አባ ግርማ ከበደን ከጌይ ጋር ሰልፍ ያስወጣ እዉነት ይህ ጽሁፍ ብቻ ነዉ???
December 26, 2012
በዶ/ር ወንድሙ መኮንን
ቀን፡ 25.12.2012
ቀን፡ 25.12.2012
ርዕሰ አድባራት ለንደን ደብረ ጽዮን ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን ከዘረኛው የወያኔ አገዛዝ ተጽዕኖ የጸዳች፤ በUK ለሚገኘው ስደተኛ የእምነቱ ማዕከልና ኢትዮጵያው ጭምር ናት!!
አደጋ ላይ ነች፤ አድኑኝ ትላለች
የዘመናት ታሪክ ባለቤትና ከትውልድ ወደ ትውልድ በመተላለፍ፤ ወደፊትም ለዘለዓለም የምትኖር የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን እውነተኛ የክርስቶስ ማደሪያ የምትባለው ዛሬ ኖሮ ነገ ለማይኖረው አምባ ገነንና ዘረኛ አገዛዝ መሣሪያ ሳትሆን ከተበደለውና መብትና ነጻነቱን ከተገፈፈው የኢዮጵያ ሕዝብ ጎን መቆም የቻለች እንደሁ ብቻ ነው።
ላለፉት 21 ዓመታት ይህንን እውነተኛ ክርስቲያናዊ ሥራ ተግባራዊ በማድረግ ከወያኔ ተጽዕኖ ነጻ በመሆን በዓለም ሁሉ ተዘርቶ ለሚገኘው ኢትዮጵያዊ መኩሪያና መመኪያ ተበለው ከሚጠቀሱት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ርዕሰ አድባራት ለንደን ደብረ ጽዮን ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን አንዷ ነች።
ኢትዮጵያ ውስጥ የተንሰራፋው ዘረኛው የወያኔ አገዛዝ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መንፈሳዊ የበላይ፤ ሕግ አውጪና ወሳኝ የሆነው የቅዱስ ሲኖዶስን መንፈሳዊ ዓላማና ውሳኔ በሥራ ላይ እንዳይውል፤ እውነት የሚናገሩ አባቶችን በማስፈራራት፤ በማስደብደብ፤ በጠመንጃና በደህንነት ኃይል በማስገደድ በሃገሪቱ የመንግሥት መዋቅር ውስጥ እንደሚፈጸመው ሁሉ በቤተ ክህነትም ሆነ በየአብያተ ክርስቲያኑ ወሳኝ በተባሉ ቦታዎች ሁሉ የአገዛዙን የጎሳ አባላትና ደጋፊዎች በመሰግሰግ ቤተ ክርስቲያንም የዘረኛ አገዛዝን ሥርዓትን ተከትላ እንድትዋቀር አድርጓት እንደሚገኝ ይፋ ከሆነ ወራትና አመታት ተቆጥረዋል።
የዘረኛው ቁንጮ የሆኑት መለስ ዜናዊና አባ ጳውሎስን ሞት ቢወስዳቸውም ዘረኛው ሥርዓት በቅድስት ቤተ ክርስቲያን ላይ የሚያደርገው ተጽዕኖና መከፋፈል በከፋ ሁኔታ ቀጥለ እንጂ ሲሻሻል አልታየም።
ለንደን ደብረ ጽዮን ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን ላለፉት 21 ዓመታት በአባ ጳውሎስ አማካኝነት የተቃጣባትን የወያኔን አገዛዝ ጣልቃ ገብነት በሙሉ በመመከትና በመከላከል በዘረኛው አገዛዝ አቀነባባሪነት በጅማ፤ በአሩሲ፤ በአሰቦትና በሌሎችም ቦታዎች በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንና በተከታዮቿ ላይ ጥቃት ሲደርስ ማንንም ሳትፈራ በነፃነት ድርጊቱን አጋልጣለች፤ ተቃውሞዋን ለዓለም አሰምታለች፤ አቅም በፈቀደም ለተጎዱት ክርስቲያኖች ድጋፍ አድርጋለች።
በቅርቡም የዋልድባ ገዳም በአገዛዙ ሲደፈርና ሲጠቃ፤ መነኮሳት ሲታሰሩና ሲሰቃዩ ሌሎች እንግሊዝ ሃገር ያሉ በወያኔ አገዛዝ ጫና ሥር ያሉ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያናት ፀጥ እረጭ ሲሉ ቤተ ክርስቲያናችን ግን በድፍረትና በነፃነት ታላቅ ሰላማዊ ሰልፍ በማካሄድ አገዛዙ በእምነት ውስጥ ጣልቃ በመግባት የሚፈጽመውን በደል አጋልጣለች ተቃውሞዋንም ለዓለም አሰምታለች።
ይህ የቅርቡ ትዝታ ሲሆን እንደ አውሮጳ አቆጣጠር በ2005 ዘረኛው የወያኔ አገዛዝ ወንድ ሴት ሳይለይ ህጻን ወጣት፤ ጎልማሳና አዛውንት ሳይቀር በአሰቃቂ ሁኔታ በጨፈጨፈበት ወቅት ቤተ ክርስቲያናችን ከፍተኛ ተቃውሞ ከማሰማት ባሻገር በአገዛዙ የተገደሉት ኢትዮጵያኖች እንደ ሰው ሳይሆን እንደ ውሻ ተቆጥረው ፍትሐትም ሆነ ጸሎት አይደረግላቸው ተብሎ በአባ ጳውሎስ አማካኝነት ሲታገድ ለንደን ደብረ ጽዮን ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን ግን በግፍ ለተገደሉት ኢትዮጵያኖች መሉ ጸሎት አድርጋለች።
ከዚህም በማስከተል ብጹ ወቅዱስ በማለት የአባ ጳውሎስ ሥም በቤተ ክርሲያኗ ውስጥ አይጠራም በማለት ቤተ ክርስቲያኗ የወሰደችውን የጠራ የአቋም ባሉት ሚዲያዎች ተጠቅማ ለዓለም ሁሉ አሳውቃለች። ይህንን ተከትሎ በቤተ ክርስቲያኗ ውስጥ የነበሩ የዘረኛው ወያኔ አገዛዝ ደጋፊዎች ቤተ ክርስቲያኗ ውስጥ ለሞቱት መጸለዩንና በአባ ጳውሎስ ላይ የተወሰደውን አቋም በመቃወም ከቤተ ክርስቲያኗ ተለይተው ስላሴ ቤተ ክርስቲያንን ሊያቋቁሙ ችለዋል።
የተፈጠረው የአቋም ልዩነት እንጂ የሃይማኖት ልዩነት ባለመሆኑም በአንድ ሃይማኖት ጥላ ሥር ሆኖ በአቋም ልዩነት ሕዝብ ከህዝብ ከሚቃቃርና ከሚናቆር ተለያይቶ ማምለኩ መፍትሔ ሰጪ ሊሆን ችሏል።
በእርግጥ ርዕሰ አድባራት ለንደን ደብረ ጽዮን ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን እ.አ.አቆጣጠር በ1993 የዘረኛ ሥርዓት አራማጅ ተወካይ የሆኑት አባ ጳውሎስ የቤተ ክርስቲያኗ አባላት ሳይጋብዟቸው መጥተው በማሳፈርና በማዋረድ መልሳ አባራቸዋለች ያም ሆኖ ግን የአባ ጳውሎስን ስም ብጹዕ ወቅዱስ ብላ ትጠራ ስለነበር መልሰን በእጃችን እናገባታለን በሚል ተስፋ የተለያዩ የተንኮል ሙከራዎች ይደረግባት ነበር እንጂ በለየለት ጠላትነት ተፈርጃ የከፋ ጥቃት ሳይሰነዘርባት ቆይታ ነበር።
እ.አ. አቆጣጠር ከ2005 በኋላ ግን ቤተ ክርስቲያኗ በመንበረ ፓትርያርኩኗ በአባ ጳውሎስ በለየለት ጠላትነት ተፈርጃ በርካታ ቀጥተኛና ተዘዋዋሪ ጥቃት የደረሰባት ሲሆነ ከዚህም ውስጥ የማይዘነጋው ቤተ ክርስቲያኗ የምትገለገልበትን ህንፃ ቤተ ክርስቲያን ለመግዛት ሕዝበ ክርስቲያኑ ገንዘብና ጉልበትን በማስተባበር ደፋ ቀና ሲል በአባ ጳውሎስ የተፈረመና ከመንበረ ፓትሪያርክ ለእንግሊዝ ቤተ ክርስቲያን በተጻፈ ደብዳቤ ቤተ ክርስቲያኑ በእንግሊዝ ሃገር በስደት ላይ ለሚገኙ ኢትዮጵያዊያን እንዳይሸጥላቸው የወጣው ማገጃ ነው።
ይህንን ማገጃ ግን በስደት ላይ ያለው ሕዝበ ክርስቲያን እንዲሻር በማድረግ የቤተ ክርስቲያኑንና በግቢው ውስጥ የሚገኘውን የቪካሬጅ ህንፃ በ£1.700.000 (አንድ ሚሊዮን ሰባት መቶ ሺህ ፓውንድ) በመግዛት የስደተኛው ኢትዮጵያዊ ዘላለማዊ ሃብትና ቅርስ እንዲሆን አድርጎታል።
ይህንን ሕዝብ ጥሮና ግሮ ያፈራውን ቅርስ ነው ዛሬ አባ ግርማ ከበደና (በግራ) መሪጌታ ዓለማየሁ ደስታ (በቀኝ) በተባሉ ካህናት አስተባባሪነት ቤተ ክርስቲያኗም ሆነች ሃብትና ንብረቷ
የቅዱስ ሲኖዶስና የመንበረ ፓትርያርክ ነው በማለት በቅዱስ ሲኖዶስ ስም ለዘረኛው የወያኔ አገዛዝ ሥርዓት አራማጆች በኤምባሲ አማካኝነት ለማስረከብ ከፍተኛ ትግል በማድረግ ላይ የሚገኙት።
ይህንን የክህደት ተግባራቸውን የቤተ ክርስቲያኗ አባላት እንዳማይደግፉት ሲረዱ የወያኔ ሥርዓት ደጋፊ የሆኑ ሰዎችን በተለያየ ዘዴ ወደ ቤተ ክርስቲያኗ በመጥራት የቤተ ክርስቲያኗ አባላት በብዛት እንዲዋጡና እየተስፈራሩ ከቤተ ክርስቲያን እንዲባረሩ በማስደረግ ላይ ይገኛሉ።
የኢትዮጵያ ሕዝብ ሰብዓዊ መብቱ በወያኔ ተረገጠ፤ ፍትሕ በኢትዮጵያ ጠፋ፤ ዘረኝነትና የአንድ ጎሳ የበላይነት በኢትዮጵያ ነገሰ፤ የሃገር ሃብትና ንብረት በዘረኞች እጅ ወደቀ እያልክ የምትቆረቆርና ድምጽ ለሌለው የኢትዮጵያ ሕዝብ ድምጽ የሆንክ ሁሉ ዘረኛው ወያኔ ከኢትዮጵያም አልፎ በጥቂት ካህናትና ደጋፊዎቻቸው አስተባባሪነት እዚህ እንግሊዝ ሃገር የሚገኘውን የስደተኛው ኢትዮጵያዊ ንብረትና ቅርስ ሊወርስ እየጣረ ነውና አንዳችም ማመንታት ሳታደርግ ወደ ቤተ ክርስቲያን በመምጣት በተለመደውና በምትታወቅበት ወኔ ወያኔን አዋርደህ እንድታባርር ቅድስት ማርያም ጠርታሃለችና አታሳፍራት!!
ላለፉት 21 ዓመታት ከዘረኛው የወያኔ አገዛዝ ተጽዕኖ ነፃ አድርገህ በነፃነት እንዳኖርካት ዛሬም ቤተ ክርስቲያንህ በጥቂት የግል ጥቅም አሳዳጅ ካህናት አማካኝነት በወያኔ ደጋፊዎች እጅ እንዳትወድቅ መጥተህ ታገልላት።
የፊታችን አሑድ 30/12/12 ክቀኑ ሰምንት ሰአት፤ በቤተ ክርስቲያናችን ውስጥ ዓዲስ አመራር ኮሚቲ ለመምረጥ ስብስባ ጠርተዋል። ስሞኑን ብዙ የማናውቃቸው ስወች ወደ ቤተ ክርስቲያናችን መምጣት ጀምረዋል። ይህም ‘አባላትን” ሕጋዊ ባልሆነ መንገድ በማብዛት፤ ቤተ ክርስቲያናችንን፤ ንብርተዋንና አስትዳደርዋን፤ አሳልፎ፤ ለወያኔ፤ ለመስጠት ነው። ስለዚህ፤ በእለቱ ተገኝታችሁ፤ ቤተ ክርስቲያናችሁን አድኑ። ወደፊትም በቤተ ክርስቲያናችን ውስጥም ሆነ ከቤተ ክርስቲያናችን ውጭ በሚደረጉ ስብሰባዎች ላይ ተገኝታችሁ፤ርዕሰ አድባራት ለንደን ደብረ ጽዮን ቅድስት ማርያምን አድኑ!!!
No comments:
Post a Comment