Jan 29, 2013
ህወሐት ለሁለት ተሰነጠቀ፤ ወረቀት ለአባለት ተበተነ
ዛሬ በመቀሌ ለአባላትና አልፎም ለህዝቡ በተበተነ የትግርኛ ፅሁፍ እነ ስዩም መስፍን፣ አባይ ፀሐዬ፣ ፀጋዬ በርሔ ከነባለቤታቸው
እንዲሁም ሌሎች ከድርጅቱ እንዲባረሩ በተበተነው መግለጫ ተጠቁሞዋል። በመግለጫው፥ ከጀርባ አሉ የተባሉትና « የዚህ መኅንዲስ»
ተብለው የተፈረጁት ስብሃት ነጋ እርምጃ እንዲወሰድባቸው ከተባሉት መካከል በዋነኛነት ተፈርጀዋል። እነ ቴውድሮስ ሃጎስ፣አዜብ
መስፍንና በረከት እጃቸው እንዳለበት የተነገረለት ይኸው መግለጫ ተከታዩን ይመስላል፤
«ተቆርቋሪ ለሆናችሁ የትግራይ ተወላጆ በሙሉ፤
«ድርጅትህ ሕወሐት እስከ ዛሬ ታግላ እዚህ ደረጃ አድርሰሃለች። በተለይም የሁሉም ነገር አድራጊና ፈጣሪ የነበረው ባለ ራዕይው መሪህ
በቅርብ ጊዜ አጥተኽል።
“ዛሬ እነዚህን ደካማ ጐኖች ተጠቅመው ለጠላት አሳልፈው ሊሰጡህ የሚፈልጉ ያውም ደግሞ የእኔ የምትላቸው ጅቦች ተነስተውብህ
ይገኛሉ። ይህንን ግልፅ ለማቅድረግ አሁን በቅርብ ጊዜ በመቀሌ የድርጅቱ ማ/ኰሚቴ ስብሰባ አካሄደን ነበር። በዚህ ስብሰባ ላይ ነው
እንግዲህ ተከታዩ ነገር የተነሳው። ይኽውም፥ እነ ስዩም መስፍን፣ አባይ ፀሐዬ፣ ፀጋዬ ከሚስቱ ጋርና ሌሎችም ያሉበት ይህን አሉ፤
«ድርጅታችን ጨርሶ ተዳክሞዋል። እኛ የኢትዮጲያ ሕዝብ ትግል መስራች ሆነን ሳለ ወደኋላ ተገፍትረን በአንፃሩ ሌሎች ከእኛ ኋላ
የተፈጠሩና ራሳችን ያሳደግናቸው ሲጠናከሩ ድርጅታችን ግን እየተዳከመ በመሄድ ላይ ነው። ባዛው መጠን ሕዝባችን እየተጎዳ ነው።
ስለዚህ አሁን ካጋጠመን አደጋ መውጣት ካለብን ከድርጅቱ -የተወገዱትን ግን በመጥፎ ጎዳና ያልተሰማሩትን መልሰን ወደ ፓርቲው
ማስገባት አለብን። ይህ ካልሆነ ግን የሕዝብ ትግል አውላላ ሜዳ ላይ ጅብ በልቶት ሊቀር ነው።» በማለት ከጠላቶቻችን ጋር እንታረቅ
እያሉን ነው።
“ሕዝባችን አስተውል። በዚህ አይነት ዳግመኛ በድርጅታችን ተኃድሶ እንደሚያስፈልገን ነው የተገነዘብነው። በሚቀጥለው የካቲት ወር
በሚካሄደው ጉባኤያችን ይህንን ጉዳይ ትኩረት ሰጥቶና አጥርቶ (ውሳኔ አሳልፎ) እንደሚወጣና እነዚህንና መሰሎቻቸው ከሚያራምዱት
አቋም ጋር ጠራርጐ እንደሚያስወግድልን ተስፋ እናደርጋለን። በዚህም እያንዳንዱ እንደከዚህ ቀደሙ የተለመደ አስተዋፅኦ (ሚና)
እንደሚያበረክት አንጠራጠርም።
በተጨማሪ ከጀርባ ሆኖ የዚህ አፍራሽ ዋና ቀያሽ መሃንዲስ ስብሃት ነጋ መሆኑን ደርሰንበታል።»
ከመቀሌ…..
ኢትዮሚድያ - Ethiomedia.com
January 28, 2013
Subscribe to:
Post Comments (Atom)
No comments:
Post a Comment