Jan 31, 2013

ተመስገን ደሳለኝ ክስ ላይ ብይኑ አልደረሰልኝም በማለት ሌላ ቀጠሮ ሰጥቷል


ኢሳት ዜና:-የፌደራሉ ከፍተኛው ፍርድ ቤት 16ኛ ወንጀል ችሎት ዛሬ ጠዋት በጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ክስ ላይ ብይን ለመስጠት የተሰየመ ቢሆንም ፍርድ ቤቱ ብይኑ አልደረሰልኝም በማለት ቀጠሮ ሰጥቷል።
የችሎቱ ዳኛ ፣ ጋዜጠኛ ተመስገን እና አሳታሚው ማስተዋል የህትመት ስራ ድርጅት ዋና ስራ አስኪያጅ የነበረው አቶ ማስተዋል ብርሀኑ መኖራቸውን ካረጋገጡ በሁዋላ ብይኑን ለመስጠት ለየካቲት አንድ ቀጠሮ ሰጥተዋል።
የጋዜጠኛ ተመስገን ጠበቆች በችሎቱ ላይ አልተገኙም። በችሎቱ ዲፕሎማቶችን ጨምሮ የጋዜጠኛው ቤተሰቦች፣ አድናቂዎችና ስራ ባልደረቦች ተገኝተዋል።

No comments:

Post a Comment