Jun 18, 2013

የአባይ ጉዳይ የዛፍ ላይ እንቅልፍ የሆነባት ግብጽ እና ለስልጣን ጸብ ጫሪው ህውሃት!

ማክሰኞ ሰኔ 11 ቀን 2005 ዓ.ም. (Tuesday, June 18, 2013)

የአባይ ጉዳይ ለግብጽ የዛፍ ላይ እንቅልፍ ነው። ዛፍ ላይ ሆነህ እንቅልፍ ይወስድሃል? ሸለብ እንኳን ያደርግሻል ዛፍ ላይ ሆነሽ? እነደዚያ ነው የአባይ ጉዳይ ለግብጽ። ይኽ እንቅልፍ ማጣት እና ስጋት ዛሬ የጀመረ አይደለም። ባጭሩ ልተርክ። ሪቻርድ ፓንክረስት በግብጽ የተገኙ መረጃዎችን መሰረት በማድረግ ክርስቶስ ከመወለዱ ከ3 ሺ አመቶች በፊት ጀመሮ የግብጽ ነጋዴዎች በእግራቸው የአባይን ወንዝ ዳርቻ ተከትለው እንዲሁም በቀይ ባህር በነፋስ በሚገፉ ጀልባዎች ዛሬ ኢትዮጵያ (ያኔ የፐንት ግዛት) በሚባለው ግዛት ውስጥ ከሚኖረው ህዝብ ጋር የንግድ ልውውጥ ማድረጋቸውን እና ግዛቱን ምድረ ታ-ኔትጄሩ (Land Ta-Netjeru) ማለትም “ምድረ አማልዕክት” እንደሚሉት እና “የመጀመሪያ አገራችን ነው” ይሉም እንደነበር የኢትዮጵያውያን ድንበር-መሬቶች (The Ethiopian Borderlands) በሚለው መጽሐፉ ዘርዘር አድርጎ ጽፏል። የቅርቡን ብንመለከት ደግሞ በተለይ ከ1813 ዓ. ም. ጀመሮ ግብጽ የኢትዮጵያ ባለቤትነቷን በጦርነት ለማረጋገጥ የዮሐንስን ኢትዮጵያ ከሱዳን ቀላቅላ ለመግዛት በአራት አቅጣጫዎች ወረራዎች ከፍታ ሳይሳካለት ወደ መጣችበት መመለሷን ተክለ ጻዲቅ መኩሪያ “ዐፄ ዮሐንስ እና የኢትዮጵያ አንድነት በሚለው መጽሐፉ በሰፊው ተርኳል። በኃይለስላሴ እና በደርግ ዘመንም ለኢትዮጵያ ተቃዋሚዎች የጦር መሳሪያ እና ስልጠና በማቀነባበር፣ ገንዘብ በመለገስ፣ በመካከለኛው ምስራቅ አረብ አገሮችን በማስተባበር፣ የአማርኛ ስርጭት ሬዲዮ በመክፈት ድጋፍ ማድረጓን እናውቃለን። ህውሃት ከተጠቃሚዎቹ ተቃዋሚዎች ውስጥ አንዱ ነው። በአባይ ጉዳይ ከጥንት ጀምሮ ግብጽ ከስጋት ነፃ የሆነ እንቅልፍ የለታም። ዛሬም ሆነ ወደፊት ግብጽ የሰላሙን መንገድ ትታ የጸበኛነቱን መንገድ ከመረጠች እንቅልፍ አይኖራትም። ይኽን የግብጽ ጭነቀት እና ስጋት ህውሃት ጠንቅቆ ያውቃል። ስለዚህ ግንቦት 20 ቀን ጸብ ጫረ። ላብራራ።
የጥናቱን ውጤት ተቀበለችውም አልተቀበለችው ስለ አባይ ጉዳይ በጥናት ላይ የተሰማራው ኤክስፐርቶች ቡድን ሪፖርት እየጠበቀች ሳለች ድንገት ግንቦት 20 ቀን 2005 ዓ. ም. ህውሃት የአባይ ወንዝ የፍሰት አቅጣጫ መቀየሩን ሰበር ዜና ተሰራጨ። የኢትዮጵያ ሽብርተኛው ኢ.ት.ቭ. አስተጋባ። ዜናው ግብጽ ደረሰ። ከጥንት ጀምሮ የአባይ ጉዳይ የዛፍ ላይ እንቅልፍ የሆነባት ግብጽ ተደናገጠች። አምባገነኑ ሞርሲ ከገበባት የውስጥ ችግር ለማምለጥ የህውሃትን ቁስቆሳ ተጠቀመ። አካራሪ የግብጽ ተቃዋሚ ፖለቲከኞችን ጋበዞ ‘እኔ ሳልሞት ግብጽ አትጠማም’ አለ። ያጀቡት አክራሪዎችም ‘ግፋ’፣ ‘በርታ’፣ ‘አይዞህ ከጎንህ ነን’ አሉት። ይኽ ምክክራቸው ዜና ሆኖ አደባባይ ወጣ። ህውሃት ሁካታውን ያልጫረ መስሎ ለኢትዮጵያ ህዝብ ግብጽ ልትወጋህ ነው የሚል ፕሮፖጋንዳ ጀመረ። የቀድሞ አባቶቻችን ድሎች ሳይቀሩ እየተጠቀሱ የቀረርቶ ድምጽ በአዲስ አበባ እየጎላ መጣ። አልባራዳይን የመሰሉት የግብጽ ዴሞክራሲ ኃይሎች የግብጽን መንግስት ወቀሱ። የኢትዮጵያ ዴሞክራሲ ኃይሎችም ቀረርቶው ገደብ ይበጅለት አሉ። የኢትዮ-ግብጽ የጦርነት ሁካታ አነሳሱ ይኽን ይመስል ነበር። ህውሃት የማያስፈልግ ጸብ ጭሯል።
ለመሆኑ ለምን የአባይ ወንዝ አቅጣጫ ግንቦት 20 ቀን ተቀየረ? ዜናውስ ለምን ግንቦት 20 ቀን አደባባይ ወጣ? ለዚኽ ጥያቄ አቶ በረከት ስሞዖን ሰኔ 7 ቀን ግድም 2005 የሰጠውን መግለጫ እንመልከት፥ የአባይ ወንዝ አቅጣጫ ግንቦት 20 ቀን የተቀየረው በአጋጣሚ እንጂ ህውሃት ሰልጣን ከጨበጠበት ቀን ጋር እንዲገጣጠም ሆን ተብሎ የተደረገ እንዳልሆነ ሊያስተባብል ሞክሯል። ይኽ የበረከት ስሞዖን ማስተባበያ በሽብርተኛው ኢ.ቲ.ቭ. እና በኢሳት ተዘግቧል። የአቶ በረከትን መቀላመድ ወደ ጎን አድርገን እውነቱን ሃቁን እንመልከት። የአባይ ወንዝ ፍሳሽ አቅጣጫ ግንቦት 20 ቀን እንዲቀየር ያስደረገው ህውሃት ነው። ዜናው ግብጽ እንዲደርስ ያደረገውም ህውሃት ነው። ግቡም ስልጣን ነው። ላብራራ! (1ኛ) የተለየ አሳቢ እና ከድኽነት ነፃ አውጪህ እኔ ህውሃት ነኝ የሚል መልዕክት ለኢትዮጵያ ህዝብ ለማስተላለፍ እንዲችል ሆን ብሎ የአባይ ፍሳሽ የተቀየረበትን ቀን ስልጣን ከጨበጠበት ግንቦት 20 ቀን ጋር አገጣጠመው። የዚኽ እርምጃ ፖለቲካዊ ግብ ህዝቡ እንዲያመልክበት እና ስልጣኑ እንዲጠናከር ነው። ግድብ መገንባት አይደለም ግቡ። በተጨማሪ (2ኛ) የአባይ ጉዳይ የዛፍ ላይ እንቅልፍ ለሆነባት ግብጽ የአባይ ፍሳሽ አቅጣጫ መቀየር ዜና የጦርነት ፖለቲካ ውስጥ እንደሚያስገባት ጠንቅቆ ስለሚያውቅ በምላሹ የኢትዮጵያን ህዝብ በአገር ወዳድነት ስሜት አሳውሮ በሚፈልገው የፖለቲካ አቅጣጫ ለማስጓዝ አስልቶ ነበር። የዚኽም ፖለቲካ ስሌት ግቡ የኢትዮጵያን ዴሞክራሲ ኃይሎች ለመምታት እና ስልጣኑን ለማጠናከር ነበር። በአገር ከሃዲነት እና በሽብርተኛነት ሽፋን። ይሁን እንጂ የኢትዮጵያ ዴሞክራሲ ኃይሎች ፈጥነው ስላጋለጡት የኢትዮጵያን ህዝብ በአባይ ስሜት አሳውሮ የዴሞክራሲ ኃይሉን ለመምታት የሚያስችለው ጊዜ ሳያገኝ ቀረ። ከሸፈበት።
ህውሃት ከግድቡ ይልቅ ስልጣኑ እንደሚበልጥበት ለአንዲት ደቂቃ እንኳን መዘንጋት አያስፈልግም። ወደፊትም ሌሎች ጸቦች ሊጭር እና ከዚያ ግብጽ ልትወጋን ነው ይልሃል። የዴሞክራሲ ኃይሎች የነፃነት ሰላማዊ ትግላቸውን አጠናክረው በመቀጠል እራሳቸውን ከህውሃት ማጭበርበር እና ጥቃት መጠበቅ አለባቸው።

የቢሮ ኃላፊው በሙስና ላይ ምስክር ሳይሆኑ ተገደሉ


June 17, 2013
Allegations of Corruption Emerge Against Federal Government Examiners
በነበራቸው የስራ ሃላፊነት በድብቅ መረጃ ሲያሰባስቡ ቆይተው ለመንግስት ካጋለጡ በኋላ ራሳቸውን ደብቀው የነበሩት አቶ ተስፋዬ ኢሬሣ ምሳ እየተመገቡ ህይወታቸው ማለፉ ተሰማ። አቶ ተስፋዬ ሰኞ ለጸረ ሙስና ኮሚሽን የምስክርነት ቃላቸውን ለመስጠት ከኮሚሽነር አሊ ሱሌማን ጋር ቀጠሮ ይዘው ነበር።
Former Gambella Regional President, Mr. Omot Obang Olom
በቅርቡ ወደ ፌደራል መንግስት የተዛወሩት የጋምቤላ የቀድሞ ፕሬዚዳንት የነበሩት አቶ ኡሞት ኦባንግ፣ ከ83 ሚሊዮን ብር በላይ አላግባብ ለግል ጥቅማቸው ማዋላቸውን፣ እንዲሁም በክልሉ የሚፈጸሙትን የተጭበረበሩ የበጀት አፈጻጸሞችንና ምዝበራዎችን የሚያጋልጡ ሰነዶችን በሚስጥር በማደራጀት ለኢህአዴግ ያቀረቡት አቶ ተስፋዬ አሟሟታቸው አነጋጋሪ ሆኗል።
አቶ ተስፋዬ ኢሬሳ ከፍተኛ ምስጢር ያላቸውን ሰነዶች በመያዝ ከመታሰራቸው በፊት መሰወራቸውን፤ “የቢሮ ሃላፊው ይዘው የተሰወሩት መረጃ አቶ ኦሞት የፈረሙባቸው ከፍተኛ የገንዘብ ሰነዶችና ሙስና የተከናወነባቸው የኮንስትራክሽንና የተለያዩ መረጃዎች ናቸው። መረጃዎቹ አንድ ቀን ህዝብ ፍርዱን ይሰጥ ዘንድ ይፋ ይሆናሉ” በሚል ጎልጉል ምንጮቹን ጠቅሶ በ (ጥቅምት 19፤2005/October 29, 2012) መዘገቡ ይታወሳል
ቀደም ሲል የጋምቤላ የፋይናንስ ቢሮ ሃላፊ የነበሩት አቶ ተስፋዬ ከላይ የተጠቀሰውን የሙስና ወንጀል በማጋለጣቸው ጋምቤላ መኖር ሳይችሉ ቀርተው ራሳቸውን ሸሽገው ለመኖር ተገደው እንደነበር የሚያውቋቸው ለጎልጉል አስረድተዋል።
“አቶ ተስፋዬ ሙስናን በማጋለጣቸው በፍርሃቻ ራሳቸውን ደብቀው ሊኖሩ አይገባም” በማለት ኢህአዴግ ከለላ እንደሚሰጣቸው ቃል በገባላቸው መሰረት ከተሸሸጉበት የወጡት አቶ ተስፋዬ ሰንጋተራ ትንሳዔ ሆቴል ከጋምቤላ ልጆች ጋር መገናኘት ይጀምራሉ።
ባለፈው ሳምንት ከፌዴራል የጸረ ሙስና ኮሚሽነር አሊ ሱሌማን ጋር ለመገናኘት ቀጠሮ ከያዙ በኋላ ኮሚሽነሩ በድንገት ለለቅሶ ወደ ጎንደር በመሄዳቸው ቀጠሮው ለሳምንት ይራዘማል። ለሰኞ (ሰኔ10፤2005) አዲስ ቀጠሮ ይይዛሉ።
በስልክ ያነጋገርናቸው ትንሳዔ ሆቴል አካባቢ እንደነበሩና ለጉዳዩ ቅርበት እንዳላቸው የሚገልጹ የጋምቤላ ተወላጅ የስራ ሃላፊ እንዳሉት አቶ ኦሞት ኦባንግ ለአቶ ተስፋዬ ስልክ ደውለው ነበር። አቶ ተስፋዬ ህይወታቸው ከማለፉ ሁለት ቀን በፊት የቀድሞው የጋምቤላ ክልል ፕሬዚዳንት የነበሩት አቶ ኦሞት በስልክ ተማጽንዖ አቅርበው ነበር።
አቶ ኦሞት “እውነት ነው ጸረ ሙስና ኮሚሽን ቀጠሮ የያዝከው?” በማለት ይጠይቃሉ
“አዎ! እውነት ነው” በማለት አቶ ተስፋዬ መልስ ይሰጣሉ።
አቶ ኦሞት መልሰው “እንግዲያውስ ጸረ ሙስና ኮሚሽን ከመግባትህና ከማነጋገርህ በፊት ሁለታችን መገናኘት አለብን። የምንነጋገረው ነገር አለ” የሚል ጥያቄ ያቀርባሉ። አቶ ተስፋዬ ስለ ስልክ ልውውጡ እንደነገሯቸው የተናገሩት እኚሁ ሰው፣ አቶ ኦሞት በስልክ ደጋግመው በመደወል ያቀረቡትን የ”እንነጋገር” ጥያቄ አቶ ተስፋዬ አልቀበልም ይላሉ።
ጋምቤላ ስራቸውን ለቀው ራሳቸውን ደብቀው የኖሩት በእርሳቸው ምክንያት መሆኑን፣ ፍትህ እንደሚፈልጉ፣ አሁን ለመነጋገር ጊዜው እንዳልሆነ፣ ዘርዝረው ለአቶ ኦሞት መናገራቸውን ያወሱት የጎልጉል ምንጭ፣ ጥያቄያቸው ውድቅ የተደረገባቸው አቶ ኦሞት በንዴት ተዛልፈው ነበር።
ከዚህ ሁሉ በኋላ ነው እንግዲህ አቶ ተስፋዬ ትንሳዔ ሆቴል ሰዎችን በመላላክና በመታዘዝ ከሚኖር አንድ የጋምቤላ ሰው /አቶ ተስፋዬ የሚረዱት በምግባር ጉዳይ የሚታማና ጸበኛ የሚባል ሰው ነው/ አብረው ተቀምጠው ምሳ እየበሉ ሳለ አቶ ተስፋዬ አረፋ ይደፍቃቸዋል። ወዲያው ከተቀመጡበት ተንሸራተው መሬት ይወድቃሉ። ቀጥሎም ሰውነታቸው ይዝልና ኮማ ውስጥ ይገባሉ። ከአፋቸው እየተዝለገለገ የሚወጣው ፈሳሽ በመጨመሩና የተለያየ ርዳታ ቢደረግላቸውም ሊተርፉ ስላልቻሉ ሆስፒታል ተወስደው ህይወታቸው ማለፉ ተረጋግጧል።
አቶ ተስፋዬ ሆስፒታል ከመድረሳቸው በፊት እንደሞቱ የሚናገሩት የጎልጉል ምንጭ አሟሟታቸው ከመርዝ ጋር የተያያዘ እንደሆነ ተናግረዋል። አቶ ተስፋዬ በሙስና ወንጀል ላይ ያሰባሱትን መረጃ ለተለያዩ አካላት የበተኑ ስለሆነ እሳቸውን በመግደል ማድበስበስ እንደማይቻል አስታውቀዋል። አቶ ተስፋዬ ሙስና ካጋለጡ በኋላ መሰወራቸውን መዘገባችን የሚታወስ ነው። በተያያዘ በጋምቤላ ኢንቨስትመንት ላይ ከተሰማሩ ባለሃብቶች ውስጥ ከ70በመቶ በላይ የሆኑት የህወሓት የቀድሞ ታጋዮች የነበሩና የክልል አንድ ተወላጆች መሆናቸው የአቶ ተስፋዬን አሟሟት ይበልጥ ውስብስብ እንዳደረገው አስተያየት እየተሰጠ ነው፡፡
የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ ዋና ዳይሬክተር አቶ ኦባንግ ሜቶ “የአቶ ተስፋዬ ሞት አሳዛኝና አስደንጋጭ ነው። ብዙ ሳይታወቅ የተገደሉ ተስፋዬዎች አሉ” በማለት ስለ አቶ ተስፋዬ ሞትና አሟሟት መረጃ እንደደረሳቸው አስታውቀዋል።
“አቶ ተስፋዬ ለእውነት ሲል ሞቷል። ኢህአዴግ ውስጥ በርካታ የወንጀል መረጃ ያላቸው ወገኖች አሉ። እንዲህ ያሉ ዜጎች በየትኛውም ዘመን አይረሱም። የቀን ጉዳይ ካልሆነ በስተቀር ስማቸውና ታሪካቸው ከጨዋነታቸው ጋር ተመልሶ ህያው ይሆናል። ሌቦችና ነፍሰገዳዮች ወደ ህግ ሲያመሩ፣ እንደ አቶ ተስፋዬ አይነቶቹ የመጪው ትውልድ ታላቅ ምሳሌ ሆነው እየተወደሱ ህያው ሆነው ይኖራሉ” የሚል አስተያየት የሰጡት አቶ ኦባንግ፤ አቶ ተስፋዬ ያሰባሰቧቸው የሙስናና ተመሳሳይ ወንጀሎች ማሳያ ሰነዶች እጃቸው ላይ ስላለ አቶ ተስፋዬን በመግደልና በማስገደል ወንጀል ማድበስበስ እንደማይቻል ተናግረዋል።
የአቶ ተስፋዬ የቀብር ስነስርዓት ጋምቤላ መፈጸሙን ለመረዳት ተችሏል። ቤተሰቦቻቸውን በማግኘት ሆስፒታሉ ስለ አሟሟታቸው የሰጠውን አስተያየት ጠይቀን ለመረዳት ያደረግነው ሙከራ አልተሳካልንም።

Jun 14, 2013

እነሱ ከአባቶቻቸው አይበልጡም እኛም ከአባቶቻችን አናንስም!!!

እነሱ ከአባቶቻቸው አይበልጡም እኛም ከአባቶቻችን አናንስም!!!
ከሰማያዊ ፓርቲ የተሰጠ መግለጫ
ግብፅ በኢትዮጵያ ላይ ወረራና ደባ መፈፀም የጀመረችው ኢትዮጵያ ዛሬ በአባይ ላይ ግድብ ለመስራት ከመነሳቷ እጅግ በርካታ አመታት በፊት ጀምሮ ነው፡፡ ሀገራችን ከግብፅም ሆነ ከሌሎች የተቃጣባትን ተደጋጋሚ ወረራዎች በመመከትና ጠላቶቿንም ድባቅ በመምታት ነፃነቷን ጠብቃ መኖሯ ለጠላቶቿ መራር የሆነ እውነት ነው፡፡ በተለይም ከጥንት ጀምሮ የአባይን ምንጭ ለመቆጣጠር ጥልቅ ምኞት የነበራት ግብፅ በሃገራችን ላይ የፈፀመችውን ግልፅና ድብቅ ወረራ በመመከት ተደጋጋሚ ሽንፈትን አከናንበን መልሰናታል፡፡
ሀገራችንን በጦር አውድማዎች ማሸነፍ እንደማትችል በቂ ትምህርት የወሰደችው ግብፅ ከቅርብና ሩቅ ታሪካዊ ጠላቶቻችን ጋር በማበር ዛሬ በኤርትራና በኢትዮጵያ በስልጣን ላይ የተቀመጡ አማፅያንን በማስታጠቅና ሁለንተናዊ ድጋፍ በመስጠት ኤርትራ ከኢትዮጵያ እንድትገነጠልና ኢትዮጵያም እንድትዳከም ከፍተኛ ደባ ፈፅማለች ፡፡ ግብፅ ይህን ሁሉ ግልፅ እና ስውር ደባ የምትፈፅመው ኢትዮጵያ በወንዞቿ መጠቀም የማትችል ደካማ ሐገር እንድትሆን ለማድረግ ነው፡፡ ይህ ጥረቷ ግን ደካማ ኢትዮጵያን ለመፍጠር ከመሞከሯ ውጭ የምኞቷን ያህል አልተሳካላትም፡፡ ቢሆንም እኛን ኢትዮጵውያንን እርስ በእርሳችን በማናከስ በጦርነትና በክፍፍል ተጠምደን ወንዞቻችንን የመጠቀም አቅም በማሳጣት ለዘለዓለም ብቸኛ ተጠቃሚ ሆና መኖር ትፈልጋለች፡፡ ይህ ካልተሳካላት ቀጥተኛ ወረራ በመፈፀም የወንዞቻችን ምንጮች ለመቆጣጠር እንደምትመኝ የየዘመናት ሙከራዎቿ ያረጋግጣሉ፡፡
ኢትዮጵያ በአባይ ወንዝ ላይ የጀመረችውን ግድብ አስመልክቶ ሰሞኑን ከግብፅ በኩል የሚሰማው ዛቻና ማስፈራሪያም ከላይ የተገለፁት እውነታዎች ነፀብራቅ ነው፡፡ በመሠረቱ በአባይ ወንዝ ላይ የተጀመረው ግድብ ከሐገራዊ ጠቀሜታው ይልቅ የገዥውን ፓርቲ የስልጣን እድሜ ለማራዘም የታለመና ለፕሮፓጋንዳ ፍጆታ የሚደለቅ ከበሮ መሆኑን ፓርቲያችን ይገነዘባል፡፡ የግድቡ ሥራ የገዥውን ፓርቲ የተለየ አሣቢነትና ተቆርቋሪነት የሚያሳይ አድርጎ ለማቅረብ የሚደረገው ልፈፋ ከተራ ጩኸት በዘለለ የዜጎችን ልብ የሚያማልል አይደለም፡፡ በአንፃሩ ከገዥው ፓርቲ አመለካከት ውጭ ያሉ ዜጎችን የግድቡ ሥራ የማይመለከታቸው አድርጎ ለማቅረብ የሚደረገው የወሬ ክምር ልብን የሚሰብር ርካሽ ፕሮፓጋንዳ ነው፡፡ በመሆኑም ለኢትዮጵያ ክብርና ኩራት መሠዋት ለዜጎችም ጥቅም መጠበቅ እነማን ምን እንደከፈሉና እንደሚያስቡ ለታሪክ በመተው ሃገርን መክዳትና መጥላትን በሌሎች ላይ ለመለጠፍ የሚደረገው ሩጫ ግን እንዲታሰብበት እንመክራለን፡፡
የግድቡ ሥራ ከስም አወጣጥ ጀምሮ የፕሮጀክቱ አነዳደፍ፤ የፋይናንስ አሰባሰብ፣ ግንባታውን የሚያካሂዱ ድርጅቶች አመራረጥና ሌሎችም ጉዳዮች እጅግ ግልፅነት የጎደላቸውና ባለቤትነታቸውም ከኢትዮጵያ ህዝብ ተነጥቆ ለተወሰኑ ቡድኖች በተለይም ለገዥው ፓርቲ ፍላጎት ማሳኪያ እየዋለ መሆኑ ቀርቶ ሁሉንም ኢትዮጵያውያን በሚያስማማ ሁኔታ እንዲካሄድ ፓርቲያችን አጥብቆ ይጠይቃል፡፡
ሐገራችን ለሚያስፈልጋት ዓላማ ሁሉ በወንዞቿ መጠቀሟን በመቃወም በግብፅም ሆነ በሌላ በማንኛውም አካል የሚፈፀሙ ዛቻም ሆነ ሌሎች አሉታዊ ድርጊቶችን ፓርቲያችን አጥብቆ ያወግዛል፡፡ የሃገራችንን ጥቅም ለማስጠበቅም ማንኛውንም መሰዋዕትነት መክፈልን ከጀግኖች አባቶቻችን የወረስነው አኩሪ ታሪካችን በመሆኑ ይህን ቃል ኪዳን ማክበርና መጠበቅ የፓርቲያችን የፀና አቋም ነው፡፡
በመጨረሻም አሁን የተፈጠረው ውጥረት በውይይት እንዲፈታ የኢትዮጵያ መንግስት ጠንካራ ዲፕሎማሲያዊ ጥረት እንዲያደርግ እያሳሰብን ነገር ግን ግብፅ ይህን አልቀበልም በማለት ፍላጎቷን በሃይል ለማስፈፀም የምትፈልግ ከሆነ የአባቶቻችንን ታሪካዊ አሸናፊነት የምንደግመው መሆኑን ከታሪክ እንድትማር ለማስታወስ እንገደዳለን፡፡
ሰኔ 7 ቀን 2005 ዓ.ም

ሕዝብን ለጦረነት አገርን ለጥቃት አሳልፎ ከሚስጥ ጋር መተባባር አገራዊ [ብሔራዊ] ወንጀል ነው።

የአንድ አምባ ገነን ሥራዓት ማንንት ባሕርይም ሆነ ተግባር ሊታይና ሊገመገም የሚገባው ሥራአቱ በአገሪቱና በዜጎች ላይ ከሚፈጽመው ብሔራዊ ወንጀልና ከሚያደርስው አገራዊ ጉዳት አኩያ ነው።
እንደሚታወቅው ወያኔ  ከአፈጣጠሩ ጀምሮ በካሃዲ በጸረ ኢትዮጵያውያን የመንደር ስብስቦች ጥላቻ ተረግዞ፤ በግራ ቀደም ፖለቲካ ስንኩል ትርኪምርኪ አመለካከት ተጠምቆ ወንድሞቹን ሲያርድ ሲያሳረድ የኖረ፤ የአባቶቹን የእናቶቹን የአያቶቹን የወንድሞቹን የልጆቹን የዘመዶቹን በርሃብ ማለቅ ግድ ያላለው፣ የማይለው፣ ስብዓዊነት የማይስማው፣ ለርሃብተኞች የመጣውን እርዳታ ቀምቶ ከሱዳን እስከ ሊቢያ ሲቸረችር የኖረ የኢትዮጵያን ታሪካዊ ማንነቷን ሕልውናዋን ስንደቃላማዋን የካደ፤  አገር አስገንጣይ፤  በኢትዮጵያ ጠላቶች ያደገ የተመነደገ አገርና ሕዝብን ዘርፎ የሚያዘርፍ፤  በትውልድ ኢትዮጵያዊ የሆነ ግን አጥፍቶ ጠፊ መሰሪ፤  በፋሽቱ ቪኒቶ ሞሶሎኒ የከፋፍለህ ግዛ አስተምህሮ፤  በሂትለርና በስታሊን የድርጅታዊ የፕሮፓጋንዳና ቅስቀሳ ብሂሎችን እራሱን የካነ፤ እራሱ ደንቁሮ አገርንና ሕዝብን፤ የሚያደነቁር፤ የሃገሪቱን ዋና ዋና መሠረታዊ መንግስታዊ መዋቅሮችን በቁጥጥር ስር አድረጎ በአባሪ ተባባሪዎቹ የሆድ አደር አጋሰስ አጋርነት፤ በባእድ አገር የፖለቲካና የገንዘብ ለጋሲነት እርዳታ ብድር ሰጭነት፤ አማካሪነት እየታገዘ፤ ሕዝብን ሃገርን በንቅዘት በምዝበራ አደህይቶ አገርን ለመበታተን ቆርጦ የተነሳ እኩይ ስብስብ ለመሆኑ፤ ከሆድ አደሮቹ፣ከአባሪ ተባባሪዎቹ በስተቀር ማንም ኢትዮጵያዊ በጥሞና የሚያውቀው ማስረጃዎች በዋቪነት የያዙት፤ በታሪክ መሓደር ተረቆ ያለ የማይታበል ሃቅ ነው

የተዚህ ቀደሙ ወንጀል ሳያንስ ዛሬ ደግሞ ወያኔ በቡኅ ላይ ቆረቆር ሆኖ ሕዝብን ለጦርነት፤ ሀገርን ለጥቃት ለማዘጋጀትህዳሴ ግድብ በሚለው ማታለያ፣ በአድርባይ ሆድ አደር ጠርናፊ አስጠርናፊ ስብስብ አቀንቃኝ  ሊቀመኩዋሶች ታዳሚዎች  እየታጀበ ግብጽን እየተነኮስና እየቀሰቀስ በመቀጠሉ የአባይ ውሀ አንድም ጠብታ አይቀነሰብኝም ከምትለው ከስግብግቧ ግብጽ ጋር ጦርነትንእየጋበዘን ነው።

አገራችን ኢትዮጵያና ሌሎች ሀገሮች በነጭና ጥቁር አባይ የመጠቀም መብታቸው የተጠበቀ መሆኑ አያክራክርም ።በአለም አቀፍ ህግ መሰረትም ሌሎች ከወንዞቹ ተጠቃሚ ሀገሮች ውሃ እንዳያገኙ ማድረግ የሚፈቀድ አይደለም። አባይን በተመለከተተንኮለኛው አጋብሶ አደር የእንግሊዝ ቅኝ አገዛዝ ሱዳንና ግብጽን ብቻ ይዞ የወሰነው የውሀ ድርሻ/ክፍፍል ትክክለኛ አለመሆኑምአከራራክሪ ኣይደለም-- ግብጽና ሱዳን አሌ ቢሉም። ግብጽ በረሀዋን ልታለማና ሚሊዮኖችን ልታሰፍር በመፈለግ የአባይን ውሀበተጨማሪ ደረጃ መፈለጓና የተፋሰስ ሀገሮችን ጥቅም ከቶም አላዳምጥ ማለቷም የሚደገፍ አይደለም  ወያኔ በአሁኑ ጊዜ ትልቅግድብ በሌለ ገንዘብ እሰራለሁ ብሎ የተነሳው ለኢትዮጵያ አስቦ (ወያኔና የኢትዮጵያ ጥቅም ሆድና ጀርባ ናቸውናሳይሆን የሕዝባዊአመጽ ነፋስ ወደ ሀገራችንም እንዳይነፍስ በሚል የህዝብን እይታ ለማደናገር የሸረበው ተንኮል መሆኑ ክርክርን አይጠይቅም ።በኢትዮጵያ እስከዛሬ የተሰሩት ግድቦችና ገና ያላለቀው ግልገል ጊቤ ቁጥር ሶስትንም ጨምሮ ለሀገሪቷ የመብራት ሀይል ፍጆታ ከበቂበላይ ሆነው ሳለ ዛሬም በብዙ ከተሞች መብራት በፈረቃ እየተሰጠ እንዳለ ሕዝባችን የሚያውቀው ነው። ግዙፍ ግድብ ለመገንባትመነሳትና ይህንንም ግብጽ እንደምትቃወም እየታወቀ በስልት ጉዳዩን በመያዝ ፈንታ ድንፋታና ፕሮፓጋንዳን ማስቀደሙ፤ ቦንድ ብሎሕዝብን ማስጨነቁና ማስገደዱ፤ ሀገር ወዳድ መስሎ ለመቅረብ መፍጨርጨሩ ሕዝብን ሊያደናግር የሚችል አይደለም።የለመዳባቸው የወያኔ የገደል ማሚቴዎችና አደናጋሪዎች --በባድሜ ጦርነት እንዳየነው ሁሉ-- ሀገር ልትጠቃ ነው ኡኡ በሚል ወያኔን በመታገል ፈንታ ሕዝብ እንዲደግፍና ከጎኑ እንዲሰለፍ ለማድረግ ከወዲሁ የተንኮል ቅስቀሳ፤የማደራጀት ስራና ጫጫታ ጀምረዋል።ሁሉም ሀገር ወዳድ ዜጋ ይህንን በሚገባ ተገንዝቦ ውጉዝ ከመ አርዮስ መባል አለባቸው።

የግብጽ ሕዝብ ጠላታችን አይደለም። አንዋር ሳዳት የአባይ ወንዝ ከተገደበብን ጦርነት የግድ ይሆናል ያለውንምአንረሳውም--ዛሬም የግብጽ መሪ ተመሳሳይ አቅዋም በመውሰድ እሱም በበኩሉ ልክ እንደ ወያኔ ውስጣዊ ውጥረቱን ዘወር ለማድረግይፈልጋል። ተጨባጭ ሁኔታውንና አቅምን ሳያውቁ ሳይመዝኑ ህዳሴ ግድብ ይሰራል ብለው ጫጫታ ላይ ያሉት ክፍሎች ቅዠት ላይናቸው 
ከግብጽ ጋር ጦርነት ቢነሳ ይህ የኢትዮጵያ ሳይሆን የወያኔ ነው።ልክ እንደ ባድሜ። 130  ዜጋ አልቆ ምን ተገኘ ወያኔናአጫፋሪዎቹ--አንዳንዶቹ ደግሞ ተቃዋሚ ነን ሊሉም ኢትዮጵያ,በአባይ ልትጠቀም ስትነሳ በግብጽ ተጠቃች ወይም ልትጠቃ ነው በሚል ሀገር ወዳድ ሁሉ ተነሳ ለማለትና ለማደናገር አቅደዋል። የሚሞኝላቸው አይኖርም ማለትም አይቻልም። ለነገሩ ግብጽ ኢትዮጵያን ሊወር አይችልም-- አይሮጵላኖች አስነስቶ ግድብ ተብየውን ሊደበድብ ይችላል። የሚያቆመውም አይኖርም ዕድሜ ለወያኔ ስንት ሚሊዮን ብር የፈሰሰበትን አየር ሃይል በትኖ በጀሌዎቹ ሞልቶት ይቀልዳል። መካላከያ ተብየው ሆኖ ሕዝብንም ከፋፍሎና አሽመድምዶ ይገኛል

ኢትዮጵያ መብቷን ለማስከበር አቅም የላትም። ወያኔ የአሜሪካ ሎሌና ተገዢ ነው-- አሜሪካ ደግሞ ግጭት ከተነሳ ግብጽን መቃወም ኣንችልም/ ብላ ለወያኔ አስጠንቅቃለች። የወያኔ አገዛዝ ከድጡ ወደ ማጡ ሊከተን ነው እየጣረ ያለው። ይህን መቃወም ደግሞ ለሀገራችን ደህንነት ወሳኝ ነውና ወያኔና ቅጥረኞቹን ወግዱ እረፉ ማለት ግድ ነው።ዛሬ ባለንበት ሁኔታ ከግብጽ ጋር ግጭቱ ለኢትዮጵያ የሚጠቅማት አይደለም። የኢትዮጵያ መንግሥት የለም አገርም በመንግስት ስም የሚገዙዋት ሕዝብን ለጦረነት አገርን ለጥቃት አሳልፎ የስጠ የሚሰጥ በአገራዊ [በብሔራዊ] ክህደት ወንጀለ የሚጠየቅ የወያኔ ስብስብና ተባባሪዎጩ ናቸው። 

ወያኔ ስልጣን ሲይዝ ከግብጽ ጋር ተፈራርሞ የሀገርን ጥቅም መሽጡንም መርሳት አንችልም። ወያኔ ጫካ ሳለም በግብጽ መረዳቱንና የተከዜ ድልድይን ሊያፈርስ መሞከሩንም የምንረሳው አይደለም። ወያኔ ከስረ መሰረቱ ፀረ ኢትዮጵያዊጥላቻን መስረት በማድረግ ከባንዳ አያቱና፤  አባቱ፤  ዘመድ አዝማዶቹ፤  የባኤላ አሹቅ እየቃመ፤ቂጣ እየገመጠ፤በለስ እየጋጠ፤ ጥሕሎ እየዋጠ፤  እሳት ዳር ተኮልኩሎ፤  በባላባታዊ የስልጣን ትንንቅ አባዜ የወደቁ ለጠላት ያደሩ ቅድመ አያቶቹ፤ አባቶቹ  ያወረሱትን ቂም በቀል የጎሳ ጥላቻ አፈታሪክ አንግቦ፤ በስነልቦና የበታችነት ማንነት በሽታ ተጠምዶ ያደገበትን ማንነት ባሕሪ መሰረት በማድረግ፤ኢትዮጵያ የቅኝ ገዥ አገር ናት፤ ትግሬን ነፃ አገር እናደርጋለን፤ትግሬ ለትግራዊ  የሚል ፋሽታዊ ብሂል አንገቦ ፈጣሪውን ሻቢያን ተገን አድርጎ በባእዳን አገራት አጋርነት አደራጅነት አማካሪነት የፖለቲካና የዲፕሎማቲክ፣ የእርዳታ ገንዘብ ለጋሲነት፤ በወገን ደም ሰክሮ ስልጣንን በመጨበጥ፤ የኢትዮጵያ ታሪክ የመቶ አመት ታሪክ ነው በሚል ጸረ ኢትዮጵያዊነት ቅዥት ውስጥ ተዘፍቆ ፤በመላው ኢትዮጵያውያን አንድነትና ትብብር አጥንታቸውን ከስክሰው ደማቸውን አፍስሰው አባቶች እናቶች ያቆዩንን ታሪክ፤ የአማራ ገዥዎች የጻፉት ተረት ተረት ነው በሚል ስንኩል ቱሪናፋ ዲስኩር ፕሮፓጋንዳ፤ የሽግግር መንግስት፤ነፃነት ውይንም ባርነት፤ብሔር ብሔረስቦች፤ የብሔር ብሔረስቦች እስከመገንጠል በሚል፤በወንድሞቹ ደም የተጠመቀውን ጠብመንጃ በሕዝብና በአገር ላይ ወድሮ፤ ያላንዳች ሕዝባዊ ውክልና፤አገርን አስገንጥሎ፤ አገርን ያለባሕር በር ያስቀረ፤ ትውልደ ኢትዮጵያን የባእዳን ቅጥረኛ ምሁራንን በፋሽስቱ ቪኒቶ ሞሶሎኒ መርዝ የተለወስ ወያኔያዊ ሕገመንግስት እራሱ አስረቅቆ እራሱ በአምሳሉ በፈጠራቸው የጎሳ አቀንቃኝ ድርጅቶችና ሆድ አደር ስብስቦች በማስወስን፤ አገርን በአስራ አንድ ጎሳንና ቛንቛን መአከል ያደረገ 1928 በፋሽት የኢጣሊያ የአምስት አመቱ ወረራ ጊዜያዊ አገዛዝ ቻርታ የተነደፈውን የቅኝ አገዛዝ ሥነስርዓት አማካኝ ያደረገ፤ ከግማሽ ምዕተ ዓመት በኋላ ከተቀበረበት ጕድጒድ አውጥቶ የአፍሪቃ የነጻነት ተምሳሌት የሆነችዋን ውድ ሃገራችንን በጎሳ በቋንቋ ተከፍላ በጥቂት ወያኔ ግርቢጦች፣ የውጭ ቅጥረኛ ጎስኞች መዳፍ ውስጥ ገብታ በሃያ አንደኛው ክፍለዘመን፤ አገር የጎሳ ባላባታዊ አንባ ገነን ሥነመንግሥታዊ አገዛዝ ሥር እንድትወድቅ የመከረ ያስመከረ የተገበረ፤ ሕዝብና አገርን የካደ፤ የሃገርና የሕዝብን ጥቀም አሳልፎ የሰጠ የሚሰጥ፤ አጥፊ፣ መስሪ ስብስብ፤ ትላንትም ሆነ ዛሬ ምግባሩ ሥራውም በጥፋት ላይ ጥፋትን ያነጣጠረ መሆኑ ለማንም አገር ወዳድ ግልጽ ነው። ወያኔአገርን ለባዕድ ሻጭ ጸረ ኢትዮጵያ ሀይል ነበረ--አሁንም ነው። ለዚህም ነው ከባዕድ ጋር የፍጥጫን ጎዳና መርጦ ሀገራችንን ለጥቃት ሊያጋልጥ እየተፍጨረጨረ ያለው። በመሆኑም ነው ሕዝብን ለጦረነት አገርን ለጥቃት አሳልፎ ከሚስጥ አገራዊ [ብሔራዊ] ወንጀለኛ፣ አገርና ሕዝብ ገዳይ አንባገነን ስነስርአት ጋር አገራዊ ትብብር ሊኖር የሚያስችል ምንም ጉዳይ የሌለው። በአባይ ስም ሕዝብን በጦርነት ለመማገድ፣  አገርን ለጥቃት አሳልፎ ለመስጠት፣ ከሚያሴሩ ጠርናፊ አስጠርናፊ የወያኔ ቅጥረኞች ተንኮል እራሳችንን አውጥተን፣ ሕዝብና አገርን በጋራ እንታደግ ለነጻነት ትግል በጋራ በመቆም አምርረን እንነሳ።


ድል ለኢትዮጵያ !!!