Feb 19, 2013

የዋሾ መንግስት ጩኸት


ውሸት!ውሸት! ውሸት! ውሸት!

ሉሉ ከበደ
ሰሞኑን ወያኔ የተለመደ የውሸት ድራማ ሰርቶ፤ ሲሞን በረከት በሚባል፤ የማያምር፤ የማያፍር የኤርትራ ሰው፤ ጭራሹን አማራ ነኝ ብሎ እንዲያታልል ወያኔ የቀጠረው ባእድEthiopian Muslims, we are all Abubeker የፕሮፓጋንዳ ሚኒስቴር፤ የሀሰት ፊልም ደራሲና የበላይ አዘጋጅ የሆነ ሰው፤ ሰርቶ ጨርሶ ያሳለፈውን “ጂሀዳዊ ሀረካት” በሚል ርእስ ባለፉት ሀያ ሁለት አመታት ከሚያደርገው ነገር የተለየ ባይሆንም፤ ቀጣይ የማናደድ ስራቸውን ለኢትዮጵያ ህዝብ አቅርበው ነበር። እንደድሮው አረፍተነገርና የስእል እንቅስቃሴ እየበጣጠሱ፤ ቆርጠው እየቀጣጠሉ፡ እየገጣጠሙ፤ ውሸት እየደራረቱ፤ ለራሳቸው ያሳምናል ብለው እንደመሰላቸው ለኢትዮጵያ ህዝብም ይመስለዋል ብለው በታመመ አእምሮ ስለሚያስቡ ለቀውታል።
ከኢትዮጵያዊው ሙስሊም የመብት ጥያቄ ጋር እንዲሁም ባህሪ ጋር ከቶም ከቶ የማይገናኝ፤ የንጹሀን ሙስሊም ወንድሞቻችንን ስም ለማጥፋት፤ መልካሙን የኢትዮጵያ ሙስሊም ሀይማኖትና ወደር የለሽ መልካም ስነምግባር ጥላሸት ለመቀባት፡ ይህንን ውብ መልኩን ለማጠልሸት፤ ብሎም ከኢትዮጵያዊ ክርስቲያን ወንድሙ ጋር ለማጋጨት ደም ለማቃባት፤(የማይቻል መሆኑን ቢያውቁትም) የሀሰት ፕሮፓጋንዳ ነዝተዋል።
ኢትዮጵያዊው ሙስሊምና ኢትዮጵያዊው ክርስቲያን ተቃቅፎ፤ ተደጋግፎ፤ በሞት በልደት ተጠያይቆ፤ ተቀባብሮ፤ ተዛዝኖ፤ የሚኖር፤ ክርስቲያኑ የሙስሊሙን አውድአመት አክብሮ፤ ኢድ አልፈጥር፤ ኢድሙባረክ ተባብሎ፤ ሙስሊሙ የክርስቲያኑን አውዳመት አክብሮ እንኳን ለገና እንኳን ለመስቀል አደረሳችሁ ብሎ፡አብሮ በልቶ፤ ጠጥቶ፤ ተደስቶ፤ ሰምና ወርቅ ሆኖ ለዘመናት የኖረ፤ እየኖረ ያለ፤ ወደፊትም የሚኖር ህዝብ ነው።
ወያኔዎች፤ የጣሊያን ጻእረመንስ ርኩሳን፤ የኢትዮጵያን ህዝብ ዘርን ከዘር በማጋጨት አልሆን ሲላቸው፤ በሀይማኖቱም ሞክረው ባይሳካላቸውም፤ አሁን ያደረጉት ነገር የሚያሳየው ተስፋ አለመቁረጣቸውን ነው። “አንድቀን እናያይዛቸዋለን” የሚል ህልም እስካሁን እንዳላቸው ይህ ፊልም ያረጋግጣል።
እንደዚያ መሰሪ አለቃቸው ከርሰመቃብር ካልወረዱ ጥረታቸው እስከመጨረሻው ይቀጥላል። ግን..ግን..ሁለት ሁለቱን እያጣመረ እግዜር እየወሰደ እሰከሚጨርሳቸው እኛም የምንጠብቅ ከሆነ ጅሎችና ፈሪዎች ነን። እግዚአብሄር ጀምሮ አሳይቶናል። የስርአቱን እስትንፋስ መጨረስ የኛ ፈንታ ነው።
በፈጠራው ፊልም ለማሳየት የተሞከረው የመላውን አለም ቀልብ የሳበውን፤ የብዙ ሀገር መንግስታት ያስቀናውን፤ በየትም ያልታየውን፤ ፍጹም ሰላማዊ የሆነ ኢትዮጵያዊ ሙስሊም ንቅናቄ፤ ናይጄሪያ ውስጥ እንዳሉት እብዶች፤ ማሊ፤ ሶማሊያ፤ አፍጋኒስታን አሁን አለማችን ካለችበት የስልጣኔ ደረጃ እጅግ በራቀ ሁኔታ ወደሗላ ተመልሰን እንተዳደር፤ የሚሉ፤ ቅዱስ ቁርአንንም ጠንቅቀው ያልተረዱ፤ ነብያችን ሙሀመድ ያሉትንም ጠንቅቀው የማያውቁ አሸባሪዎች፤ናቸው ተብሎ የሚነገርላቸው ጂሀዲስቶች፤የሚያደርጉትን ነገር፤ ኢትዮጵያዊው ሙስሊም የመረጣቸው መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላት፤ መሪዎች ሊያደርጉ የተዘጋጁ ወይም የሚያደርጉ ናቸው የሚል ነው።
ኢትዮጵያዊው ሙስሊምማ አሸባሪ አልቃይዳ ቢሆን ኖሮ እየተገደለ ሰላምን ለማምጣት ባልጣረ ነበር። ኢትዮጵያዊው ሙስሊምማ አልቃይዳ ቢሆን ኖር ገና የመጀመሪያዋ ጥይት ከወያኔ ስትተኮስበት አፈርድቤ ባስጋጣቸው ነበር። ችግሩ ትንንሽ ሰዎች ታላላቅ ሰዎቸን የሚያስተዳድሩ ሆነ። ይህንን ፊልም ለኢትዮዮጵያ ህዝብ ከሚያሳዩት ይልቅ፤ለምእራባውያን ጌቶቻቸው፤ ወይንም ለቻይና የንግድና የሌብነት ሸሪኮቻቸው ቢያሳዩት ስለሚታመኑ እንደልማዳቸው የገንዘብ እርዳታ በማጭበርበር ማግኝት ያስችላቸው ነበር። ለኢትዮጵያ ህዝብ ማሳየታቸው ከንቱ ድካም ነው። ተስፋ ያለመቁረጠቸው አስገራሚ ሊሆን ይችላል።
ኢትዮጵያዊው ሙስሊም ለኢትዮጵያ ህዝብ ብቻም አይደለም ለመላው ዓለም በየትም ባልታየ መልኩ ታላቅ ትምህርት እያስተማረ ይገኛል። እየተገደለ፤ እየተገረፈ፤ እየታሰረ፤ መብቱን ለማስከበር “በዲናችን እንጽና “ ብሎ በጽናት መታገል ይዟል።ሚሊዮኖች ህዝብ፤ አንድ ሀይማኖት፤ አንድ ህዝብ፤ አንድ አቋም! “ ሕገመንግስታዊ መብታችን ይከበር! ድምጻችን ይሰማ!” ሌላ ነገር የለም።
ለኢትዮጵያውያን ክርስቲያኖች፤ ሙስሊም ወንድሞቻችን እህቶቻችን የሚጠይቁት የሀይማኖት ነጻነት የሚመለከተን አንገብጋቢ ጥያቄ ነው። ፈሪሀ እግዚአብሄር የሌላቸው፤ ሀይማኖት የሌላቸው፤ ኢትዮጵያዊ ሰብእናናሞራል የሌላቸው፤ በጦር ሀይል መደራጀት የቻሉ ሌቦች፤ ዝቃጭ የህብረተሰብ ክፍሎች፤ኢትዮጵያን የምታህል ትልቅ ሀገር መቆጣጠር የቻሉ ፍጹም እድለኛ ወንጀለኞች ይዘውናል። እስላምንም እኛ የምንፈጥረውን ካልሆነ፤ ክርስትናውንም እኛ የምንፈጥረውን ካልሆነ ምንም መሆን አትችሉም ብለው ዘጠና ሚሊዮን ህዝብ ወጥረዋል። እኛ ነን እነሱ ናቸው ብዙና ሀይለኛ?
የኢትዮጵያ ሙስሊም እንኳን ጂሀድ ሊያውጅ፤ እየተገደለ፤ እየታሰረ፤ እየተገረፈ፤ ባሳለፈው አንድ አመት ጠጠር አንስቶ የወረወረ ሕዝብ አይደለም። ሕዝቡ ታላቅ የሰላም ሀዋርያ ነው። ወደ አላህ ከማልቀስ በቀር ያደረገው ነገር የለም። የኢትዮጵያን ህዝብ ታላቅነት ያመለከተ ታላቅ ተግባር ነው። ትግስት። ይህ ስልጣን ላይ ላሉት ባለጌ የባንዳ ልጆች ትርጉም የሚሰጣቸው ነገር አይደለም።
ጂሀድ!..አዎ.. ትክክለኛ ወያኔያዊ ጂሀድ! በኢትዮጵያ ከሰፈነ ሀያ ሁለት አመት አስቆጥሯል። በሰይፍ ዘረኝነትን ማስፋፋት፤ በሰይፍ ህዝብን መከፋፈል፤ በሰይፍ የግለሰብን የሀገርን ሀብት መዝረፍ፤ በሰይፍ የኔ ዘር እንጂ የማንም ዘር ጦር መሆን አይችልም ብሎ የአንድዘር ሚሊሺያ ተቀበሉ ማለት፤ በሰይፍ ዜጎችን እየገደሉ መሬታቸውን ለባእዳን መሸጥ፤ በሰይፍ ተቃዋሚን ሁሉ ማጥፋት፤ በሰይፍ እኔ ያመጣሁልህን ሀይማኖት ተቀበል ማለት፤ ሀያ ሁለት አመት! የኢትዮጵያ ህዝብ ሊዋጋው የሚገባ ጂሀድ ይህ ነው።
ለብዙ ሺህ ዘመናት ተፋቅሮ በየትኛውም አለም በሌለ መልኩ ተከባብሮ የሚኖርን ህዝብ ለማባላት “እስላም ጂሀድ ሊያውጅብህ ነው” ብሎ ክርስቲያኑን ቢያስፈራራ፤ ህይወትም ዩኒቨርስቲ ነውና ሀያ ሁለት አመት ሙሉ የመከራ ዩኒቨርስቲ ውስጥ ያሳለፈ ህዝብ ለእያንዳንዱ ሰው ከእድሜው ቁጥር በላይ እየዋሹ ላያቸው ህዝብ ቢነግሩት ሊገባው የሚችል ነገር አይደለም።
ሙስሊም ወንድሞቻን ትርፍ ነገር አይደለም የጠየቁት። ወያኔ አስተዳድርበታሉ የሚለውን ሕገመንግስት እንዲያከብር ነው። ሕገመንግስቱን ካከበረ፤ ለህገመንግሰቱ ከተገዛ                   በኢትዮጵያ ምድር ሰላም ወረደ። ይህ የጋጠወጦች ቡድን ሕዝቡን ሰላም እየነሳ ያለው ራሱ ሕግን እየጣሰ፤ የፈለገውን ነገር እያደረገ መኖርን ስራ ስላደረገው ነው። ወንድሞቻችንና እህቶቻችን አሁንም እየጠየቁ ያሉት “ሕገመንግስቱ ይከበር፤ ድምጻችን ይሰማ” ነው። “መንግስት በሀይማኖታችን ጣልቃ አይግባ” ነው። “መሪዎቻችንን እኛው እንምረጥ፤ መንግስት አይደለም እነ እገሌ ናቸው የሚመሯችሁ የሚለን” ነው።
አዎ!.. ዘጠና ጊዜ ቢደጋገም ትርጉም የለውም። ሕገመንግስቱ “መንግስት በሀይማኖት ጣልቃ አይገባም” ይላል። እርግጥ ነው አንደመንግስት ጣልቃ የሚገባበት ጊዜ አለ። ያ የሚሆነው በሀይማኖት ስም በሀገርና በህዝብ ደህንነት ላይ ወንጀል የሚፈጽም ሀይል መኖሩ ሲረጋገጥ  ነው። ይህን አይነት ወንጀል ስልጣን ላይ ካሉት ሰዎች የበለጠ በኢትዮጵያ ውስጥ ያደረገ ህይማኖትም ዘርም; የለም፤.. የለም።
የኢትዮጵያን ህዝብ የምጠይቀው አንድ ነገር አለኝ። እነዚህ ሰዎች ከመጡ ጊዜ በሗላ እንዳየነው እስላምና ክርስቲያን ተጋጭቶ ቤት ተቃጠለ፤ ሰው ሞተ የሚባል ዜና ሰምታችሁ ታውቁ ነበር? ባለፈ አመትና ሁለት አመት በጅማ አካባቢና ወደደቡብ የተደረገ ነገር የኢትዮጵያዊ ሙስሊምና ክርስቲያን ተግባር የነበረ ድርጊት ነው ትላላችሁ? የወያኔ ስራና ፈጠራ አይደለም ብላችሁ የምታምኑ አላችሁ?.. አስረዱኝ።
አዎ!.. ህዝቡ ነጻነት ያስፈልገዋል። የሚፈልገውን የመምረጥ፤ የመሾም፤ የመሻር፤ ከየቤተ እምነቱ እስከላይ መንግስቱ፤ ዲሞክራሲ ያስፈልገናል። እኔ አውቅልሀለሁ የመባል የሩቅ አሮጌ ዘመን ያስተዳደር ስልት ይበቃናል። በኢትዮጵያ ምድር የመጨረሻዎቹን ድኩማን የትግራይ ፍልፈሎች ስናስወግድ ነገሩ የሚያልቅ ይመስለኛል።
እንደ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን በቄስና በጳጳስ ልብስ፤ የትግሬና የአድርባይ ሆዳም መንጋ መልምሎ፤ ቤተክርስቲያኒቱንና፤ ሕዝበ ክርስቲያኑን እያመሰ፤ እንዳሽመደመደ፤ ሙስሊሙንም አሽመድምዶ ሊያስቀር፤የማያቋርጥ ጥረቱን አለማቆሙ የኢትዮጵያን ህዝብ መዳከም የሚያሳይ ትልቅ ምልክት ነው።
ይህ ለኢትዮጵያ ህዝብ ግልጽ ነው። ሙስሊም ወንድሞቻችን ወደ አላህ አለቀሱ እንጂ ጂሀድ አላወጁም። እየተገደሉ አልገደሉም። ለመግደልም አልተዘጋጁም።የኢትዮጵያ ህዝብ ሲገደል የመጀመሪያው አይደለም። ሸፈተ? ለመግደል ተነሳ? ሀያ ሁለት አመት። ለመላው አለም ታላቅ ትምህርት ነው። ኢትዮጵያውያን ሙስሊም ወንድሞቼ እንደወያኔና እንደ እኔ አይነት ደካማ አስተሳሰብ ያላቸው ዜጎች ቢሆኑ ኖሮ በወያኔ ላይ ጂሀዲ ከታወጀ ቆይቷል። ወያኔን መግደል ከተጀመረ ቆይቷል። ወያኔ መንግስት ነኝ ካለ በሗላ የኢትዮጵያን ህዝብ መግደል ሲጀምር እኛም ወያኔን መግደል ጀምረን ነበር።…ግና የኢትዮጵያ ህዝብ እንደ እኔ አይነትም አይደል፤ እንደ እነሱ አይነትም አይደል፤ እየተገደለ ሰላምን ለማምጣት የሚጥር በአለም ላይ የመጀመሪያው ታላቅ ህዝብ ነው።
እርግጥ አንባገነን መንግስታት ሁለመናቸው ውሸትነው። መዋሸትን የሚፈሩበት ምክንያት የላቸውም። ምክንያቱም ለሚያስተዳድሩት ህዝብ ስለዋሹ እናጣዋለን የሚሉት ጥቅም የለም። እናጣዋለን የሚሉት ስልጣን የለም። ሁሉም ነገር በጃቸው ነው። ዲሞክራሲ ባለበት ሀገር ከፍ ያለ ስልጣን ላይ ያለ ሰው (ፖለቲከኛ)፤ ውሸት ቢናገር ለብዙዎች ከፍተኛ ስልጣን ላይ ላሉ ከስራ መባረር ምክንያት ይሆናል። ለፓርቲውም የወደፊት ምርጫ እድል መበላሸት ምክንያት ይሆናል። ለራሱም ይከሰሳል። ጦሱ ብዙ ነው።
እንደ ወያኔ አይነት የሽፍታ ቡድን አገር የመግዛት እድል ባገኘበት ምድር ይህ የአደባባይ ውሸት የሚገርም ነገር አይደለም። ኮሎምቢያ ውስጥ ከባድ የወንጀለኞች ቡድን ህገወጥ ድርጅት አለ ። ጣሊያን ውስጥ  ከባድ የወንጀለኞች ቡድን ማፊያ እስካሁን መንግስት መሆን አልቻለም። ኢትዮጵያ ውስጥ  የወንጀለኞች ቡድን መንግስት መሆን ቻለ። ወያኔ።
የኢትዮጵያ ህዝብ ስንቱን በደል ነው ተሸክሞ የሚኖረው?..ሳያጠፉ መታሰር፤..በፈጠራ ክስ ፍርድ ቤት መቅረብ፤..ሰውን እያሰቃዩ ያላደረገውን ያላለውን አደረኩ አልኩ ማስባል፤… ሌላ ቦታ ስለሌላ ጉዳይ የተናገረውን ቆርጠው ቀጣጥለው ለጣጥፈው ለክሳቸው የሚስማማ አረፍተነገር በመስራት ለህዝብ ማሰማት..የሀሰት ምስክሮችን መልምሎ አሰልጥኖ ማስመስከር፤ ሕሊናቸውን የሸጡ ዳኞችን በየፍርድቤቱ ኮልኩሎ ከላይ በሪሞት ኮንትሮል እንደ አሻንጉሊት እየተቆጣጠሩ የሚፈልጉትን ነገር ማስፈረድ፤መንግስት ነኝ የሚለውን የዘራፊዎች ቡድን ይቃወማል የተባለውን ዜጋ ሁሉ ረጅም እስራት፤ እድሜ ልክ፤ ሞት ማስፈረድ….እስከመቼ?..እስከመቼ?…እስከመቼ?..
ከቶውንም ወንድሞቻችን ሙስሊሙ ማሀበረሰብ የመረጣቸው መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላት ሲታሰሩም ያለምንም ምክንያት የውንብድና ስራ ሰለባ በመሆናቸው ብቻ ነበር።
ሀያ ሁለት አመት የኢትዮጵያን ህዝብ እየገደለ፤ እየዘረፈ፤ የሽብር ፐሮፓጋንዳ እየነዛ፤ ፈንጅ እያፈነዳ፤ እያሸበረ፤ የሚኖር የወሮበሎች ቡድን ኢትዮጵያዊውን ሙስሊም አሸባሪ ቢለው የኢትዮጵያ ህዝብ አይደለም በሌላውም ዓለም ያለ ህዝብ እንደሚሳለቅበት ምንም ጥርጥር የለውም። ምክንያቱም በኢትዮጵያ ውስጥ ያለ አሸባሪ ወያኔ ብቻ መሆኑን ዓለም ስለሚያውቅ።
የኢትዮጵያ ህዝብ ለመብቱ ከሙስሊም ወንድሞቹ ጎን መቆም ይጠበቅበታል።እስላምና ክርስቲያኑ አብሮ ከቆመ፤ የኢትዮጵያ ህዝብ ማለት ይኸው ነው። ወያኔንም የሚያስፈራው የሙስሊሙና የክርስቲያኑ መደጋገፍና አንድ መሆን፤ የኢትዮጵያ ህዝብ አንድ መሆን ሰለሆነ የሁለቱ ታላላቅ ሀይማኖቶች አንድ መሆን ማለት ወያኔ ዘርን ከዘር እያባላ የመኖር ፊልሙ ተቃጠለ ማለት ነው። ምክንያቱም የኢትዮጵያ ብሄረሰቦች ሁሉ ወይ ክርስቲያን ወይ እስላም ናቸው። ከሁለቱ ውጭ ያሉ እመነቶች በጣም ጥቂት ናቸው። ስለዚህ ክርስቲያን እስላም አንድሁን! ተባበር!
በመሰረቱ ሙስሊም ወንድሞቻን የጠየቁት የሀይማኖት ነጻነት መሰረታዊ መብት ነው። ትርፍ ነገር አይደለም። ሕገመንግስቱ ያሰፈረው ነገር ነው ( ህገ መንግስት በሀገሪቱ ገዢዎች ዘንድ ትርጉም አለው ባንልም) እኛ እንደ ህዝብ ትርጉም አንዲኖረው የጋጠወጦቹን ቡድን ማስተማር ይጠበቅብናል። እና ሙስሊም ወንድሞቻችን ያሉት “ህገመንግስቱ ይከበር! ድምጻችን ይሰማ” ነው። ወያኔ የኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያኒቱን እያመሰ ያለው ይህንኑ መሰረታዊ መብት በመንፈግ ነው።
አሁን ደሞ ይባስ ብሎ “እስላም ሊፈጅህ ነው;። ጂሀድ ሊያውጅብህ ነው። የእስላም መንግስት ሊያቆምብህ ነው።” እያለ የውሸት ሽብር በህብ ላይ ይነዛል። በራሱ በህዝቡ ግብር በሚተዳደር ራዲዮና ቴሌቪዥን። ይህን የሚያደርገው መንግስት ጋዜጠኞችን “ዋሻችሁ ህዝብና መንግስትን የሚያጣላ አንዲት አረፍተ ነገር ጻፋችሁ” ብሎ አመት ሁለት አመት የሚያር መንግስት ነው።
በስደት ያለው ሲኖዶች የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ አባቶች የኢትዮጵያን ሙስሊም ክርስቲያን ህዝብ ያስደሰተ፤ መግለጫና መልክት አስተላልፎ ነበር። በሙስሊም ወንድሞቻችን ላይ ወያኔ እያደረሰ ያለውን በደል እንዲያቆም የሚያወግዝ፤ ለኢትዮጵያ ህዝብ ወንድማማችነት ታላቅ ግብአት ነው። ለወያኔ ታላቅ ፍርሀትና ጭንቅ ነው።ለዚህም ነው ይህ የሌቦች ቡድን ያለ የሌለ ውሸት እየፈጠረና እየደራረተ ሙስሊሙንና ክርስቲኑን ለማበጣበጥ ያለመታከት እየሰራ ያለው።
ኢትዮጵያዊው ክርስቲያን ሆይ! እስቲ ያንተም ጥያቁ መንግስት በሀይማኖታችን ጣልቃ አይግባ ይሁን! የታሰሩት የሙስሊም መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላት ባስቸኳያ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ይፈቱ በል፡ የፖለቲካ እስረኞች ይፈቱ በል፡ የታሰሩ ጋዜጠኞች ይፈቱ በል። የኢትዮጵያን ህዝብ ወያኔ ካሰናዳለት ጥፋት የሚያድነው አንድ መሆን ብቻ ነው።መደጋገፍ ብቻ ነው።
በሰላማዊ ትግል ለውጥ ይመጣል ብለህ የምታምን ሙስሊም ወንድሞቻችንን ተከተል። ወያኔ አፍ የፈታበትንንና እስከ አሁን የሚናገረውን የጡንቻ ቋንቋ የተረዳህ ካለህ፤ በሚገባው ቋንቋ ሊያናግሩት የቆረጡ ጀግኖቻችንን ተቀላቀል። ሀያሁለት አመት ለተስፋና ለትግስት ከበቂ በላይ ነው። ከንግዲህ በሗላ ያለው ዝምታ የፍርሀት ነው። ለወያኔ ደግሞ  በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ ሰንሰለቱን የበለጠ የሚያጠብቅበትና መሬቱን ሸጠው ሲጨርሱ እንደባሪያ ህዝቡን በሰንሰለት አስረው መሸጥ የሚጀምሩበት ጊዜ ነው። በጉዲፈቻና በግርድና ስም ልጆቻችንንና እህቶቻችንን መሸጡ በቂ አልሆነም።
ሙስሊሙ አርብ ቤተ መስጊድ ተሰብስቦ ከጁምአ መልስ የሚያደርገውን “አላሁአክበር፤”  ለእግዚአብሄር አቤቱታ፤ ክርስቲያኑም እሁድ እሁድ በየቤተክርስቲያኑ ከጸሎት መልስ ላምላኩ “እግዚኦ” በማለት ተመሳሳይ ተማጽኖ ማድረግ አለበት። የሙስሊም ወንድሞቻችን እንባ ወያኔን እሳት ሆኖ ይፈጀዋል። የክርስቲያኑም ይጨመርበት ይብሱን በቁም ይቀቅለዋል። ወጣቶች ይህን ሚና መጫወት ህብረተቡን እየቀደሙ መምራት ይጠበቅባቸዋል።
ዛሬ በኢትዮጵየያ ያለው የተማረ ወጣት ትውልድ ከሀምሳ እጅ በላይ ስራ አጥ ነው። በከንቱ የሚንገዋለል ነው። ከፊቱ ድቅድቅ ጨለማ ተጋርዷል። የሚያየው የሚጨብጠው ተስፋ የለውም። በአረቄ፤ በጫትና በሀሺሽ እየደነዘዘ ሲቃዥ ከሚኖር ለምን አንድ ሆኖ አይነሳሳምና ሕዝቡን ለለውጥ አያነሳሳም? ሀገሪቱ ከአንድጎሳ በተውጣጡ ጥቂት ጋጠወጦች መዳፍ ውስጥ ወድቃ ከጊዜ ወደ ጊዜ ሰንሰለቱን እያጠበቁ ወያኔ ወጣቶቻችንን ባሪያ አድርጎ ሊሸጣቸው ሊለውጣቸው ሲዘጋጅ አፍጦ የሚያስተውለው ወጣት የተሻለ ቀን እንደመና ከሰማይ ይወርዳል ብሎ እየጠበቀ ይሆን?
ኢትዮጵያ ለዘለአለም ትኑር!

የኢትዮጵያ ትምህርት ፖሊሲና ችግሮቹ


ወያኔ በ21 ዓመት ቆይታው በትምህርት ፖሊሲው ላይ ይዞት የመጣው የኣንድ ቢሔር ብቻ የመጥቀም ኣላማውን ከግብ ለማድረስ በ1984ዓ ም ኣዲስ የትምህርት ፓሊሲ ቀርፆ 10ዓመት ባልሞላ ውስጥ ሶስት ጊዜ የመማሪያ መጽሐፍትን በመቀያየር ትምህርትን ከግዜ ወደ ግዜ ጥራቱ በማሽቆልቆል ዕነሆ ዛሬ ሞገደኛና በራሱ የማይተማመን ትውልድ ሊፈራ ችሏል። የወያኔን የትምህርት ፖሊሲ በተለያየ ጊዜ ያገባኛል የሚሉ መምህራን፤ተማሪዎችና ወላጆች የትምህርት ፖሊሲዎ ያለበትን ችግርና ያመጣዎን ኣሉታዎ ተግባር በተደገፈ መረጃ ቢያቀርቡም ወያኔ በማንኣለብኝነት ጥያቄዎን ለኣነሱ ሀገር ወዳድ ሙህራን ምላሹ ዕስራት፤ሞትና ስደት ገጥሟቸዋል።
ወያኔ ዕንደፈለገዎ በህዝብ ላይ ዕንዲፈነጭ ሲያደርጉት የነበሩ ምራባዊያን፤ኣሜሪካና ኣለም ባንክ ዛሬ ግን ችግሩ ኣፍጥጦ ወደ ራሳቸው ሲመጣ የችግሩን ኣሳሳቢነት በጥናትና ምርምር በተደገፈ ሰነድ በማስረዳትና ከሌሎች ኣገሮች ጋር በማወዳደር የኢትዮጰያ ትምህርት ፖሊሲ ከፍተኛ ችግር ያለበት መሆኑን በማጉላትና በዚሁ ከቀጠለ ሀገሪቱን ኣደጋ ላይ እንደሚጥላት እየገለጹ በኣስቸኳይ የሁሉም ክፍሎች የትምህርት ካሪኩለም መከለስና መለወጥ እንዳለበት ኣለም ባንክ ኣስጠነቀቀ።
ከዚህ በመቀጠል የሁለተኛ ደረጃ የትምህርት ፖሊሲ መለወጥን ኣስመልክቶ ኣለም ባንክ ያወጣውን ሪፖርት በማየትና የራሴን በስራ ዘመን በቆየሁባቸው ጊዜ የታዘብኋቸውን ኣንኳር ጉዳዮች ኣጭር ባጭሩ ለመዳሰስ እሞክራለሁ።
ኣለም ባንክ በዲሲ7፡2012 እ ኣ ሂልተን ሆቴል በሰጡት መግለጯ ኣንኴር ነገሮቸን ኣንስተዋል እነዚህ ኣንኳር ጉዳዮች መረጃን ድጋፍ ባደረገ በ221 ገጽና በ9 ምዕራፎች በተከፈለ የችግሩን ኣሳሳቢነት በማጉላት መንግስት በኣስቸኳይ ርዕምት እንዲወስድ ኣስጠንቅቋል። እኔም የችግሩ ኣካል የሆነዉን በመለየትና ዓለም ባንክ በጥናታቸዉ ያቀረቡትንና  የራሴን ትዝብት በመጨመር ከዚህ በታች እንደሚከተለዉ ኣቀርባለሁ።
1. በክፍል ዉስጥ ያለዉን የተማሪ መጠን በተመለከተ በኢትዮጵያ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ዉስጥ ባንኩ በጥናቱ የኣገኘዉ በኣማካኝ 64 ተማረዎች ይበል እንጂ በኣንዳንድ ት/ቤቶች 100ና ከዚያ በላይ እንደሚገኙ የኣደባባይ ሚስጥር ነዉ።በኣንድ ወቅት ወደ ኣዋሳ ኣካባቢ ት/ቤቶችን ለመጐብኝት ዕድሉን ኣግኝቼ ነበርና የኣንድ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት  የተማሪዎችን ቁጥር በክፍል ዉስጥ ምን ያህል እንደሆነ ርዕሰ መምህሩን ስጠይቀዉ ከ100 እሰከ 120ይደርሳሉ ኣለኝና ለመሆኑ ፈተና እንዴት ትሰጣላችሁ ብዩ ስጠይቀው ወረቀት እናባዛና ለእያንዳንዱ ተማሪ በመስጠት ዉጭ ሰርተው ይመጣሉ ሲለኝ እጅግ ተገርሜ ይህ ነው እንግዲህ ወያኔ ትምህርትን በጥሪትና በፍታዎነት እሰጣለሁ የተዛባ ሪፖሪት ለህዝብና ለኣለም ዓቀፍ ድርጅቶች ሲቦተልክ የቅየዉ፡ይህን የገዘፈ የተማሪ ቁጥር ዓለም ባንክ በጥናቱ ያረጋገጠና ችግሩም በኣስቸኳይ እርምት እንዲዎስድ ባንኩ ኣስጠንቅቋል።
2. የተማሪዎችን የዕድሜ መጠን ማነስ በተመለከተ፤
ወያኔ በራሱ ፍላጎት ተማሪዎችን፤መምህራንና የተማሪ ወላጆችን ሳያማክር እኔ ኣውቀዋለሁ በማላት ከ6፡2፡4 ወደ8፡2፡2 እና 3ዓመት ዪኒበርስቲ ቆይታ ግዜ በ1984ዓ ም የት/ ፖሊሲ ቀርፃል፤በዚህ የት/ፖሊሲ ምሁራን፤ ተማሪዎችና ወላጃች በተለያየ ጊዜ የፖሊሲዎን ችግር ሲያነሱ ቢቅይም ወያኔ የተለያየ ስም በመስጠት ለእስራትና ለስደት ዳርጔቸዋል።የመጀመሪያ/ ኣንኳር ችግር ብሎ ዓለም ባንክ በጥናቱ የዓረጋገጠዉ 10ኛ ክፍልን በ15ዓመት መጨረስና ወደ ቴክኒክ ሙያ ሲሄዱ የ1 ዓመት፤ የ2 ዓመትና የ3 ዓመት ስልጠና ወስደዉ ወደስራ ሲሰማሩ በዓለም ዓቀፍ ከተቀመጠዉ የእድሜ ክልል ማለትም ከ18 ዓመት በታች ስለሚሆኑ ይህ የት/ ፖሊሲ ችግር እንደለበት ዓለም ባንክ  ያሰምርበታል።
3. በክፍል ውስጥ ያላቸው የተማሪዎች ተሳትፎ ኣናሳ መሆን፤
ከላይ ለምግለጽ እንደሞከርሁት ተማሪዎች ያልተቀበሉትና ያልተሳተፉበት የት/ ፖሊሲ በመሆኑ በክፍል ዉስጥ ያላቸዉ ተሳትፎ ኣሉታዎ መሆኑ በግልጽ ተማሪዎች በሚያመጧቸዉ ዉጤቶች መገንዘብ እንደሟቻል የ10ኛ ክፍል ፈተና ላይ 20% ብቻ ማለፋቸዉ በት/ ፓሊሲዎ  ላይ ከፍተኛ ችግር መኖሩን ያመላክታል።
4. የመጽሐፍ ጥምርታን በተመለከተ፤
  • መጽሓፍት ወቅቱንና ግዚዎን ጠብቅ ኣለመስጠት በተማሪዎች ዉጤት የመጣዉ ኣሉታዊ ድርጊት ይገልጻል።
  • ጭራሽ መጽሓፍት ሳይታደሉ የት/ ዘመኑ መገባደዱና ማለቁ የተማሪዎችን ውጤት ማሽቅልቅል ምክንያት ሆኗል።
  • የመጽሓፍት ዕደላ በጋራ መሆን ተማሪዎች የቤት ስራቸዉን ሳይሰሩ በመምጣት በክፍል ውስጥ ትምህ               ርቱ ለመከታተል ሲያዳግታቸዉ ይታያል።
5.  ቤተሙከራ ኣለመኖሩ በተማሪዎች ዉጤት ላይ ከፍተኛ ተጽኖ ኣምጥቷል፤
  • የቤተሙከሪዎ ህንጻው ሳይኖር ት/ቤት መክፈት
  • በቤተ ሙከራ ዉስጥ ምንም ኬሚካልና ኣፓራተስ ኣለመኖሩ
  • መምህራን በቤተሙከራ ያላቸው ብቃት ማነስ
  • የቤተ ሙከራ ክፍለ ጊዜ ኣለመኖር
  • ቤተ ሙከራ ክፍሎች ቢኖሩም ከተማሪዎች ቁጥር ጋር የተመጣጠነ አለመሆኑ
ከዚህ በላይ የተገለጹት ችግሮች በሳይንስ ውጤት ላይ አሉታዊ ተጽኖ አምጥቷል።
6.  ቤተ መጽሃፈት አለመሟለት አንዱ የትምህርቱን ጥራት ውድቀት ነው
ይኽውም፤
  • ማጣቀሻ መጸሃፍት በግባቡ አለመገኘት
  • የቤተ መጸሃፍት ህንጻ ሳይኖር ት/ቤቶችን መክፈት
  • በሙያው የሰለጠነ ባለሙያ አለመኖር
7. የመማሪያ ክፍሎች ምቹ አለመሆን የትምህርቱን ውድቀት ሊያጎላው ችሏል
እነሱም፤
  • ት/ቤቶች ሲገነቡ የአካባቢውን የአየር ጸባይ ያገናዘበ ያለመሆን
  • የተማሪዎች መቀመጫ ያለመሟላት
  • በክፍል ውስጥ የተለያዩ ግብዓት ያለመሟላት
8. የትምህርት ማበልጸጊያ አለመኖር እና በሙያው ብቁ የሆነ መምህር አለመመደቡ የትምህርቱን ጥራት ሊያጎድለው ችሏል።
9. የካሪኩለሙ መክበድና ወደ ቀለም ትምህርት ማዘንበሉ ና የየክፍሉ ትምህርቶች ክህሎትን የሚያጎለብቱ አለመሆናቸው።
10. በየክፍሉ ባሉመጸሃፍትላይ ድግግሞሽ፤ ተከታታይነት የሌላቸው ይዘቶች መቀመጣቸው ና መጸሃፍት ሲዘጋጁ ሙያተኛን አለማሳተፍ
11. ደረጃዎን የጠበቀ ካሪኩለም ኣለመዘጋጀት በተማሪዎች፤በመምህራንና በወላጆች ላይ ኣሉታዎ ኣመላካከት ኣምጥቷል።ለምሳሌ ያህል የኣለም ባንክ በጥናቱ የጠቀሰዉ በእንግሊዝ ኣገር የሒሳብ ትምህርት ያለዉን ይዘት 3ኛ ክፍል ሲጀምሩት ኢትዮጵያ ይኽንኑ የትምህርት ይዘት 1ኛ ክፍል ይጀምራሉ ይላል ይህ ዓነቱ የትምህርት ፓሊሲ ደረጃዎን ያልጠበቀና የተማሪዎችን ኣቅም ያለገናዘበ በማለት ሲጠቅስ ወደፊትም መንግስት ሊያስብበት እንደሚገባ ያስጠነቅቃል::
12. የመምህራን የትምህርት ዝግጅት መብዛት መምህራን ትምህርቱን ከማንበብ ፈንታ ብዙን  ግዜ የሚያሳልፍት የትምህርት ዝግጅት ሲያወጡ  ነዉ።
13. ከኣቅም በላይ የመምህራን ክ/ግዜ መብዛት በተለይ በገጠር ኣካባቢ የሚያስተምሩ መምህራን በቀን ከ6እስከ 7 ፔሬድ በማስተማር የተጠመዱ መሆናቸው
14. የፆታ ክፍተት
  • ኣብዛኛውን85% የሆነው ህዝብ በገጠሪቱ ኢትዮጵያ እንደሟኖር ይታወቃል ከዚህ 85% ውስጥ ወደ ት/ቤት የሚመጡት ሴት እህቶቻችን ቁጥር ኣናሳ መሆን የፆታ ኢፍታውነቱን ኣጉልቶታል።
15. የመንግስትፓለቲካዊ  ጫና በትምህርቱ ላይ የፈጠረው ኣሉታዊ
  • ት/ሚ የሰጠውን የትምህርት ጊዜ ሰለዳ በመንግስት ፖለቲከኛች በመዳጥ ለፖለቲካዊ ስብሰባ ቅድሚያ በመስጠት ት/ ቤቶችን በተለያየ ጊዚ ሲዘጉ ይታያሉ፡ ይህ ክፍተት መምህራን ትምህርቱን በወቅቱ እንዳይጨርሱ ስለሚያደርጋቸው በመማር ማስተማሩ ላይ ኣሉታዊ ውጤት ኣምጥቷል።
16. የመምህራን ጥቅማጥቅም ኣለመከበር በትምህርቱ ጥራት ላይ ውድቀት ኣስከትሏል
  • ትምህርት የኣንድ ሐገር የእደገት ቁልፍ መሳሪያ መሆኑ እየታወቀ ወያኔ የራሱን ዕድሜ ማራዘሚያ የሆኑትን ሴክተሮች መርጦ ደሞዝ በመጨመር የትምህርቱን ዕድገት ቆልፎ ይዞታል።
  • ደሞዝ ከሌሎች ኣቻ የትምህርት ዝግጅት ጋር እኩል ኣለማግኝት
  • የትምህርት እድል ብሔርን ፤ ጐሳን ማእከል ማድረጉ
  • በገጠር ኣካባቢ ለሚገኙ መምህራን የመኖሪያ ቤት ባለመመቻቸቱ በተለይ ሴት መምህር እህቶቻችን በተለያየ ጊዜ ለወሲብ ጥቃት ሲጋለጡ ይታያሉ።
17. ተማሪዎችን ለፈተና ብቻ ማዘጋጀት /paper based test/ የትምህርት ፖሊሲው ተማሪዎች አካባቢያቸውን ወይም ሂወታቸውን ሊለውጥ በሚችል መልክ ባለመዘጋጀቱ ተማሪዎች ተስፋሲቆርጡና የትምህርት ጥቅም ጎልቶ አለመውጣቱ ይታያል። የአለም ባንክምየትምህርት ፖሊስዊ አካባቢያቸውን በሚያገናዝብ/ሂይዎታችውን/ ሊለውጥ በሚችልና ምርምር በሚያመጣ መንገድ እንዲዘስጋጅ አስጠንቅቌል።
18.  መ ምህራን ለሙያቸው ተነሳሽነት አለማሳየት
  • መንግስት በሙያቸው ጣልቃ መግባት
  • መምህራን ለትምህርት ፖሊሲው እውቅና አለመስጠት
  • መንግስት የመምህራንን ሙያ ከሌሎች ሙያ አውርዶ ስላስቀመጠው
19. የህብረተሰብ ተሳትፎ አለመኖር
  • መንግስት ለራሱ የመረጠውን የትምህርት ፖሊሲ እደፋሽን በፈለገው ጊዜ በመቀያየር ና በመጫን የህብረተሰብ ተሳትፎ በሚፈለገው መጠን እንዳያድግ ገድቦታል።
20. የበጀት አመዳደብ ችግር
  • ፍትሃዊነት የጎደለው በጀት ማስቀመጥ
  • በጀት ሳይመድቡ ት/ቤቶችን መክፈት
  • በጀትን በተማሪ ቁጥር ሳይሆን በጎሳና በብሔር መመደብ
በነዚህና በሌሎችም ባልተጠቀሱ ምክናያቶች ኢትዮጲያ በአለምላይ ትምህርትን ጥቅም ላይ ያላዋለች አገር አድርጓታል። ስለዚህ ከላይ የተጠቀሱትን  ችግሮች መነሻ በማድረግ መወያሰድ ያለባችው እርምጃዏች ብሎ አለምባንክ ያስቀመጠውንና የራሴን አስተያየት እንደሚከተለው አስቀምጣለሁ።
  • አዲስ የመጸሃፍት ዝግጅት በሁሉም የትምህርት ክፍሎች አካባቢያችውን በሚያገናዝብና ለሂይዎታችው ለውጥ በሚያመጣ መልኩ መዘጋጀት አለበት።
  • ካሪኩለሙ በኣዲስ መልክ መከለስን መስተካከል ካልተደረገ ከዝቅተኛ  ወደ መካከለኛ ገቢ ወዳላት አገር በ2024/2025 መግባት እጅግ ያስቸግራታል/አለምባንክ/
  • የመምህራንን ሙያዊ ብቃት በተለያዪ ስልጠና ማጎልበት
  • የትምህርት ቤት ርዕሰ መምህራን ምደባ በፖለቲካዊ መስፈርት ሳይሆን ሙያዊ ብቃትን ያማከለ መሆን አለበት
  • ቅድመ በጀትና እቅድ በአግባቡ ተዘጋጅቶ ት/ቤቶች መተዳደር አለባችው
  • ተማሪዎች አካባቢያቸውን ያገናዘበና የፈጠራ ክህሎታቸውን የሚያጎለብት የትምህርት ፖሊሲ መዘጋጀት አለበት /አለም ባንክ/
  • አላማ ያለው ካሪኩለም ማለትም ምን እሰራለሁ፤ ምን እሆናለሁ ብለው ተማሪዎች ራሳችውን የሚጠይቁበት ካሪኩለም መዘጋጀት አለበት/አለም ባንክ/
  • የት/ፖሊሲው ICT/information communication technology/ የሚያሳድግ መሆን አለበት/አለምባንክ/
  • የት/ፖሲው ፍትሃዊነትን መአከል ያደረገ መሆን አለበት
  • የመምህራን የስራክብር/professional recognition/ መስጠትና በሙያቸው ጣልቃ አለመግባት
  • የመምህራንን ጥቅማጥቅም ደሞዝ ደረጃ እድገት ህክምና ቤት ነጻ የትምህርትእድል በፍትሃዊነትመዳረስ አለበት
እነዚህንና ሌሎችንም ያልተጠቀሱትን ምክነያቶች በመመርመር ትምህርትን ከወደቀበት ማንሳት ካልተቻለ መንግስትበ2024/2025 ከዝቅተኛ ወደ መካከለኛ እገባለሁ ብሎ ያለመው ህልም ቅዠት ይሆናል።
የትምህርትን ጥራት እንጠብቅ!

መንግስት ከመንበሩ ወርዶ ፊቱ ላይ ጭምብል በማጥለቅ ውድ ዋጋ ያላቸውንም ሞባይልና የወርቅ ጌጣጌጥ የመሳሰሉ ንብረቶችንም እንደሚዘርፉ ተሰምቷል


ምፃችን ይሰማ
ምሽት ላይ ሙስሊሞች በቤታቸው መቀመጥ አልቻሉም
የፍርድ ቤት ማዘዣና ምክንያት የሌላቸው የሌሊት ፍተሻዎች በአዲስ አበባ
ከሁለት ቀናት በፊት አዲስ አበባ ላይ መተግበር የጀመረውና ከዚህ ቀደም በተለይም በደቡብ ወሎ በስፋት ተግባራዊ ሲደረግ የነበረው የሙስሊም መኖሪያ ቤቶችን ድንገት በመውረር የሚካሄድ ፍተሻ ተጠናክሮ መቀጠሉ ተሰማ፡፡ ባለፉት ሁለት ሌሊቶች የተካሄደው ድንገተኛ የቤት ውስጥ ፍተሻ ኮልፌ ቀራንዮ፣ ጉለሌ፣ እና ልደታ ክፍለ ከተሞችን ያጠቃለለ ሲሆን ዛሬ ደግሞ እርምጃው ወደ የካ እና ቦሌ ክፍለ ከተሞች ሰፍቷል፡፡ ትላንት በኮልፌ ቀራንዮ ከፍተኛ የሙስሊም ቁጥር አለበት በሚባለው ቤተል እና አካባቢው በተለየ መልኩ የበርካታ ሙስሊሞችን ቤቶች ለፍተሻ እና ዘረፋ ተጋልጧል፡፡ የቤት ውስጥ ፍተሻ ሕገ መንግስቱ እንዳስቀመጠው የፍ/ቤት ማዘዣ ሊኖረው እንደሚገባ ቢታወቅም ፍተሻው ያለ ምንም ማስጠንቀቂያ እና የፍርድ ቤት ማዘዣ እየተካሄደ ይገኛል፡፡
ፈታሽ የሚባሉት የፌዴራል ፖሊስ አባላት በአካባቢው በሚገኙ ካድሬዎች አማካኝነት የሙስሊም ቤት በመጠቆም በቁጥር በርክተው አንድ ቤት ውስጥ የሚገቡ ሲሆን፤ ፖሊሶቹ ባልተለመደ መልኩም ፊታቸው ላይ ጭምብል እንነደሚያደርጉ ተነግሯል፡፡ ፖሊሶች ኢስላማዊ የሚባሉ መጻህፍትን በፍተሸው ወቅት እንደሚሰበስብ የታወቀ ቢሆንም ውድ ዋጋ ያላቸውንም ሞባይልና የወርቅ ጌጣጌጥ የመሳሰሉ ንብረቶችንም እንደሚዘርፉ ተሰምቷል፡፡ ይህ ተግባር ከዚህ ቀደም በብዙ ክልሎች በተለይም በአወሊያ፣ በደሴና በአንዋር መስጊድ ግርግር ወቅት በስፋት መስተዋሉ የሚታወስ ነው፡፡ ብዙ ሙስሊሞችም ንብረታቸውን በጸጥታ ሀይሎች ተዘርፈዋል፡፡
የፍተሸው እና የዚሁ አዲስ ዘመቻ አላማ ከወዲሁ የታወቀ ሲሆን በዋነኝነትም በከፍተኛ ጥንካሬ ተቃውሞውን እያካሄደ ያለውን ሙስሊም ኅብረተሰብ ለማስደንበር እና ስጋት ውስጥም ለመክተት የታለመ ነው፡፡ ምንም እንኳ ካለፉት 12 ወራት ወዲህ ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች የፖሊሶች እና የደህንነት አካላት ያልተቋረጠ ድብዳበ እስርና መሰል ፍተሻዎች እና እንግልቶች ሰላባ ሆነን መቆየታችን እሙን ቢሆንም፤ የሚፈጸምብንን ሁሉ ኢ-ሰብአዊ ድርጊትና ማስፈራሪያዎች ወደ ጎን ገሸሽ አድርገን በተቃውሞአችን መቀጠላችን መንግስትን የበለጠ እልህ ውስጥ እየከተተው ተስፋ ቆርጧልም ብለን እንድናስብ የሚያደርጉ ተግባራት ላይ ተሰማርቷል፡፡
መንግስት አሁን ባለው ሁኔታ የትኞቹንም የህገ መንግስትና የሰብአዊ መብት ድንጋጌዎች ያለ ሀፍረት በአደባባይ እየጣሰ የተስፋ መቁረጡን ከፍታ እያሳየንም ይገኛል፡፡ መንግስት ከሀገር ውስጥና ከውጪው አለም ከፍተኛ ትችትና ነቀፌታ የተቀበለበት ጅሀዳዊ ሀረካት ፊልምና፤ ፊልሙን በማሰራጨት ከተላለፋቸው የሕገ መንግስቱ ድንጋጌዎችና የፍርድ ቤት ትዕዛዝ በተጨማሪም ፊልሙ ያስገኝልኛል ብሎ የገመተው ውጤት ሙሉ በሙሉ መና ቀርቶ በተቃራኒው ሕዝቡን ለከፍተኛ ተቃውሞ ማነሳሳቱ፤ መንግስትን መሰል የተሰፋ መቁረጥ መገለጫ እርምጃዎች ውስጥ ከተውታል፡፡ ዛሬም መንግስት ጥያቄዎቻችንን ይመልስ፤ መሪዎቻችንንም ይፍታ የሚለው መልእክታችን አለ፡፡ ይህ ካልሆነ ትግላችን በአዲስ መንፈስና ምዕራፍ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አስረግጠን እንገልጻለን፡፡
አላሁ አክበር!

ይች ሀገር የት ናት!!!!!

ውሸት ተደማጭነት ካገኘ 21 ዓመታት አስቆጥሮ ሕዝብን ያሰለቸ ከመሆኑ ባሻገር ወያነን እርቃኑን እንዳወጣ ገና አልተረዱም ምክንያቱም ውሸታቸው የተራመደውን ያህል እንድተበላ ጎማ መላላጡንና አሻራም እንድሌለው አይናቸውን ጭምር ደፍኖት አይምሮአቸውን አሻግቶት ሕሊናቢስነታቸውና ሰውነታቸውን እንደዘነጉ መንገዱም መጨረሻቸው ለመሆኑ ከእለታዊ ምግባራቸው እያስመሰከሩ ነው፡
ነገርግን አንድ የሚያሳስብና የሚያስጨንቅ ራሴንና ሌላውንም ወገኔ ምን እያሰብ መሆኑን ለመረዳት እያቃተኝ ነው ኢትዮጵያውያን የሙስሊም እምነት ተከታይ ወንድሞቻችን፡ የመብት ጥያቄ የእምነት ጥያቄ የኛም ክርስቲያኖች ጥያቄ በመሆኑ የትግሉ አጋሮች በመሆን በውህደት የኛንም ታሪካዊና ጥንታዊ ኦርቶዶክስን የማዳን ኃላፊነት አለብን ታድያ ምን ለመጠበቅ ነው በፍራቻና በጥርጣሬ ከዳር በመቆም የወያነን የማስፈራርያ ውሸት በመመራት የተነሱበትን ድምፃችን ይሰማ ጥያቄ የታሰሩት መፍትሄ አፈላላጊ ሽማግሌዎች በሕብረት በመቆም ይህ ጥያቄ መልስ እንዲያገን ለማድረግ ሌሎቹንም ጥያቄዎች እንዲመለሱልን የፍርሃት ብልኮአችንን አውልቀን እንደወንድሞቻችን በትባትና በቆራጥነት ወያነን ይበቃል በማለት መነሳት ይኖርብናል፡ ላለፉው አንድ ዓመት በመታሰር በሞሞት በመሰደድ የጠፋው ሁሉ የእስልምናን እምነት ብቻ ያዘለ ሳይሆን መብታችን እምነታችን ይጠበቅ በመሆኑ የሁላችን አድርገን መነሳት ተገቢ ነው፡
ጎርፉ ተሯሯጠ ጊዘውነው መሰለኝ
ሕዝቡ ነቃ ድምጹን አሰማ መገዛት መረረኝ
ጥላቻ ብቀላ በጥቂት ሆዳሞች
አብቃለት ውሸት የበረከት ድርሶች
የጎሳ ባንዲራ የጽንፈኞች መዝሙር
ብቀላ አድርባይ የነበረው አጥር
ፈረሰ በሕዝቦች ሰላምን በሚጥር
ተጋለጠ ሴራ ግድያ መፈክር
ከላይ ከእርካኑ የዘቀጠ በውሸት
አሸባሪ ሆኖ በራሱላይ ሁከት
ልማት በሌለበት በዘራፊዎች ሰአት
ከሸፈ በንቃት የወያኔ ምታት
አስርበው ጨቁነው ለመግዛት
ሕዝብን በማጋጨት ፈረዳአቅቸው ውድቀት
ሕጋቸው አይጸና ተለዋጭ በለት
ሹመኛው አድርባይ የሌለው ብቃት
ውሸት ውሸት ከመሆን ያለማለፉ እየታየ በመሆኑ፤ሊያደርጉ የማችሉትን በጥቂት ከማን እንደተወለዱና እናት ይሁን አባት የማያውቁ ወንድምና እህት ፍቅር ምነን እንደሆነ የማይገባቸው ለፍጥረት ዴንታ የሌላቸው ጥቂት የወያኔ የአጋዚ አንጋቾች በጭካኔ ያለርህራሄ የሚያደርጉት ተግባር ሳንብረከረክ በትባት እጅ ለእጅ ተያይዘን እናምክናቸው ጣልያን የተሸነፈው በመሳራ እጦት ሳይሆን በቆራጥነት ሃገራዊ ራኢ የሌለው በመሆኑ እኛ ግን አጋዚን የምንዋጋው በሀገር ፍቅርና በሃይማኖት ጽናት በመቆም ስለሆነ የድሉ ባለቤቶች ነን።
ድል ለመላው የመብት ተከራካሪዎች ለ እውነትና ለሃገር ለወግን የቆሙ በሙሉ
ውድቀት ለሆድ አደሮችና ከፋፋዮች
ኢትዮጵያ በነጻነቷ ለዘላለም ትኑር

በእነ አቶ በረከት/በኢህአዴግ ያኮረፉ ባለሥልጣናት ወደ ጎራው መቀላቀላቸውን ቀጥለዋል


junedinsado(ከተበዳይ ኮሚኒኬተሮች የተጻፈ ዜና) በኢህአዴግ ከአሸባሪዎች ጎራ ሊቀላቀል ሴራ እየተሸረበላቸው ያለውና በዚህም በእጅጉ ያኮረፉት የቀድሞው የሲቪል ሰርቪስ ሚኒስቴር
 ሚኒስትር አቶ ጁነዲን ሳዶ የተበዳይ ኮሙኒኬተሮችንና ያኮረፉ ባለሥልጣናትን ጎራ ለመቀላቀል ያቀረቡት ጥያቄ በጥምረቱ ጥምር ኮሚቴ ውድቅ ተደረገ፡፡ ባለፈው ሳምንት የተበዳይ ኮሚዩኬተሮችና ያኮረፉ ባለስልታናት ጥምረት ኮሚቴ ለአቶ ጁነዲን ምስጢራዊ ሰነዶችንና ዶክመንቶችን እንዲሁም የሚያውቁትን የኢህአዴግ ምስጢር ሁሉ በምስልም ሆነ በድምጽ እነዲሰጧቸው ጥያቄ አቅርቦላቸው ነበር፡፡ አቶ ጁነዲንም በምስጢር በተወካዮቻቸው በኩል የተበዳይ ኮሙዩኬተሮችንና ያኮረፉ ባለስልታናትን ጎራ መቀላቀል ትግሉንም መምራት እንደሚፈልጉ፣ ስለጠየቁት ምስጢራዊ መረጃም ያላቸውንና የሚያውቁትን በሙሉ እንደሚሰጧቸው አረጋግጠዋል፡፡
አቶ ጁነዲን እንዳሉትም በተለይ በአሁኑ ሰዓት ኢህአዴግ ሊያስራቸው እየተንቀሳቀሰ በመሆኑ ወህኒ ከመውረዳቸው በፊት በእጃቸው ያለውንና የሚያውቁትን ምስጢራዊ መረጃ ሁሉ ለተበዳይ ኮሚኒኬተሮችና ላኮረፉ ባለስልጣናት ጥምረት በአስቸኳይ አሳልፈው መስጠት እንደሚፈልጉ ገልጸውላቸዋል፡፡ በአንድ ሳምንት ጊዜ ውስጥም መረጃውን ሊያስረክቡአቸው እንደሚችሉም ቃል ገብተዋል፡፡ ወደ ተበዳይ ኮሚኒኬተሮች ጎራ ተቀላቀሉም አልተቀላቀሉም መረጃውን ለማስረከብ ጊዜ መውሰድ እንደማይፈልጉም ተናግረዋል፡፡ (በነገራችን ላይ በኢህአዴግ ያኮረፉ ባለስልጣናት በአግር ውስጥም በውጭም የሚገኙ ሲሆን አብዛኞቹም ኢህአዴግነት የተሰናበቱ ናቸው፡፡ ከዛው ሆነው ከውስጥ የሚታገሉም አሉ፡፡)
ሆኖም ግን የተበዳይ ኮሚዩኬተሮችና ያኮረፉ ባለስልታናት ጥምረት ኮሚቴ የአቶ ጁነዲንን የመቀላቀል ጥያቄ አልተቀበለውም፡፡ ምክንያቱ ደግሞ የአቶ ጁነዲን ጉዳይ ከአሸባሪነት ጋር ስለሚያያዝና ይሄኛው ትግል ግን ዛሬ ለጥንቃቄ ሲባል ምስጢራዊ ቢሆንም ነገ በሰላማዊ መንገድ በአገር ውስጥ መታገል  የሚፈልግ ከመሆኑ ጋር የተያያዘ ነው ተብሏል፡፡ እናም የአቶ ጁነዲንን ወደ ጎራው የልቀላቀል ጥያቄ ለጊዜው አንቀበልም በለዋል፡፡ ይህ  የተበዳይ ኮሚዩኬተሮችና ያኮረፉ ባለስልታናት ጥምረት  በቂና አስተማማኝ መረጃ ካገኘ በሁዋላ በተለያዩ መንገዶች ለህዝቡ በስሙ በተዘጋጀ ዌብሳይትና በሌሎች የሚዲያ ዘዴዎች በመጠቀም የሚያሰራጭ ይሆናል፡፡
ይህ በእነዲህ እያለ አቶ ጁነዲን ሳዶ በሰሞኑ የአርሂቡ መጽሔት ላይ በተነበበው መሰረት በተለይ የሚታሰሩ ከሆነ ምስጢር እንደሚያወጡ ኢህአዴግን አስጠንቅቀዋል፡፡ እንደ አርሂቡ መጽሄት ዘገባ ከሆነ አቶ ጁነዲን ማነኛውንም መንግስታዊ/ኢህአዴግአዊ  ምስጢር ለማውጣት ማንንም እንደማይፈሩ ገልጸዋል፡፡ በተለይም እርሳቸውን ለማሰር የሚደረገው እንቅስቃሴ ካለልቆመና በሰላም ለመኖር የማይችሉ ከሆነ ምስጢር ለመማውጣት ወደሁዋላ እንደማይሉ ነው የተነናገሩት፡፡ አለኝ የሚሉትን ምስጢራዊ መረጃም ለየተበዳይ ኮሚዩኬተሮችና ያኮረፉ ባለስልታናት ጥምረት ኮሚቴ አሳልፈው እንደሰጡ የሚያሳይ ዘገባ ነው አርሂቡ ያስነበበን፡፡
በሌላም መልኩ ባለፈው ቅዳሜ ለንባብ የበቃችው ቆንጆ መጽሔት አቶ ሬድዋንና አቶ በረከት ለኢህአዴግ የማታለልና የማስመሰል ጉዞ እንደማሳያ በሚል ርእስ ባስነበበችው መሰረት አቶ በረከት ኮሙኒኬተሮቻቸውን በከፍተኛ የደሞዝ ልዩነትና በልዩ ልዩ ጥቅማጥቅሞች ከፋፍለው እንደሚያስተዳድሩና በዚህም በየፌደራል መስሪያ ቤቱ የሚገኙ ኮሙኒኬተች የተለዬ ቡድን መስርተው እይተንቀሳቀሱ እንደሆነ፣ የተለያዩ ምስጢራዊ መረጃዎችንም ሊለቁ በዝግጅት ላይ እንደሆኑ የሚያሳይ ዘገባ ተዘግቧል፡፡ አቶ በረከትም ከመንግስት የተሰጣቸውን የምንግስት ኮሚኒኬተሮችን የማሰልጠንና የማብቃት ሚና እየተወጡ እንዳልሆነና ምንግስትንም/ኢህአዴግንም እያታለሉ እንደሆነ ተገልጾአል፡፡
አቶ በረከት ለኮሙዩኒኬተሮቻቸው የሚያሳዩት ንቀትና የማታለል መንገድ አሁንም እንደቀጠለ ነው፡፡ በዝምታቸው ቀጥለዋል፡፡ የተለመደው ሥልጠናው ነገ፣ በሚቀጥለው ሳምንት፣ ወዘተ ይሰጣል የሚለው የእነ አቶ በረከትማስመሰያና ማባበያቸውም ቀጥሎአል፡፡ የተበዳይ ኮሙዩኒኬተሮች ዝም ማለት ግን የእነ አቶ በረከትንና የድርጅታቸውን ገመና የበለጠ ለመሰብሰብና መረጃን በበቂ ሁኔታ ለማጠናከር እነደሆነ ከኮሚቴው ውስጥ ያሉ ሰዎች ገልጸውልናል፡፡ እንዲያውም የእነ አቶ በረከት ንቀትና ማስመሰል እንዲሁም እንደህጻን መደለል እጅግ እንዳበሳጫቸውና ለበለጠ ክፋት እንዳነሳሳቸው አስረድተዋል፡፡ ጉዳዩንም በበሳል አመራር ለመምራት እየሰሩ መሆኑን አስረድተዋል፡፡ ምንም ድምጽ ሳያሰሙና ሳያስነቁ ባልታሰበና ባልተጠበቀ መልኩ አደጋ ለመጣል ነው እንቅስቃሴአቸው፡፡ ምንም አያመጡም በማለት በንቀት ለሚመለከቷቸው አቶ በረከትም ምንም አለማምጣታችንን እናሳያለን ብለዋል፡፡ ውስጣቸውም ለከፍተኛ በቀል እንደተነሳሳና ከምንም በላይ አቶ በረከትና ጽ/ቤታቸው ላሳዩአቸው ንቀትና ማታለል መበሳጨታቸውን ገልጸው በምሬት ነግረውናል አስተባባሪዎቹ፡፡
ሁሉም ተበዳይ ኮሙኒኬተር ብቻ ሳይሆን በኢህአዴግ የመከፋፈልና የአድሎ አመራር የተማረረ ዜጋ ጎራቸውን እንዲቀላቀል አሳስበዋል፡፡ የባለስልጣናትና ከፍተኛ አመራሮች ቁጥርም እየቸመረ መሆኑንና የአመራር ቦታውንም እያጠናከሩ መሆኑን ገልጸውልናል፡፡ በተለይ ኮሙኒኬተሮች ለዚህ ትግል እንዲታጠቁ፣ መረቡንም እስከ ወረዳ ድረስ እንዲዘረጉ አሳስበዋል፡፡ ወደ ጎራው ለመቀላቀልም ከፈለጉ አስተባባሪዎች አድራሻቸውን በሚስጢር እያሳውቁ እንደሆነ ገልጸዋል፡፡ ለማነኛውም ለሚያደርጉት ትግል ፈንድ እያገኙና የበጀት ችግርም እንደማይገጥማቸው ገልጸዋል፡፡ እናም አሁን የእነ አቶ በረከትን ሥልጠናም ሆነ ጥቅማጥቅም እንደማይጠብቁና በራሳቸው መንገድ ግን የእነርሱን ብቻ ሳይሆን የአገሪቱን ምስኪን ዜጎች መብት ለማስጠበቅ እንደሚታገሉ ገልጸዋል፡፡ ቀጣይ እርምጃቸው መቼና ምን እንደሚሆን ግን ከመግለጽ ተቆጥበዋል፡፡ ይህም ሚስጢር ነው ብለዋል፡፡
የእኛንም አስተያየት እንጨምር፡፡ ይህ የኮሙኒኬተሮች ጉዳይ እነ አቶ በረከትን ብቻ የሚመለከት አይመስለንም፡፡ ኢህአዴግም ቆም ብሎ ቢያስብበት መልካም ነው፡፡ ሠራተኛን መናቅና መከፋፈል ሁሌ መጨረሻው ያው መከፋፈልና ጥፋት ነው፡፡ መከፋፈሉ የሚጎዳው እነ አቶ በረከትን ሳይሆን አገርን ሊሆነ እንዳይችል መጠንቀቅ ያስፈልጋል፡፡ መረጃዎችም የብሄርና የሃይማኖት ግጭት የሚያስከትሉ እንዳይሆኑ መጠንቀቅ ያስፈልጋል፡፡ የኢህአዴግ አመራርም ለምን ዝም እንደሚል ግልጽ አይደለም፡፡ ይህ ተራ ነገር ነው ብሎ ብቻ መቀመጥ ሳይሆን ሠራተኛን በአግባቡ መያዝ ሳይሻል አይቀርም፡፡ ለማነኛውም መረጃው የገር ጥፋት የማያስከትላና ኢህአዴግን ብቻ የሚጎዳ ቢሆን መልካም ነው፡፡ አቶ በረከትን ለመበቀል ሲባል አገር እንዳይበትን ጥንቃቄ……..

Feb 16, 2013

Teddy Afro to receive peace award



On February 15, 2013 the highly-acclaimed and legendary Ethiopian Musician, Teddy Afro will accept an Commendation Award from the City of San Jose on behalf of the Ethiopian and Eritrean Friendship forum EEFF. Theaward acknowledges EEFF’s dedication to peace and reconciliation.
On this distinguished occasion, artist Teddy Afro will be honored for his role in promoting peace and reconciliation. The award ceremony will take place on Friday, February 15, 2013 from 5:00-6:00pm at 2500 Masonic Center in San Jose.
This great singer came out with a new album in 2012. He named his album “Tikur Sew”. This album praises the work of the great king of Ethiopia, Atse Menilik. Like his past albums, this “Tikur Sew” album contains numerous messages. The number of cassettes and CD’s sold is a record in Ethiopian history.
The Ethiopian & Eritrean Friendship Forum (EEFF) strives to create an empowering environment for ordinary Eritreans and Ethiopians where honest people-to-people dialog, based on trust and mutual respect, can take place with the aim of healing past wounds and building bridges for a brighter future in the region.
About Teddy Afro:
Teddy Afro or Tewodros Kassahun was born on 14 July 1976 to parents of artistic talents and fame. While his mother, Tilaye Arage, was well known in Ethiopia for her professional dancing in her younger days, his late father, Kassahun Germamo, was a renowned and highly-regarded Ethiopian songwriter. From South Africa to North America, the Middle East and Australia, he criss-crossed the world to entertain and convey messages of peace, love, hope and unity in a language almost anyone can understand. For more information about Teddy Afro, visit: http://teddyafro.info/
Teddy Afro will perform live in the Bay Area on February 16 at the Indian Community Center , 525 Los Coches St, Milpitas, Ca 95935. For more information contact:             408-701-8538      

ባለራዕይ ወጣቶች ማህበር በመንግስት የደረሰበትን አፈና አጋለጠ – ፍኖተ ነፃነት ጋዜጣ


ባለራዕይ ወጣቶች ማህበር ጠቅላላ ጉባዔ እንዳናደርግ ስብሰባ እንዳንሰበስብና ቋሚ አመራሮችን እንዳንመረጥ ተደርገናል ሲሉ የካቲት 4 ቀን 2005 ዓ.ም በሰማያዊ ፓርቲ አዳራሽ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ አስታወቀ፡፡
ማህበሩ እንዳስታወቀው በሰሜን ሆቴል፣ በፓኖራማ ሆቴል፣ በኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር ማሰልጠኛ ተቋም አዳራሾች ጉባኤ ለማካሄድ በደብዳቤ ጠይቀን ስምምነት ላይ ከደረስን በኋላ የማህበሩን ጠቅላላ ጉባዔ እንዳናደርግ ተደርገናል ሲሉ የተስማሙበትን ማስረጃ አያይዘው አቅርበዋል፡፡
ethiopian-envየማህበሩ አመራሮች ጨምረውም በአባሎቻችን ወጣቶች ላይ የአካል ጥቃት በማድረስና የሀሰት ክስ በመመስረት የገዥው ፓርቲ ኢህአዴግ አባላትና የደህንነት አባላት ነን የሚሉ ግለሰቦች እንቅፋት እየፈጠሩብን ነው ሲሉ አስታውቀዋል፡፡ በተለ
ይም የማህበሩ አመራር አባል  የሆነችውን ወጣት ወይንሸትስለሺን ታህሳስ 30 ቀን 2005 ዓ.ም በማህበሩ  ቢሮ አካባቢ ሳለች መርፌ በመውጋትና አፍኖ በመውሰድ ለአንድ ሌሊት በኤሌክትሪክ ሾክድ በማድረግና በብረት በመምታት ካሰቃዩአት በኋላ መንገድ ዳር ጥለዋት ሄደው ጉዳዩ በፖሊስ እየተጣራ እንደሆነም ገልፀዋል፡፡ የወጣት ወይንሸት ጉዳት በህክምና ማስረጃ የተረጋገጠ ሲሆን ያሰቃዩበትም ምክንያት የማህበሩ አመቻች ኮሚቴ ዋና ሊቀመንበር የሆነው ወጣት ሀብታሙ አያሌው ከአሸባሪ ድርጅቶችና ግለሰቦች ጋር ይገናኛል ብለሽ እመኚ በሚል እንደሆነ በመግለጫው ተጠቁሟል፡፡
የባለራዕይ ወጣቶች ማህበር አያይዞም ማህበራችን ነፃ ማህበር ነው፣ ነገር ግን አዳራሾችን ገንዘብ ከፍለን እንኳ እንዳንሰበሰብ በመደረጉና የተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲዎች ስለተባበሩን ለመጠቀም ተገደናል እንጂ የማንም የፖለቲካ ድርጅትን ወግኖ እንደማይሰራ ገልፀዋል፡፡ በግል መገናኛ ብዙኋን በተለይም ፍትህ ጋዜጣ፣ ፍኖተ ነፃነት ጋዜጣና አዲስ ታይምስ መፅሔት ከህትመት እንዲቋረጡ መደረጉ በህገ-መንግስቱ አንቀፅ 29 ላይ የተቀመጠውን ዜጎች መረጃ የማግኘት መብታቸውን የሚጋፋ በመሆኑ እንደሚቃወም ገልጧል፡፡
ሌላው ወጣቶች በሀገራቸው የኢኮኖሚና ማህበራዊ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ማህበሩ እየሰራ ቢሆንም የባለራዕይ አባላት ብቻ ተለቅመው የሥራ እድሉ እየተነፈጋቸው ነው፡፡ ለዚህም የኢትዮጵያ ኤርፖቶች ድርጅት የጉልበት ስራ የሚሰሩ ወጣቶች ማክቤል በተባለ ኤጀንሲ ተመልምለውና የአሻራ ምርመራ አድርገው ውጤታቸውን ያስገቡ ቢሆንም የማህበሩ አባላት ብቻ ተለይተው የሥራ እድሉ ተጠቃሚ እንዳይሆኑ የተደረጉ ሲሆን ስራውን ያከናወነው ኤጀንሲም ከማህበሩ ጋር ግንኙነት አለው በሚል እድሉን መነጠቁን አስታውቋል፡፡ ከማክቤል የተነጠቀው እድልም መሊፎ (ማህበር፣ሊግ፣ፎረም) የተባለ ድርጅት በማቋቋም በኢህአዴግ ወጣቶች ሊግ በኩል  ብቻ ምልመላው እንዲካሄድ ተደርጓል፤ ይህም  በዜጎች መካከል ልዩነትና አድሎአዊነትን በመፍጠር ህገ-መንግስቱን የጣሰ በመሆኑ ማህበሩ አጥብቆ እንደሚያወግዝ ገልጧል፡፡
በመጨረሻም በመጪው ሚያዚያ 2005 ዓ.ም ለሚደረገው ምርጫ የህዝብ ታዛቢ ለመሆን ከ3 ወራት በፊት እንደማንኛውም የሲቪክ ማህበር በደብዳቤ ጥያቄ ቢያቀርብም እስካሁን መልስ እንዳልተሰጠው፤ ነገር ግን በኢቲቪ ለሲቪክ ማህበራት ምርጫውን እንዲታዘቡ ፍቃድ እንደሰጠ አድርጎ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ መግለፁ የቦዱን ነፃ አለመሆን የሚገልፁ አካላትን ትክክለኛነት የሚያሳይ እንደሆነ አስታውቋል፡፡
በመግለጫው ወቅትም በአዲስ አበባ የሚገኙ የ‹‹ባለራዕይ ወጣቶች ማህበር›› የሁሉም ክፍለ ከተሞች ከፍተኛ አመራሮች የተገኙ ሲሆን ከጋዜጠኞች ለቀረበላቸው ጥያቄም ምላሽ በመስጠት  ማህበሩ ኢትዮጵያዊ አንድነትን መገንባት ዋነኛ አላማው በማድረግ የወጣቶችን ተጠቃሚነት ማረጋገጥ መሆኑን አረጋግጠዋል፡