Jan 18, 2013

የመቀበያው የመተቃቀፊያ የእርቀ ሠላም ጊዜ አሁን ነው!


የማገገሚያ ጊዜ፤ የመቀበያው የመተቃቀፊያ የእርቀ ሠላም ጊዜ አሁን ነው!
በክዱስ ጽሁፍ እንደሰፈረው፤ “ለማንኛውም ሁኔታ ወቅት አለው፤ከሰማይ በታች ላሉት ነገሮች ሁሉ ለየምክንያቱ ጊዜ አለው።” ለማልቀስ ጊዜ አለው፤ ለሃዘንም ወቅት አለው፤ ድንጋይ ለመወርወርም ጊዜ አለው። ለመገንባትም ጊዜ አለው፤ ለመናገርም ጊዜ አለው። እንዲሁም ለመተቃቀፍም ጊዜ አለው ለሠላምና ለማገገምም ጊዜ አለው። ለእርቀሰላምም የራሱ ጊዜ አለው።

አሁን ነው ጊዜው፤ -- ትክለኛው ጊዜ-- ለኢትዮጵያውያን ወጣቶች በትምህርት ቤቶች፤ በዩኒቬርስቲዎች፤ በስራ ቦታዎች፤ በአጎራባች መንደሮችና በመንገድም ላይ የማገገሚያው ወቅት። ጊዜው----- ትክክለኛው ጊዜ---- የኢትዮጵያ ወጣቶች በወንድማማችነት በአህትማማችነት ስሜት መተቃቀፍ መተሳሰብ እጅ ለእጅ በመያያዝና አንድ በመሆን ብዛታቸውን ለቅድመአያቶቻቸው ክብርና ለታሪካቸው መከበርያ ማድረግ የሚገባቸው።

ለሁሉም ኢትዮጵያዊያን ወጣቶች የጎሳ ጥላቻን የብጥብጥን አዙሪት የመበጠሻ ጊዜው አሁንነው። አላስፈላጊውን የቅሬታ ልምድ የማክተሚያ፤ የፍርሃትን ባህል፤ ጥላቻን፤ አውልቆ የመጣያው ትክክለኛው ጊዜው አሁን ነው።

ለኢትዮጵያውያን ወጣቶች ጣቶቻቸውን በማቆላለፍ እጅ ለእጅ በመያያዝ የፍርሃትን እከክ ማራገፊያቸው፤ ጥላቻን፤ግጭትን፤ከልባቸው ፤ ከሕሊናቸው፤ ከመንፈሳቸው አውጥተው መጣያ ጊዜያቸው አሁን ነው። ጓደኞቻቸውንና የትምህርት ባልደረቦቻቸውን እንደጠላትና ባላጋራ መመልከትን ማቆሚያቸው ጊዜ አሁን ነው።

ሰላም ፈጥረው እርስ በርሳቸው እንደወንድምና እህት የሚተቃቀፉበት ጊዜ አሁን ነው። የኢትዮጵያ ብልህና ምርጦች አንድ ላይ በመስራትና በመተጋገዝ የተሸለን ነገ ለመፍጠር የሚችሉበት፤በረጋና ጠንካራ በሆነ የሕግ የበላይነት ላይ፤ ሰብአዊ መብትና ዴሞክራሲ የተከበሩበት አማራጭ ሂደቶች ያሉበት መትለሚያው ጊዜ አሁን ነው። ኔልሰን ማንዴላ እንዳስተማሩት “ከጠላት ጋር ሠላምን መፍጠር ካስፈለገህ፤ከጠላትህ ጋር ተጓድነህ መስራት አለብህ፤ ያን ጊዜ ጠላትህ ወዳጅህ ይሆናል።” እነዚያን ጠላት የምንላቸውን ወንድምና አህት አብሮ ተማሪዎች ና ወዳጅ ማድረጊያ ጊዜው አሁን ነው።

በዩኒቨርሲቲ ግቢያችን ውስጥና ከግቢያችንም ውጪ ጥላቻንና የጥላቻ ወንጀልን ለማጥፋት መተባበርያው ጊዜ አሁን ነው።

ከሕሊናችንና ከመንፈሳችን ውስጥ የጥላቻ ቋጠሯችንን ማጥፊያው፤ የፍርሃትን ሰንሰለትና ካቴና መበጠሸውጊዜ አሁን ነው። የኢትዮጵያ አቦሸማኔዎች ካለፈው ጫና እራሳቸውን ለማላቀቅና ነጻ ለማድረግ ጊዜው አሁን ነው።

ለሁሉም ኢትዮጵያዊያን ወጣቶች ቆንጨራውን በመቅበር ለአንድዬና ለመጨረሻው ጊዜ “አሻፈረን! አንዳችን ሌላውን የዚህ ወይም የዚያ ጎሳ ስለሆንን ለመጠላላት አሻፈረን፤ እምቢ! መባያችን ጊዜው አሁን ነው። አሻፈረን! ምክንያቱም ሁላችንም በተለያየ ስም በምንጠራው የጋራችን በሆነው አምላክ ስር አለያም የሁላችን በሆነችው ሀጋራችን የተለያየ ማእዘን ነዋሪዎች ነንና። እምቢ! በምንም መልኩ ለመጠቀሚያነትና እንደ አሻንጉሊትነት ሆነን በሚጠቀሙብን ለጥላቻ ለእርስ በርስ መቆራቆስ መጠቀሚያ አንሆንም፤ እምቢኝ! የሠለጠንን ነንና ለጥላቻ አንሰለፍም። አዳኝ እንደሚያሳድደው የሚታደን አውሬ ለመሆን እምቢኝ!

ከአንድ ጉማሬ ጥቂት ቃላት ለበርካታዎቹ አቦሸማኔዎች
በርካታ አቦሸማኔዎች ምናልባትም ጉማሬውን ትውልድ ማዳመጡ ያስገርማቸው ይሆናል።

እኛ ጉማሬዎች “በዕውቀት የተጋረድን” “ራዕይ የጎደለን” “የራሳችን ምንጭ እስካልደረቀብን ድረስ ጠቅላላው ሃገር ቢደረማመስ ደንታ የሌለን “ ነን ተበለን አነታወቃለን። ያም ሆኖ ወጣቱን ትውልድ በአክብሮት እባካችሁ ጆሯችሁን አውሱኝና ለመደመጥ እድል ስጡኝ እላለሁ።

ጀግኑ!
  • የመጀመርያው የኢትዮጵያ ትውልድ በመሆን፤ እራሳችሁን ከሰንሰለቱ ነጻ በማድረግ ካለፈው የጫና ሰቆቃ እኛንም አራሳችህሁንም ለማላቀቅ ብቁ።
  • የመጀመርያው የኢትዮጵያ ትውልድ በመሆን፤ ታሪካዊ ጥላቻን፤ ቅሬታን በማጥፋት፤ መግባባትንና መቻቻልን በማምጣት አዲስ እርቀሰላም በኢትዮጵያ ታሪክ ጀምሩ።
  • የጥላቻን ቁስል ለማዳን የመጀመርያዎቹ ትውልዶች በመሆን ለዘመናት ያመረቀዘውን በማጥፋት ለመጪው ትውልድ ያለፈው ትውልድ ስህተትና ጥፋት እስረኞች እንደማይሆኑ አረጋግጡላቸው።
  • የመጀመርያዎቹ ትውልዶች በመሆን ሁላችንም በእኩልነት የሰው ዘር አባላት በመሆናችን ይህንንም በጎሰኝነት ለማቀደም ብለን አዘቅት አንውረድ።
  • የመጀመርያዎቹ ትውልዶች በመሆን አንደኛችን ለሌላው ይቅርታን በመቸር ለአንድዬና ለመጨረሻ ጊዜ ቆንጨራውን በመቅበር፤ ጣቶቻችንም የጠመንጃ ቃታና ምላጭ ለመሳብ፤ጣቶቻችን የጥላቻ መነሾ የሆኑ ቃላትን በየግድግዳው ላይ ለመለቅለቅ ሳይሆን እጆቻችን የሚዘረጉት የመግባባት የመተሳሰብ ሰላምታ ለመለዋወጥና ለችግርም ይሁን ለደስታ እጅ ለመዋዋስ ብቻ አንድሆን ማረግ ያሻል።
  • የመጀመርያዎቹ ትውልዶች በመሆን የተለያዩት እምነቶቻችን መለኮታዊነታቸውን ማረጋገጥ እንቻል።
  • የመጀመርያዎቹ ትውልዶች በመሆን አሻፈረኝ! አምቢ! በማለት ውስጥ ውስጡን ከሚበላን የጎሳ የሃይሞነት የጻታ ልዩነት በተቃርኖ እንቁም።
  • የመጀመርያዎቹ ትውልዶች በመሆን በመኝታ ቤቶች፤ በቤተመጻህፍት፤በመጸዳጃ ቤቶችም ያሉትን አስነዋሪና በታታኝ፤ ጎሰኝነትን የሚያቅራሩ ቃላታን በእርቀሰላም፤ በመግባባት፤ በውህደት፤ በፍቅር አሰባሳቢ ቃላቶች እንሸፍናቸው።
  • የመጀመርያዎቹ ትውልዶች በመሆን የወደፊቷ ሃገራችን መሪ ሻምበሎች እናንት ኩሩ አቦሸማኔዎችእንጂ፤ የደከሙት፤ሙሰኞቹ፤ ምግባረብልሹዎቹ፤ እራሳቸውን የሚያስተናግዱ ጉማሬዎች ሊሆኑ አይችሉም።
  • የመጀመርያዎቹ ትውልዶች በመሆን ለመሆን የምትመኘውን ሁሉ በመሆን፤ለመሆንም ለማሰብ ቀደምት አንሁን።
  • የመጀመርያዎቹ ትውልዶች በመሆን የትላንቱን የመረረ ስሜት በዛሬውና በነገው ጣፋጭ እርቀሰላም፤ መግባባት፤ አንድነት፤ መሰረት ላይ መልሳችሁ አዋቅሩት።

የሃቅ ወቅቱ ደርሷል፡ አቦሸማኔዎቹ እራሳቸውን በማዳን ለእኛም መድህን ይሆኑን ይሆን ?
  • ለኢትዮጵያ ምርጡና ብሩሁ የሃቅ ወቅት ደርሷል!
  • የኢትዮጵያ ምርጥና ብሩህ አቦሸማኔዎች ካለፈው ጫናና መከራ እራሳቸውን በማዳንና የጎሳ መጎጃጃ፤ የሃይሞነት አክራሪነትን የጨቋኝ ስጦታ በመጣል እራሳቸውን ማዳን ይችሉ ይሆን?
  • እነዚህ አቦሸማኔዎች ተጠራጣሪዎቹን፤ የመሸጉትን ምስኪን ጉማሬዎች ከራሳቸው ነጻ ያወጧቸው ይሆን?
  • ከጎሳ መቆራቆስ ወደ ጎሳ ፍቅር፤መቻቻል አንድነት፤ መግባባትን ያበቁን ይሆን?
  • አቦሸማኔዎቹ ስብእናችንን ከጎግፍ ማነቆና ከአውሬ አስተሳሰብ ያላቅቁን ይሆን?
  • አቦሸማኔዎች የእርቀ ሰላምን ጥበብ ያስተምሩን ይሆን? በእርቀሰላም ቋንቋ ያናግሩን ይሆን?
  • የኢትዮጵያ ብልህና ብሩሆች አንድ የወጣት ግብረሃይል በመሆን 2013ን የአቦሸማኔዎች ዓመት ያደርጉት ይሆን? አንድ ላይ በመቆም የጎሳ ጥላቻን ቆንጨራ በመስበር የወገንተኛነትን ጎራዴ በማቅለጥ የእርቀሰላምን ሙሉነት ያስመርቱን ይሆን?

የአላንዳች ጥርጥር አዎን ይቻላቸዋል!
ባለፈው ሳምንት 2013 የኢትዮጵያ አቦሸማኔዎች ዓመት ብዬ ስተነብይ፤ የኢትዮጵያን ወጣቶች ለማስተማር፤ ለማዳረስ፤ለማሳመን ቃል ገብቼ ነበር። አኛ ጉማሬዎች አቦሸማነዎችን አናስተመራለን የሚል አምነትም ነበረኝ። ጉማሬዎችን አቦሸማኔዎችን ያስተምራሉ ብዬ አልገመትኩም ነበር። ለዚህ ነው እኛ ጉማሬዎች ግራ የተጋባ ሸውራራ (የተዛባ አመለካከት) ቅርብ አዳሪነት፤ጠባብ አስተሳሰብ፤ የምያጠቃን። ለአቦሸማኔዎች የማስተማርያ ወቅት ሊኖር ስለመቻሉ ጥርጣሬዬ የመጣው።

ስለዚህም የኢትዮጵያ አቦሸማኔዎችና ጉማሬዎች በርካታ ግብግቦች የሚገጥሟቸው። የአቦሸማኔዎቹ ፈታና ጉማሬዎቹን የእርቀሰላምን ጥበብ ማስተማሩ ላይ ነው። የጉማሬዎቹ ፈተና ደግሞ ከአቦሸማኔዎች የእርቀሰላምን ጥበብ መማሩ ላይ ነው።

አቦሸማኔዎች ታሪካዊ ገድል የመፈጸም እድል ቀርቦላቸዋል፡- ይሄዉም በምሳሌነት ማስተማር።
በአዲስ አበባው ዩኒቨርሲቲ አጋጣሚ የተሳተፉትን፤ ወዳዳጆቻቸውንና ሌሎቹም ጭምር በግቢያቸው የተፈጸመውን አስጸያፊ የግጭት ሁኔታና ሁከት አስመልክቼ የማቀርበው ጥሪ ሁኔታውን ወደ ውብና ያማረ ፍቅርና ሰላም የሞላበት ፍሬያማ ውጤት ለማምጣት የአንድነት አውድማ ላይ እንዲሰባሰቡ ነው። እያንዳንዳቸው ወደ ሌላው በመቅረብ ይቅርታን እንዲጠይቁና እንዲቀባበሉ እጠይቃለሁ። አንዲት በጣም ትንሽ የሆነችውን “ይቅርታ” የምትለውን ቃል ለመተንፈስ ወኔ ይጠይቃል።

በራሳቸው ውህደት እንዲፈጥሩ እጠይቃለሁ----አንድ ለአንድ፤ በትንሹና በበርካታው ስብስብ-----ልዩነታቸውን ይወያዩበት ይነጋገሩበት ይምከሩበት። አንደኛቸው የሌላው ጉዳትና ግፍ ይሰማው። አንዱ የሌላው ፍርሃትና ጥርጣሬ ይሰማው። አንዱ ለሌላው እንባ ንቀት አይኑረው።

በብሩህ ህሊና፤ በንጹህ ልቦና፤ አእምሮና መንፈስ ሊነጋገሩ ግድ ነውና ይህንንም እጠይቃለሁ።

እያንዳንዳቸው የሌላውን ስሜትና ጥርጣሬ እንዲረዱ እጠይቃለሁ። በጓደኞቻቸው ጫማ ውስጥ ሆነው ለኪሎሜትር እንዲራመዱ እጠይቃለሁ። በመጫሚያም ይሁን በባዶ እግራቸው ፈገግ ሊያሰኛቸው የሚችል ሁኔታ ያጋጥማቸዋል።

የኢትጵያ አቦሸማኔዎችን 2013ን የእርቀሰላምና የሰላም ዓመት እንዲያደርጉት እጠይቃለሁ።

ጃንዋሪ 2 1013 በታሪክ የኢትዮጵያ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የጎሳ ጥላቻን ቆንጨራ፤የሃይሞነት ወገንተኝነት፤ የጾታ ልዩነት የተቀበሩበት ዕለት ሆኖ ዘወትር አንድታሰብ ይሁን። በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የተከሰተው አስጸያፊ ሁኔታ ለሕዝብ ማስተማሪያነት ያገልግል።

ጥንካሬን ከችግር ወልዳችሁ፤ አንድነትን ከከፋፋይ ተምራችሁ፤ ከጓደኞቻችሁ ተማሪዎች ጋር ለመደማመጥና የመግባባትን፤ የመቻቻልን፤ የውህደትን ዘር ለማፈስ እንድትበቁ እማጸናችኋለሁ።

የኢትዮጵያ አቦሸማኔዎች ጉማሬዎችን እንደመሩ እጠይቃለሁ። እኛን አትከተሉን፤መሄጃችንን አናውቀውምና።እኛ የጠፋው የጉማሬ ትውልዶች ነን።

ይህን ግብግብ በመቀበል፤ ትክክለኛውን እንደትክክል፤ስህተቱንም ወደ ትክክለኛነት ካልለወጣችሁት፤ አቦሸማኔዎች በስልጠና ላይ ያሉ ደካማ ጉማሬዎች ናቸው የሚል ትችት ላይ መውደቅ ይመጣል።
ለሁሉም ጊዜ አለው። ለኢትዮጵያ አቦሸማኔዎች፤ ለማገገምና ለእርቀሰላም ሰዓቱ አሁን ነው።
የኔ ጥያቄ ለእዮጵያ ወጣቶች ይህ ነው:- አሁን ስንት ሰአት ነው!?!
የተባበሩት የኢትዮጵያ አቦሸማኔዎች ፈጽሞ ለውድቀትና ለሽንፈት አይዳረጉም!

No comments:

Post a Comment