Sep 24, 2013

ኦሮማይ፣ ትግሉ በሚቻለውና በማንኛውም መንገድ!

September 21, 2013

ከቴዎድሮስ ሓይሌ (tadyha@gmail.com)
Ato Andargachew Tsige, Ginbot 7ሠሞኑን የግንቦት ሰባት ዋና ፀሐፊ የሆኑት አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ስለ ኤርትራ ቆይታቸውና ስለድርጅታቸው ቀጣይ የትግል እንቅስቃሴ ሠፊ ገለጻና ማብራሪያ በኢሣት ቴሌቪዠን ከሠጡ ወዲህ የዘረኛው የትግሬ ነጻ አውጪ ግንባር ደጋፊ የሆኑት መርገማዊ ልሳኖች( አይጋ ፎረም ፤ ትግራይ ኦላይንና አውራንባ ታይምስ) እና አንዳንድ ተንበርካኪ የመንደር ሬድዮኖች ሰፊ የውግዘትና የህዝብን መንፈስ ያሸብርልናል በተቃዋሚዎችም ላይ ጥርጣሬ ይዘራልናል በሚል ደካማ ግንዛቤ እያካሄዱ ካለው አሰልቺና ኋላቀር ፕሮፓጋንዳ እጅግ ተጋኖ እየቀረበ ያለው ከሻብያ ጋር አብሮ መስራት ታላቅ የሃገር ክህደት ስለመሆኑ እፍረት የለሽ ኡኡታ በማሰማት ላይ ይገኛሉ።
ይህንን ጽሑፍ እንድጽፍም ያነሳሳኝ ይህ የወያኔ በቀቀኖች ልቅ ያጣ የፀረ ሻብያ ውትወታ ወያኔ የምትባለው የጠባብ ዘረኞች ቡድን ለዚህ ዛሬ ለደረሰችበት የዘረፋና የልዕልና ደረጃ የበቃችው ከቶ በማን ትከሻ ሆነና ነው ። ዛሬ ሌሎች ኢትዮጽያውያን ወደ ኤርትራ ስለሄዱ ይህ ሁሉ ውንጀላ ደጋፊ ተብዬቹ የሚነዙት ወያኔ በሻብያ ሁለገብ ድጋፍ የማቴሪያል የትጥቅ የዕቅድና የሃሳብ መመሪያ ውጪ እንኳን ሚኒሊክ ቤተመንግስት ልትደርስ ቀርቶ ተከዜንም ባልተሻገረች ነበር።በአንድ ወቅት የኤርትራው መከላከያ ሚንስትር ጀነራል ስብሃት ኤፍሬም ስለ ወያኔዎቹ ያለውን እጅግ የወረደ ንቀት የገለጸበትን አባባል እንዳስታውስ አሰገደደኝ ‘’እኛ ከነጀነራል ደምሴ ቡልቱና ከነጀነራል ረጋሳ ጅማ ጋር በመዋጋታችን ኩራት‘’ የሚሰማን በመሆኑ ከነዚህ የፍየል እረኛ ወያኔዎች ጋር ፈጽሞ ለንጽጽር የማይቀርቡ እጃቸውን ይዘን ለዚህ ያደረስናቸው እኛነን ሲል ነበር ከአመታት በፊት የተናገረው። ወያኔዎች በሻብያ የበላይ ሹማምንት ብቻ ሳይሆን በተራው ተጋደልቲ ጭምር የሚናቁና እንደ ሻብያ አገልጋይ የሚታዩ ስለመሆናቸው ከሁለት አስዕርተ አመታት በኋላ እንኳ አለመለወጡን በረባው ባረባውም በባነኑ ቁጥር የሻብያ ስም እንደሚያስበረግጋቸው ዘወትር ከአፋቸው አለመጥፋቱን የምናስተውለው ሲሆን የሰሞኑ ደግሞ ተባብሶ የሚታየው ጫጫታ አንዱ የወያኔዎች የፍርሃት ማሳያ ይመስለኛል።
የወያኔ መሪዎች የትግራይን ገበሬ ልጆች በግዴታ ለሻብያ አሰልፈው እያዘመቱ ፈንጅ ማምከኛና በማስደረግ የፈጸሙት የሎሌነት አሳፋሪ ገሃድ እየወጣ ባለበት በአሁኑ ወቅት አበው በቆማጣ ቤት አንድ ጣት ብርቅ ነው እንዲሉ እሱ ብቻ ሕልመኛ እሱ ብቻ ባለራዕይ የነበረውና በሞት ተለይቶ እንኳ ወሬው የገነነለት መለስ ዜናዊ እንዲህ ለራሱ የሚያሸረግድ አድርባይ የሎሌ መንጋ ትቶ እንደሄደ ትላንት እርሱም ለሻብያ ካድሬዎች ይንበረከክ እንደነበረ ታሪኩን የሚያውቁት ሲመሰክሩ ቆይተዋል በተለይም ወያኔዎች ከሻብያ ጫማ ስር ለመዋላቸው የሚቀርብባቸው ማስረጃ የኢትዮጽያን ተፈጥሯዊ የባህር በር አሣልፈው ከመስጠት አልፈው የኤርትራ ነጋዴዎች የጅማን ቡና የለገደንቢን ወርቅ ከማህል ሃገር በብር እየገዙ ለውጭ ገበያ በዶላር ያቀርቡ የነበረበትን ሁኔታ አንድ እግር ቡና የማታብቅለው ኤርትራ ከቡና ላኪ ሃገሮች ተርታ መሰለፍ እስክትደርስ ድረስ የተካሄደውን የወያኔ ተንበርካኪነት ስናስታውስ ሻብያ በአዲስ አበባው ኤንባሲ ውስጥ የጥቁር ገበያ የዶላር ምንዛሬውን ሲያደራ እዚያው ኤንባሲ ውስጥ እስር ቤት አቋቁሞ የፈለገውን ሲያደርግ የነበረበት የጌታና የሎሌ ታሪክ የተዘነጋ ይመስል ወያኔና ጭፍሮቿ ሻብያን ቀንድና ጭራ ልትቀጥልልለት የምታደርገው መፍጨርጨር ተመልካች የማይታደምበት ተራ ኮሜዲ ከመሆኑም በላይ እውነተኞቹ የትግራይ ልጆች እንደ አስራት አብረሃምና እንደ ገብረመድህን አርዐያ ያሉት ይህንን የሚታወቅ ታሪክ በተባ ብዕራቸው ትውልድ እንዲያውቀው ከትበው ያስቀመጡት በመሆኑ ዝርዝር ሃተታ አያስፈልገውም ።
ዘረኝውና ዘራፊው የወያኔ ጥርቃሞ በእንዲህ ያለ የሻብያ የጭን ገረድነት የገለማ ታሪክ እያለው ዛሬ ሌሎች ኢትዮጽያውያን ከሻብያ ጋር ቢተባበሩ ከኢሳያስ ጋር ቢነጋገሩ ከቶ ሊቃወም የሚችልበት የሞራል መሠረት የሌለው መሆኑን ወናፍ ፕሮፓጋንዲስቶቹ ሊረዱ በተገባ ነበር። የኢትዮጽያ ልጆች በመረጡት አጀንዳ በመሰላቸው የትግል ስትራቴጂ ከማንኛውም ምድራዊ ሃይል ጋር የመነጋገር የመተባበር ሙሉ መብትና የተሟላ የሞራል የበላይነት ስላላቸው ላለፉት 22 አመታት የህዝባችንን ደም በመምጠጥ ላይ ያለውን ዘራፊ ሌባና ሰውበላው ወያኔን ለማስወገድ ከሻብያ ጋር አይደለም ከሴጣንም ጋር ቢዋወሉ የሚያስመሰግን እንጂ ከቶም የሚያስወቅስ አለመሆኑን ማንም ሊያሰምርበት የሚገባው አብይ ነጥብ ሃገራችንና ሕዝባችን ከወያኔ የከፋ ምድራዊ ጠላት የለውምና ነው። ኢትዮጽያዊ ሃይሎች ከማንኛውም ወገን የሚደረግላቸውን የገንዘብ የማቴሪያልና የስልጠና እገዛ ሃገርና ወገንን ለመታደግ እስካዋሉት ድረስ ከማንም ጋር ቢተባበሩ ከቶም በታሪክ ሊያስወቅሳቸው የሚያስችል ባለመሆኑ በያዙት ጎዳና በልበሙሉነትና በወኔ ሊጓዙ በመቃተት ላይ ያለው የወገናቸው የሰቆቃ ድምጽ ግድ ይላቸዋል። ነገር ግን የሃገርን ብሄራዊ ጥቅም በሚጎዳ ማናቸውም ውልና ስምምነት ውስጥ ቢገቡ ወያኔ ለሻብያ ቂጣ ጋጋሪና መንገድ መሪ በመሆን እንደፈጸመው የውርደት ታሪክ እነሱም እንዳይደግሙት ሊጠነቀቁና አካሄዳቸውን ከጊዜያዊ ፍላጎት አንጻር ሳይሆን ከዘላቂ ጥቅም አንጻር እንዲያደርጉ ይጠበቅባቸዋል።
ከዚህ ባሻገር ወያኔን ለመደምሰስና ለማስወገድ የሚደረገው ትግል በተቀናጀና ሁሉን ወገን ባሳተፈ መልኩ እንዲሆን ሠፊ የፖለቲካ የዲፕሎማሲና የፕሮፓጋንዳ ስራ በስፋትና በጥራት እንዲካሄድ ከህዝቡና ከአጋር ወገኖች የሚገኝ ትግሉን በጥንካሬ ለመወጣት እንዲቻል የሚያግዝ ከፍተኛ የገንዘብ አቅም በማፈላለጉ ላይ ያለይሉኝታ ሊንቀሳቀሱ ይገባል። እዚህ ላይ ባለፈው ሰሞን እንደትልቅ የሃገር ክህደት ወያኔዎችና አንዳንድ ህዝባችን የተጫነበት ድቅድቅ የዘረኝነትና የግፍ ጭለማ ያልታያቸውና የሃገራችን እጣፋንታ ያልገባቸው በተቃውሞው ጎራ የተሰለፉ ቅንጡ ፖለቲከኞች ሲያራግቡት የሰነበቱት የማጥላላት ዘመቻ ግንቦት 7 ከሻብያ ግማሽ ሚለዮን ብር የመቀበሉ ቱማታ በእኔ እምነት የሚያስወቅስ ሳይሆን የትግሉ እድገት አንድ ደረጃ እንደደረሰ ማሰያ በመሆኑ ከወያኔ ጋር ለሚደረገው እልህ አስጨራሽ ትግል የገንዘብም ሆን የቁሳቁስ ድጋፍ ከሻብያ አይደለም ከሠይጣንም ቢገኝ አመስግኖ መቀበል የሞራል ድጋፍ ያለው አካሄድ በመሆኑ አስፈላጊ አይደለም እንጂ የተገኘው ድጋፍ በአደባባይ ቢገለጽ የሚያኮራ እንጂ የሚያሳፍር አይደለም። በተለይ በተቃውሞው ጎራ ያለው ወገን ቆም ብሎ ሊያስብ የሚገባው መሠረት በሌለው እንቶፈንቶ ለመነታረክ ግዜ ከማጥፋት ይልቅ በየራሳችን ይዝን የተነሳንውን አላማ ከግብ ለማድረስ መትጋት ላይ ትኩረት ማድረግ ቢቻል ወያኔ ይህን ያህል ችግር አትሆንብንም ነበር ። ስለሆነም ከኛ ቁጥጥር ውጪ የሆነንን የሌሎችን እንቅስቃሴ ሂደቱን ባንደግፍ እንኳ ተቋዋሚ ልንሆንበት የሚያስችላን አንዳች የፖለቲካ አመክንዮ ስለሌለን በመተባበር በጋራ መቆም ባንቸል በመከባበር በየራሳችን መንገድ መጓዙ የመከራውን መንገድ የሚያሳጥር በመሆኑ ላይ ግንዛቤ ሊኖረን ይገባል።
በኤርትራ በኩል የአመጽ ትግሉን እናካሂዳለን ብለው በድፍረት የቀረቡትን ወገኖች ስለቁርጠኝነታቸው አድናቆት መቸር ሲገባ አንዳንደ የዘረኛው ቡድን ተላላኪዎችና የመንደር ራድዮ ጣቢያዎች ጉዳዩን አጣመው ስላቀረቡት ብቻ ያን ይዞ የትችትና የስድብ ዘመቻ ማካሄድ ተገቢም ካለመሆኑም በላይ በእርስ በርስ ሽኩቻ የሕዝባችን መከራ እንዲራዘም ማድረግ ስለሚሆን ሁሉም ወገን ተገቢነት ባለውና ስልጡን በሆነና መቻቻልን ባሰላሰለ መንገድ ሁሉም የትግል ሃይሎች ቢቻል ጎን ለጎን ካልሆነም በመከባበር ግባቸው ላይ ብቻ ትኩረት በማድረግ ከጎንዮሽ መጠላለፍ እንዲታቀቡ የደጋፊው ህብረተሰብ አሰላለፍ ከስሜታዊነትና ከጠባብ የቡድን አመለካከት ባሻገር ሠፊውን አላማ ላይ ያነጣጠረ ብልህ አካሄድን ማቀናጀት ሁሉም አትራፊ የሚሆንበት የፖለቲካ ሂሳብ በመሆኑ ላይ ትኩረት መስጠት ይኖርብናል። ከዚህ ባሻገር ካሮጌ ፖለቲካችን የወረስነው የስማበለው የባልቴቶች የአሉባልታ ተረት ተረት ይዞ መጓዝ የደረስንበት ዘመን የማይዋጀውና የንቃተ ህሊና ደረጃ ወደማይፈቅድበት የማሰብ አድማስ የሰፋበት ሁኔታ መከሰቱን በመረዳት በሎጅክና በትንተና ሃሳባችንን እስካላስረገጥን ድረስ አዲሱ ትውልድ የማይቀበለው ባለመሆኑ በተለይ እድሜ ጠገብ ፖለቲከኞቻችን ከዚህ አንጻር የትውልድና የአመለካከት መጠነሰፊ ሽግሽግ በግዜ ሂደት መከሰቱን አውቃችሁ በየአቅጣጫው እየተካሄደ ያለውን ትግል በጥራትና በግልጽ ለውይይት እንዲቀርብ በማድረግ በአመጽ ጎዳና እንዘምታለን የሚሉትን ሃይሎች በነጠረ ሂስና ግለሂስ ጥንካሬና ድክመታቸውን እንዲለዩ ህዝባችንም አቅጣጫውን እንዲያስተካክል የሚረዳ ተሳትፏችሁ በጥበብ የተሞላ መሆን ይኖርበታል። አለያ የኔብጤው ወኔና እውቀት አጠር ዲያስፖራ ሠልፍ እንኳ ለመውጣት በደረቅ በጋ ስካርቭ የሚደርብና አርቴፊሻል ጢም የሚቀጥል ፍርሃት ያራደው አውታታ ፤ የወያኔን አገዛዝ ለመደምሰስ ዱር እንገባለን የሚሉትን ሃይሎች መደዴ በሆነ ቋንቋ ሲዘልፍና የግለሰቦችን ስብዕና ሲዘልፍ ላስተዋል ምን ያህል ከሞራል አልባነት ከኋላቀርነት ያልተላቀቀ ምስኪን ወገን በመኖሩ እንዲህ አይነቱ የስድብ ሱሰኛ በምክር አይደለም በጸበልም የሚተወው ባለመሆኑ ለእንዲህ አይነቱ የአስተሳሰብ ድውይ ከማዘን በስተቀር ሌላ ሃይል ማበከን ተገቢ አይመስለኝም ።
አዲሱ ትውልድ ይጠይቃል በበቂ መልስለት ይከተልሃል፤ ይህ ነው መሬት ላይ ያለው ሃቅ ቅንጅት ሚሊዮኖችን ያነቃነቀው ሕዝባዊ አጀንዳና የሚታይ ራዕይ ስላስቀመጠ ነበር። በቅርቡ የተመሠረተው ሠማያዊ ፓርቲ በመሪዎቹ ቁርጠኝነትና ባቀረቡት ወቅታዊ አጀንዳ አንጻር ከስምንት አመታት በኋላ ታላቅ ህዝባዊ ሠልፍ በማድረግ የፈጠሩት መነቃቃት ፓርቲው ከተመሰረተ አጭር ግዜው ቢሆንም ያለው ተደማጭነቱ ከአንጋፋዎቹ ልቆ እንዲገኝና ተስፋ እነዲጣልበት ያደረገው የድርጅቱ መርሆ በሎጅክ የተቃኘና አላማውን ግልጽ በማድረጉ ይመስለኛል። ሕዝብ የሚከተለው ትውልዱ ለትግል የሚነሳው ወቅቱ ከፈጠረው አዲስ ሁኔታ አንጻር እንጂ በታሪክ ቡልኮ ተጀቡኖ በተረትና ሃሜት በሚነዳ የፖሮፓጋንዳ ዘመቻ አይደለም፤ ያ በስማ በለው በደመነፍስ ትውልድ ከሚነዳበት የስብስቴ አመለካከት ላያዳግምና ተመልሶ ላይመጣ በማስተዋልና በስልጣኔ እየተሻረ በመሄድ ላይ በመሆኑ ብዙዎች ያወሩለትን ጥቂቶች ጀምረው ያቆሙትን የአመጽ ትግል በአዲስ መልክ እናስቀጥላለን ብለው የተነሱትን ሃይሎች የማይደግፍበት ምክንያት ቢኖረው እንኳ ከመርህ አንጻር ሊቃወም የሚችልብት ምንም በቂና ውሃ የሚቋጥር አሳማኝ ምክንያት ባለመኖሩ ሂደቱን በጥንቃቄ ይከታተላል።
በዚህ የስልጣኔና የጥበብ ዘመን ላይ ቆመን ከቶስ ስል አመጽ ትግል ማንሳት ለምን አስፈለገ ጦርነት የሰውን ልጅ የሚበላ እሳት ነው። አመጽ ሃገር የሚያወድም መሠረተ ልማትን የሚንድ ኋላቀር መፍትሔ ነው፤ የሰላሙን ትግል ማበረታታት ሲገባ ለምን የአመጽ መንገድ እንደ መፍትሔ ይቀመጣል የሚሉ ወገኖች በርካቶች ናቸው። እርግጥ ነው ዲያቢሎስ ካልሆነ በቀር ጦርነትን መልካም ነው የሚል አንዳችም ጤነኛ አዕምሮ ያለው ፍጡር አለ ለማለት አይደፈርም። እንደምኞታችን ነገሮች በተቃውሞ ሠልፍና በሕዝባዊ እንቢተኝነት ቀለውልን ከላያችን የተጫነው ግፈኛ አገዛዝ አሽቀንጥረን ብንጥል መልካም ነበር። ይህ ግን ቀላል ሆኖ አልተገኘም የተከፈለውና በመከፈል ላይ ያለው መስዋዕትነት አንሶ አልነበረም አመጽ ታሳቢ የሆነው። ሃገራችንን የወረረው የወያኔ ቡድን ፖለቲካና ርዕዮተ ዓለምን መሠረት ያደረገ ሣይሆን ፤ የዘር አመለካከትን ዶግማና ቀኖናው በማድረግ ኋላቀር አካሄዱንና፤ ኢ ዲሞክራሲያዊነቱን የተቃወመውን ወገን በሙሉ የሚመለከትበት ሸውራራ አተያይ ፀረ ትግራይ በሚል በመሆኑ ከእንዲህ አይነቱ ጠባብና ድኩማን አመለካከት ባለው ሃይል ከሚመራ ቡድን ጋር የሚደረግ ስልጡን የፖለቲካ ትግል ውጤቱ ፍሬ አልባ በመሆኑ ሊገዳደረው የሚችል የሃይል እንቅስቃሴ አማራጭነቱ ሁሉን ወገን ከተረዳው የከረመ ቢሆንም አለመታደል ሆኖ የትግሉን እንቅስቃሴ ማቀናበሪያ ወሳኝ ኮሪደር በማግኘት ዙሪያ ስንቸገርና ባለውም ጠባብ አማራጭ ለመጠቀም ሳንችል የቆየንባቸው ትርምስ የተሞላ ሰፊና ወርቃማ ግዜያቶች ባክነዋል።
አመጽ የጭቁኖች ድምጽ ነው ሲል የተናገረው ጠቢብ ማን ነበር ፤ አዎን አመጽ የሰውነት ክብርን ማረጋገጫ የነፃነት እስትንፋስ ማግኛ የባርነት ሰንሠለትን የሚበጥስ ጽኑ መዶሻ ነው። በሃገራችን የዛሬን አያድርገውና እንኳን ሃብትና ንብረቱ እየተቀማ ከነ ቤተሰቡ ጎዳና ሊጣል ቀርቶ ክፉ ቃል ተናግሮ ስብዕናውን የተዳፈረውን አደብ ሳያስገዛ የማይኖር ከምንም ነገር በላይ ለክብሩ ዘብ የሚቆም ማንነቱ ተዋርዶ በሞቀ ጎጆው ከመኖር ይልቅ ክብሩን ለማስመለስ ዱርቤቴ ማለትን የሚመርጥ ጀግና ሕዝብ እንደ እባብ ተሽሎክሉኮ በገባው የማንም መደዴና ቀን የሰጠው ወፍዘራሽ ዘረኛ የወያኔ መቀለጃ ሆኖ ለስደት ለሞት ለእስርና ለምድራዊ ስቃይ የተዳረገው መብቱን ለማስከበር አመጽን አማራጭ ባለማድረጉ መሆኑን እያየንው ነው።
ወያኔዎች በለስ ቀንቶዐቸው ድፍን ኢትዮጽያን ሲወሩ በየሄዱበት ያገኙትን አሮጌ አካፋና ቀደዳ በርሜል ሳይቀር እየጫኑ ወደትውልድ ስፍራቸው ሲያግዙ ከነበረበት ቅራቅንቦ ሰብሳቢነት እድሜ ለታላቋ ሃገራችን ዛሬ ይህው እኒያ ከገላቸው እድፍና ከጎፈሬያቸው ተባይ ውጪ የረባ ጃኬት እንኳ ያልነበራቸው ሽፍቶች ይህው ዛሬ ድፍን ሃገር በጠኔ እየተመታ በረሃብ አለንጋ በሚለበለብበት ልጆቹን በፈረቃ የሚቀልብበት የኑሮ ምስቅልቅል ውስጥ ወድቆ ልጆቹ በየትምህርት ቤቱ ደጃፍ ረሃብ አዙሮ እየጣላቸው ባለበት ሁኔታ ላይ የወያኔው አባላት ጉቶ እየሞቁ ድብዳብ ላይ ተወልደው እዛው አጎዛ ላይ እንዳላደጉ ይህው የህዝብን ሃብት በመዝረፍ በህንጻ ላይ ህንጻ በሃብት ላይ ሃብት እያከማቹ ከራሳቸው አልፈው በድብቅ ላስቀመጧቸው እቁባቶቻቸው ወርቅና አልማዝ መኪናና ቪላ ስጦታ የሚያቀርቡበት ታጋይ ከበርቴዎችና ልማታዊ ዘራፊዎች ሕገ ወጥ ብልጽግና አካብተው ቅንጦት የሚያደርጋቸውን ባሰጣበት በዚህ ወቅት ትውልዱ ኑሮ ዳገት ሆኖበት የከፋውን ስደት ተያይዞት የሲናይ በርሃ አሸዋ ሲሳይ የቀይባህር አሳ ቀለብ እየሆነ እንደወጣ የቀረው የእምዬ ኢትዮጽያ ልጅ የሚደርስበት ሰቆቃ ዓለምን እስኪሰለች ድረስ የተለመደ የሰርክ ተግባር በመሰለበት በዚህ ዘመን ፤ በሃገር ውስጥ ያለው በገፍ በሚቀርብለት ጫት ደንዝዞ በምዕራቡ ዋልጌ ባህል ነፍዞ ከሞቱት በላይ ከቆሙት በታች በሆነ የሞራልና የተስፋ መቁረጥ ጭለማ ተውጦ የትግሬው ነጻ አውጪ አባላት ልጆች ከህዝብ በሚዘረፍ ገንዘብ በአውሮፓና በኣሜሪካ ውድ ኮሌጆች እንዲማሩ እየተደረገ ባለበት የፋሽስት አገዛዝ ውስጥ የአንድ አናሳ ብሄር ሰዎች ተጨፍልቆ እየቃተተ በስቃይ በሚኖርበት ሁኔታ ውስጥ ህዝባችን ቢያምጽ ይነሰው በእውነቱ ይህ ትውልድ እነዚህን የቀን ጅብ ወያኔዎች ለመታገል ከሰይጣንስ ጋር ቢተባበር ከቶ ወንጀሉ ምኑ ላይ ነው?
ተወልደው ካደጉበት ጎጆ ቀልሰው ትዳር ይዘው ጫካ መንጥረውና ከአውሬ ታግለው ከባዱን የኑሮ ዳገት በላብ በወዛቸው አቅልለው በሰላም ሃገሬ መንደሬ ብለው የእርሻን ጥበብ የአኗኗር ዘይቤን ሃይማኖትንና ግብረገብነትን በየሄዱበት አስተምረው በቋንቋና በባህል የተለያቸውብ ወገን የራሳቸው አድርገው ተዛምደውና ተጋብተው በሰላም ለዘመናት ከኖሩበት ቅዬ ሃገራችሁ አይደለም በሚል ያፈሩትን ሃብት ነጥቆ ተማሪዎች ከትምህርታቸው በግድ እንዲፈናቀሉ በማድረግ በክፋትና ቂም በቀል አንድን ህዝብ ለማጥፋት የሚያደባውን እርጉሙን የትግሬ ነጻ አውጪ ቡድን ይህ ሕዝብ መፋለም ይነሰው በጉራፈርዳ በቤኒሻንጉል በአፋርና በጋንቤላ እንዲሁም በሌሎች ቦታዎች የተፈጸመው የዘር ማጥፋትና ሁን ብሎ በድህነት የመቅጣት ወያኔያዊ ሴራ በእውነቱ ከወንጀልም ወንጀል ከሃጢያትም ሃጢያት የሚሆነው ይህንን ሳጥናዔላዊ ቡድን አለመታገል ብቻ ነው።
ነብሳቸውን ይማረውና አያቴ ‘’ ጣሊያን ምን አጠፋ በከንቱ ኩነኔ ሃገሩን አጠፉት መለስና ላይኔ’’ ብለው ነበር ያኔ ገና ወያኔ ሃገር ስትወር ፋሽስት ጣሊያን ያልፈጸመውን ግፍ ኦርቶዶክስና አማራ የሚባል ተቋምና ህዝብን ለማጥፋት እቅድ ነድፎ መርዝ አዘጋጅቶ የመጣን አርዮሳዊ ሃይል ለሺህ ዘመናት የውጪና የውስጥ ሃይሎችን በጽናት በመመከት ህልውናዋን አስጠብቃ የኖረችውን የታሪክ ማህደሯን ቅድስት ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን እንድትከፋፈል የዘረኞች ምሽግ በመሆን ሃዋርያዊ ሃላፊነቷን ዘንግታ የጥፋት አላማው ማራመጃ ለማድረግ በመለመላቸው ጥቅመኛና ዘረኛ ጻጻሳትና ፓትርያርክ ተብዬ በማዘጋጀት በቤተክርስቲያኒቱና በምዕመኑ ላይ ሲደርሰ የቆየው በደልና ግፍ በቀላሉ ተዘርዝሮ አያልቅም። ወያኔ በቤተክርሰቲያኒቱ ላይ ያለውን ጥላቻ በማስፋፋት ይደረጋል ተብሎ አይደለም ሊታሰብ እነኳ የማይሞከረውን ታላቁን የዋልድባ ገዳም ለስኳር ልማት በሚል በገዳሙና በመናኝ ባህታውያኑ ላይ የተፈጸመው ግፍ ስንቃኝ የውጭ ወራሪ ሃይል ይህን ያህል ይዳፈራልን? ታዲያስ ይህ ጉግማንጉግ ፀረ ኦርቶዶክስ የሆነ የወያኔ መንጋ ከቶስ ከሰይጣን የሚለየው በምንድን ነው? ይህንን ወንጀለኛና መንጋ ዘረኛ ይወገድ ዘንድ የዚህች ታላቅ ሃይማኖት ካህናትና ምዕመናን አድዋ ላይ ጌቶቹ ጣሊያኖችን በጸሎትና በሰይፍ እንዳሸነፈ በዚህም ሃገር በቀል የፋሽስት ሎሌን ለማስወገድ የሚደረገውን ትግል በውግዘትም በሞራልም ማገዝ ለቤተክርስቲያኗ ሰላም መረጋገጥን ለምዕመኖቿ መረጋጋትን የሚያስገኝ ትርጉም ያለው መልካም ሁኔታ ሊገኝ የሚችለው ይህ የዘረኛ መንጋ ተጠራርጎ ሲወገድ ብቻ በመሆኑ ይህንን ትግል ማገዝ የቤተክርስቲያኒቱና የምዕመናኑ መንፍሳዊ ግዴታ ጭምር ነው።
የሃይማኖት ተቋማትን ማጥፋት የትግራይ ነጻ አውጪ ግንባር እኩይና ሠይጣናዊ አላማ ሌላው ያነጣጠረበት የኢትዮጽያ ሙስሊም ማህበረሰብ ከአመታት በፊት ይህው ከፋፋይ ዘረኛ የወያኔ ቡድን የሙስሊሙን ማህበረሰብ የስልጣኑ ማደላደያ በማድረግ ከጎኑ ለማሰለፍ የሞከረበት እኩይ አላማው ከቅርብ አመታት ወዲህ ከታወቀ በኋላ መላው ሙስሊም በአንድ ድምጽ ያቀረበውን የሃይማኖት ነጻነት ጥያቄ በሃይለ ለመጨፍለቅ ከምዕመኑ ጋር ያደረገው ትንቅንቅ የሙስሊም ወንድሞቻችን ዓለምን ያስደመመ እጅግ ዘመናዊና ሰላማዊ የትግል እንቅስቃሴ ቢያደርጉም ጨዋነትን ምንም ያህል መርሐቸው ቢያደርጉም የወያኔ ቡድን ሠላማዊ ቋንቋ የሚገባው ባለመሆኑ ለሠላት የወጣውን የሙስሊም ማህበረሰብ ህጻን ከአዋቂ ሣይመርጥ በተለያዩ ቦታዎች የፈጸመውን ጅምላ ፍጅት የምታስታውስ ሙስሊም ወገን ይህንን የደደቢት ጭራቅ ለማስወገድ የሚደረገው ትግል በመንፈሳዊ ቡራኬም ሆነ በቀጥተኛ ተሳትፎ
ክንድህን ሠብስበህ እንዳትታገለው ከቶስ የሚያግድህ ምንድነው? እየተጨቆኑ መኖር ለሃገርህና ለእምነትህ ታግለህ በክብር ማለፍ ነው።
ለማጠቃለል ኢትዮጽያ እንደሃገር ትቀጥል ዘንድ ትውልዷም ተሰዶ ከማለቁ በፊት ይህን ሃገር አፍራሽና መንጋ ቅጥረኛ ከቅድስት ሃገራችን ለማስወገድ እየተካሄደ ያለውን ማንኛውም እንቅስቃሴ ዘር ሃይማኖት ሳንለይ በጋራ ቆመን በጽናትና በብርታት የመደገፍ የማበረታታት የማገዝ ታሪካዊም ሞራላዊም ሆነ መንፈሳዊ ግዴታ አለብን። በትግል አለም መውደቅ መነሳት ያለና የነበረ በመሆኑ ትላንት በሄድንባቸው መንገዶች ውጤት ባናገኝም ስልታችንን በማስተካከል ጥበብ በተሞላበትና ቁርጠኝነት ባለው መልኩ እንጓዝ ዘንድ መሪ ሃይል ሆናችሁ የወጣችሁ ሃይሎች በየትኛውም የትግል ስልትና ያላችሁ ያለ የሌለ ሃይላችሁን በማስተባበር የወያኔን ተፍጻሜተ መንግስት ለማቅረብ የሚረዳ አመራር በመቀየስ ታግላችሁ እንድታታግሉን ግዜው ግድ ይላችኋል።
ታላቁ ደራሲ ኦሮማይ በሚለው መጽሃፉ የሳላቸው የገሃዱ ታሪካችን አካል የነበረው ቀይ እንቡጥ የተባለው በለጋ ወጣቶች የተመራው የሃገር ፍቅር ሰራዊት ውጤቱ የማታ ማታ ቢበላሽም በለጋ እድሜያቸው በቆራጥነትና በጀግንነት አንድ ስትራቴጂክ ተራራ ለማስለቀቅ የከፈሉት ወደር የሌለው መስዋዕትነት ይህ ትውልድ ዞር ብሎ በማሰብ ነፃነቱን ረግጠው በሃገሩ ባይተዋር ባደረጉትና ሃገራዊ ድርሻውን ነጥቀው ባቋቋሙት የንግድ ኢንፓየር እነሱ በቁንጣን ሲወጠሩ የሃገሬ ወጣት ከረሃብ ጋር ሲታገል በየድልድይ ስር የሚያድርበት የአፓርታይድ አገዛዝ እንዲያከትም መፍትሄው ያለው በአዲሱ ትውልድ መዳፍ ውስጥ በመሆኑ ያአህዛብ አሽከርና የችጋር ጓደኛ ሆኖ ተሰቃይቶ ከመሞት ታሪክ ሰርቶ ለታሪክም ለህሊናም የሚጠቅም በጎ ተግባር ፈጽሞ ለመገኘት በሚቻለውና በማንኛውም መንገድ የሚደረገው ትግል በማገዝ ህዝባችንን ልንታደግ ሃገራችንን ልንጠብቅና ሃይማኖታችንን አስከብረን በነጻነት እንድንኖር ወያኔን ለማስወገድ የሚካሄደውን ሁለገብ ትግል በትጥቅ ይሁን በሰላም ከኤርትራ ይሁን ከሱዳን ከሱማሌ ይሁን ከጅቡቲ በሚነሳ የአመጽ ሃይል ይሁን በሕዝባዊ ንቅናቄ ሁሉን ባለን አቅምና ጉልበት ልናግዝ ታሪክ ትውልድ ሞራልና መንፈሳዊ ሕይወታችን ግድ ይለናል። በጽናትና በጋራ ቆመን ጠላቶቻችንን ለመደምሰስ እግዚያብሄር ሃይልና ብርታት ይሁነን።
ኢትዮጽያ ለዘላለም ትኑር!!!

Sep 16, 2013

ለንደን ደብረ ጽዮን ቅድስት ማርያም አደጋ ላይ ነች

አባ ግርማ ከበደን ከጌይ ጋር ሰልፍ ያስወጣ እዉነት ይህ ጽሁፍ ብቻ ነዉ???

December 26, 2012

በዶ/ር ወንድሙ መኮንን
ቀን፡ 25.12.2012
ርዕሰ አድባራት ለንደን ደብረ ጽዮን ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን ከዘረኛው የወያኔ አገዛዝ ተጽዕኖ የጸዳች፤ በUK ለሚገኘው ስደተኛ የእምነቱ ማዕከልና ኢትዮጵያው ጭምር ናት!!
አደጋ ላይ ነች፤ አድኑኝ ትላለች
London Ethiopian Orthodox Tewahdo Churchየዘመናት ታሪክ ባለቤትና ከትውልድ ወደ ትውልድ በመተላለፍ፤ ወደፊትም ለዘለዓለም የምትኖር የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ  ቤተ ክርስቲያን እውነተኛ የክርስቶስ ማደሪያ የምትባለው ዛሬ ኖሮ ነገ ለማይኖረው አምባ ገነንና ዘረኛ አገዛዝ መሣሪያ ሳትሆን ከተበደለውና መብትና ነጻነቱን ከተገፈፈው የኢዮጵያ ሕዝብ ጎን መቆም የቻለች እንደሁ ብቻ ነው።
ላለፉት 21  ዓመታት ይህንን እውነተኛ ክርስቲያናዊ ሥራ ተግባራዊ በማድረግ ከወያኔ ተጽዕኖ ነጻ በመሆን በዓለም ሁሉ ተዘርቶ ለሚገኘው ኢትዮጵያዊ መኩሪያና መመኪያ ተበለው ከሚጠቀሱት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ርዕሰ አድባራት ለንደን ደብረ ጽዮን ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን አንዷ ነች።
ኢትዮጵያ ውስጥ የተንሰራፋው ዘረኛው የወያኔ አገዛዝ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መንፈሳዊ የበላይ፤ ሕግ አውጪና ወሳኝ የሆነው የቅዱስ ሲኖዶስን መንፈሳዊ ዓላማና ውሳኔ በሥራ ላይ እንዳይውል፤ እውነት የሚናገሩ አባቶችን  በማስፈራራት፤ በማስደብደብ፤ በጠመንጃና በደህንነት ኃይል በማስገደድ በሃገሪቱ የመንግሥት መዋቅር ውስጥ እንደሚፈጸመው ሁሉ በቤተ ክህነትም ሆነ በየአብያተ ክርስቲያኑ ወሳኝ በተባሉ ቦታዎች ሁሉ የአገዛዙን የጎሳ አባላትና ደጋፊዎች በመሰግሰግ ቤተ ክርስቲያንም የዘረኛ አገዛዝን ሥርዓትን ተከትላ እንድትዋቀር አድርጓት እንደሚገኝ ይፋ ከሆነ ወራትና አመታት ተቆጥረዋል።
የዘረኛው ቁንጮ የሆኑት መለስ ዜናዊና አባ ጳውሎስን ሞት ቢወስዳቸውም ዘረኛው ሥርዓት በቅድስት ቤተ ክርስቲያን ላይ የሚያደርገው ተጽዕኖና መከፋፈል በከፋ ሁኔታ ቀጥለ እንጂ ሲሻሻል አልታየም።
ለንደን ደብረ ጽዮን ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን ላለፉት 21 ዓመታት በአባ ጳውሎስ አማካኝነት የተቃጣባትን የወያኔን አገዛዝ ጣልቃ ገብነት በሙሉ በመመከትና በመከላከል በዘረኛው አገዛዝ አቀነባባሪነት በጅማ፤ በአሩሲ፤ በአሰቦትና በሌሎችም ቦታዎች በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንና በተከታዮቿ ላይ ጥቃት ሲደርስ ማንንም ሳትፈራ በነፃነት ድርጊቱን አጋልጣለች፤ ተቃውሞዋን ለዓለም አሰምታለች፤ አቅም በፈቀደም ለተጎዱት ክርስቲያኖች ድጋፍ አድርጋለች።
በቅርቡም የዋልድባ ገዳም በአገዛዙ ሲደፈርና ሲጠቃ፤ መነኮሳት ሲታሰሩና ሲሰቃዩ ሌሎች እንግሊዝ ሃገር ያሉ በወያኔ አገዛዝ ጫና ሥር ያሉ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያናት ፀጥ እረጭ ሲሉ ቤተ ክርስቲያናችን ግን በድፍረትና በነፃነት ታላቅ ሰላማዊ ሰልፍ በማካሄድ አገዛዙ በእምነት ውስጥ ጣልቃ በመግባት የሚፈጽመውን በደል አጋልጣለች ተቃውሞዋንም ለዓለም አሰምታለች።
ይህ የቅርቡ ትዝታ ሲሆን እንደ አውሮጳ አቆጣጠር በ2005 ዘረኛው የወያኔ አገዛዝ ወንድ ሴት ሳይለይ ህጻን ወጣት፤ ጎልማሳና አዛውንት ሳይቀር በአሰቃቂ ሁኔታ በጨፈጨፈበት ወቅት ቤተ ክርስቲያናችን ከፍተኛ ተቃውሞ ከማሰማት ባሻገር በአገዛዙ  የተገደሉት ኢትዮጵያኖች እንደ ሰው ሳይሆን እንደ ውሻ ተቆጥረው ፍትሐትም ሆነ ጸሎት አይደረግላቸው ተብሎ በአባ ጳውሎስ አማካኝነት ሲታገድ ለንደን ደብረ ጽዮን ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን ግን በግፍ ለተገደሉት ኢትዮጵያኖች መሉ ጸሎት አድርጋለች።
ከዚህም በማስከተል ብጹ ወቅዱስ በማለት የአባ ጳውሎስ ሥም በቤተ ክርሲያኗ ውስጥ አይጠራም በማለት ቤተ ክርስቲያኗ የወሰደችውን የጠራ የአቋም ባሉት ሚዲያዎች ተጠቅማ ለዓለም ሁሉ አሳውቃለች። ይህንን ተከትሎ በቤተ ክርስቲያኗ ውስጥ የነበሩ የዘረኛው ወያኔ አገዛዝ ደጋፊዎች ቤተ ክርስቲያኗ ውስጥ ለሞቱት መጸለዩንና በአባ ጳውሎስ ላይ የተወሰደውን አቋም በመቃወም ከቤተ ክርስቲያኗ ተለይተው ስላሴ ቤተ ክርስቲያንን ሊያቋቁሙ ችለዋል።
የተፈጠረው የአቋም ልዩነት እንጂ የሃይማኖት ልዩነት ባለመሆኑም በአንድ ሃይማኖት ጥላ ሥር ሆኖ በአቋም ልዩነት ሕዝብ ከህዝብ ከሚቃቃርና ከሚናቆር ተለያይቶ ማምለኩ መፍትሔ ሰጪ ሊሆን ችሏል።
በእርግጥ ርዕሰ አድባራት ለንደን ደብረ ጽዮን ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን እ.አ.አቆጣጠር በ1993 የዘረኛ ሥርዓት አራማጅ ተወካይ የሆኑት አባ ጳውሎስ የቤተ ክርስቲያኗ አባላት ሳይጋብዟቸው መጥተው በማሳፈርና በማዋረድ መልሳ አባራቸዋለች ያም ሆኖ ግን የአባ ጳውሎስን ስም ብጹዕ ወቅዱስ ብላ ትጠራ ስለነበር መልሰን በእጃችን እናገባታለን በሚል ተስፋ የተለያዩ የተንኮል ሙከራዎች ይደረግባት ነበር እንጂ በለየለት ጠላትነት ተፈርጃ የከፋ ጥቃት ሳይሰነዘርባት ቆይታ ነበር።
እ.አ. አቆጣጠር ከ2005 በኋላ ግን ቤተ ክርስቲያኗ በመንበረ ፓትርያርኩኗ በአባ ጳውሎስ በለየለት ጠላትነት ተፈርጃ በርካታ ቀጥተኛና ተዘዋዋሪ ጥቃት የደረሰባት ሲሆነ ከዚህም ውስጥ የማይዘነጋው ቤተ ክርስቲያኗ የምትገለገልበትን ህንፃ ቤተ ክርስቲያን ለመግዛት ሕዝበ ክርስቲያኑ ገንዘብና ጉልበትን በማስተባበር ደፋ ቀና ሲል በአባ ጳውሎስ የተፈረመና ከመንበረ ፓትሪያርክ ለእንግሊዝ ቤተ ክርስቲያን በተጻፈ ደብዳቤ ቤተ ክርስቲያኑ በእንግሊዝ ሃገር በስደት ላይ ለሚገኙ ኢትዮጵያዊያን እንዳይሸጥላቸው የወጣው ማገጃ ነው።
ይህንን ማገጃ ግን በስደት ላይ ያለው ሕዝበ ክርስቲያን እንዲሻር በማድረግ የቤተ ክርስቲያኑንና በግቢው ውስጥ የሚገኘውን የቪካሬጅ ህንፃ በ£1.700.000 (አንድ ሚሊዮን ሰባት መቶ ሺህ ፓውንድ) በመግዛት የስደተኛው ኢትዮጵያዊ ዘላለማዊ ሃብትና ቅርስ እንዲሆን አድርጎታል።
Aba Girma Kebede London
Aba Girma from London Ethiopian orthodox church
ይህንን ሕዝብ ጥሮና ግሮ ያፈራውን ቅርስ ነው ዛሬ አባ ግርማ ከበደና (በግራ) መሪጌታ ዓለማየሁ ደስታ (በቀኝ) በተባሉ ካህናት አስተባባሪነት ቤተ ክርስቲያኗም ሆነች ሃብትና ንብረቷ
የቅዱስ ሲኖዶስና የመንበረ ፓትርያርክ ነው በማለት በቅዱስ ሲኖዶስ ስም ለዘረኛው የወያኔ አገዛዝ ሥርዓት አራማጆች በኤምባሲ አማካኝነት ለማስረከብ ከፍተኛ ትግል በማድረግ ላይ የሚገኙት።
ይህንን የክህደት ተግባራቸውን የቤተ ክርስቲያኗ አባላት እንዳማይደግፉት ሲረዱ የወያኔ ሥርዓት ደጋፊ የሆኑ ሰዎችን በተለያየ ዘዴ ወደ ቤተ ክርስቲያኗ በመጥራት የቤተ ክርስቲያኗ አባላት በብዛት እንዲዋጡና እየተስፈራሩ ከቤተ ክርስቲያን እንዲባረሩ በማስደረግ ላይ ይገኛሉ።
የኢትዮጵያ ሕዝብ ሰብዓዊ መብቱ በወያኔ ተረገጠ፤ ፍትሕ በኢትዮጵያ ጠፋ፤ ዘረኝነትና የአንድ ጎሳ የበላይነት በኢትዮጵያ ነገሰ፤ የሃገር ሃብትና ንብረት በዘረኞች እጅ ወደቀ እያልክ የምትቆረቆርና ድምጽ ለሌለው የኢትዮጵያ ሕዝብ ድምጽ የሆንክ ሁሉ ዘረኛው ወያኔ ከኢትዮጵያም አልፎ በጥቂት ካህናትና ደጋፊዎቻቸው አስተባባሪነት እዚህ እንግሊዝ ሃገር የሚገኘውን የስደተኛው ኢትዮጵያዊ ንብረትና ቅርስ  ሊወርስ እየጣረ ነውና አንዳችም ማመንታት ሳታደርግ ወደ ቤተ ክርስቲያን በመምጣት በተለመደውና በምትታወቅበት ወኔ ወያኔን አዋርደህ እንድታባርር ቅድስት ማርያም ጠርታሃለችና አታሳፍራት!!
ላለፉት 21 ዓመታት ከዘረኛው የወያኔ አገዛዝ ተጽዕኖ ነፃ አድርገህ በነፃነት እንዳኖርካት ዛሬም ቤተ ክርስቲያንህ በጥቂት የግል ጥቅም አሳዳጅ ካህናት አማካኝነት በወያኔ ደጋፊዎች እጅ እንዳትወድቅ መጥተህ ታገልላት።
የፊታችን አሑድ 30/12/12  ክቀኑ ሰምንት ሰአት፤ በቤተ ክርስቲያናችን ውስጥ ዓዲስ አመራር ኮሚቲ ለመምረጥ ስብስባ ጠርተዋል። ስሞኑን ብዙ የማናውቃቸው ስወች ወደ ቤተ ክርስቲያናችን መምጣት ጀምረዋል። ይህም ‘አባላትን”  ሕጋዊ ባልሆነ መንገድ በማብዛት፤ ቤተ ክርስቲያናችንን፤ ንብርተዋንና አስትዳደርዋን፤ አሳልፎ፤ ለወያኔ፤ ለመስጠት ነው። ስለዚህ፤ በእለቱ ተገኝታችሁ፤ ቤተ ክርስቲያናችሁን አድኑ። ወደፊትም በቤተ ክርስቲያናችን ውስጥም ሆነ ከቤተ ክርስቲያናችን ውጭ በሚደረጉ ስብሰባዎች ላይ ተገኝታችሁ፤ርዕሰ አድባራት ለንደን ደብረ ጽዮን ቅድስት ማርያምን አድኑ!!!

Aba girma kebede VS Gay right movement! London

የወያኔ ወኪሎች የዩኒቨርሲቲ መምህር ወንድሙ መኰንን ላይ ሊያደርሱ ያሰቡትና ያቀዱት ጥቃት። የርዕሰ አድባራት ለንደን ደብረ ጽዮን ቤተ ክርስቲያን አስተዳዳሪ አድርጎ ሾሟቸው የነበረውን ሕዝብ በመክዳት ስልጣኔን ከምለቅ ቤተ ክርስቲያን ተዘግቶ ሕዝበ ክርስቲያንም ተበትኖ ሃይማኖቱም ቢሻው ጥንቅር ብሎ ይቅር በሚል አቋም የሰላምና የፍቅር ቦታ የሆነችውን ቤተ ክርስቲያን የጸብና የሁከት መድረክ ያደረጉት አባ ግርማ ከበደና ተከታዮቻቸው 30 August 2013 በዕለተ ዓርብ ምሽት ስብሰባ በማድረግ፡ በትምሕርት ገበታ ላይ ሳለ ጀምሮ ላለፉት 22 ዓመታት ለኢትዮጵያ ሕዝብ ሰብዓዊ መብት መከበርና ለሰው ልጆች ነጻነት በመታገል በዘረኛው የወያኔ አገዛዝ ድምጽ አልባ ለሆነው ሕዝባችን ድምጽ በመሆን እውነትን ፍንትው አድርጎ በመናገርና በመጻፍ የሚታወቀው የዩኬ ከፍተኛ ትምህርት አካዳሚ ሙሉ “Fellow of Higher Education” ወንድሙ መኰንን የቤተክርስቲያኗ አባል በሆነበትና አስቀድሶ በሚቆርብበት በርዕሰ አድባራት ለንደን ቤተ ክርስቲያን ውስጥ የተፈጠረውን ሁኔታ አስመልክቶ በተለይም አባ ግርማ ከበደ የፈጸሙትንና በመፈጸም ላይ ያሉትን ከመነኩሴ የማይጠበቅ ተግባር ሁሌም እንደሚያደርገውና እንደሚታወቅበት ሥራው እውነትንና እውነትን ብቻ አብጠርጥሮ በመጻፉና ለሕዝብ በማሳወቁ ይህንን ሰበብ በማድረግ አባ ግርማ ከበደና ተከታዮቻቸው ታይቶም ሆነ ተሰምቶና ታስቦ በማያውቅ እጅግ በሚያስገርም ሁኔታ በፈጠራ ወንጀል ከግብረ ሰዶማውያን ነጻነት እንቅስቃሴ አባሎች (Gay right movement) ጋር ነገሩን እንደምንም ብለው ጎትተው አገናኝተው፣ በማበር የሚያስተምርበት University of Buckingham ድረስ በመሄድ የተቃውሞ ሰልፍ እናካሂድበት የሚል ዕቅድ በመንደፍ ተግባራዊ ለማድረግ መስማማታቸውን እራሳቸው ለተከታዮቻቸው ካሰራጩት ቴክስት (የተንቀሳቃሽ ስልክ መልዕክት) ለማወቅ ተችሏል። እንዲህ ነው እንጂ ክርስትና! አባ ግርማ ከበደና ተከታዮቻቸው በነደፉት ዕቅድ መሠረትም ሦስት አውቶብሶችን (coaches) ለራሳቸው በመከራየት ከዛም የግብረ ሰዶማውያን ነጻነት (Gay right movement) አባሎች በተጨማሪ በሁለት አውቶብሶች (coaches) ላይ በመሆን በድምሩ አምስት አውቶብስ ሙሉ ሰውን በመያዝ የተቃውሞ ትዕይንቱን ለማካሄድ መስማማታቸውን በቅጽል ስሙ Endexye የሚባለውና ትክክለኛ ስሙ እንዳለ ወንዳፍራሽ የተባለው ግለሰብ ካሰራጨው text መልዕክት ለማረጋገጥ ተችሏል።
የቴክስቱም ቀጥተኛ ቅጂ ቀጥሎ የተመለከተው ነው።
Date: 31/08/2013 Sent from Endexye (his real name is: Endale Wondafrash  “Yesterdays meeting went well!! As agreed we will be renting three coaches, our compatriots from the gay right movement will have another two coaches! We will drive to Buckingham university, as planned we will meet with student unions, and we will demonstrate against the imposter so called phd holder who according the university in Ireland who plagiaries his post graduate papers and banned from being named as Dr! Who writes unethical articles against our church leaders, and who vividly exhibits homophobic stances in his communication will be exposed to his colleagues and prospective students for comparing our monk and priest with terrorists that maimed and disturbed the peace of planet, because of his bitchy know it all character to full fill divisive mission to smear the integrity of our religion and clergy men.”

Respond from Dicon Mengesha Melke “Endex complaining to the university were Wondimu work should be practical because he damage the image of our church and the biography of our fathers and sisters.” ይህ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ አስከፊ ስድብ ከመሳደብና ለአንባ ጓሮ ከመጋበዝ በስተቀር አንድም ቀን ከስሙ በፊት በሚጠራበት ድቁና አንዳችም የክህነት አገልግሎት ሲሰጥ ታይቶም ሆነ ተደምጦ የማይታወቀው መንገሻ ተክሌ የተባለው ግለሰብ፣ ዲያቆን ተብሎ ለመጠራት የቻለበትን የክህነት ማዕረግ ከየት እንዳገኘው የታወቀ ነገር ባይኖርም፣ ዲያቆን ነኝና፣ የካህናት ጉባኤ አባል ነኝ ባይ በማለት እንደውም ከካህናቱ ቀድሞ ለመታየት የሚዳዳው ነው። ይህንን ድርጊቱን ከአፉ፣ ለማረጋገጥ http://www.youtube.com/watch?v=gnLIKSGIqJs ይመልከቱ።በUK ሆነ በመላው ዓለም የምትገኙ ሃገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን ሁሉ በአሁኑ ወቅት የወያኔ የጎሳ አፓርታይድ አገዛዝ በየዕለቱ ሰብዓዊ መብቱን በመረገጥ ድምጹን አፍኖ ግፍ ለሚፈጽምበት የኢትዮጵያ ህዝብ ድምጽ በመሆን የሚጮሁትን የዲያስፖራ ታጋዮች ዝም ለማሰኘት ዕቅድ ነድፎ በመንቀሳቀስ በተለይ በሃይማኖት ተቋማት ውስጥ ወኪሎቹንና ሰላዮቹን አስርጎ በማስገባት በዲያስፖራው ውስጥ አሉ የተባሉ ሃገር ወዳዶችና የሰብዓዊ መብት ታጋይ ኢትዮጵያኖች እያደኑ የተለያየ ጥቃት እንዲደርስባቸው ማድረግ አንዱ ዘዴው በመሆኑ በዚህ እድሜውን ሙሉ ለኢትዮጵያ ሕዝብ ሲጮህና ሲከራከር በኖረ ታጋይ ወንድማችን በወንድሙ መኰንን ላይ ለማድረስ የሚቃጣው ጥቃት የዚሁ አካል መሆኑን በመገንዘብ እነዚህ ስደተኛ በመምሰል ከስደተኛው ህብረተስብ ጋር በመቀላቀል የወያኔ የጥቃት መሣሪያ ሆነው በመሰለፍ በቤተ ክርስቲያንም ሆነ በሌላ ተቋማት የተሰገሰጉ ቅጥረኛ ባንዳዎችን መንጥሮ በማውጣትና በማጋለጥ ለድምጽ አልባው ሕዝባችን ድምጽ ሆነው የኖሩ ጀግኖቻችንን ከነሱ የጥቃት በትር መጠበቅና መከላከል ይኖርብናል። ኢትዮጵያ በክብርና በነጻነት ለዘላለም ትኑር!!

Sep 11, 2013

'' ትግሉን አለመቀላቀላችሁ ጊዜዉን ያረዝመዉ ይሆናል እንጅ ለዉጥ ከማምጣት አያግደንም ''እርዮት አለሙ

አንዲትን ወጣት ሴት መምህር ጋዜጠኛ ከእስኪሪቢቴ እና እንጀራ ውጭ በእጇ ይዛ የማታውቅ በቤተሰቦቿ በጓደኞቿ በስራ ባልደረባዎቿ የተከበረችና የተወደደች በህይወት ዘመኗ በምንም አይነት መጥፎ ተግባር ላይ ተሳትፋ የማታውቅ ምንም አይነት የወንጀልም ሆነ የክስ ሪከርድ የሌለባት ብዙ ጊዜዋን ከተማሪዎች ጋር እና ከምታስጠናቸው ህጻንት ጋር የምታሳልፍ፤ የቀረውን ጊዜዋን ደግሞ ስትታዘብ የዋለቻቸውን ስርዓቱ የፈጠራቸውን ችግሮች፤ ስለ ህግ የበላይነት መጓደል፤ ስለዜጎች እኩልነት፤ ስለ አደርባይነት፤ ስለ እምነት ነፃነት… በድፍረትና በሀቀኝነት ስትከትብ ታሳልፋለች፡፡ መምህርና ጋዜጠኛ ርዕዮት አለሙ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ በእንግሊዘኛ ቋንቋ እና በቲያትሪካል አርት ሁለት ድግሪ ያላት ሲሆን፤ በአሁኑ ሰዓት በቃሊቲ እስር ቤት አስከፊ የእስር ጊዜ እያሳለፈች ነው፡፡
ይሄ መቼም የሚተቻቸውን በሰበብ በአስባቡ ማሰር የአምባገነኖች መለያ በመሆኑ ከልጅቱ ጥንካሬ አንጻር አይደንቅም፡፡ የሚገርመው ከ5 ወር በፊት ርዕዮት በጠና ታማ በነበረበት ሰዓት ማረሚያ ቤቱ ወደህክምና ቦታ ለመውሰድም ሆነ መድሀኒት ለማቅረብ ፍቃደኛ አለመሆኑ ብዙዎቻችንን አስደንግጦን ነበር፡፡ ዛሬ ደግሞ ከእናቷ ውጭ ማንም እንዳያያት ከልክለዋል፤ ለዚች ወጣት ሴት ይሄ ሁሉ ጭካኔ ለምን?
ዛሬ በርዕዬት ላይ እየተፈጸመ ያለውን ግፍ እያየን አንዳንዶቹ አልሰማንም አላየንም ብለን ቁጭ ፤ አንዳንዶቻችን እግሬ አውጪኝ ብለን ሸሽት፤ አንዳንዶች እስከመጨረሻው አብረው ቆመዋል፡፡ ዛሬ ግን የሁላችንንም ድምጽ ከያለንበት መስማት ትፈልጋለች፡፡ ቢያንስ ቢያንስ ታስራ እንኳ ሰብአዊ መብቷ ሊከበር ይገባል፡፡
ርዕዮት ከማንም የተለየ የዚህችን ሀገር ሀላፊነት የመሸከም እዳ የለባትም፤ የእኛን ሁሉ እዳ ነው የተሸከመችው!

የሼኽ ኑሩ ወንድ ልጅ በእስር ላይ እንደሚገኝ ተነገረ! (ድምፃችን ይሰማ)

September 8, 2013

 
የእስሩ መንስኤ ‹‹አባቴን የገደለው መንግስት ነው!›› በማለቱ ነው ተብሏል!
ከሁለት ወራት በፊት በሰው እጅ ሕይወታቸው የጠፋው ሼኽ ኑሩ ወንድ ልጅ በመንግስት ደህንነቶች ታፍኖ ተውስዶ መታሰሩ ተሰማ፡፡ በደሴ አረብ ገንዳ አካባቢ ነዋሪ የነበሩትና መንግስት ለፖለቲካ ጥቅም ሲል ገድሏቸዋል ተብሎ በስፋት የሚታመነው ሼኽ ኑሩ ወንድ ልጅ በመንግስት ደህንነቶች ታፍኖ ከተወሰደ በኋላ አሁን ያለበት ቦታ በውል መታወቅ አልቻለም፡፡ እንደ አከባቢው ምንጮች ከሆነ የሼኽ ኑሩ ልጅ የታሰረው ከአባቱ ግድያ ጋር በተያያዘ ‹‹አባቴን ያስገደለው መንግስት ነው!›› በሚል በዙሪያው ላሉ ሰዎች በመናገሩ ነው ተብሏል፡፡ ይህ ወጣት ተመሳሳይ እስር ሲያስተናግድ ለሁለተኛ ጊዜ ሲሆን ከጥቂት ሳምንታት በፊትም ተመሳሳይ ንግግር በመናገሩ በደህንነቶች ለቀናት ታፍኖ ከተወሰደ በኋላ ማስፈራሪያና ምክር ተለግሶት ተፈቷል፡፡ ሆኖም ከተፈታ በኋላም የመንግስት ደህንነቶች ያስጠነቀቁትን ‹‹ከአሁን በኋላ አባቴን መንግስት አስገድሎታል እንዳትል!›› የሚል ምክር ጥሶ በመገኘቱ ለድጋሚ እስር ተጋልጧል፡፡
መንግስት ከሼኽ ኑሩ ግድ ጋር በተያያዘ ለሳምንታት የዘለቀ ከፍተኛ የፕሮፖጋንዳ ዘመቻ ሲያካሄድ መቆየቱ የሚታወቅ ሲሆን በዚህ ዘመቻ ኢሕአዴግ ውስጥ ያሉ ፓርቲዎችን ጨምሮ በርካታ የመንግስት ተቋማት መግለጫ በማውጣት ከፍተኛ የሚዲያ ሽፋን ለመስጠት ተሞክሯል፡፡ በተጨማሪም በበርካታ የገጠር ከተሞች በተሌም በአማራ ክልልና ደቡብ ወሎ ‹‹ሕዝቡ የሼኽ ኑሩን ግድያ እንዲቃወም›› በሚል የግዳጅ ሰልፍ እንዲወጣ ከመደረጉም በላይ ‹‹ግድያውን የፈጸሙት ሙስሊሞች ናቸው›› በሚል ‹‹መንግስት እርምጃ ይውሰድ!›› የሚል መልእክቶች በተከታታይ በመንግስት ሚዲያዎች ሲያሰራጭ ነበር፡፡ ሆኖም ከሼኽ ኑሩ ግድያ ጋር በተያያዘ ሙስሊሙ ኅብረተሰብ ምንም ንክኪ እንደሌለውና ሙስሊሙ ኅብረተሰብ የሚያደርገው ተቃውሞ ፈጽሞ ይህን መሰል ጸየፍ ድርጊቶችን የሚስተናግድበት መርህ እንደሌለው በማስረገጥ፤ በዋነኝነትም የእንቅስቃሴው መርህ የሆነው ‹‹የምንሞትለት እንጂ የምንገድልበት አላማ የለንም›› መፈክር ተደጋግሞ ተጠቅሷል፡፡ ሙስሊሙ ህብረተሰብም በሃይል እርምጃዎች የማያምንና የሚሰነዘርበትን ዱላ በጸጋ ከመቀበል ውጪም አጸፋ የሰጠበት አጋጣሚ እንደሌለ በአስረጂነት ቀርቧል፡፡
አሁን የት እንደታሰር በውል የማይታወቀውና ከቤተሰብ ጋር እንዳይገኛኝ የታቀበው የሼኽ ኑሩ ወንድ ልጅ የገለጸው ሀሳብ አብዛኛው ህብረተሰብ የሚያምንበትና በተለይም በደሴ ከተማ ሕዝብ ዘንድ ግድያውን መንግስት እንደፈጸመው በስፋት የሚታወቅ እውነት ነው፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞም በተለያዩ ወቅቶች ከሼኅ ኑሩ ግድያ ጋር በተገናኘ የመንግስት ረጅም እጆች መኖራቸው የሚያመላክቱ መረጃዎች ወጥተዋል፡፡ ሼኅ ኑሩ ከመንግስት ሀላፊዎች ጋር በቅርበት ሲሰሩ የቆዩ ቢሆንም በሞታቸው የመጨረሻ ወቅቶች ግን ከአካባቢው አስተዳደር ሀላፊዎችና የጸጥታ ሹሞች ጋር በአካሄድና መርህ ላይ ባለመስማማታቸው ስብሰባ ረግጦ እስከውጣትና ዳግም አብሮ የመስራት ፍላጎት እንደሌላቸውም ሲገልጹ ነበር፡፡ መንግስት ሞታቸውን ተከትሎም የአስከሬን ምርመራ እንዳይደረግና የቀብር ስነ ስርአቱ በአፋጣኝ እንዲፈጸም በማስደረግ የግድያው ሁኔታ ተሸፋፍኖ እንዲቀር ለማድረግ ጥረት አድርጓል፡፡ የሼህ ኑሩ ግድያ ‹‹በመንግስት የተፈጸመ ድራማ ነው›› ሲል ሕብረተሰቡ ደጋግሞ መግለጹ ይወሳል፡፡