Jan 30, 2013

ሻዕቢያው በረከት ህወሃትን ሊነዱት ይሆን?


የአቶ በረከት ስምዖንና የአቶ ስብሃት ነጋ የደፈጣ ውጊያ ገሃድ መውጣቱን የሚያመላክት መረጃ ይፋ መሆኑን ተከትሎ በህወሃት መንደር ውስጥ ከፍተኛ መደናገጥ ተፈጥሯል። ጉዳዩን የሚከታተሉ እንደሚሉት ልዩነቱን ለማርገብ በከፍተኛ ደረጃ ጥረት ቢደረግም ሊሳካ አልቻለም።
ከፍተኛ ስልጣን የያዙትንና አቶ መለስ ለመተካካት ያዘጋጇቸውን አዳዲስ አመራሮች፣ በቅርቡ ደንብና ህግ በመጣስ ሹመት የሰጡዋቸውን ጨምሮ የሰራዊቱን አዛዦችና ደህንነቱን ከጎናቸው ያሳተፉት ክፍሎች የተፈጠረው ልዩነት እልባት ማግኘት ይገባዋል የሚል አቋም መያዛቸውን የሚጠቁሙ ክፍሎች እነማን ተለይተው እንደሚመቱ ለመገመት አስቸጋሪ መሆኑንን ይገልጻሉ።
“ፓርቲያችን ከእንጥሉ በስብሷል” በማለት ከዛሬ አስራአንድ ዓመት በፊት በአገር ክህደት ሊያስወግዷቸው የተነሱትን ጓዶቻቸውን የረቱት መለስ የተጠቀሙበት ዋንኛ ስልት አባይ ጸሃዬን “ከውህዳኑ” ጋር በማሰለፍ ነበር። ዛሬ ለህወሃትና ለትግራይ ህዝብ በትግርኛ ቋንቋ ተጽፎ ተሰራጨ የተባለውና ይህንኑ መረጃ ዋቢ በማድረግ ኢየሩሳሌም አርአያ በተለያዩ ድረገጾች ይፋ እንዳደረጉት አቶ አባይ ጸሐዬ የተመደቡት ወጥመዱ ከተጠመደባቸው ዘንድ ነው።
“ድርጅትህ ኢህአዴግ እስከዛሬ ታግሎ እዚህ አድርሶሃል። በተለይም የሁሉም ነገር አድራጊና ፈጣሪ የሆነው ባለ ራዕዩን መሪህን በቅርቡ አጥተሃል” የሚል የአምልኮ መሪ ቃል ያለበት የጥሪ ወረቀት “ተቆርቋሪ ለሆናችሁ የትግራይ ተወላጆች በሙሉ” በማለት ጥሪ አቅርቧል። ኢየሩሳሌም አርአያ ቃል በቃል በትምህርተ ጥቅስ አኑረው ባሰራጩት በዚህ ጉልህ ዜና “እነ አቶ በረከት፣ ወ/ሮ አዜብ፣ ቴዎድሮስ ሃጎስ” ወረቀቱን አዘጋጅተው እንዳሰራጩ ያስረዳል።
በኢየሩሳሌም አርአያ ዜና ላይ እንደተመለከተው እነ አቶ ስዩም መስፍን፣ አባይ ጸሐዬ፣ አለቃ ጸጋዬ ከነባለቤታቸው የትግራይን ህዝብ ለጠላት ለመስጠት በዝግጅት ላይ መሆናቸውን ያወሳል።  “… የኔ የምትላቸው ጅቦች ተነስተውብህ ይገኛሉ” የተጠቀሱትንና ሌሎች ደጋፊዎቻቸውን “ጅቦች” ሲል የሚጠራው መልዕክት፣ “… ከእኛ ኋላ የተፈጠሩና ራሳችን ያሳደግናቸው ሲጠናከሩ ድርጅታችን ግን እየተዳከመ በመሄድ ላይ ነው” ሲል ያሳስባል። እነማን እንደሆኑ በግልጽ ሳይዘረዘር “የተወገዱ ግን በመጥፎ ጎዳና ያልተሰማሩን መልሰን ወደ ፓርቲው ማስገባት አለብን። ይህ ካልሆነ ግን የህዝብ ትግል አውላላ ሜዳ ላይ ጅብ በልቶት ሊቀር ነው ከጠላቶቻችን ጋር እንታረቅ እያሉን ነው” የሚል ማስጠንቀቂያ ያስቀምጣል። በስተመጨረሻ  “ከጀርባ ሆኖ የዚህ አፍራሽ ዋና ቀያሽ መሃንዲስ ስብሃት ነጋ መሆኑን ደርሰንበታል” ይላል።
“የኢህአዴግ ስኬት የመስመር እንጂ የግለሰብ አይደለም” በማለት የመለስን አምልኮ ለመቃወም ቀዳሚ የሆኑት አቶ ስብሃት ኤፈርትን ለወ/ሮ አዜብ ካስረከቡ በኋላ ከድርጅቱ ጋር ያላቸው ግንኙነት የላላ መሆኑን ለማሳየት እንደ ሩቅ ተመልካች አስተያየት ሲሰጡ ባብዛኛው ባልተለመደ መልክ ይዛለፉ ነበር። በተለይም አቶ በረከትን የማኮሰስና ምናምንቴ አድርጎ የማሳየት ስልት ሲጠቀሙ ቆይተዋል። ይህ እንዳለ ሆኖ አለመግባባቱ ሊከሰት ግድ እንደሆነ አስቀድመው የተነበዩም ነበሩ።
“… መለስ ስለሌሉ የወንበር ቡቅሻው የማይቀር ነው። በድርጅቱ አመራሮች ዘንድ የሌባና ፖሊስ፣ የሃይል ሚዛንና ቅኝት፣ አሰላለፍን የማሳመር ሰልፍ እየታየ ነው፤ … የመለስ ማለፍ በድርጅቱ ውስጥ ታፍኖ የቆየውን ቁርሾ ማፈንዳቱ አይቀርም…” ሲሉ ኦክቶበር 25 ቀን 2012 ለጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ ቃለ ምልልስ የሰጡት አሁን በትምህርት ላይ የሚገኙ የኢህአዴግ ሰው፣ የኢህአዴግ ድልድይ ተሰብሯል፤ የጋራ ነጥብም የለውም ብለው ነበር።
አውራምባ ታይምስ በበኩሉ ምንጩን አዲስ አበባ በማለት በተመሳሳይ የህወሃትን አደጋ ውስጥ መውደቅ ሲያበስር በስም ከዘረዘራቸው አመራሮች መካከል አቶ ስብሃት ነጋን አልጠቀሰም። ኢየሩሳሌም አርአያ አቶ በረከት የሚዘውሩትና የእነ ወ/ሮ አዜብ መስፍን ወገን በዋናነት ለመምታት ያሰበው አቶ ስብሃት ነጋን እንደሆነ ለአባላት ተበተነ የተባለውን የማስጠንቀቂያ ወረቀት በመጥቀስ ይገልጻል።
አውራምባ ታይምስ “እያጣራሁ አቀርበዋለሁ” በማለት ያወጣው ትኩስ ዜና ለህወሃት አባላት ተሰራጨ የተባለውን ደብዳቤ “ማን እንደጻፈው አልታወቀም” በማለት ብዥታ የሚያጭር መልክት ሲያስተላልፍ፣ ኢየሩሳሌም አርአያ ከአውራምባ ድረገጽ ባለቤት አቶ ዳዊት ከበደ በተለየ መልኩ ዜናውን በትነው አስረድተዋል። በሁሉም በኩል እንደተጠቀሰው ህወሃት ቀውስ ውስጥ ተነክሯል።
በየካቲት ወር በሚደረግ ድርጅታዊ ግምገማ ጠራርገው እንደሚያስወግዷቸው እንደ ከባድ ሚዛን ቦክስ ቀጠሮ በመያዝ እነ አቶ ስብሃት፣ ስዩም፣ አባይና አለቃ ጸጋዬን በመጥቀስ የተሰራጨው  ወረቀት በስተመጨረሻ ስብሃት ነጋ ላይ ክርኑን አስደቁሶ እንደሚያበቃ የህዋሃትን ጓዳ አስመልክቶ በተደጋጋሚ ለየት ያለ ዜና የሚያስነብቡት ኢየሩሳሌም አርአያ ያበቃሉ።
ከጎልጉል ጋር ቃለ ምልልስ አድርገው የነበሩት የኢህአዴግ ሰው ይህንን ዜና አስመልክተው ምን አስተያየት እንዳላቸው ጠይቀናቸው ነበር። “በሌሎቹም አቻ ድርጅቶች ውስጥ በተመሳሳይ ይህ ሁኔታ ይከሰታል። የመበስበሱ በሽታ ሁሉም ዘንድ ነው” በማለት መልሳቸውን ይጀምራሉ። ለጊዜው ደኢህዴንና ብአዴን አንድ ላይ መሆናቸውን ያስታወቁት እኚሁ አስተያየት ሰጪ የኦህዴድ አቋም አለመጥራቱን ነው የሚናገሩት።
“የድጋፉ ጉዳይ የፎርሙላ ነው። ዶ/ር ደብረጽዮንና በረከት ስለላውን፣ ጦር ሃይሉን፣ የፖሊስና የልዩ ሃይሉን ሙሉ በሙሉ ስለተቆጣጠሩት በአሸናፊነት እንደሚወጡ ጥርጥር የለውም” ካሉ በኋላ አቶ ስብሃት ሰሞኑን “አማራውን ከሰደብኩ እኔ ታምሜያለሁ ማለት ነው ሆስፒታል መሔድ አለብኘኝ” በማለት የሰጡት መግለጫ ሲዘልፉትና ሲረግሙት የኖሩትን አማራና ብአዴንን ተለሳልሶ ለመቅረብ ያደረጉት እንደሆነ በተዋረድ ለብአዴን አባሎች መገለጹን እንደሚያውቁ አስረድተዋል።
“ምንም ተባለ ምን በመከላከያውና በደህንነቱ ሃይል ተጠቅመው የፈለጉትን መወሰንና የማስወሰን፣ ባላቸው በሚሰራው የፖለቲካ መዋቅር እስከታች መመሪያ በማውረድ የእነ በረከት ወገን ባለድል እንደሚሆን ጥርጥር የለውም። ቀድሞ ታጋይ የነበሩ፣ የደህንነት ሃይሉን እየረዱ ብር የሚያመርቱ ግርግሩ ስለማይመቻቸው ሃይል ካለው ወገን ጋር በመሆናቸው እነ ስብሃትን ያቀላጥፏቸዋል። ይህ ሁሉ የሚሆነው ግለሂስ አድርገው አርፈው ለመቀመጥ ካልተስማሙ ብቻ ነው” በማለት አስተያየታቸውን ይደመድማሉ፡፡
ይህንን መረጃ በሚያጠናክር መልኩ ከዚህ በፊት ከጻፍናቸው ዜናዎች መካከል አቶ በረከትና አቶ ሃይለማርያም የመለስ የቅርብ ሰዎች መሆናቸውንና አቶ መለስ ወደ ውጪ ሲወጡ የሥልጣኑን ቁልፍ የሚሰጡት ለአቶ በረከት እንደሆነ፤ የአቶ ሃይለማርያም ሹመት መነሻውም በዚሁ ቀደም ሲል በተፈጠረ “የቤተሰብ መሰል” ግንኙነት መሆኑን በመናገር ስማቸው ሳይጠቀስ ቃላቸውን ለአሜሪካ ድምጽ ሬዲዮ የሰጡ የኦህዴድ ሰው ጠቅሰን መጻፋችን የሚታወስ ነው፡፡ አቶ መለስ በሞቱ ማግስት ከኢህአዴግ ምክርቤት እና ከፓርላማው ውሳኔ በፊት አቶ ሃይለማርያም ጠ/ሚ/ር ሆነው እንደሚቀጥሉ በመናገር የተጠባባቂ ጠ/ሚ/ርነት ሥልጣን ይዘው እንደሚሠሩ አቶ በረከት በወቅቱ በሰጡት ቃለምልልስ መናገራቸው የሚታወስ ነው፡፡ አቶ ሃይለማርያም ለፎርማሊቲ በፓርላማ ፊት ቀርበው ምህላ እንደሚፈጽሙ አቶ በረከት በግላቸው በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ መናገራቸው ይህንኑ ቤተሰባዊ ግንኙነት የሚያጠናክር መሆኑን መዘገባችን የሚጠቀስ ነው፡፡

Jan 29, 2013

ህወሐት ለሁለት ተሰነጠቀ፤ ወረቀት ለአባለት ተበተነ


ዛሬ በመቀሌ ለአባላትና አልፎም ለህዝቡ በተበተነ የትግርኛ ፅሁፍ እነ ስዩም መስፍን፣ አባይ ፀሐዬ፣ ፀጋዬ በርሔ ከነባለቤታቸው
እንዲሁም ሌሎች ከድርጅቱ እንዲባረሩ በተበተነው መግለጫ ተጠቁሞዋል። በመግለጫው፥ ከጀርባ አሉ የተባሉትና « የዚህ መኅንዲስ»
ተብለው የተፈረጁት ስብሃት ነጋ እርምጃ እንዲወሰድባቸው ከተባሉት መካከል በዋነኛነት ተፈርጀዋል። እነ ቴውድሮስ ሃጎስ፣አዜብ
መስፍንና በረከት እጃቸው እንዳለበት የተነገረለት ይኸው መግለጫ ተከታዩን ይመስላል፤
«ተቆርቋሪ ለሆናችሁ የትግራይ ተወላጆ በሙሉ፤
«ድርጅትህ ሕወሐት እስከ ዛሬ ታግላ እዚህ ደረጃ አድርሰሃለች። በተለይም የሁሉም ነገር አድራጊና ፈጣሪ የነበረው ባለ ራዕይው መሪህ
በቅርብ ጊዜ አጥተኽል።
“ዛሬ እነዚህን ደካማ ጐኖች ተጠቅመው ለጠላት አሳልፈው ሊሰጡህ የሚፈልጉ ያውም ደግሞ የእኔ የምትላቸው ጅቦች ተነስተውብህ
ይገኛሉ። ይህንን ግልፅ ለማቅድረግ አሁን በቅርብ ጊዜ በመቀሌ የድርጅቱ ማ/ኰሚቴ ስብሰባ አካሄደን ነበር። በዚህ ስብሰባ ላይ ነው
እንግዲህ ተከታዩ ነገር የተነሳው። ይኽውም፥ እነ ስዩም መስፍን፣ አባይ ፀሐዬ፣ ፀጋዬ ከሚስቱ ጋርና ሌሎችም ያሉበት ይህን አሉ፤
«ድርጅታችን ጨርሶ ተዳክሞዋል። እኛ የኢትዮጲያ ሕዝብ ትግል መስራች ሆነን ሳለ ወደኋላ ተገፍትረን በአንፃሩ ሌሎች ከእኛ ኋላ
የተፈጠሩና ራሳችን ያሳደግናቸው ሲጠናከሩ ድርጅታችን ግን እየተዳከመ በመሄድ ላይ ነው። ባዛው መጠን ሕዝባችን እየተጎዳ ነው።
ስለዚህ አሁን ካጋጠመን አደጋ መውጣት ካለብን ከድርጅቱ -የተወገዱትን ግን በመጥፎ ጎዳና ያልተሰማሩትን መልሰን ወደ ፓርቲው
ማስገባት አለብን። ይህ ካልሆነ ግን የሕዝብ ትግል አውላላ ሜዳ ላይ ጅብ በልቶት ሊቀር ነው።» በማለት ከጠላቶቻችን ጋር እንታረቅ
እያሉን ነው።
“ሕዝባችን አስተውል። በዚህ አይነት ዳግመኛ በድርጅታችን ተኃድሶ እንደሚያስፈልገን ነው የተገነዘብነው። በሚቀጥለው የካቲት ወር
በሚካሄደው ጉባኤያችን ይህንን ጉዳይ ትኩረት ሰጥቶና አጥርቶ (ውሳኔ አሳልፎ) እንደሚወጣና እነዚህንና መሰሎቻቸው ከሚያራምዱት
አቋም ጋር ጠራርጐ እንደሚያስወግድልን ተስፋ እናደርጋለን። በዚህም እያንዳንዱ እንደከዚህ ቀደሙ የተለመደ አስተዋፅኦ (ሚና)
እንደሚያበረክት አንጠራጠርም።
በተጨማሪ ከጀርባ ሆኖ የዚህ አፍራሽ ዋና ቀያሽ መሃንዲስ ስብሃት ነጋ መሆኑን ደርሰንበታል።»
ከመቀሌ…..
ኢትዮሚድያ - Ethiomedia.com
January 28, 2013

Jan 28, 2013


TPLF ከመግደል ሙከራ ወደ ክስ



ኢሳት በትግራይ ሕዝብ የከፈተው የጥላቻ     /የጦርነት ዘመቻ በአስቸኳይ ያቁም    



የጽሑፉ ዓላም 
ሕዝብ በዙሪያው ምን እየሆነ እንዳለ ለማሳወቅ ተጻፈ። በተለይ ደግሞ ጥቂት ለማይባሉ ጊዜያት             
ደህና ረገብ ብሎ የነበረና ጎሳን ያማከለ ይፈጠሩ የነበሩ ግጭቶች እየተወገዱ ብዙሐኑ የኢትዮጵያ ሕዝብ ወደ መረዳት              
እየመጣበት ባለበት ሰዓት ይህ ከቅርብ ጊዜያት በፊት       "ኢሳት" የሚል ስያሜ ይዞ በነፃ ሚድያ ስም የተቋቋመው የትጥቅ ትግል አራማጅ ኃይሎች የፕሮፖጋንዳ ማእከል የሆነው ተቋም የልባቸውን ምኞትና ክፉ ሐሳብ  

 "ታማኝ ምንጮች እንዳሳወቁት፣ ውስጥ አዋቂዎች ለምናችን እንደገለጹት፣     ...” እየተባለ ከዚህም አልፎ ተልዕኮቸው የማይታወቁ በቆዳቸው ነጮች ዳሩ ግን ለኢትዮጵያ ሕዝብ የሞት መልዕክተኞች የሆኑ ግለሰቦች ፈረንጆች   "እንዲህ አሉ" እያለ በሕዝብ መካከል  ከሚዘራው መጥፎ ዘር የተነሳ ይኸው በቅርቡ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የተፈጠረውን ችግር ሁነኛ ምሳሌ ነው። እንዲህ  ያለ ድርጊት ደግሞ ዜጎች በዜግነትታችን የዜግነት ግዴታችን ካልተወጣን ነገ         "ኢትዮጵያ የሚልዋት ሀገር ነበርች    "  ተብሎ ከተረት ያለፈ ሀገር እንደማትኖር ልንጠራጠር አይገባንም። ከዚህም የተነሳ ጸሐፊው ይህን ጽሑፍ ተከትሎ በግላቸው  ከየትኛውም አቅጣጫ ሊመጣ ያለውንና የሚችለውን ማንኛውም ዓይነት ጥላቻና እክል ሳይበግራቸው በቁርጠኝነት  ለሀገራቸውና ለሕዝባቸው ያላቸውን ጽኑ ፍቅር ገልፀዋል።

በድጋሜ ይህ ድምጽ   : 
• ሰሜኑም ደቡቡም የሀገሪቱ ክፍል በቋንቋ፣ በነገድ፣ በባህል፣ በልዩ ልዩ ልማዶችና ወጎች አንዱን ከሌላውን            
ሳይለያይ በአንዲት ኢትዮጵያ የሚያምን ኢትዮጵያዊ ልብ ያለው ሕዝብ ሁሉ ድምጽ ነው።          
• ይህ ድምጽ:  ስለ ኢትዮጵያ ምድርና ስለ የኢትዮጵያ ሕዝብ መጻኢ የነፍሱን፣ አንድ ሰው ሰለ ጓዳው ቀዳዳ            
የሚጨነቀው ያክልም ስለ ሀገሩና ስለ ሕዝቡ ግድ የሚለው ኢትዮጵያዊ ሕብረተሰብ ሁሉ ድምጽ ነው።            • ይህ ድምጽ: የሚናገረውን የማያውቅ ፍሬ ከርስኪ ሁላ ፖለቲከኛ ስለ ሆነባት ሀገርና ዓይነ መርፌው ስለ ጠፋበት            
የኢትዮጵያ ፖለቲካ ሕመም የሚሰማው በር የተዘጋበትና በደጅ የቆመው ዜጋ ሁሉ ድምጽ ነው፣
• ይህ ድምጽ: በግልጽም በስውርም፣ በሰውም በእግዚአብሔር ፊትም፣ ስለ ሀገሩና ስለ ሕዝቡ ፊቱ የጠቆረ፣ ልቡ           
የተሰበረና በቆመበት ስፍራ ለሚያዩት ሁሉ ዓይኖቹ እንደ ተከፈተ መጽሐፉ የልቡን ሐዘን የሚያስነብቡና የሚናገሩ            
ኢትዮጵያዊ ሁሉ ድምጽ ነው    !! 
• ይህ ድምጽ:  በአንደበት ቃል ብቻ ሳይሆን ኢትዮጵያዊነቱ ከቃል በዘለለ እውነተኛ ሀገራዊ ፍቅር ያለው እንዲህ           
ባለ ክፉ ቀን   :  የኦሮምኛ ቋንቋ ተናጋሪ ሳለ ስለ ትግርኛ ቋንቋ ተናጋሪው ኢትዮጵያዊ ወገኑ ግድ የሚለው፣           
የአማርኛ ቋንቋ ተናጋሪ ግለሰብ    /ሕዝብ ሆኖ ሳለ ስለ ደቡብ ቋንቋ ተናጋሪ ሕዝብ የሚቆረቁረው እውነተኛ         … 
ሀገራዊ ፍቅር ያለው ኢትዮጵያዊ ዜጋ ሁሉ ድምጽ ነው።        
• እንዲህ ያለ እምነት   የትግራይ ክልል ተወላጅ ከሆነ ግለሰብ ብቻ የሚመነጭ እምነት ሳይሆን አሁንም እንዲህ ያለ           
ድምጽ የመላ ኢትዮጵያውያን እምነትና ድምጽ     ለመሆኑ ዕድል ከተሰጣቸው ጸሐፊው ነገራቸውን በዝግታ     
እንደሚከተለው ያስረዳሉ መልካም ንባብ።    


ሐተታ
ከተቋቋመ ሁለት ዓመታት ያስቆጠረ የጣቢያው መጠሪያ ስሙም ኢሳት በመባል የሚታወቀው በዋናነት በኢትዮጵያ           
ውስጥ ለውጥ የሚመጣ በጠመንጃና በጠመንጃ ብቻ ነው       ! ብሎ በሚያም ቀቢጸ ተስፋዎች የሚመራና ትግሉ እንመራለን      
የሚሉ ግለሰቦቹም  "መንግሥተ እግዚአብሔር" በሚያስረሳ፣ ኑሮ በሞቀበትና ነገር ዓለሙ ሁሉ በተደላደለበት ልጆቻቸውና       
ሚስቶቻቸው ይዘው የዓለማችን ምዕራቡ ክፍል በሆነ ምድር ከትመው ሲያበቁ በምስኪኑ ኢትዮጵያዊ ድሃና ረዳት አልባ             
ወጣት ሀገር ተረካቢ ዜጋ ህይወት ቀጥፈው፣ በደሙና አጥንቱም ተረማምደው፣ ደም አቃብተውና ሀገር ምድሩንም            
አተረማምሰው ምንሊክ ቤተ መንግሥት ዙፋን ላይ ቁጢጥ ብለው ተቀምጠው ያሹትን ሲፍልጡና ሲቆርጡ በህልም            
እየታያቸው ቅዠት ከሰው ልክና መልካም ጤንነት ያወጣቸው ግለሰቦች የሚያራምዱት የከሰረ የትጥቅ ትግል ፖለቲካ ኢሳት             እንደ ነሐሴ ዝናብ በነጋ በጠባ ቁጥር ሰፊ ሽፋን በመስጠት በኢትዮጵያ ምድር ጎሳ መሰረት ያደረገ አላስፈላጊ ግጭት               
እንዲቀሰቀስ ግንባር ቀደም የፕሮፖጋንዳ ማዕከል ሆኖ ሲሰራ ቆይተዋል። አሁንም በዚህ መሰረት በሌለውና በፈጠራ            
ሥራው አንድ ቀን በሕግ ፊት ከተጠያቂነት የማያመልጠበት ድርጊት ላይ ተጠምዶ ይገኛል።          
በተጨማሪም ይህ የትጥቅ ትግል አራማጅ ኃይሎች የሆኑ ፕሮፖጋንዳ ማዕከል የሆነው ኢሳት ሌላው ገጽታም            
አንዱን ብሔር ከሌላውን ብሔር በመነጠልና በመለያየት ዜጎች ኢትዮጵያዊነታቸውን ዘንግተው ቀበሌ ተኮር የሆነ ማንነት            
እንዲላበሱና ኢትዮጵያዊነት ቀርቶ የአንዱ ብሔር ተወላጅ ሌላውን ብሔር ተወላጅ ወገኑን በጎሪጥ ዓይን የሚያይበትና            
በሕዝቦችም መካከል አለመተማመንና ጥርጣሬም በመዝራት የተሰጠው የጥፋት ተልዕኮ ወደ ዳር እየገፋ ይገኛል።           
ለምሳሌ ያክል  ሙግት ዶሮ አለቅቤ አለዳኛ        የሚለውን የአበው ብሂል ዜናም አለ ትግሬ     አይጥምም የሚል
ተጨምሮበት በዋናነት የማዕከሉ ሰላባና ዒላማ የሆነ ብሔር       /ክልል/ሕዝብ የተመለከትን እንደሆነ የትግራይ ክልልና ሕዝብ     
በቀዳሚነት የሚጠቀስ ይሆናል። ይህ ሊሆንበት የቻለበት ምክንያትም በኢትዮጵያ የፖለቲካ ሥልጣን ላይ የትግራይ ክልልን            
በመላ የማይወክል የአድዋ ትወላጆች ሥልጣኑ ይዘዉታል በሚል አንድምታ ነው። ይህን በተመልከተ ማለት ሥልጣን ላይ             
ከተቀመጡት የትግራይ ተወላጆች የተነሳ የትግራይ ሕዝብ እንደ ሕዝብ ከሌላው ኢትዮጵያዊ ወገኑ የተለየ ተጠቃሚ            
እንዳልሆነና እንደው የትግራይ ሕዝብ በከፋ የባርነት አገዛዝ ቅንበር ሥር እየማቀቀ የሚገኝ ሕዝብ ለመሆኑ ከዚህ ቀደም              
ለንባብ በበቁ ጽሑፎቼ እውነታው ለማጸባረቅና ለማካፈል ስለሞከርኩ አሁን ወደኃላ ተመልሼ በዚህ ዙሪያ ላይ የምለው             
ነገር አይኖረኝም።
እውነታው ይህ ሆኖ ሳለ የትግራይ ሕዝብ በኢሳት ዘንድ ያለው መልክና ገጽታ ግን ፍጹም የተለየ ነው። የትግራይ               
ሕዝብ ማለት እንደ ልዩ ባለ መብት፣ የኢኮኖሚያዊና የፖለቲካ ተጠቃሚ፣ አጥቂ፣ ጭ           ቋኝና የደላው፣ ከፍ ባለ ዙፉንም    
የተቀመጠ፣ ኢትዮጵያ የምትባል አገር አንቀጥቅጦ የሚገዛ ሕዝብ እንደሆነና እየተደረገም የሚሰሩ የጥላቻ ፕሮፖጋንዳ           
ዜናዎችና ሐተታዎች ስፍር ቁጡር የላቸው። እንግዲህ የዚህ ጽሑፍ የመዘጋጀቱ ዋና ዓላማም እንዲህ ያለ ሸውራራ ዕይታና              
ከጠማማ ልብም ዘንድ የሚመነጨው ሰንካላ አስተሳሰብ ለማቃናትና ለማስተካከል ነው።         ይህ ተቋም ከሚዘራው በሬ ወለደ   
ወሬዎቹና ከሚያሰራጨው የጥላቻ ቃል የተነሳም ነገ በምድሪቱ ሕዝቦች መካከል ለሚፈጠረው ማንኛውም ዓይነት ክፍተትና            
ይህም ተከትሎ ለሚከሰተው ግጭት፣ ለሚጠፋ ነፍስና ለሚወድም የሀገሪቱና የሕዝብ ሀብት ተጠያቂ ነው።           
ይቀጥላል

ጸሃፊው የኢትዮጵያን ሕዝብ ስለሚጠሉትስ ምን ይላል



   
  ( TPLF ማለት እና ትግራይ ህዝብ  ልዩነቱን ልታብራሩለት ከፈለጋችሁ  ጸሃፊውን እነሆ)
ዲ/ን ሙሉጌታ ወልደገብርኤል   
E- mail yetdgnayalehe@gmail.com
United States of America


ፓርላማው የላከው ቡድን የላሊበላ ቤተ ክርስቲያናት አደጋ ላይ ናቸው አለ

 የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የቅርስ፣ የባህልና የመገናኛ ብዙኅን ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በሰሜን የአገሪቱ ክፍሎች የሚገኙ የአገሪቱ ቅርሶችን እንዲታዘብና ሪፖርት እንደያደርግ የላከው የሕዝብ ተወካዮች ቡድን፣ የላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናት በአሳሳቢ አደጋ ላይ መሆናቸውን ሪፖርት በማድረግ አስቸኳይ መፍትሔ እንዲደረግ አሳሰበ፡፡

በላሊበላ ተገኝቶ በዓለም ቅርስነት የተመዘገቡትን አብያተ ክርስቲያናት የጎበኘው የፓርላማው ቡድን ከተመለሰ በኋላ፣ የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትር ዴኤታ ወይዘሮ ታደለች ዳለቾና ሌሎች በሚኒስቴሩ ሥር የሚገኙ የሥራ ኃላፊዎችን ባለፈው ሰኞ በመጥራት ምልከታውን በማቅረብ ማሳሰቢያም ሰጥቷል፡፡ 


በንጉሥ ላሊበላ በ12ኛው ክፍለ ዘመን ከአለት ተፈልፍለው የተሠሩት ውቅር አብያተ ክርስቲያናት በከፍተኛ የመሰንጠቅ አደጋ ላይ መሆናቸውንና አስቸኳይ መፍትሔ ካላገኙም ሊፈርሱ እንደሚችሉ ቡድኑ ለኃላፊዎቹ ሪፖርት አድርጓል፡፡ 


በተለይም የቤተ ጊዮርጊስ፣ ቤተ ጐለጐታ፣ ቤተ መርቆርዮስና ቤተ ደናግል አብያተ ክርስቲያናት በከፍተኛ ሁኔታ ከተጎዱት መካከል እንደሚገኙበት በሪፖርታቸው አመልክተዋል፡፡ 


በመሆኑም ሚኒስቴሩ በአገሪቱ የሚገኙ ምሁራንና ተመራማሪዎች እንዲያጠኑት ተደርጎ አስቸኳይ መፍትሔ እንዲሰጠው ቋሚ ኮሚቴው አሳስቧል፡፡ ለሚኒስቴሩ ተጠሪ የሆነው የኢትዮጵያ ቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለሥልጣን ዳይሬክተር አቶ ዮናስ ደስታ ተቋማቸው ጉዳዩን በቅርበት እየተከታተለ መሆኑን፣ በመጪዎቹ ወራት ውስጥም መፍትሔ የመስጠት ሥራ እንደሚጀመር ተናግረዋል፡፡ 


አብያተ ቤተ ክርስቲያናቱ የተሠሩት ከአለት ተፈልፍለው በመሆኑ እንደሌሎቹ ዓይነቶች ቅርሶች በቀላሉ ጥገና በማድረግ የገጠማቸውን የመሰንጠቅ አደጋ ለማቆም በአገር ውስጥ ባለው የአቅም ደረጃ የሚቻል እንዳልሆነ፣ መሰንጠቁ የተፈጠረው በጂኦሎጂካል ምክንያት በመሆኑ ነው ብለዋል፡፡ 


ጂኦሎጂካል ምክንያቱ በየትኛው የአለቱ ክፍል ላይ እንደተፈጠረ ማወቅ በራሱ ከፍተኛ ጥናትን ይጠይቃል ብለው፣ መፍትሔም ሊያጣ የሚችልበት ሁኔታ ሊፈጠር እንደሚችል አብራርተዋል፡፡ 


ቢሆንም ባለሥልጣኑ በዚህ መሰል ቅርሶች ጥገና ላይ ልምድ ካለውና ከጣሊያን ወደ አገሩ ተቆራርጦ የገባውን የአክሱም ሐውልት በማያያዝ በአክሱም የተከለው ድርጅት፣ በላሊበላ ቅርሶች ላይ የተፈጠረውን ችግር በመመርመር መፍትሔ እንዲያመጣ ሥራው ተሰጥቶታል ብለዋል፡፡ ኩባንያውም ሥራውን ለመጀመር በመጋቢት ወር ወደ ኢትዮጵያ እንደሚመጣ ለምክር ቤቱ ቋሚ ኮሚቴ አብራርተዋል፡፡ 

“የትግራይ ክልል ተወላጅ ካልሆናችሁ በዚህ ገዳም መኖር አትችሉም” ተብለናል


(ደጀ ሰላም፤ ጥር 12/2005 ዓ.ም፤ ጃኑዋሪ 20/2013/ )፦ የዋልድባ የዋልድባ አብረንታንት ገዳም ቤተ-ሚናስ ማኅበረ መነኮሳት አቤቱታቸውን ለአማራ ብሐየራዊ ክልላዊ መንግሥት ርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት እና ለኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን አቀረቡ። በመነኮሳት ላይ የሚደርሰውን የሰብዓዊ መብት ረገጣ የዘረዘረው ደብዳቤው የክልሉ መንግሥት በሰላማውያን መነኮሳት ላይ የሚደርሰውን እንግልት እንዲያስቆም ጠይቀዋል። የታሰሩ፣ የተንገላቱ፣ ሰብዓዊ መብት ጥሰት የደረሰባቸውን መነኮሳትም ዝርዝር አቅርበዋል። ሙሉ የደብዳቤው ሐሳብ ቀጥሎ ሰፍሯል።
የክልሉ መንግሥት የመናንያኑን አቤቱታ ይቀበል ይሆን? የምናየው ይሆናል።
ቸር ወሬ ያሰማን አሜን




ቀን፡ ጥር 16 2005 ዓ.ም.
ለአ/ብ/ክ/መ ርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት
እና ለኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ባህርዳር ቅርንጫፍ

ጉዳዩ፡ የዋልድባ አብረንታንት ገዳም ቤተ-ሚናስ ማኅበረ መነኮሳት መብታችን እየተጣሰ ስለሆነ የእርምት እርምጃ እንዲወሰድልን ስለመጠየቅ
ዋልድባ አብረንታንት ገዳም ሀገራችን ኢትዮጵያ ካሏት መንፈሳዊ ቅርሶች ውስጥ በቀዳሚነት ሊጠቀስ የሚችል መሆኑ ይታወቃል፡፡ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መምህራንን፣ ጳጳሳትን፣ መነኮሳትን በማፍራት፣ በመንፈሳዊ ትህርምትና ተጋድሎ ለሀገርና ለቤተ ክርስቲያን በመፀለይ የእግዚአብሔርን  በረከት ለመቀበል በርካታ መናንያን በቦታው ይኖራሉ፡፡ መንግሥት የዋልድባን ቅዱስ መካንና ሌሎች የሀገሪቱን ቁሳዊና መንፈሳዊ ቅርሶችና ሀብቶች የመጠበቅ ኃላፊነትና የሕዝብ አደራ እንዳለበት እንገነዘባለን፡፡ ስለሆነም የደረሱብንን የመብት ጥሰቶች በሙሉ ዘርዝረን ማቅረብ ባንችልም የሚመለከተው የመንግሥት አካል መፍትሔ እንዲሰጠን ዋና ዋና የሆኑ ችግሮቻችንን ጠቅሰን አቅርበናል፡፡

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ዋልድባ የሚለውን ስም መጥራት ሁሉ የተለየ ይዘት እየተሰጠው ሁሉም ነገር አዲስ እየተገነባ ካለው የስኳር ፋብሪካ ጋር እየተያያዘ መምጣቱ ይታወቃል፡፡ ይሁንና በዚህ ማመልከቻ እየጠየቅን ያለነው ጥያቄ ከፋብሪካው ጋር የተገናኘ ሳይሆን በራሱ ለረዥም ጊዜያት የቆየ አሁን ግን ችግሩ ከመጠን አልፎ አብዛኞቹን ማኅበረ መነኮሳት ያሰደደ፣ ገዳም እንዲቀይሩ ያደረገ፣ ለተለያዩ የመብት ጥሰቶች ያጋለጠ እንጅ ከግድቡ ግንባታ ጋር በቀጥታ የሚያያዝ አለመሆኑን እንድትገነዘቡልን እንፈልጋለን፡፡

መንፈሳዊ ቦታ በማንም ላይ የዘር መድሎ ሳይደረግበት የሚገለገልበት መሆን እንዳለበት ግልፅ ነው፡፡ በቤተክርስቲያናችን ቅዱሳት መጻህፍት የተፃፉትን ለጊዜው ትተን የሀራችን ሕገ-መንግሥትና ሌሎች የመንግሥት ሕግጋት ማንኛውም ኢትዮጵያዊ በፈለገበት የሀገሪቱ አካባቢ የመኖርና መብቱ እንዲጠበቅለት የመጠየቅ ሰብዓዊ መብት እንዳለው ተደንግጓል፡፡ ይሁንና የፀለምት ወረዳ አስተዳደርን የተቆጣጠሩ ግለሰቦች ለዘመናት አንድነቱ ተከብሮና የዘር መድልዎ ሳይደረግበት ማንኛውም መናኝ በሃይማኖታዊ ምክንያቶች ብቻ ተመርምሮ ይኖርበት በነበረው ቦታ ግልጽ በሆነ መልኩ የትግራይ ክልል ተወላጅ ካልሆናችሁ በዚህ ገዳም መኖር አትችሉም በማለት በልዩ ልዩ መልክ ማኅበረ-መነኮሳቱን በመከፋፈል፣ ለዚህ ዓላማም በጣት የሚቆጠሩ መነኮሳትን፣ የአካባቢውን ታጣቂና የሚሊሻ ኃይል በመጠቀም ማኅበረ-መነኮሳቱን ለከባድ እንግልትና የመብት ጥሰት እየዳረጉን ይገኛሉ፡፡ ከመብት ጥሰቶቹም የሚከተሉት ዋና ዋናዎቹ ናቸው፡፡
·                     የወረዳው አስተዳዳሪ አቶ ሲሳይ መረሳ የመንግሥትን ኃላፊነት ከተቀበሉበት ጊዜ ጀምሮ መንግሥት በሃይማኖት ጣልቃ መግባት የለበትም የሚለውን መርህ በመጣስ ማኅበረ-መነኮሳቱን በዘር በመከፋፈልና የራሳቸውን የፖሊስ ታጣቂና የሚልሻ ኃይል በመጠቀም እያሰሩ በተደጋጋሚ በማስደብደብ፣ ለዚህም የማናውቀውን ፖለቲካ እንደ ሽፋን ሲጠቀሙበት ቆይተዋል፡፡
·                     ከ1997 ዓ.ም. ጀምሮ እስከ አሁን ድረስ በወረዳው ውስጥ ያሉ የተወሰኑ ታጣቂዎችንና ሚሊሻዎችን በዛቻና በፍጥጫ አልፎ አልፎም በድብደባ በማስገደድ መነኮሳቱን ምግብ እንዲያቀርቡላቸው ማስገደዳቸው፣
·                     ለጸሎት ከምንገለገልባቸው ቅዱሳት መጻህፍት ውጭ ምንም የሌለንን መናንያን መነኮሳት በምንናገረው ቋንቋ ምክንያት አድልኦ በማድረግ ድብቅ የጦር መሳሪያ ይዛችኋል እያሉ ማስፈራራትና ብርበራ ማካሄድ፣

ድብደባና የመብት ጥሰት ከደረሰባቸው ገዳማውያን መካከል የሚከተሉት ይጠቀሳሉ
v    አባ ገብረ ስላሴ ዋለልኝን ሐምሌ 13, 2004 ዓ.ም. ከምሽቱ 12 ሰዓት ከገዳሙ በሚሊሻና በሁለት ፖሊሶች አስወጥተው እንኮይላህም ድረስ ከወሰዷቸው በኋላ ተከትለው የሄዱ ሌሎች መነኮሳትን ስንቅ ማቀበል እንደማይችሉ ገልጸው ማይጸብሪ ከተማ ፖሊስ ጣቢያ ወስደዋቸዋል፣ በጊዜውም ደብድበዋቸዋል፡፡
v     አባ ወልደጊዮርጊስ ኃይለ ማርያም እና አባ ገ/ማርያም ገ/ዮሐንስን ሐምሌ 21 ቀን 2004 ዓ.ም በገዳሙ ስርዓት መውጣት በማይቻልበት የህርመት ሰዓት ከሱባኤ አስወጥተው የጦር መሳሪያ አላችሁ በማለት ቤታቸው ከተበረበረ በኋላ ምንም አለመገኘቱ እየታወቀ ከመነኮሳቱ ለይተው ወደ ማይጸብሪ ወስደዋቸዋል፡፡ ፖሊስ ጣቢያ ሳይሆን የጸጥታ ፖሊስ ቢሮ እያሳደሩ ሌሊት ሌሊት በሽፍን መኪና እየወሰዱ የምንኩስና ቆባቸውንና ቀሚሳቸውን በማስወለቅ ሰረንቲያ በተባለ ወንዝ በሽቦ በተደጋጋሚ ደብድበዋቸዋል፡፡ ዋልድባ መኖር አትችሉም ብሎ አስተዳዳሪው ከለከላቸው፡፡ አክሱም ጸሎት እያደረግን እንኑር ሲሉ አስተዳዳሪው "አክሱምስ ቢሆን የማን ግዛት ነው?" በማለት ሙሉ በሙሉ ከትግራይ ካልወጣችሁ ትገደላላችሁ፣ ገዳያችሁም አይታወቅም ብሏቸዋል፡፡ አሁን የት እንዳሉ አናውቅም፣ ከደረሰባቸው ግፍ አንጻርም ሁሉን ሰው ስለሚጠራጠሩ በስልክ ለማግኘት ያስቸግራል፡፡
v    መናኝ ክንፈገብርኤል ወልደሳሙኤል ነሐሴ 2004 ዓ.ም. ከአባ ነፃ አካባቢ ለገዳም ተልዕኮ ሲንቀሳቀስ ተይዞ ማይገባ አስገብተው ወልቃይት ወረዳ ላይ ለሳምንት አስረው ከደበደቧቸው በኋላ ማይጸብሪ ወረዳ ፖሊስ ጣቢያ ታስሮ ለአራት ወራት ፍርድቤት ሳይቀርብ ታስሮ ለበዓለ ልደት ተለቋል፡፡
v    አባ ገ/ስላሴ ገ/እግዚአብሔር ነሐሴ 20 2004 ያለምንም ምክንያት ጠቅላይ ሚኒስትሩንና አቡነ ጳውሎስ በመሞታቸው ደስ ብሎሃል ብለው  ከገዳሙ አስወጥተው ፖሊሶች ወልቃይት ወረዳ ማይገባ አስረውኝ ከ9 ቀን በኋላ ፍ/ቤት በዋስ ተለቀዋል፡፡
v    መናኝ ወልደሩፋኤል ወልደሳሙኤል ከገዳሙ ውስጥ ለተልዕኮ ሲንቀሳቀስ ነሐሴ 26 ቀን 2004 ዓ.ም. ላይ ፌዴራል ፖሊሶችና የአካባቢ ሚሊሻዎች አገርህ የት ነው ብለው ከጠየቋቸው በኋላ ደበደቧቸው፣ ደብዳቢው መዝን የተባለ ታጣቂ ነው፡፡ ከደበደቡት በኋላ ሌሎች ማኅበረ-መነኮሳት ወዳሉበት ማይለበጣ አምጥተውት ብዙዎቻችን እየሰማን "ዱላው ተስማማህ ወይ?" እያሉ ተዘባበቱበት፡፡ በድብደባውም እጃቸው ተሰብሯል፡፡ ከዋልድባ ውስጥ በድብደባው ምክንያት አብረንታንትን ለቀው ዋልድባ ዳልሻ ከተባለው ቦታ ይገኛሉ፡፡
v    ቤተ-ሚናስ ውስጥ በመነኮሳት መካከል የጠፈጠረውን አለመግባባት ለመፍታት የአካባቢው ነዋሪዎች ለማስታረቅ ማህበረ መነኮሳቱን ፈቃድ ጠይቀው ማህበረ መነኮሳቱም ስለተስማማ ለሽምግልና 40 የሐገር ሽማግሌ ተመርጠው በገዳሙ ማኅተም ጥሪ ተደርጎላቸው ነበር፡፡ ለህጋዊነትም መንግሥት እንዲያውቀው የወረዳውን አስተዳደር ጠይቁ ብሎ ማኅበረ መነኮሳቱ ስለጠየቁ የማይፀብሪ አስተዳደር መነኮሳቱን የምታስታርቁ ከሆነ እርምጃ እወስድባቸዋለሁ አላቸው፡፡ ይህን ማስጠንቀቂያ የሰሙት ሽማግሌዎች ሲቀሩ  ከሽማግሌዎቹ መካከል አራቱ ማለትም አቶ አለምሸት ሙሉ፣ አቶ ተክሌ ገ/ኪዳን፣ አቶ አምባቸው ጥላሁንና አለቃ መሀቤ ገ/መስቀል ይህን ስላልሰሙ ወደ ገዳሙ ለማስታረቅ ስለመጡ ሀሙስ ዕለት ጥር 2፣ 2005 ዓ.ም የማይጸብሪ ወረዳ ጸጥታ ሰራተኛ ነኝ ያለ አቶ ረዘነ የተባለ ሰው አስሮ ይዟቸው ሄዶ ፍ/ቤት ሳይቀርቡ ከባድ ማስጠንቀቂያ ሰጥተዋቸው ለቀዋቸዋል፡፡ ከሽማግሌዎቹ አንዱን አቶ አለምሸትን የትግራይ ተወላጅ ስላልሆንክ ወደ ሀገርህ ወደ ክልል ሦስት ለቀህ ሂድ በማለት አዘውታል፡፡
v    ጥር 2 2005 ዓ.ም. አባ ወ/ገብርኤል ገ/ስላሴና አባ ገ/ህይወት ተ/ማርያምን ማይለበጣ ገዳሙ ውስጥ እያለን የማይጸብሪ ፖሊሶች በዓታችን ውስጥ እያለን ከጓደኞቻችን ለይተው ካስወጡን በኋላ ትፈለጋላችሁ ብለው ከባላገር ቤት ለየብቻ አሳደሩን፡፡ ለሽንት እንኳ እንውጣ ብለን ስንጠይቅ በጥፊ እየደበደቡ አሳደሩን፡፡ ጠዋትም እንደናንተ ያለ ሽፍታ መነኩሴ አግኝተናል ብለው ለጸሎት ደንደረቋ ከተባለ ቤ/ክን ስመለስ አባ ኃ/ማርያም ገ/ስላሴን እና መናኝ ታዲዮስ ገ/መድህንን ጨምረው ማይጸብሪ ወስደው አሰሩን፡፡ ለአራት ቀን ካቆዩን በኋላ ነጻ ናችሁ ተብለን ተለቀቅን፡፡ በግምት 10 ኪ.ሜ ያህል ወደ ገዳሙ መመለስ ከጀመርን በኋላ እንደገና በሽፍን መኪና ተከታትለው እናንተ ሽፍቶች ቁሙ ብለው መልሰው እያዳፉ እስር ቤት መለሱን፡፡ የወረዳው አስተዳዳሪ ከእስር ቤት አስጠርቶ ቢሮው ከወሰደን በኋላ ከስራ ባልደረቦቹ ጋር ሆኖ "እናንተ ተመልሳችሁ ወደ ገዳም መግባት አትችሉም፣ የወጡትም አይመለሱም፣ በገዳሙ የቀሩትንም እየመነጠርን እናወጣቸዋለን፤ እንገባለን ካላችሁ ገዳያችሁን ሳታውቁ ትገደላላችሁ ብሎናል፡፡ የጎጃም፣ የጎንደርና የሸዋ ሌባ ተሰብስባችሁ ከገዳሙ ልትቀመጡ አትችሉም ብሎናል፡፡ በተደጋጋሚ ባደረገው ንግግር ከማሰርና ከመደብደብ አልፎ አማርኛ ቋንቋ ተናጋሪዎች ወደ ዋልድባ ገዳም መግባት አትችሉም፣ ከውስጥ ያሉትንም ጠራርጌ አወጣቸዋለሁ በማለት፣ ይህን ባታደርጉ ግን ገዳያችሁ ማን እንደሆነ ሳይታወቅ ትገደላላችሁ ስለተባልን አቅም ያለን መነኮሳት ወጥተናል፡፡

በተጨማሪም ከገዳሙ ለመውጣትም ሆነ ወደ ገዳሙ ለመግባት በምንንቀሳቀስበት ጊዜም የትግራይ ክልል ነዋሪ መሆናችሁን የሚያሳይ የቀበሌ መታዎቂያ ካላመጣችሁ እያሉ ያስገድዱናል፡፡ የገዳሙ ማኅተም ያለበት መታዎቂያ ስናሳይ ተቀባይነት የለውም እየተባልን መንቀሳቀስ እንዳንችል ተደርገናል፡፡ አሁን ወደ ጎንደር ስንመጣም ያስሩናል ብለን በትክክለኛው መንገድ መውጣት አልቻልንም፡፡ ስለሆነም ተጨማሪ የሁለት ቀን የእግር መንገድ በርሃ ለበርሃ ተጉዘን ጎንደር ገባን፡፡ በዋናው መንገድ ለመምጣት የሞከሩት ታስረዋል፡፡ ማኅበረ-መነኮሳቱን በዘረኝነት ከበተኑ በኋላ 31 ያህል መነኮሳት ይህን ማመልከቻ ስናቀርብ ሌሎች ብዙዎች ገዳም ቀይረው ሄደዋል፡፡ እኛን ካስወጡ በኋላ የገዳሙን አስተዳደር ከወረዳ አስተዳደር የተላኩ ሚሊሻዎችን ይዘው መምህር፣ እቃቤትና ሌሎች ሰራተኞችን በአዲስ አዋቅረዋል፡፡ ይህም ግልጽ የሆነ ጣልቃገብነት ነው፡፡ የገዳሙንም ስርዓት ያልጠበቀ ነው፡፡

ይህ ሁሉ የመብት ጥሰት የሚደርስብን ምንም ጥፋት ተገኝቶብን አይደለም፡፡ በእኛ እምነት ይቅርና የብዙ ዘመን ታሪክ ያለው ዋልድባ አብረንታንት ገዳም ማንኛውም የኢትዮጵያ ክፍል ውስጥ ባለ ገዳም ውስጥ መንፈሳዊ ስርዓቱን ተከትለን የመኖር መብታችን ሊጠበቅልን ይገባል፡፡ ይሑንና በተደጋጋሚ ያለአግባብ እየታሰርን፣ እየተደበደብን፣ የመንቀሳቀስ ነፃነታችን ተገድቦ፣ የግድያ ማስፈራሪያ በመንግሥት ባለስልጣን እየደረሰን በገዳማችን ለመኖር አልቻልንም፡፡ ዋስትናም አጥተናል፡፡ የሌላ ሀገር ዜጋ የሆንን ይመስል ያለጥፋት በመንፈሳዊ በዓታችን እንዳንኖር የማናውቀውን ፖለቲካ ተገን ባደረገ ዘረኛ አስተሳሰብ በገዳማችን የመቀጠል መብታችንና የገማኅበረ-መነኮሳቱ ህልውና አደጋ ላይ ወድቋል፡፡ በገዳሙ መነኮሳት ላይ እየደረሰ ያለው ችግር በእኛ ብቻ ሊያቆም የሚችል ሳይሆን ውሎ አድሮ መጥፎ ጠባሳ የሚተው ጉዳይ በመሆኑ የሚመለከታቸው የመንግሥት አካላት በሙሉ መፍትሄ እንዲሰጠን እንዲያደርጉልን እንጠይቃለን፡፡

ስለሆነም የሚመለከተው የመንግሥት አካል ወደ ገዳማችን ያለችግር መግባት እንድንችል ዋስትና እንዲሰጠን፣ መደብደብና ማስፈራራት እንዳይደርስብን፣ በነጻነት የመኖርና የመንቀሳቀስ መብታችንን እንዲያስጠብቅልን፣ መብታችንን በተደጋጋሚ የጣሱብንን የመንግሥት አካላትም ላይ የእርምት እርምጃ እንዲወስድልን፣ የወረዳው የጸጥታ አካላትና አስተዳደርም ህገ-ወጥ በሆነ መልኩ በገዳሙ አስተዳደር ላይ ሹም ሽር ማስደረግን ጨምሮ የሚፈጽሙትን ግልጽ የሆነ ጣልቃ ገብነት እንዲያቆሙልን እንዲደረግልን በቤተክርስቲያን አምላክ ስም እንጠይቃለን፡፡
የአመልካች ማኅበረ-መነኮሳት ስም ዝርዝርና ፊርማ
1.              አባ ገ/ዮሐንስ ወ/ሳሙኤል
2.             አባ ገ/ስላሴ ገ/እግዚአብሔር
3.             አባ ወ/ተክለሃይማኖት ዮሐንስ
4.             አባ ገ/መድህን ወ/ገብርኤል
5.             አባ ገ/ስላሴ ጥሩነህ
6.             አባ ገ/ስላሴ ወ/ሳሙኤል
7.             አባ ገ/ሚካኤል ኃ/ማርያም
8.             አባ ገ/ስላሴ ገ/መድህን
9.             አባ ገ/ስላሴ
10.           አባ ገ/ሚካኤል ወ/ሳሙኤል
11.             አባ ኃ/ማርያም ገ/ስላሴ
12.            አባ ገ/ህይወት ተክለማርያም
13.            አባ ወ/ገብርኤል ገ/ስላሴ
14.           አባ ገ/ህይወት
15.            አባ ገ/ማርያም ወ/ህይወት
16.           መናኝ ኃ/መለኮት ሐዋዝ
17.            መናኝ ታዴዎስ ገ/መድህን
18.           መናኝ ገ/ሚካኤል ሰሎሞን
19.           መናኝ ኃ/ስላሴ ዳዊት
20.          መናኝ ሠይፈስላሴ ወ/ሳሙኤል
21.            መናኝ ገ/መድህን ወ/ሳሙኤል
22.           መናኝ ገ/እግዚእ
23.           መናኝ ወ/ሩፋኤል ወ/ሳሙኤል
24.          እማሆይ ፅጌ ድንግል
25.           እማሆይ ወለተሰንበት
26.          እማሆይ ወለተስላሴ
27.           እማሆይ አመተኢየሱስ
28.          እማሆይ ወለተፃድቅ
29.          እማሆይ ወለተማርያም
30.          እማሆይ አፀደማርያም
31.            እማሆይ ሂሩተሥላሴ

ግልባጭ፡
ü    ለሰሜን ጎንደር ሀገረስብከት ጽ/ቤት
ü    ለሰሜን ጎንደር ዞን አስተዳደር

ቤተ ክህነት የአዲሱን ፓትርያርክ ምርጫ የሚቃወሙትን እንደምትከስ አስፈራራች


(ደጀ ሰላም፤ ጥር 20/2005 ዓ.ም፤ ጃኑዋሪ 28/2013/ PDF)፦ ስድስተኛውን ፓትርያርክ ለመምረጥሰላማዊ የሽግግር ጊዜውን ለማደናቀፍ የሚገኙ ቡድኖችን፣ የመገናኛ ብዙኅንና ግለሰቦችን የመንበረፓትርያርክ ጠቅላይ ጽሕፈት ቤት ማስጠንቀቁን ሪፖርተር ጋዜጣ ዘግቧል። “የስድስተኛውን ፓትርያርክአሿሿም በሚመለከት ሕገ ደንብ ወጥቶ ምርጫውን ተግባራዊ ለማድረግ በእንቅስቃሴ ውስጥ መሆኑንየሚያውቁ አንዳንድ የመገናኛ ብዙኅን፣ ከውስጥ አፍራሽ ኃይሎች የሚቀበሉትን ፀረ ሰላምና ከእውነትየራቀ አሉባልታ ከድረ ገጽ ያገኙ በማስመሰልና ‘ምንጮቻችን’ እያሉ በውጭና በአገር ውስጥ ያለውንምዕመናን እያወናበዱ በሚገኙት ላይ” ቤተ ክህነት ክስ መመሥረቷን የዘገበው ጋዜጣው መግለጫውንየሰጡት ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት ሳይሆኑ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ እስክንድር ገብረ ክርስቶስመሆናቸውን አብራርቷል።


የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ እስክንድር ገብረ ክርስቶስ የተጠቀሙባቸው ቃላት በርግጥ ጉዳዩ የቤተ ክርስቲያን ሳይሆን ሌላ አስመስሎታል። “ፀረ ሰላም፣ ማደናቀፍ፣ አፍራሽ ኃይሎች” የሚሉትን ቃላት በቤተ ክህነት ሳይሆን በቤተ መንግሥት አደባባይ ሲነገር ስለምናውቃቸው አሁንም ማስጠንቀቂያው የማን ነው የሚለውን እንድንጠይቅ ያደርገናል። ማስፈራራት ግን መልስ አይደለም። ግዴላችሁም ልብ መግዛት ይሻላል። ለማንኛውም የዚህን ዜና ዝርዝር ከዚህ በታች መመልከት ይቻላል።       

ቸር ወሬ ያሰማን አሜን