May 23, 2013

ከሰማያዊ ፓርቲ የተሰጠ ማብራሪያ l ሕገ ወጥነት ከዓላማችን አይገታንም!!!

Submitted by Admin on Thu, 05/23/2013 - 16:44

ከሰማያዊ ፓርቲ የተሰጠ ማብራሪያ
ሕገ ወጥነት ከዓላማችን አይገታንም!!!
ሕግ ምን ይላል?
አዋጅ ቁጥር ፫/፲፱፻፹፫ ዓ.ም
ስለ ሰላማዊ ሰልፍና ሕዝባዊ ስብሰባ ሥነ ሥርዓት የወጣ አዋጅ፤ ሰላማዊ ሰልፍ የጠራው አካል ስላለበት ግዴታ በአንቀጽ ፬ ላይ እንዲህ ይላል
አንቀጽ ፬፤የማሳወቅ ግዴታ፤
፩/ ሰላማዊ ሰልፍ ወይም ህዝባዊ የፖለቲካ ስብሰባ የሚያዘጋጀው ማንኛውም ግለሰብ፣ ቡድን ወይም ድርጅት የታሰበው ሰላማዊ ሰልፍ ወይም ሕዝባዊ የፖለቲካ ስብሰባ ከሚካሄድበት ጊዜ ቢያንስ ከ፵፰ ሰዓታት በፊት በጽሑፍ የማሳወቅ ግዴታ አለበት፡፡
፪/ የማሳወቂያው ጽሑፍ ሰላማዊ ሰልፉ ወይም ሕዝባዊ የፖለቲካ ስብሰባ በከተማ ከሆነ የሚደረገው ለከተማው አስተዳደር ጽ/ቤት፤ ከከተማ ውጭ ከሆነ ለአውራጃው አስተዳደር ጽ/ቤት ይሆናል፡፡
መልስ ሰጪው አካል የከተማ ወይም የአውራጃው አስተዳደር ጽ/ቤት ያለበትን ግዴታና ኃላፊነት አንቀጽ ፮ ላይ እንዲህ ብሎ ደነግጋል፡፡
አንቀጽ ፮፤ የከተማው ወይም አውራጃው አስተዳደር ጽ/ቤት ኃላፊነት፣
፩/ ከተማው ወይም የአውራጃው አስተዳደር ጽ/ቤት የሰላማዊ ሰልፍ ወይም ሕዝባዊ የፖለቲካ ስብሰባ ጥያቄ በጽሑፍ ሲቀርብለት ሰላምን ከማስፈን ጸጥታን ከማስጠበቅና የሕዝቡን ዕለታዊ ኑሮ እንዳይሰናከል ከማድረግ አንጻር አስፈላጊውን ዝግጅት ሁሉ የማድረግ ኃላፊነት አለበት፡፡
፪/ ከተማው ወይም የአውራጃው አስተዳደር ጽ/ቤት በዚህ አዋጅ አንቀጽ ፮ ንዑስ አንቀጽ ፩ የተመለከቱትን ሁኔታዎች በማገናዘብ ሰላማዊ ሰልፉ ወይም ሕዝባዊ የፖለቲካ ስብሰባ በሌላ ጊዜ ወይም በሌላ ሥፍራ ቢደረግ ይሻላል የሚል አስተያየት ካለው ምክንያቱን በመግለጽ ይህንኑ ጥያቄው በደረሰው በ፲፪ ሰዓት ውስጥ በጽሑፍ ለአዘጋጁ ማሳወቅ ኃላፊነት አለበት፡፡ ሆኖም የከተማው ወይም አውራጃው አስተዳደር ጽ/ቤት ሰላማዊ ሰልፉ ወይም ሕዝባዊ የፖለቲካ ስብሰባው ምን ጊዜም በየትኛውም ቦታ ሊካሄድ አይችልም ማለት አይችልም፡፡
ምን ተደረገ?
ሰማያዊ ፓርቲ የጠራውን የተቃውሞ ሰልፍ ማወቅ የሚገባው በአዲስ አበባ ማዘጋጃ ቤት የሰላማዊ ሰልፍና የህዝባዊ ስብሰባ ማሰወቂያ ቢሮ እንዲያውቅ የሚያደርግበትን ደብዳቤ ግንቦት 14 ቀን 2005 ዓ.ም ከጧቱ 4፡00 ሰዓት የተጠቀሰው ቢሮ ድረስ አቅርቧል፡፡ የቢሮው ኃላፊ ደብባቤ አልቀበልም በማለታቸው ከሰዓት በኋላም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ላይ ደብዳቤውን እንደገና አቅርቦ አሁንም አልቀበልም በማለታቸው ጉዳዩ ይመለከታቸዋል የተባሉ የተለያዩ አካላት እስከ ከንቲባው ፅ/ቤት ኃላፊና የካቢኔ ጉጋዮች ምክትል ኃላፊ ድረስ በመሄድ ደብዳቤውን እንዲቀበሉ ቢጠየቁም “ደብዳቤ እንዳንቀበል ከበላይ ታዘናል” በማለት በቃል ተመሳሳይ የአንቀበልም መልስ ሰጥተዋል፡፡ ከብዙ ጥረት በኋላ ከፓርቲው በኩል ሦስት ሰዎች ከማዘጋጃ ቤቱ ደግሞ ሦስት ሰዎች የአይን ምስክርነት ባሉበት በሰላማዊ ሰልፍና የህዝባዊ ስብሰባ ማሰወቂያ ቢሮ ኃላፊ ጠረጴዛ ላይ አስቀምጠው ወጥተዋል፡፡ ከዚህም በጠጨማሪ ደብዳቤው በፖስታ ቤት በኩል በሪኮመንዴ እንዲደርስ ተልኳል፡፡
ምን ይደረጋል?
ሰማያዊ ፓርቲ በሕግ የተቋቋመ ህግ የሚያከብር ፓርቲ ነው፡፡ ፓርቲው የሚገዛው ለህግ እንጅ ለውንብድና ባለመሆኑ ሰልፉን በዚህ መልኩ ለማሰናከል የማይቻል መሆኑን የሚመለከታቸው አካላት ሁሉ እንዲያውቁት ማሳሰብ ይፈልጋል፡፡ ሰልፉን ለማድረግ እስከ አሁኗ ሰዓት ድረስ በህግ በኩል የጎደለ አንድም ቅንጣት ነገር ባለመኖሩ ሰልፉ በታቀደው ቦታና ስዓት የሚካሔድ መሆኑን ያሳውቃል፡፡
ግንቦት 15 ቀን 2005 ዓ.ም
አዲስ አበባ

May 20, 2013

አቶ ገብረዋሃድ ማነው….የማይገፋ ቋጥኝ..! ስሮቹ በርካቶች..!



96e5c789d9b8bf3a9e86699e2b445aec_M
ገብሬ የጉምሩክ መንፈስ ነው፣የገቢዎች ቆሌ!!፣የደረቅ ወደብ ጂኒ፣ የገቢዎች ሾተል! የገበረዋህድ አይን በክፉ ያየችው አራሙቻ ነው! ተነቅሎ ይጣላል! ገብሬ የተከለውን ህዝቦች አይነቀንቁትም! የገብረዋህድ ቃል አይታጠፍም! ከሊቅ እስከ ደቂቅ የቃሉ አዳሪዎች ናቸው! ግን ምን ዋጋ አለው! በርካቶችን ቃሊቲ ያከተመች ወንበር ገብሬንም ቀላቅላዋለች፡፡ አቶ ገብረዋህድ በኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን የህግ-ማስከበር ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ነበር፡፡ ሰውዮው በባለስልጣን መ/ቤቱ የማይገፋ ቋጥኝ ነበር! ስሮቹ በርካቶች ናቸው! የዛሬን አያድርገውና አርጋጁ ብዙ ነበር! ከእነዚህ አርጋጆቹ መካከል ጥሩነህ በርታ፣አታክልቲ፣ተወልደ፣ተኽላይ… እያሉ በርካቶችን ይጠቅሣሉ የውስጥ ምንጮች፡፡ ግን አታክልቲ እዚያ ቤት ምን ይሆን ሥራው? አታክልቲ ለበርታ አመታት የባለስልጣን መ/ቤቱ የዘርፍ መዋቅር ውስጥ አይታወቅም ይሉቁንም በባለስልጣን መ/ቤቱ የኢህአዴግ አደረጃጀት ተጠሪ በመሆኑ ብቻ ከ7000 ብር በላይ እየተከፈለው የሚኖር ቅልብ ነው። እንዲያውም አንድ ወዳጄ እንደ ነገረኝ አትክልት ከዩኒቨርሲቲ ቀጥታ ባለስልጣን መስሪያ ቤቱን የሚቀላቀሉ እንስቶችን በጥሩ ቦታ ላይ እመድብሻለሁ ከረሜላ በርካታ እንስቶችን ጉድ የሠራ ጉደኛ ነው ብሎኛል፡፡ አንገቱን የውሻ ማሰሪያ በሚያክል የወርቅ ዘለበት አጊጦ ሁሌ ተፍ ተፍ ነው አሉ የአታክልቲ ነገር! ግን ለምን እስከ አሁን እንዳልታሠረ ግራ ገብቶናል ይላል ወዳጄ!
አቶ ገብረዋህድ ላይ መንግስት እርምጃ መውሰዱ ለባለስልጣን መ/ቤቱ ሠራተኞች ብቻ ሣይሆን የሰውየውን ቁልፍነት ለሚያውቁ ሁሉ ግርምትን ፈጥሯል፡፡ሠውየው በተለይም ከ2000 ዓ.ል ወዲህ ለበርካታ አዳዲስ ባለሀብቶችና ለአያሌ አዲስ ከሣሪ ነጋዴዎች መፈጠር ትልቁን ሚና ተጫውቷላ! ኢህአዴግ ለሚያከብራቸውና ለሚያደኸያቸው ነጋዴዎች አፈፃፀም ትልቅ አስተዋፅኦ ነበረውና! አየለ ደበላ፣ገብረኪዳን ሞሮኮ፣አቶ ከበደ፣አቶ ሌንጮ… ለእነዚህ ሁሉ በአራጣ መጥረቢያ ለወደቁት ዛፎች ሁሉ ቆራጭ መጥረቢያው ገብሬ ነበርና! ለዘመን አመጣሽ የትግራይ ባለሀብቶችም እድገትና እብሪት ዋናው ክንድ ገብረዋህድ ነው ይላሉ ባለስልጣን መ/ቤቱን በሀገሪቱ ኢኮኖሚ ላይ ያለውን ከፍተኛ የመበየን አቅም የተረዱ ሰዎች፡፡
ጊዜን የሚገለባብጥ የሆነው አላህ ፈቃድ ሆነና ዛሬ ገብሬ ቀን ዞሮበታል! እልፎችን በስኒ ቡና ቫት የማገደበትን ዘብጢያ ይጎበኝ ዘንድ ግድ ሆኗል፡፡ በስኒ ቡና ታሳሪዎች እንጅ በመልቲ ሚሊዮን አጭበርባሪ ነጋዴዎች ላይ የማይጨክነው ገብሬ በባለስልጣን መ/ቤቱ መለስን መስሎ፣መለስን ተከንድቶ፣አዜብን ክንድ አድርጎ የኖረ ይሉታል! የውስጥ ምንጮች፡፡ ገብረዋህድ ወቅት ያተበተው አምባገነን ነበር አሉ! በአንዳንድ መድረኮች ተናገራቸው ከተባሉት እና ከውስጥ ምንጮች የሠማሁትን እንሆ፡
በአንድ ወቅት የኮሚቴዎቻችን መታሠር ተከትሎ ባለስልጣን መ/ቤቱም እንደ ቀበሌዎቻችን ሁሉ በሃይማኖት አክራሪነት ዙሪያ ባደረገው ስብሰባ ላይ ገብሬ የመድረክ መሪ ሆኖ ያችን የመለስን አምባገነናዊ አዲስ ራዕይ በአምባገነን አንደበቱ እያደረቀና እያከረረ ሲያቀርብ የባለስልጣን መ/ቤቱ ሠራተኞች በተለይም ሙስሊሙ ክፉኛ ሞገቱት አሉ! እናማ ገብሬ “ለብዙሐኑ መብት ሲባል ትጨፈለቃችሁ!!” ሲል በማን አለብኝነት ጠረንጴዛውን እየደበደበ ይናገራል በዚህ ጊዜ አንጀታቸው የቆሠለው ሙስሊም ሠራተኞች አላህ ይጨፍልቅህ ሣይሉ አይቀርም መቼም ይሄው ኮሚቴው የተጨፈለቀበትን የስቃይ ማዕከል እሱም እንዲጨፈለቅበት ሆኗል፡፡
በሌላኛው ተመሣሣይ መድረክ ነው ደግሞ አሉ ሠራተኞቹ አንድ መቐሌ ዩኒቨርሲቲ የተማረ ሙስሊም ወንድማችን በመቐሌ ዩኒቨርሲቲ በሚማርበት ወቅት አንድ መምህሩ ክፍል ውሥጥ “እኔ እንዴት ማስተማር እችላለሁ እነ አህመድ፣እነ መሬማ፣እነ ሙሐመድ፣እነ ሠዓዳ እየበለጧችሁ እነሱ እየሰቀሏችሁ እንዴት ማስተማር እችላለሁ!!” ብሎ ልጁ በሚማርበት ክፍል መናገሩ “ከአንድ የዩኒቨርሲቲ መምህር የማይጠበቅ መሆኑንና ይህ አይነቱ የዘቀጠ አስተሳሰብ ሙስሊም ተማሪዎች በዩኒቨርሲቲዎች ውሥጥ ለሚደርስባቸው መገለል እና ትንኮሳ ማሳያ ነው ይህ የእኔ መምህር እኔ ባለሁበት ክፍል የተናገረው ነው” ብሎ ገብረዋህድን ይጠይቃል፡፡ገብረዋህድ ንግግሩ ጭቃ ነው! ሲናገር ዘር ካልጎተተ አይሆንለትም ይላሉ ሠራተኞቹ። እናማ ገብረዋህድ ምን ብሎ መለሰለት መሠላችሁ “ይህ አባባል ምናልባት ትግሬ ወደ መቀሌ አማራ ወደ ቀበሌ ከሚሉት እንዱ ትመስለኛለህ!!” ብሎ ወንድማችንን የሚያሸማቅቅ መልስ መለሰለት አሉኝ!! መቐለ ዩኒቨርስቲን ስለጠቀሰ ብቻ ይህን መልስ ምናመጣው ጎበዝ?
ጎበዝ!ብቻ ብዙ ነው የዚያ ቤት ጉድ አሉ እናማ መላኩና ገበረዋህድ አይንናናጫ ናቸው አሉ! መላኩ የበላይ ቢሆንም ዙፋኑ ግን የገብሬ ነው፡፡ ገቢዎች ሄደህ ገብረዋህድ ማነው ብትል “የመለስ ሾተል!” ይሉኃል፡፡ አለፍ ብለህ ከጠየቀክም “የአዜብ ማሣላጫ!” ይልሃል አንዱ የገቢዎች ተገፊ! አልበቃህ ብሎ ጥያቄ ከጨመርክም “ ገብረዋህድ እኮ ጋዜጦች የማያውቁት የመለስ እጅ ነው!” ይሉኃል አየህ ወያኔዎች አራሙቻቸውን የሚነቅሉት በገብረዋህድ ጸረ-አራሙቻ ኬሚካል ነው! ወንበራቸውን የሚተክሉትም፣ኤፈርትም ሆነ ሌሎች ዘመን አመጣሽ ዘውግን መሠረት ያደረጉ ባለሐብቶች የሚደልቡትም ሆነ እኔና እንተን በቀኝ አዙር የሚገዙን በገብረዋህድ ይሁንታ ነው! እንዴት? ብለህ ከጠቅክ ቀሽም ነህ! የኢትዮጵያ ኢኮኖሚና የባለሐበቶቿ ሎተሪ የሚቆረጠው በገብረዋህድ ቢሮ ነው እያልኩህ ነው! ታዲያ አሉ ሰውየው የሟቹ መንፈስና የባለቤታቸው ትልቅ ድጋፍ ነበራቸው አሉ! እንዴት? ብለህ ከጠየቅክ የመላኩንና የገብሬን አለመግባባት የሚያውቁ ውስጥ አዋቂዎች “መላኩ በአዋጅ ምክትሎቹን የመመልመልና በጠ/ሚኒስቴሩ የማስሾም ስልጣን ቢኖረውም እዚያ ቤት የሚሾሙ ምክትሎች ግን በግብሬና በአዜብ ይሁንታ ነው ይሉኃል፡፡”
ታዲያ ሰሞኑን የፀረ-ሙስናው አሊ ሡለይማንም ሆኑ የሙት መንፈስ አምላኪ ተብለው የተናቁት የአሁኑ ጠ/ሚኒስቴሩ በዚህች ኦፕሬሽን ጥርስ ማብቀል መጀመራቸውንና በተለይ በገብሬና በኔትወርኮቹ ላይ የተወሰደውን እርምጃ በማድነቅ ብዙዎች “ይበል!” የሚያስብል እርምጃ ብለውታል! ግና ምን ዋጋ አለው! ሁሉን ነገር ከሟቹ ሰውዮ ጋር ካላጣቡ የማይሆንላቸው ኢህኤደጎች ኦፕሬሽኑን አከሸፉት እንጅ! አየህ ይህ ኦፕሬሽን በአንድ ወገን የአሁኑን ጠ/ሚኒስቴር ዝና ከፍ የሚያደርግ ሲሆን በሌላ ወገን ደግሞ “አባይን የደፈረ ጀግና!” ብለው የስዘመሩለት መለስ ገብረዋህድን መድፈር አቅቶት ነበር የሚል ትርጉም ይሰጣል! አለፍ ብሎም ገብረዋህድ ከቤቱ ካርታ ብዛት የተነሣ በአጥሚት ካርታውን ቢያቀጣጥሉት አንድ አንስተኛ ጎጆ ይሠራ ነበር እኮ! የተባለለትን ህገ-ወጥ ሐብት ሲሰበስብ የሟቹ ጠ/ሚኒስቴር አብሺር ባይነት ነበር! የሚል የውሥጥ መረጃ ይወጣል! ታዲያ ሟቹ ጠ/ሚኒስቴር የኢትዮጵያችን መስራችና አባት ተደርጎ ሌጋሲ ምና ምን በሚባልበት ዘመን እንዲሁም እንደ እመቤቴ ማርያም ምስል በየካድሬ ቤቱ ማዕዘን ላይ ተሰቅሎ፣ በዘመንኛ ባለሐብቶች ቢሮ ጠረንጴዛ ላይ የመለስ ፎቶ በትልቁ ምስል ተቀምጦ ከርቤና እጣን በሚጨስለት ዘመን ይህች ጉድ ከወጣች ምን ሊፈጠር እንደሚችል የተገነዘቡት ወያኔዎችና አጋሮቻቸው በአሊ ሠሉይማን አንደበት ያስተላለፏት መልዕክት በልሳናቸው ሪፓርተር ጋዜጣ “የሰሞኑ የፀረ-ሙስና ጥናት በቀድሞው ጠ/ሚኒስቴር ትዕዛዝ” ነው ተብሎ እንዲዘገብ ተደረገ! ይች እንግድህ አንድም የአሁኑን ሰውዮ ስም መቃናት ለመመቅኘት ሁለትም የአቤቶ መለስን ተመላኪነት ላለማጉደፍ ሲባል መሆኑ ነው!
ገብሬ በኢተቪ አፍ በክፉ ከመግባቱ ሁለት ሣምንት ቀደም ብሎ መለስ ፃፋት ያላትን “የተሀድሶው መሥመርና የኢትዮጵያ ህዳሴ” የተሰኘች መፅሀፍ መሠረት አድርጎ የቪዲዮ ኮንፈረንስ ለባለስልጣኑ ሠራተኞች ሲያሰለጥን እኛ እንደ ደርግ “እምቢ ላለ ሰው ጥይት አጉርሰው!” እያልን አንገዛም ሲል ነበር አሉ። አሁንስ ምን ይል ይሆን? እንጃ! የመለስ መሞትን ተከትሎ የባለስልጣኑን አዳዲስ ሰራተኞች ሲያሰለጥን “በዚህ ሠዓት በዚህ ደቂቃ የመለስ ልጆች ሜዳ ላይ ናቸው! የአንድ ጠ/ሚኒስቴር ልጆች አንዲት ቤት እንኳን ሣይኖራቸው!” እያለ መድረኩን በ ሣቅ እንባ አራጭቶት ነበር አሉ! እሲኪ አሁን ከዚያ ሁሉ የቤት ካርታ አንዱን ቢሠጣቸው ምናለበት! ኧረ እንዲያው ቢያከራያቸው እንኳን! ያሳዝናል! በአህለ ሡና ወልጀማዓው ፕሬዝዳንት ትእዛዝ ፊርደውስ ውሥጥ ያለው መሌ! ይህን ስግብግብነት ቢሰማ በእውኑ ምን ይል ይሆን? እንደ ታምራት ላይኔ “ስኳር የጣለው ተጋዳላይ” ይለን ይሆን ወይስ “የመንግስት ሌቦች!!” እያለ አትስረቁ እያለ ያስዛርፈን፣ያሰዘርፈን ይሆን?………. ***ገብሬ የመለስ ሾተል! ግን እውነት ነው!!*** አጅሬ ገብረዋህድ ሳይሆን ገብረ ዜናዊ ነበር!

May 15, 2013

Høy temperatur på Etiopia-debatt




Både utviklingsminister Holmås og Høyres Peter Gitmark viste stortengasjement i debatten på Litteraturhuset mandag.


Utviklingsmandag: Lokalene var fylt til randen. Det er mye engasjement i det etiopiske miljøet i Norge. Flere av tilhørerne holdt opp plakater med krav om at den norske regjeringen blir tøffere i forholdet til Etiopiske myndigheter. Det var også veldig mange som ønsket å stille spørsmål direkte til ministeren og til Høyres Peter Gitmark som varsler endringer i norsk Etiopia-politikk om hans parti kommer til makten etter høstens valg.

Diskusjonen fortsatte: Da Utviklingsfondet dro fra Litteraturhuset,
 to timer etter at debatten var ferdig, 
satt ministeren fortsatt å diskuterte
 med engasjerte norsk-etiopere.
Kritisk til regimet
Noe som har blitt debattert i det siste og som også var sentralt under mandagens debatt er hvordan Norge burde forholde seg til etiopiske myndigheter.
Både Heikki Holmås og Peter Gitmark uttalte seg kritisk til det etiopiske regimets åpenbare menneskerettighetsbrudd.
- Jeg vil se en tøffere linje fra norske myndigheter. Det går i feil retning i Etiopia, ved valget i 2005 ble kun én representant fra opposisjonen valgt inn. Etiopias donorer har nedprioritert menneskerettigheter, sa Peter Gitmark.
Høyre har tidligere varsla at de ønsker å kutte i bistanden til Etiopia. Under gårsdagens debatt utdypet Gitmark tidligere uttalelser og sa at det først og fremst er støtten til offentlige velferdsgoder og støtten til energi Høyre vil kutte.
- Støtte som går gjennom den etiopiske stat blir brukt som symbol på at omverden støtter det etiopiske regimet, sa han.
Også energiutbygging har denne effekten ifølge Gitmark.
- Når du får tilgang på energi får du automatisk sympati for regjeringen. I 2005 ble det installert en rekke solcellepaneler. I ettertid ble denne forbedringen bruk om og om igjen som et bevis på at omverden støtter det etiopiske regimet. Og det ble truet med at støtten ville forsvinne dersom det etiopiske regimet ikke fikk beholde makten.
- Høyre vil støtte den etiopiske befolkningen og ikke regimet. Vi vil lære av diasporaen og ha med diasporaen i kontakten med regimet, fortsatte han.
- Det var en god oppklaring. Det har tidligere hørtes ut som om Høyre vil kutte all støtte til Etiopia svarte Holmås.
Også han var tydelig på at det er noen klare dilemmaer når man gir bistand til Etiopia.
- Vi ønsker ikke å støtte regimet, men å trekke seg helt ut vil ramme mange.
Både Holmås og Gitmark har selv besøkt Etiopia.
 Bildet er fra Holmås besøk på et av Utviklingsfondets prosjekter
 i landsbyen Semre i Tigray i mai i fjor. Foto: Trond Viken, Utenriksdepartementet.



Hvilke rettigheter?
Holmås pekte på balansen mellom politiske og økonomiske rettigheter. Å prioritere politiske rettigheter høyest er ikke alltid riktig. Dersom Norge og andre bistandsaktører kutter støtten til Etiopia kan det hindre oppfyllelsen av for eksempel retten til mat var hans budskap.
Det var tydelig at den etiopiske disporaen satte pris på å få møte representanter for både den sittende og en mulig fremtidig regjering. Og debattiveren var gjensidig. To timer etter at debatten offisielt var ferdig satt utviklingsminister Heikki Holmås fortsatt å diskuterte med etiopisk diaspora.
Stemmen fra Etiopia
I panelet satt også Dr. Million Belay, Direktør for Movement for Ecological Learning and Community Action (MELCA). MELCA er en av Utviklingsfondets partnerorganisasajoner i Etiopia og driver miljøsensitive utviklingsprosjekter i landet. Belay hadde også noen oppfordringer til de norske politikerne.
- Jeg tror ikke sanksjoner vil virke. Spørsmålet om man skal gi bistand til Etiopia burde ikke kobles med andre spørsmål.
Han hadde også noen tanker om prioriteringer i bistanden.
- Jeg vil råde norske politikere til å satse på utvikling av elektrisitet.
Takk for en god debatt!

ለህይወታችሁ ሳትፈሩ ይህንን መረጃ የሰጣችሁ ሁሉ የአገር ጀግኖች ናችሁ፤ አሁን አትታወቁም። አሁን ልንገልጻችሁ አንችልም። ጊዜና ወቅት ጀግንነታችሁን እስኪገልጹት ግን አትረሱም

አኢጋን ታሪካዊ ያለውን ሰነድ አተመ!

"ባይዘመርላችሁም ጀግኖች ናችሁ"

በቦታው ላይ ሆናችሁ ለህይወታችሁ ሳትፈሩ ይህንን መረጃ የሰጣችሁ ሁሉ የአገር ጀግኖች ናችሁ፤ አሁን አትታወቁም። አሁን ልንገልጻችሁ አንችልም። ጊዜና ወቅት ጀግንነታችሁን እስኪገልጹት ግን አትረሱም። ልትረሱም አትችሉም። ብዙ ባይነገርላችሁና ባይዘመርላችሁም ታላቅ ስራ ሰርታችሁዋልና ክብር ይሁንላችሁበማለት አቶ ኦባንግ ሜቶ ምስጋና ያቀረቡለት ታሪካዊ ሰነድ ታተመ።

የስርዓቱ ላንቃ ስር ሆነው የህይወት ዋጋ በመክፈል መረጃ የሰጡትን ወገኖች የአክብሮት ምስጋና በማቅረብ በሚመሩት የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ ስም ለጥናቱ ተባባሪዎች ሁሉ ክብር እንደሰጡ የዘገበው የጋራ ንቅናቄው ለሚዲያ ባሰራጨው የፕሬስ ሃተታ ላይ ነው። ንቅናቄውበኢንቨስትመንት ስም የሚፈጸም የመሬት ነጠቃ፤ በኢትዮጵያበሚል ርዕስ ተተርጉሞ መታተሙን ይፋ ባደረገበት ዜናው ይህ ታሪካዊ ሰነድ ለመጪው ትውልድ በቅርስነት የሚቀመጥ እንደሆነ አመልክቷል።

ኢህአዴግ እዚህ ግባ ሊባል በማይችል ሳንቲም እየቸበቸበው ያለው የአገሪቱ ብቸኛ ሃብት መሬት አስመልክቶ ለዜጎችና ለተለያዩ አበዳሪ ተቋማት የሚቀርበው መረጃ የተሳሳተና ተራ ፕሮፓጋንዳ ላይ የተንጠለጠለ መሆኑንን የሚያጋልጠው ጥናት ከእንግሊዝኛ ወደ አማርኛ ተመልሶ መታተሙን ያወሳው አኢጋን የመሬት ነጠቃ ላይ ጥልቅ ጥናትና ምርምር ለማካሄድ ለሚፈልጉ ዜጎችና ዓለምአቀፍ ተቋማት ያመች ዘንድ መረጃዎችን ወደ አንድ ቋት ማሰባሰቡን አስታውቋል።

የኦክላንድ ተቋምና ለአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ በጋራ ያዘጋጁት ጥናታዊ ጽሁፍ፣ የጋራ ንቅናቄው ከእንግሊዝኛ ወደ አማርኛ የመለሰው ትርጉም ጥናትና ተመሳሳይ የመሬት ወረራ መረጃዎች ይተላለፉበት ዘንድ (Land Grab –http://landgrabsmne.wordpress.com/) የሚባል ብሎግ እንዲሁም በፌስቡክ Land Grab/መሬት ነጠቃ የሚባል መክፈቱን ይፋ አደርጓል። በተለይም ድረገጹ ደረጃው ተሻሽሎ እንደሚቀርብ አመልክቷል።

የጋራ ንቅናቄው በአማርኛ የተዘጋጀው ጥናት አገር ቤት ያሉ ወገኖች ያነቡት ዘንድ ሁሉም ወገኖች በሚችሉት መልኩ የማሰራጨት ሥራ እንዲሰሩ ጥሪ አስተላልፏል። በማያያዝም ጽሁፉን የሚጠቀሙ ወገኖች፣ ሚዲያዎች፣ ድርጅቶች፣ ተቋማትም ሆኑ ማናቸውም ወገኖች ጽሁፉን ላዘጋጀው አኢጋን አስፈላጊውን የዕውቅና ህጋዊ ዋጋ እንዲከፍሉ አሳስቧል። ህጋዊ ዋጋውም ምንጭን በግልጽና በትክክል የመግለጽ ሃላፊነት እንደሆነ አመልክቷል። ይህ ሳይሆን ቀርቶ ጽሁፉን የራሳቸው አድርገው ለማቅረብና የሌሎችን ድካም የግላቸው ለማድረግ ለሚፈልጉ ከዚህ ተግባራቸው እንዲታቀቡ ከወዲሁ መክሯል።

በኢንቨስትመንት ስም የሚፈጸም የመሬት ነጠቃ፤ በኢትዮጵያበሚል ርዕስ የታተመው ጥናታዊ ዘገባ እዚህ ላይ ይገኛል፡፡ አገር ቤት በሚደረገው የመረጃ አፈና ምክንያት ዘገባውን ከድረገጹ ላይ ለማግኘት የማትችሉ ሁሉ ብትጠይቁን በኢሜይ አድራሻችሁ እንልካለን፡፡

አኢጋን ያወጣውና ለሚዲያ አውታሮች ያስተላለፈው መግለጫ ሙሉ ቃል ከዚህ የሚከተለው ነው፡፡
==================
ለአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ (አኢጋን)
ግንቦት 5 2005ዓም
በኢንቨስትመንት ስም የሚፈጸም የመሬት ነጠቃ፤ በኢትዮጵያጥናት ትርጉም ይፋ ሆነ!!
በኢንቨስትመንት ስም የአገር ሃብትና ትውልድን እየበላ ስላለው የመሬት ነጠቃ አስመልክቶ የኦክላንድ ተቋምና ድርጅታችን ለአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ በጋራ ያዘጋጁት ጥናታዊ ዘገባ ይፋ ሆነ። የጋራ ንቅናቄያችን ዋና ዳይሬክተር ጥናቱ በትክክለኛ ጭብጥ ላይ ተመስርቶ እንዲዘጋጅ ለህይወታቸው ሳይሳሱ መረጃ በመስጠት ለተባበሩ ዜጎችታላቅ ክብር ይሁንላችሁ። አሁን አትታወቁም። ግን ከቶውንም አትረሱም። ክብር ለማትታወቁት ግን ለማትረሱት የአገር ጀግኖችበማለት ምስጋና አቅርበዋል።

ኢህአዴግን በደፈናው መቃወምን ዓላማው ያላደረገው ይህ ጥናታዊ ዘገባ ዜጎችን ካደጉበት፣ ከኖሩበት፣ ከቀያቸው፣ ከህልውናቸው፣ ከርስታቸው፣ ወዘተ ያለ አንዳች ውይይት፣ ምክክርና ንግግር በማፈናቀል ለውጪ ኩባንያዎችና ለራሱ ለባለጠመንጃው አገዛዝ ሰዎችና ባለሟሎች መሬት ማከፋፈሉን በማስረጃ ያሳያል። የራሱ የኢህአዴግ አካላትም በሪፖርቱ ውስጥ በአግባቡ ድምጻቸው ተካትቷል። የሚጠቀሙባቸው አዋጆችና ህጎችም አልተዘለሉም።

የውጪ ባለሃብቶችና ኩባንያዎች ወደ አገር ውስጥ መግባታቸው ለቴክኖሎጂ ዝውውር፣ በአገሪቱ ያለውን የምግብ እጥረት ለማስወገድ ይረዳልየሚሉ ምክንያቶች እያቀረበ ያለው ኢህአዴግ በተግባር ሲፈተሽ ተግባሩና ዓላማው ምን እንደሆነ የሚያመለክተው ጥናቱ የስርዓቱ ሰለባዎች፣ የኢህአዴግ ባለስልጣናት፣ ኢንቨስተሮች፣ ጉዳዩ የሚመለከታቸው ክፍሎች፣ የቅርብ ምስክሮች፣ የተለያዩ ከዓለምአቀፍ ተቋማት የተገኙ መረጃዎች፣ አገዛዙ ራሱ ይፋ ያደረጋቸው መረጃዎችና ለጥናቱ አስፈላጊ የተባሉ አኻዞች የተካተቱበት በመሆኑ እውነታውን ህዝብና ማናቸውም ወገኖች እውነቱን ለመረዳት ያስችላቸዋል ተብሎ በጉልህ ታምኖበታል።

በምሳሌ ለማሳያነት የተጠቀሰው የሳዑዲ ስታር ኩባንያ የሚያመርተውን ሩዝ ደብረዘይት በገነባው ተቋሙ አማካይነት ሩዙን የመለየትና ለኤክስፖርት የማዘጋጀት ስራ ይሰራል። የተመረጠውና መለኪያውን የሚያሟላው ሩዝ ኤክስፖርት የሚደረግ ሲሆን፣ ደቃቃውና በሚሊሜትር ተለክቶ ለኤክስፖርት ደረጃ የማይበቃው አገር ቤት እንዲቀር ይደረጋል። ከዚህ አንጻር እንኳ ቢታይ የመሬት ኢንቨስትመንት የተባለው ዓለም ጠንቅቆ ለሚያውቀው የአገራችን የምግብ እጥረት ችግር መፍትሄ ሊሆን አይችልም። በጥናቱ ዝርዝር ጉዳዩ አለ።

ኢህአዴግ በፖለቲካው ውድማ ላይ ቆሞ የሚያወራውና በተግባር የሚሆነውን እውነት ከሰለባዎቹ አንደበት በመቅዳት ሊስተባበል በማይችልበት ደረጃ ያቀረበው ጥናት፣ ዜጎች ከቀያቸው ከመፈናቀላቸው በፊት ምክክርና የስነልቦና ዘግጅት እንዲደረግ ጊዜ እንደሚሰጥ በህግ የተደነገገ ስለመሆኑ፣ ነግር ግን እውነታው የተገላቢጦሽ መሆኑንን ጥናቱ በማስረጃ ያትታል። ዜጎች ነገ ስለሚሆነው እንኳ ሊያውቁ በማይችሉበት ደረጃ ማለዳ ካረፉበት ሲነቁ ዶዘር ማሳቸውን፣ የጓሮ አትክልታቸውን፣ የኑሯቸው መሰረት የሆነውን ደናቸውን፣ ቤታቸውን ሲጠርግ እንደሚያዩ እነዚሁ መከረኞች ለህይወታቸው ሳይሳሱ መናገራቸውን ጥናቱ ትኩረት ሰጥቶ አቅርቦታል።

የመሬት ካሳ እንኳ ባግባቡ የማያገኙት ወገኖች በራሳቸው አንደበት፣ በግብር የደረሰባቸውንና ከፊት ለፊታቸው ያለውን አደጋ አስመልክቶ በዝርዝር ሚዛናዊ በማድረግ ያቀረበው ጥናት ኢህአዴግ ለማስተባበል ከፈለገ በዜናና በተራ ጩኸት ሳይሆን በመረጃ የተደገፈ፣ ሁሉንም ወገኖች ያካተተ ሚዛናዊ ሪፖርት ካቀረበ ብቻ ለአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ (አኢጋን) በማስተባበያነት እንደሚቀበለው አስቀድሞ ለመግለጽ ይወዳል።

በአገርና በግለሰብ ደረጃ መረጃ ለማዳረስ፣ በተመሳሳይ ኢህአዴግ የሚያሰራጨውን የሃሰት ፕሮፓጋንዳ ማጋለጥ፣ የሰብአዊ መብት ጥሰቱን ማሳየት፣ የተሳሳተውን ፖሊሲ ማስቀየር ዋናው የጥናቱ ዓላማ ነው። በጥናቱ በቀረበው ጭብጥ መሰረት የዓለም ባንክ፣ ወዳጅ አገሮች፣ አበዳሪ አገሮች ፖሊሲ አውጪዎች ወዘተ አካሄዳቸውን እንዲመረምሩ ለማስቻል ሰፊ ስራ የተሰራ መሆኑንን በዚህ አጋጣሚ እንጠቁማለን። በተለያዩ አጋጣሚዎች የተለያዩ የውጪና የአገር ውስጥ ሚዲያዎች እንደዘገቡት ሰፊ ስራ የተሰራ ቢሆንም፣ በዋናነት የጉዳዩ ባለቤት የሆነው የኢትዮጵያ ህዝብ ምን እየተሰራ እንደሆነ ሲረዳ ትግሉን ማቅለል፤ ውጤቱንም ማቅረብ ይቻላል የሚል እምነት አለን።

በዚህና በሌሎችም ተዛማጅ ምክንያቶች በከፍተኛ የሃላፊነት ስሜት፣ ረዥም ጊዜ ተወስዶ የተሰራው የትርጉም ሰራ ሰውን የሚያክል ክቡር ፍጥረት ከማደሪያው እንዲወጣ ተደርጎ እንዴት ወደ ጉድጓድ እንደሚወረወር ለመጪው ትውልድ በታሪክነት፣ አሁን ላለነው በመረጃነት፣ ከሁሉም በላይ ከጩኸትና ከመረጃ አልባ ክስ የምናገኘው ጥቅም አለመኖሩን በመረዳት አቋቋምን ለማስተካከል ይረዳል፣ ታላቅ ምሳሌም ይሆናል ብለን እናምናለን።

ጥናቱን በማሰራጨትና ዜጎች እጅ እንዲደርስ በማድረጉ በኩል የሁሉም ወገኖች ያልተቆጠበ ጥረት እጅግ አስፈላጊ እንደሆነ ለመግለጽ እንወዳለን። በዚህ አጋጣሚ እናወጣዋለን ብለን ካሰብንበት ጊዜ በማለፍ ተጨማሪ ሳምንታት በማዘግየታችን ታላቅ ይቅርታ እንጠይቃለን፡፡ በአገራችን ካለው የመረጃ አፈና አኳያ የጥናቱ መጠን ሰብሰብና አጠር ባለ መጠን በኢሜይል እንደሚሰራጭ ሆኖ በአዲስ መልክ ሲቀናበር ተጨማሪ ሳምንታትን መውሰዱ የግድ ሆኗል፡፡

የጋራ ንቅናቄያችን ጽሁፉን የማሰራጨቱ ስራ በጨዋነት፣ ለጽሁፉ ባለቤቶች (ለእንግሊዝኛው የኦክላንድ ተቋም ለአማርኛው ደግሞ አኢጋን) አስፈላጊውን እውቅና በመስጠት እንዲሆን በዚህ አጋጣሚ አበክረን እንሳስባለን። ከመሬት ነጠቃ በላይ የከፋ ወንጀል የለም። ዜጎችን በምድራቸው ወደ ባርነት የሚያሸጋግረው የመሬት ነጠቃ የአገሪቱን ሃብትና ንብረት እየበላ ነው።

ይህንን ወደር የሌለው ወንጀል ለማጋለጥ፣ ለመታገል፣ ለመቃወምም ሆነ ተዛማጅነት ያላቸው ተግባራት ለማከናወን ለሚፈልጉ ተቋማት፣ ግለሰቦችና ሚዲያዎች ይረዳ ዘንድ (Land Grab – http://landgrabsmne.wordpress.com/) የሚባል ብሎግ እንዲሁም በፌስቡክ Land Grab/መሬት ነጠቃ መከፈቱን ለማሳወቅ እንወዳለን።

በቅርቡ የሚሻሻለው ይህ ብሎግና የፌስቡክ ገጽ ከመሬት ወረራ ጋር በተያያዘ ሁሉም ዓይነት ማስረጃዎች የሚታተሙበት ስለሚሆን መረጃ ለሚፈልጉ ወገኖች ሁሉ መልካም አጋጣሚ ይሆናል። ጥናታዊ ዘገባውን ከድረገጻችን ላይ ለማግኘት እዚህ ላይ ይጫኑ፡፡ በኢሜይል ለማግኘት የሚፈልጉ በሙሉ በሚከተለው አድራሻ (media@solidaritymovement.org) ቢጠይቁን በቀጥታ የምንልክ መሆናችንን እናሳውቃለን፡፡

በመጨረሻም የጋራ ንቅናቄያችን ዋና ዳይሬክተር ለተርጓሚው ከሁሉም በላይ ግን የስርዓቱ ላንቃ ስር ሆነው የህይወት ዋጋ በመክፈል መረጃ ለሰጡት ወገኖች የአክብሮት ምስጋና አቅርበዋል። አቶ ኦባንግ በመልዕክታቸውበቦታው ላይ ሆናችሁ ለህይወታችሁ ሳትፈሩ ይህንን መረጃ የሰጣችሁ ሁሉ የአገር ጀግኖች ናችሁ፤ አሁን አትታወቁም። አሁን ልንገልጻችሁ አንችልም። ጊዜና ወቅት ጀግንነታችሁን እስኪገልጹት ግን አትረሱም።

ልትረሱም አትችሉም። ብዙ ባይነገርላችሁና ባይዘመርላችሁም ታላቅ ስራ ሰርታችሁዋልና ክብር ይሁንላችሁብለዋል፡፡
ለአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ
የሚዲያና ሕዝብ ግንኙነት ግብረኃይል