኅበራዊና ሥነ ልቦናዊ ቀውስ ውስጥ መክተት ይሆናል ማለታቸው ነበር።
የአማራውም ሕዝብ እንዲህ የሚሠቃየውና እንደከብት አንገቱን በስለት የሚታረደው ለአገሩ አንድነትና ኅልውና ስለሚቆረቆርና፤ ችግሩ የጥርስ ደም ሆኖበት፤ ይህ የስቃይ ዘመን ያጥር ዘንድ ፈጣሪውን እየለመነ ይገኛል። የፖለቲካ ሀሁ የማያውቁ፤ ኢትዮጵያዊ መሆናቸውን እንጂ አማርኛ ቋንቋ ከመናገር ውጭ አማራ መሆናቸውን እንኳ የማያውቁ ንፁሕ ኢትዮጵያውያን በወራሪ ደቂቀ ባንዶች ስብስብ ቀጭን ትዕዛዝ ሲንገላቱና ሲሠቃዩ እያያችሁ ዓይኔን ግንባር ያድርገው፤ የዝሆን ጆሮ ይስጠኝ የምትሉ ከሆነ ነገ ከተጠያቂነት በፍጹም አታመልጡም።
ወዮ የትግሬ ምሁራን የሆናችሁ ሁሉ፤ አሁን ያለው የከሐዲ ባንዳ ስብስብ፤ ዘራፊ ሥርዓት በዚሁ ይቀጥላል ብላችሁ የምታስቡ ከሆነ ተሳስታችኋል። ሐቁን መረዳት ተስኗችሁ ከሆነ እንኳን እየዘረፉና እየቀሙ መኖር ይቅርና በወያኔ ሥርዓት እንደ እንጉዳይ የፈሉ ሚሊየነሮችና ባለቪላ ቱጃሮች፤ እንዲሁም ያለፉበትንና ያልደከሙበትን ውድ መኪና የሚያሽከረክሩ ሁሉ በአገር ውስጥ ብቻ ሳይሆን በውጭ አገር ሳይቀር በተለያዬ ዘመድና ጓደኛ ስም እንኳ የተቀመጠ ያለአግባብ ከሕዝብ የተዘረፈ ገንዘብ ሁሉ እንደሚመለስ አትጠራጠሩ። እናንተም የሚጠብቃቸሁ ፍትህ ስለሚሆን እንደየተግባራችሁ የየሥራችሁን ማግኘታችሁ አይቀርም። ስለዚህ ከአሁኑ ወደ ኅሊናችሁ ተመልሳችሁ ከተገፋው ሕዝብ ጎን ልትቆሙ ይገባል።