Jan 28, 2013

TPLF ከመግደል ሙከራ ወደ ክስ



ኢሳት በትግራይ ሕዝብ የከፈተው የጥላቻ     /የጦርነት ዘመቻ በአስቸኳይ ያቁም    



የጽሑፉ ዓላም 
ሕዝብ በዙሪያው ምን እየሆነ እንዳለ ለማሳወቅ ተጻፈ። በተለይ ደግሞ ጥቂት ለማይባሉ ጊዜያት             
ደህና ረገብ ብሎ የነበረና ጎሳን ያማከለ ይፈጠሩ የነበሩ ግጭቶች እየተወገዱ ብዙሐኑ የኢትዮጵያ ሕዝብ ወደ መረዳት              
እየመጣበት ባለበት ሰዓት ይህ ከቅርብ ጊዜያት በፊት       "ኢሳት" የሚል ስያሜ ይዞ በነፃ ሚድያ ስም የተቋቋመው የትጥቅ ትግል አራማጅ ኃይሎች የፕሮፖጋንዳ ማእከል የሆነው ተቋም የልባቸውን ምኞትና ክፉ ሐሳብ  

 "ታማኝ ምንጮች እንዳሳወቁት፣ ውስጥ አዋቂዎች ለምናችን እንደገለጹት፣     ...” እየተባለ ከዚህም አልፎ ተልዕኮቸው የማይታወቁ በቆዳቸው ነጮች ዳሩ ግን ለኢትዮጵያ ሕዝብ የሞት መልዕክተኞች የሆኑ ግለሰቦች ፈረንጆች   "እንዲህ አሉ" እያለ በሕዝብ መካከል  ከሚዘራው መጥፎ ዘር የተነሳ ይኸው በቅርቡ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የተፈጠረውን ችግር ሁነኛ ምሳሌ ነው። እንዲህ  ያለ ድርጊት ደግሞ ዜጎች በዜግነትታችን የዜግነት ግዴታችን ካልተወጣን ነገ         "ኢትዮጵያ የሚልዋት ሀገር ነበርች    "  ተብሎ ከተረት ያለፈ ሀገር እንደማትኖር ልንጠራጠር አይገባንም። ከዚህም የተነሳ ጸሐፊው ይህን ጽሑፍ ተከትሎ በግላቸው  ከየትኛውም አቅጣጫ ሊመጣ ያለውንና የሚችለውን ማንኛውም ዓይነት ጥላቻና እክል ሳይበግራቸው በቁርጠኝነት  ለሀገራቸውና ለሕዝባቸው ያላቸውን ጽኑ ፍቅር ገልፀዋል።

በድጋሜ ይህ ድምጽ   : 
• ሰሜኑም ደቡቡም የሀገሪቱ ክፍል በቋንቋ፣ በነገድ፣ በባህል፣ በልዩ ልዩ ልማዶችና ወጎች አንዱን ከሌላውን            
ሳይለያይ በአንዲት ኢትዮጵያ የሚያምን ኢትዮጵያዊ ልብ ያለው ሕዝብ ሁሉ ድምጽ ነው።          
• ይህ ድምጽ:  ስለ ኢትዮጵያ ምድርና ስለ የኢትዮጵያ ሕዝብ መጻኢ የነፍሱን፣ አንድ ሰው ሰለ ጓዳው ቀዳዳ            
የሚጨነቀው ያክልም ስለ ሀገሩና ስለ ሕዝቡ ግድ የሚለው ኢትዮጵያዊ ሕብረተሰብ ሁሉ ድምጽ ነው።            • ይህ ድምጽ: የሚናገረውን የማያውቅ ፍሬ ከርስኪ ሁላ ፖለቲከኛ ስለ ሆነባት ሀገርና ዓይነ መርፌው ስለ ጠፋበት            
የኢትዮጵያ ፖለቲካ ሕመም የሚሰማው በር የተዘጋበትና በደጅ የቆመው ዜጋ ሁሉ ድምጽ ነው፣
• ይህ ድምጽ: በግልጽም በስውርም፣ በሰውም በእግዚአብሔር ፊትም፣ ስለ ሀገሩና ስለ ሕዝቡ ፊቱ የጠቆረ፣ ልቡ           
የተሰበረና በቆመበት ስፍራ ለሚያዩት ሁሉ ዓይኖቹ እንደ ተከፈተ መጽሐፉ የልቡን ሐዘን የሚያስነብቡና የሚናገሩ            
ኢትዮጵያዊ ሁሉ ድምጽ ነው    !! 
• ይህ ድምጽ:  በአንደበት ቃል ብቻ ሳይሆን ኢትዮጵያዊነቱ ከቃል በዘለለ እውነተኛ ሀገራዊ ፍቅር ያለው እንዲህ           
ባለ ክፉ ቀን   :  የኦሮምኛ ቋንቋ ተናጋሪ ሳለ ስለ ትግርኛ ቋንቋ ተናጋሪው ኢትዮጵያዊ ወገኑ ግድ የሚለው፣           
የአማርኛ ቋንቋ ተናጋሪ ግለሰብ    /ሕዝብ ሆኖ ሳለ ስለ ደቡብ ቋንቋ ተናጋሪ ሕዝብ የሚቆረቁረው እውነተኛ         … 
ሀገራዊ ፍቅር ያለው ኢትዮጵያዊ ዜጋ ሁሉ ድምጽ ነው።        
• እንዲህ ያለ እምነት   የትግራይ ክልል ተወላጅ ከሆነ ግለሰብ ብቻ የሚመነጭ እምነት ሳይሆን አሁንም እንዲህ ያለ           
ድምጽ የመላ ኢትዮጵያውያን እምነትና ድምጽ     ለመሆኑ ዕድል ከተሰጣቸው ጸሐፊው ነገራቸውን በዝግታ     
እንደሚከተለው ያስረዳሉ መልካም ንባብ።    


ሐተታ
ከተቋቋመ ሁለት ዓመታት ያስቆጠረ የጣቢያው መጠሪያ ስሙም ኢሳት በመባል የሚታወቀው በዋናነት በኢትዮጵያ           
ውስጥ ለውጥ የሚመጣ በጠመንጃና በጠመንጃ ብቻ ነው       ! ብሎ በሚያም ቀቢጸ ተስፋዎች የሚመራና ትግሉ እንመራለን      
የሚሉ ግለሰቦቹም  "መንግሥተ እግዚአብሔር" በሚያስረሳ፣ ኑሮ በሞቀበትና ነገር ዓለሙ ሁሉ በተደላደለበት ልጆቻቸውና       
ሚስቶቻቸው ይዘው የዓለማችን ምዕራቡ ክፍል በሆነ ምድር ከትመው ሲያበቁ በምስኪኑ ኢትዮጵያዊ ድሃና ረዳት አልባ             
ወጣት ሀገር ተረካቢ ዜጋ ህይወት ቀጥፈው፣ በደሙና አጥንቱም ተረማምደው፣ ደም አቃብተውና ሀገር ምድሩንም            
አተረማምሰው ምንሊክ ቤተ መንግሥት ዙፋን ላይ ቁጢጥ ብለው ተቀምጠው ያሹትን ሲፍልጡና ሲቆርጡ በህልም            
እየታያቸው ቅዠት ከሰው ልክና መልካም ጤንነት ያወጣቸው ግለሰቦች የሚያራምዱት የከሰረ የትጥቅ ትግል ፖለቲካ ኢሳት             እንደ ነሐሴ ዝናብ በነጋ በጠባ ቁጥር ሰፊ ሽፋን በመስጠት በኢትዮጵያ ምድር ጎሳ መሰረት ያደረገ አላስፈላጊ ግጭት               
እንዲቀሰቀስ ግንባር ቀደም የፕሮፖጋንዳ ማዕከል ሆኖ ሲሰራ ቆይተዋል። አሁንም በዚህ መሰረት በሌለውና በፈጠራ            
ሥራው አንድ ቀን በሕግ ፊት ከተጠያቂነት የማያመልጠበት ድርጊት ላይ ተጠምዶ ይገኛል።          
በተጨማሪም ይህ የትጥቅ ትግል አራማጅ ኃይሎች የሆኑ ፕሮፖጋንዳ ማዕከል የሆነው ኢሳት ሌላው ገጽታም            
አንዱን ብሔር ከሌላውን ብሔር በመነጠልና በመለያየት ዜጎች ኢትዮጵያዊነታቸውን ዘንግተው ቀበሌ ተኮር የሆነ ማንነት            
እንዲላበሱና ኢትዮጵያዊነት ቀርቶ የአንዱ ብሔር ተወላጅ ሌላውን ብሔር ተወላጅ ወገኑን በጎሪጥ ዓይን የሚያይበትና            
በሕዝቦችም መካከል አለመተማመንና ጥርጣሬም በመዝራት የተሰጠው የጥፋት ተልዕኮ ወደ ዳር እየገፋ ይገኛል።           
ለምሳሌ ያክል  ሙግት ዶሮ አለቅቤ አለዳኛ        የሚለውን የአበው ብሂል ዜናም አለ ትግሬ     አይጥምም የሚል
ተጨምሮበት በዋናነት የማዕከሉ ሰላባና ዒላማ የሆነ ብሔር       /ክልል/ሕዝብ የተመለከትን እንደሆነ የትግራይ ክልልና ሕዝብ     
በቀዳሚነት የሚጠቀስ ይሆናል። ይህ ሊሆንበት የቻለበት ምክንያትም በኢትዮጵያ የፖለቲካ ሥልጣን ላይ የትግራይ ክልልን            
በመላ የማይወክል የአድዋ ትወላጆች ሥልጣኑ ይዘዉታል በሚል አንድምታ ነው። ይህን በተመልከተ ማለት ሥልጣን ላይ             
ከተቀመጡት የትግራይ ተወላጆች የተነሳ የትግራይ ሕዝብ እንደ ሕዝብ ከሌላው ኢትዮጵያዊ ወገኑ የተለየ ተጠቃሚ            
እንዳልሆነና እንደው የትግራይ ሕዝብ በከፋ የባርነት አገዛዝ ቅንበር ሥር እየማቀቀ የሚገኝ ሕዝብ ለመሆኑ ከዚህ ቀደም              
ለንባብ በበቁ ጽሑፎቼ እውነታው ለማጸባረቅና ለማካፈል ስለሞከርኩ አሁን ወደኃላ ተመልሼ በዚህ ዙሪያ ላይ የምለው             
ነገር አይኖረኝም።
እውነታው ይህ ሆኖ ሳለ የትግራይ ሕዝብ በኢሳት ዘንድ ያለው መልክና ገጽታ ግን ፍጹም የተለየ ነው። የትግራይ               
ሕዝብ ማለት እንደ ልዩ ባለ መብት፣ የኢኮኖሚያዊና የፖለቲካ ተጠቃሚ፣ አጥቂ፣ ጭ           ቋኝና የደላው፣ ከፍ ባለ ዙፉንም    
የተቀመጠ፣ ኢትዮጵያ የምትባል አገር አንቀጥቅጦ የሚገዛ ሕዝብ እንደሆነና እየተደረገም የሚሰሩ የጥላቻ ፕሮፖጋንዳ           
ዜናዎችና ሐተታዎች ስፍር ቁጡር የላቸው። እንግዲህ የዚህ ጽሑፍ የመዘጋጀቱ ዋና ዓላማም እንዲህ ያለ ሸውራራ ዕይታና              
ከጠማማ ልብም ዘንድ የሚመነጨው ሰንካላ አስተሳሰብ ለማቃናትና ለማስተካከል ነው።         ይህ ተቋም ከሚዘራው በሬ ወለደ   
ወሬዎቹና ከሚያሰራጨው የጥላቻ ቃል የተነሳም ነገ በምድሪቱ ሕዝቦች መካከል ለሚፈጠረው ማንኛውም ዓይነት ክፍተትና            
ይህም ተከትሎ ለሚከሰተው ግጭት፣ ለሚጠፋ ነፍስና ለሚወድም የሀገሪቱና የሕዝብ ሀብት ተጠያቂ ነው።           
ይቀጥላል

ጸሃፊው የኢትዮጵያን ሕዝብ ስለሚጠሉትስ ምን ይላል



   
  ( TPLF ማለት እና ትግራይ ህዝብ  ልዩነቱን ልታብራሩለት ከፈለጋችሁ  ጸሃፊውን እነሆ)
ዲ/ን ሙሉጌታ ወልደገብርኤል   
E- mail yetdgnayalehe@gmail.com
United States of America


No comments:

Post a Comment