May 20, 2013

አቶ ገብረዋሃድ ማነው….የማይገፋ ቋጥኝ..! ስሮቹ በርካቶች..!



96e5c789d9b8bf3a9e86699e2b445aec_M
ገብሬ የጉምሩክ መንፈስ ነው፣የገቢዎች ቆሌ!!፣የደረቅ ወደብ ጂኒ፣ የገቢዎች ሾተል! የገበረዋህድ አይን በክፉ ያየችው አራሙቻ ነው! ተነቅሎ ይጣላል! ገብሬ የተከለውን ህዝቦች አይነቀንቁትም! የገብረዋህድ ቃል አይታጠፍም! ከሊቅ እስከ ደቂቅ የቃሉ አዳሪዎች ናቸው! ግን ምን ዋጋ አለው! በርካቶችን ቃሊቲ ያከተመች ወንበር ገብሬንም ቀላቅላዋለች፡፡ አቶ ገብረዋህድ በኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን የህግ-ማስከበር ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ነበር፡፡ ሰውዮው በባለስልጣን መ/ቤቱ የማይገፋ ቋጥኝ ነበር! ስሮቹ በርካቶች ናቸው! የዛሬን አያድርገውና አርጋጁ ብዙ ነበር! ከእነዚህ አርጋጆቹ መካከል ጥሩነህ በርታ፣አታክልቲ፣ተወልደ፣ተኽላይ… እያሉ በርካቶችን ይጠቅሣሉ የውስጥ ምንጮች፡፡ ግን አታክልቲ እዚያ ቤት ምን ይሆን ሥራው? አታክልቲ ለበርታ አመታት የባለስልጣን መ/ቤቱ የዘርፍ መዋቅር ውስጥ አይታወቅም ይሉቁንም በባለስልጣን መ/ቤቱ የኢህአዴግ አደረጃጀት ተጠሪ በመሆኑ ብቻ ከ7000 ብር በላይ እየተከፈለው የሚኖር ቅልብ ነው። እንዲያውም አንድ ወዳጄ እንደ ነገረኝ አትክልት ከዩኒቨርሲቲ ቀጥታ ባለስልጣን መስሪያ ቤቱን የሚቀላቀሉ እንስቶችን በጥሩ ቦታ ላይ እመድብሻለሁ ከረሜላ በርካታ እንስቶችን ጉድ የሠራ ጉደኛ ነው ብሎኛል፡፡ አንገቱን የውሻ ማሰሪያ በሚያክል የወርቅ ዘለበት አጊጦ ሁሌ ተፍ ተፍ ነው አሉ የአታክልቲ ነገር! ግን ለምን እስከ አሁን እንዳልታሠረ ግራ ገብቶናል ይላል ወዳጄ!
አቶ ገብረዋህድ ላይ መንግስት እርምጃ መውሰዱ ለባለስልጣን መ/ቤቱ ሠራተኞች ብቻ ሣይሆን የሰውየውን ቁልፍነት ለሚያውቁ ሁሉ ግርምትን ፈጥሯል፡፡ሠውየው በተለይም ከ2000 ዓ.ል ወዲህ ለበርካታ አዳዲስ ባለሀብቶችና ለአያሌ አዲስ ከሣሪ ነጋዴዎች መፈጠር ትልቁን ሚና ተጫውቷላ! ኢህአዴግ ለሚያከብራቸውና ለሚያደኸያቸው ነጋዴዎች አፈፃፀም ትልቅ አስተዋፅኦ ነበረውና! አየለ ደበላ፣ገብረኪዳን ሞሮኮ፣አቶ ከበደ፣አቶ ሌንጮ… ለእነዚህ ሁሉ በአራጣ መጥረቢያ ለወደቁት ዛፎች ሁሉ ቆራጭ መጥረቢያው ገብሬ ነበርና! ለዘመን አመጣሽ የትግራይ ባለሀብቶችም እድገትና እብሪት ዋናው ክንድ ገብረዋህድ ነው ይላሉ ባለስልጣን መ/ቤቱን በሀገሪቱ ኢኮኖሚ ላይ ያለውን ከፍተኛ የመበየን አቅም የተረዱ ሰዎች፡፡
ጊዜን የሚገለባብጥ የሆነው አላህ ፈቃድ ሆነና ዛሬ ገብሬ ቀን ዞሮበታል! እልፎችን በስኒ ቡና ቫት የማገደበትን ዘብጢያ ይጎበኝ ዘንድ ግድ ሆኗል፡፡ በስኒ ቡና ታሳሪዎች እንጅ በመልቲ ሚሊዮን አጭበርባሪ ነጋዴዎች ላይ የማይጨክነው ገብሬ በባለስልጣን መ/ቤቱ መለስን መስሎ፣መለስን ተከንድቶ፣አዜብን ክንድ አድርጎ የኖረ ይሉታል! የውስጥ ምንጮች፡፡ ገብረዋህድ ወቅት ያተበተው አምባገነን ነበር አሉ! በአንዳንድ መድረኮች ተናገራቸው ከተባሉት እና ከውስጥ ምንጮች የሠማሁትን እንሆ፡
በአንድ ወቅት የኮሚቴዎቻችን መታሠር ተከትሎ ባለስልጣን መ/ቤቱም እንደ ቀበሌዎቻችን ሁሉ በሃይማኖት አክራሪነት ዙሪያ ባደረገው ስብሰባ ላይ ገብሬ የመድረክ መሪ ሆኖ ያችን የመለስን አምባገነናዊ አዲስ ራዕይ በአምባገነን አንደበቱ እያደረቀና እያከረረ ሲያቀርብ የባለስልጣን መ/ቤቱ ሠራተኞች በተለይም ሙስሊሙ ክፉኛ ሞገቱት አሉ! እናማ ገብሬ “ለብዙሐኑ መብት ሲባል ትጨፈለቃችሁ!!” ሲል በማን አለብኝነት ጠረንጴዛውን እየደበደበ ይናገራል በዚህ ጊዜ አንጀታቸው የቆሠለው ሙስሊም ሠራተኞች አላህ ይጨፍልቅህ ሣይሉ አይቀርም መቼም ይሄው ኮሚቴው የተጨፈለቀበትን የስቃይ ማዕከል እሱም እንዲጨፈለቅበት ሆኗል፡፡
በሌላኛው ተመሣሣይ መድረክ ነው ደግሞ አሉ ሠራተኞቹ አንድ መቐሌ ዩኒቨርሲቲ የተማረ ሙስሊም ወንድማችን በመቐሌ ዩኒቨርሲቲ በሚማርበት ወቅት አንድ መምህሩ ክፍል ውሥጥ “እኔ እንዴት ማስተማር እችላለሁ እነ አህመድ፣እነ መሬማ፣እነ ሙሐመድ፣እነ ሠዓዳ እየበለጧችሁ እነሱ እየሰቀሏችሁ እንዴት ማስተማር እችላለሁ!!” ብሎ ልጁ በሚማርበት ክፍል መናገሩ “ከአንድ የዩኒቨርሲቲ መምህር የማይጠበቅ መሆኑንና ይህ አይነቱ የዘቀጠ አስተሳሰብ ሙስሊም ተማሪዎች በዩኒቨርሲቲዎች ውሥጥ ለሚደርስባቸው መገለል እና ትንኮሳ ማሳያ ነው ይህ የእኔ መምህር እኔ ባለሁበት ክፍል የተናገረው ነው” ብሎ ገብረዋህድን ይጠይቃል፡፡ገብረዋህድ ንግግሩ ጭቃ ነው! ሲናገር ዘር ካልጎተተ አይሆንለትም ይላሉ ሠራተኞቹ። እናማ ገብረዋህድ ምን ብሎ መለሰለት መሠላችሁ “ይህ አባባል ምናልባት ትግሬ ወደ መቀሌ አማራ ወደ ቀበሌ ከሚሉት እንዱ ትመስለኛለህ!!” ብሎ ወንድማችንን የሚያሸማቅቅ መልስ መለሰለት አሉኝ!! መቐለ ዩኒቨርስቲን ስለጠቀሰ ብቻ ይህን መልስ ምናመጣው ጎበዝ?
ጎበዝ!ብቻ ብዙ ነው የዚያ ቤት ጉድ አሉ እናማ መላኩና ገበረዋህድ አይንናናጫ ናቸው አሉ! መላኩ የበላይ ቢሆንም ዙፋኑ ግን የገብሬ ነው፡፡ ገቢዎች ሄደህ ገብረዋህድ ማነው ብትል “የመለስ ሾተል!” ይሉኃል፡፡ አለፍ ብለህ ከጠየቀክም “የአዜብ ማሣላጫ!” ይልሃል አንዱ የገቢዎች ተገፊ! አልበቃህ ብሎ ጥያቄ ከጨመርክም “ ገብረዋህድ እኮ ጋዜጦች የማያውቁት የመለስ እጅ ነው!” ይሉኃል አየህ ወያኔዎች አራሙቻቸውን የሚነቅሉት በገብረዋህድ ጸረ-አራሙቻ ኬሚካል ነው! ወንበራቸውን የሚተክሉትም፣ኤፈርትም ሆነ ሌሎች ዘመን አመጣሽ ዘውግን መሠረት ያደረጉ ባለሐብቶች የሚደልቡትም ሆነ እኔና እንተን በቀኝ አዙር የሚገዙን በገብረዋህድ ይሁንታ ነው! እንዴት? ብለህ ከጠቅክ ቀሽም ነህ! የኢትዮጵያ ኢኮኖሚና የባለሐበቶቿ ሎተሪ የሚቆረጠው በገብረዋህድ ቢሮ ነው እያልኩህ ነው! ታዲያ አሉ ሰውየው የሟቹ መንፈስና የባለቤታቸው ትልቅ ድጋፍ ነበራቸው አሉ! እንዴት? ብለህ ከጠየቅክ የመላኩንና የገብሬን አለመግባባት የሚያውቁ ውስጥ አዋቂዎች “መላኩ በአዋጅ ምክትሎቹን የመመልመልና በጠ/ሚኒስቴሩ የማስሾም ስልጣን ቢኖረውም እዚያ ቤት የሚሾሙ ምክትሎች ግን በግብሬና በአዜብ ይሁንታ ነው ይሉኃል፡፡”
ታዲያ ሰሞኑን የፀረ-ሙስናው አሊ ሡለይማንም ሆኑ የሙት መንፈስ አምላኪ ተብለው የተናቁት የአሁኑ ጠ/ሚኒስቴሩ በዚህች ኦፕሬሽን ጥርስ ማብቀል መጀመራቸውንና በተለይ በገብሬና በኔትወርኮቹ ላይ የተወሰደውን እርምጃ በማድነቅ ብዙዎች “ይበል!” የሚያስብል እርምጃ ብለውታል! ግና ምን ዋጋ አለው! ሁሉን ነገር ከሟቹ ሰውዮ ጋር ካላጣቡ የማይሆንላቸው ኢህኤደጎች ኦፕሬሽኑን አከሸፉት እንጅ! አየህ ይህ ኦፕሬሽን በአንድ ወገን የአሁኑን ጠ/ሚኒስቴር ዝና ከፍ የሚያደርግ ሲሆን በሌላ ወገን ደግሞ “አባይን የደፈረ ጀግና!” ብለው የስዘመሩለት መለስ ገብረዋህድን መድፈር አቅቶት ነበር የሚል ትርጉም ይሰጣል! አለፍ ብሎም ገብረዋህድ ከቤቱ ካርታ ብዛት የተነሣ በአጥሚት ካርታውን ቢያቀጣጥሉት አንድ አንስተኛ ጎጆ ይሠራ ነበር እኮ! የተባለለትን ህገ-ወጥ ሐብት ሲሰበስብ የሟቹ ጠ/ሚኒስቴር አብሺር ባይነት ነበር! የሚል የውሥጥ መረጃ ይወጣል! ታዲያ ሟቹ ጠ/ሚኒስቴር የኢትዮጵያችን መስራችና አባት ተደርጎ ሌጋሲ ምና ምን በሚባልበት ዘመን እንዲሁም እንደ እመቤቴ ማርያም ምስል በየካድሬ ቤቱ ማዕዘን ላይ ተሰቅሎ፣ በዘመንኛ ባለሐብቶች ቢሮ ጠረንጴዛ ላይ የመለስ ፎቶ በትልቁ ምስል ተቀምጦ ከርቤና እጣን በሚጨስለት ዘመን ይህች ጉድ ከወጣች ምን ሊፈጠር እንደሚችል የተገነዘቡት ወያኔዎችና አጋሮቻቸው በአሊ ሠሉይማን አንደበት ያስተላለፏት መልዕክት በልሳናቸው ሪፓርተር ጋዜጣ “የሰሞኑ የፀረ-ሙስና ጥናት በቀድሞው ጠ/ሚኒስቴር ትዕዛዝ” ነው ተብሎ እንዲዘገብ ተደረገ! ይች እንግድህ አንድም የአሁኑን ሰውዮ ስም መቃናት ለመመቅኘት ሁለትም የአቤቶ መለስን ተመላኪነት ላለማጉደፍ ሲባል መሆኑ ነው!
ገብሬ በኢተቪ አፍ በክፉ ከመግባቱ ሁለት ሣምንት ቀደም ብሎ መለስ ፃፋት ያላትን “የተሀድሶው መሥመርና የኢትዮጵያ ህዳሴ” የተሰኘች መፅሀፍ መሠረት አድርጎ የቪዲዮ ኮንፈረንስ ለባለስልጣኑ ሠራተኞች ሲያሰለጥን እኛ እንደ ደርግ “እምቢ ላለ ሰው ጥይት አጉርሰው!” እያልን አንገዛም ሲል ነበር አሉ። አሁንስ ምን ይል ይሆን? እንጃ! የመለስ መሞትን ተከትሎ የባለስልጣኑን አዳዲስ ሰራተኞች ሲያሰለጥን “በዚህ ሠዓት በዚህ ደቂቃ የመለስ ልጆች ሜዳ ላይ ናቸው! የአንድ ጠ/ሚኒስቴር ልጆች አንዲት ቤት እንኳን ሣይኖራቸው!” እያለ መድረኩን በ ሣቅ እንባ አራጭቶት ነበር አሉ! እሲኪ አሁን ከዚያ ሁሉ የቤት ካርታ አንዱን ቢሠጣቸው ምናለበት! ኧረ እንዲያው ቢያከራያቸው እንኳን! ያሳዝናል! በአህለ ሡና ወልጀማዓው ፕሬዝዳንት ትእዛዝ ፊርደውስ ውሥጥ ያለው መሌ! ይህን ስግብግብነት ቢሰማ በእውኑ ምን ይል ይሆን? እንደ ታምራት ላይኔ “ስኳር የጣለው ተጋዳላይ” ይለን ይሆን ወይስ “የመንግስት ሌቦች!!” እያለ አትስረቁ እያለ ያስዛርፈን፣ያሰዘርፈን ይሆን?………. ***ገብሬ የመለስ ሾተል! ግን እውነት ነው!!*** አጅሬ ገብረዋህድ ሳይሆን ገብረ ዜናዊ ነበር!

No comments:

Post a Comment