Feb 27, 2013

የሕወሐት ፍጥጫ ቀጥሏል, “አሁን ያለው ሕወሐት ቆዳ ነው” -- እነ ስብሃት ነጋ


“አሁን ያለው ሕወሐት ቆዳ ነው” -- እነ ስብሃት ነጋ
“የሕወሐት ወራሾች እኛ ነን” -- እነ አባይ ወልዱና አዜብ
(ከኢየሩሳሌም አርአያ)
ሁለት ቦታ የተከፈለው የሕወሐት አመራር ልዩነቱን በማስፋት እየተወዛገበ መሆኑን ከመቀሌ ታማኝ ምንጮች ገለፁ። ስብሃት እና አዜብ
የሚመሩት ሁለቱ ቡድን አነጋጋሪ አቋም ይዞ መውጣቱን ምንጮቹ ጠቁመዋል። በስብሃት ነጋ የሚመራው ቡድን ባስቀመጠው አቋም«
መለስ ሕወሐትን ገድሎ ነው የሔደው! አሁን ያለው ሕወሐት ቆዳ ነው። ጥያቄው ግልፅ ነው፤ ሕወሐት መቀጠል አለበት.. ወይስ
የለበትም?»ሲሉ በድርጅቱ ቀጣይ ሕልውና ላይ ጥያቄ አሳርፈዋል። ከዚህ በተቃራኒ የቆመውና አባይ ወልዱ፣ አዜብና ከጀርባ በረከት
ስምኦን ያሉበት ቡድን በበኩሉ « የሕወሐት ወራሾች እኛ ነን፤» ሲል ለነስብሃት ምላሽ መስጠቱ ታውቋል። በተጨማሪ በሁለቱም ቡድኖች
በልዩነት ነጥብ ተደርጎ የተወሰደው በ1993ዓ.ም ከፓርቲው የተባረሩት አመራሮች « ይመለሱ» ፣ « አይመለሱም» የሚለው
እንደሚገኝበት ተጠቁሟል። የሁለቱም ጐራ ፖለቲካዊ ግብ አንዱ ሌላኛውን ገፍትሮ ከሜዳው ማስወጣትና ፓርቲውን ብሎም አገሪቱን
በፈላጭ ቆራጭነት ለመቆጣጠር ያለመ እንደሆነ አንድ የፓርቲው ቅርብ ሰው ጠቁመዋል።
በፓርቲው በተለኮሰው ስር የሰደደ ፖለቲካዊ ፍጥጫ ካድሬው ለሁለት ተከፍሎ ሲነታረክ መሰንበቱን ምንጮች ጠቁመዋል። በፓርቲው
አባላት « አደገኛ» የተባለውን ይህን ፍጥጫ መሰረት በማድረግ በቴውድሮስ አድሃኖምና ብርሃነ ገ/ክርስቶስ የሚመራ ቡድን ራሱን«
የአስታራቂ ሽማግሌዎች ቡድን» በሚል ሰይሞ ባለፉት ቀናት ሲነቀሳቀስ መቆየቱን ገልፀዋል። ሆኖም ሁለቱን ጎራዎች አቀራርቦ ለማነጋገርና
ለማስማማት የተጀመረው ጥረት በሁለቱም በኩል በሚታየው አክራሪ አቋም ምክንያት ተስፋ ሰጪ ሁኔታ እንደማይታይ ምንጮቹ
አስታውቀዋል። አሁንም ድርድሩ መቀጠሉን ምንጮቹ አልሸሸጉም።
የሕወሐት ሕልውና አጣብቂኝ ውስጥ በገባበት በአሁኑ ወቅት በሌላ ጐራ የተነሱ ወጣት የፓርቲው ካድሬዎች ባነሱት ጥያቄ ፥ ሁሉም
አንጋፋ አመራሮች ከድርጅቱ እንዲለቁ ጥያቄ ማቅረባቸውንና ይህን ለማድረግ ፈቃደኛ ካልሆኑ ግን ሕወሐት ሊፈርስ እንደሚችል
ማስጠንቀቂያ ጭምር መስጠታቸውን ምንጮቹ አያይዘው ገልፀዋል።
በተያያዘም « ጉባኤ ይጠራ» በሚል በካድሬዎች የቀረበውን ጥሪ እነ አባይ ወልዱና አዜብ ያሉበት ቡድን ውድቅ እንዳደረገው ታውቋል።
አባይና አዜብ የሚመሩት እንዲሁም ትርፉ ኪዳነማሪያም፣ ሃድሽ ዘነበ፣ አለም ገ/ዋህድ፣ በየነ ምክሩ፣ ተክለወይኒ አሰፋና ሳሞራ የኑስ
የተካተቱበት ቡድን በጉባኤው አሸናፊ ሆነው እንደማይወጡ ከወዲሁ በማመናቸውና በነስብሃት በኩል ከፍተኛ ሃይል እንደተደራጀባቸው
ጠንቅቀው ስለተረዱ ነው ሲሉ የጠቆሙት ምንጮቹ አክለውም ሳሞራ በመከላከያ እጣ ፈንታቸው ተመሳሳይ መሆኑን በማመናቸው
ከነአዜብ ጋር ተሰልፈው እንደሚገኙ ገልፀዋል።
የበላይነትን እየያዘ ነው የሚባለውና በስብሃት የተደራጀው እንዲሁም በደብረፂዮን የሚመራው ቡድን አብዛኛውን የማ/ኮሚቴ አመራር
በዙሪያው ያሰባሰበ ሲሆን ከነዚህም፥ አዲስአለም ባሌማ፣ አርከበ እቁባይ፣ ቅዱሳን ነጋ፣ ፈትለወርቅ፣ ፀጋዬ በርሄ፣ አባዲ ዘሙ፣ ሃ/ኪሮስ
ገሰሰ፣ ተ/ብርሃን…በዋንኛነት እንደሚገኙበት ምንጮቹ አመልክተዋል። የሽማግሌው ቡድን ስብስባ እንደቀጠለ ተጠቁሞዋል።
(ከኢትዮሚድያ ዝግጅት ክፍል - ያለን መረጃ እየሩሳሌም አርአያ ካቀረበችው ዘገባ እጅጉን የተለየ ነው። እንደኛ እምነት ሽማግሌው
ስብሃት ነጋ ከአልሞትኩም ባይ ተጋዳይነት አልፎ በነ አዜብና በረከት የሚመራውን አዲስ እና እየተጠናከረ ያለውን ጉልበተኛ ቡድን
የሚፈታተን ምንም አይነት ኃይል የለውም።)

Feb 23, 2013

ESAT እየለበለበዉ መሆኑን ወያኔ አንደበቱ በሆነዉ http://www.tigraionline.com ደጋግሞ እየገለጸ ይገኛል


አንድ ዲያቆን᎒ ቄስ ወይም ጳጳስ ስለ ክርስቶስ ከሚመሰክሩት በበለጠ አንድ እርኩስ መንፈስ ያደረበት ሰዉ ጸበል ቦታ የሚለፈልፈዉን ልቤ ተከፍቶ እሰማዋለሁ ምክንያቱም የጠላት ምስክርነት ወገንተኝነት እንደሌለዉ 100% እርግጠኞ በመሆኔ ነዉ᎓᎓ ስለ ESAT ታማኝ በየነ ᎒ ሲሳይ አጌና᎒ፋሲል የኔነህ᎒ አበበ ገላዉ᎒ እናም ሌሎቹ ከሚነግሩን tigraionline ᎒የዲ/ን ሙሉጌታ ወልደገብርኤል ረጃጅም ምላሶች ልፍለፋ ESAT አልጀዚራን ሊተካ እንደሚችል ማስረጃ ነዉ ይሄን ለማለት የደረስሁት እራሳችን ያለንን ገንዘብ ለግሰን በሁለት እግሩ ያቆምነዉን ESATን ያቆመዉ ወይም ዋና ደጋፊዉ ራሱአን ማስተዳደር  ያቃታትን የ TPLF ፈጣሪ እና ሞግዚት ሻብያ ወይም ኢሳያስ አፈወርቂ ነዉ ሲሉን ለቀባሪ አረዱት ሆኖብኝ ነዉ ᎓᎓ 
የዋይታዉ መብዛት ግርፋቱ ዉስጥ ሰርጎ እየተሰማቸዉ መሆኑን ያሳያል ᎓᎓

ከታች  የምታዩትን ፎቶወች በሙሉ tigraionline በተለያየ ጊዜ የወጡ ናቸዉ











እዉነታዉ

Where does ESAT get its funding?
Currently, ESAT relies on the support it receives from individual donors and contributions from the Ethiopian Diaspora. Efforts are being made to get institutional support from organizations that promote democratization and press freedom.

                                                                                        B.Tsegaye

መርዝ ከውጭ ይረጫል ወይም ከውስጥ ይመነጫል


ፕ/ር መስፍን ወልደ ማርያም
በአለፉት ሠላሳ አምስት ዓመታት ኢትዮጵያ ችግሮችን መፈልፈያ መሣሪያ ሆናለች፤ ለብዙ ምዕተ-ዓመታት ይዘናቸው (ምናልባትም አቅፈናቸው ማለት ይሻል ይሆናል) ስንንከባለል የቆዩ ችግሮች ሞልተውናል፤ እያሰብን እነዚያን የቆዩ ችግሮቻችንን በመፍታት ፋንታ ሌሎች አዳዲስ ችግሮችን እየፈለፈልን የተቆላለፉና የተወሳሰቡ፣ ውላቸው የጠፋ ችግሮችን ፈጥረናል፤ እየፈጠርንም ነው፤ አሁን በመፈጠር ላይ ያለው አዲስ ችግር እስላማዊ መንግሥት በኢትዮጵያ የሚል ነው፤ እስቲ እንመልከተው፡፡መርዝ ከውጭ ይረጫል ወይም ከውስጥ ይመነጫል
በሩቁ እንጀምር፤ እስላማዊ መንግሥታት ያቋቋሙ አገሮች አሉ፤ አንዳቸውም ሰላም የላቸውም፤ እስላማዊ ቡድኖች በምርጫ አሸንፈው ሥልጣን የያዙ አሉ፤ ለምሳሌ በቅርቡ በአረብ አገሮች በተጀመረው የፖሊቲካ እድገት ለውጥ በቱኒስያና በግብጽ እስላማዊ ቡድኖች አሸንፈው ሥልጣን ይዘዋል፤ በዚህም ምክንያት በቱኒስያና በግብጽ የለውጥ ጥያቄ አገርሽቶ አንደገና ሰዎች እየሞቱ ነው፤ በነዚህና በሌሎችም አገሮች የሚገኙት ወጣቶች የሚፈልጉት የሰው ልጆች ሁሉ መብቶች የሚከበሩባቸውና በሙሉ የግለሰብ ነጻነት የተረጋገጡባቸው አገሮች እንዲኖራቸውና በእኩልነት ኩሩ ዜጎች ሆነው እንዲኖሩ ነው፤ የአንድ አገር ዜጎች የተለያየ ዘር፣ የተለያየ የቆዳ ቀለም፣ የተለያየ ቁመትና ውፍረት፣ የተለያየ ጾታና ዕድሜ፣ የተለያየ ቋንቋ፣ የተለያየ ሃይማኖት፣ የተለያየ የፖሊቲካ አመለካከት፣ የተለያየ ትምህርት፣ የተለያየ ሙያና የተለያየ ገቢ ሊኖራቸው ይችላል፤ የጋራ ማንነታቸው ዜግነት ነው፤ እኩልነታቸው በዜግነታቸው ነው፤ አንድነታቸው በዜግነታቸው ነው፤ እኩልነታቸውንና አንድነታቸውን የሚያረጋግጥላቸውና ሚዛኑን የሚጠብቅላቸው ከበላይ ሆኖ ሁሉንም የሚገዛው ሕግ ነው፡፡
በቡድን ወይም በጅምላ የሚያስቡ ሰዎች የሕግን ባሕርይ አያውቁትም፤ ‹‹ክርስቲያኖች እስላሞችን እንጨርሳለን›› አሉ፤ ወይም እስላሞች ክርስቲያኖችን እንጨርሳለን›› አሉ፤ በሚል አሉባልታ ላይ ክስ ተመሥርቶ ሕጋዊ ፍርድ መጠበቅ አይቻልም፤ በየትም ሆነ በማንኛውም ጊዜ ጽንፈኛ እምነትና አስተሳሰብ ያላቸው ሰዎች ይገኛሉ፤ እነዚህ ግለሰቦች ሕልማቸውንም ሆነ ቅዠታቸውን በስውርም ሆነ በአደባባይ ይገልጻሉ፤ ለምሳሌ በአሜሪካ ጥቁሮችንና ይሁዲዎችን ከአገሩ ጠራርገን እናወጣና ንጹሕ የነጮች አገር እንፈጥራለን የሚሉ ግለሰቦች አሉ፤ ይህ እምነት ለአሜሪካ ማኅበረሰብ መርዝ ነው፤ አሜሪካ የነጻነት አገር ነው፤ የነጭ ዘረኞቹ መርዛቸውን ለመንዛት መብት አላቸው፤ የዘረኞቹን መብት ለማፈን የሚወሰድ የጡንቻ እርምጃ ሁሉ አሜሪካ የነጻነት አገር መሆኑን ይሽራል፤ ከዚያም በላይ የአሜሪካ መንግሥት በሚከተለው ዘዴ ከነጭ ዘረኞቹ የተሻለ አይሆንም ነበር፤ ስለዚህም ነጭ ዘረኞችን ለመቋቋም የሚወሰደው አርምጃ አሜሪካ የነጻነት አገር መሆኑን ሳይሽርና ነጭ ዘረኞቹም እምነታቸውን የመግለጽ መብታቸው ሳይደፈጠጥ መሆን አለበት፤ የነጻነት ትርጉሙ ይህ ብቻ ነው፡፡
በሥልጣን ወንበር ላይ ስለተቀመጡ ብቻ አንድ ዓይነት የፖሊቲካ እምነት ብቻ ይዞ ሌላውን መደፍጠጥ፣ መንግሥት የባረከውን አንድ ዓይነት የኦርቶዶከስ ሃይማኖት ብቻ ማደርጀትና ሌላውን ማፈን፣ መንግሥት የባረከውን አንድ ዓይነት የእስልምና ሃይማኖት ብቻ ማደርጀትና ሌላውን ማፈን ልማድና የአሠራር ባህል እየሆነ ሲሄድ ሁሉንም ነገር አንድ ዓይነት ብቻ ለማድረግ የሚታየው ጥረት የኢትዮጵያን ጉራማይሌ ባሕርይ የሚቃረን በመሆኑ ስር አይኖረውም፤ ይህ ሁሉም ሰው ሊያስብበት የሚገባው አንዱ ነገር ነው፤ ሁለተኛው አንድ ወይም ጥቂት ሰዎች በኢትዮጵያ ውስጥ እስላማዊ መንግሥት እናቋቁማለን ቢሉ አገር የሚሸበርበት ምንም ምክንያት የለም፤ ኢትዮጵያን የኦርቶዶክስ ክርስቲያን አገር ለማድረግ የሚመኙም አሉ፤ ኢትዮጵያን ሃይማኖት-አልባ የጉግማንጉግ አገር ለማድረግ የሚፈልጉ አሉ፤ ኢትዮጵያ በአንድ አጋጣሚ ወንበሩ ላይ የወጣ ጉልበተኛ የሚያትምባትን እምነትም ሆነ ሃይማኖት የማትቀበል አገር መሆንዋ ተደጋግሞ የታየ ነው፤ ኢትዮጵያን የይሁዲ አገር ለማድረግ ተሞክሮአል፤ ኢትዮጵያን የክርስቲያን አገር ለማድረግም ተሞክሮአል፤ ኢትዮጵያን የእስላም አገር ለማድረግም ተሞክሮአል፤ ሁሉም አልሆነም፤ ኢትዮጵያ የሁሉም አገር ሆና ዘልቃለች፤ ይህንን በማክሸፍ ለማንም ምንም ጥቅም አይገኝም፤ በአንጻሩ ደግሞ የሥልጣን ወንበሩ ላይ የወጡ ጉልበተኞች ሁሉ የኢትዮጵያ ሕዝብ በጉጉት የሚጠብቀውን የነጻነት ጮራ እያዳፈኑ የነጻነትን፣ የእኩልነትንና የሕግ የበላይነትን ዓላማ ለማክሸፍ የሚደረገው ጥረት ተጠናክሮ እየቀጠለ ነው፡፡
የነጻነትና የሕጋዊነት መክሸፍ የሰላም ጠንቅ ነው፤ የሰላም መክሸፍ የልማት ጠንቅ ነው፤ የልማት መክሸፍ ደሀነት ነው፤ ደሀነት የሞት አፋፍ ነው፤ ይህንን ለመገንዘብ የሚያዳግተው ሃያ አንድ ዓመት የሞላው ሰው አለ? ኢትዮጵያን ለመምራት የሚደናበሩት ሰዎች ሁሉ ሃያ አንድ ዓመት አልፎአቸዋል፤ ነገር ግን ከላይ የተገለጸው የመክሸፍ ጉዞ ጭራሽ አይታያቸውም፤የሚታየውም ሲነግራቸው የተበለጡ ስለሚመስላቸው አይሰሙትም፤ ስለዚህም የሚታየውን ሳያዩ፣ የሚሰማውን ሳይሰሙ ጊዜ የሚበላውን ጉልበታቸውን ብቻ ተማምነው በጭፍን እንምራችሁ የሚሉትን ተከትለን ለእኛ በሚታየንና ለእነሱ በተሰወረባቸው ገደል ውስጥ ለምን አብረን እንግባ? አብረን ገደል በመግባት አንድነታችንን የምንጠብቅ የሚመስላቸው ሰዎች በሁለት በኩል ይሳሳታሉ፤ አንደኛ ከአገዛዙ መሪዎች ዘንድ የሎሌ ተከታይነትን እንጂ የአኩልነት አንድነትን አያገኙም፤ እኩልነት በሌለበት አንድነት አይፈጠርም፤ ሁለተኛ ወደገደል የሚጨምር አንድነትን መምረጥ ሕይወትን ትቶ ሞትን መምረጥ ነው፡፡
በሃያ አንድ ዓመት ውስጥ መክተፍ-መከታተፍ ሙያ ሆነ፤ ብዙ ሰዎችና ድርጅቶች ሠለጠኑበት፤ መክተፍ-መከታተፍ አብሮ የመኖር ጸር ነው፤ አብሮ የመኖር ጸር የሚሆነው በፍቅር ፋንታ ጥላቻን፣ በሰላም ፋንታ ጠብን፣ በመረዳዳት ፋንታ መጋጨትን፣ በልማት ፋንታ ጦርነትን በመንዛት ነው፤ አንዳንድ ቋንቋ ተናጋሪዎችን በግልጽም ሆነ በስውር እንደጠላት መቁጠርና በእነሱ ላይ ቂምን እንዲቋጥሩ ማድረጉ የማንንም የፖሊቲካ ቡድን፣ የኢትዮጵያን ሕዝብም ይጎዳል እንጂ አይረዳም፡፡
አሁን ደግሞ በአንድ በኩል በኦርቶዶክስ ሃይማኖት ላይ በየገዳማቱና ላይ እየደረሰ ያለው ጥቃትና በሊቀ ጳጳሳት ምርጫው ላይ አገዛዙ እያሳየ ያለው ጣልቃ-ገብነት የኦርቶዶክስ ሃይማኖት ተከታዮችን እያስቀየመና እያስኮረፈ ነው፤ በሌላ በኩል በእስልምና ሃይማኖት ላይም የሚታየውን ጣልቃ-ገብነት ተከታዮቹ ፍጹም ሰላማዊ በሆነ መንገድ በርትተው በመቋቋማቸው እየደረሰባቸው ያለው ግፍ ለጆሮ እየቀፈፈና በጣም አሳፋሪ እየሆነ ነው፡፡
ይህ በሃይማኖቶች ላይ የተጀመረው ዘመቻ ውጤት ይኖረዋል፤ ውጤቱ በአገዛዙ የውስጥም ሆነ የውጭ አመራሩ ላይ ከባድ ተጽእኖ ይኖረዋል፤ የሃይማኖቶቹ ጉዳይ እንደጎሣዎች መከታተፍ በኑሮ ላይ ብቻ ጫናውን የሚያሳርፍና በምድር የሚንከላወስ አይደለም፤ ወደሰማይ ያርጋል፤ የሰማይ ሠራዊትን ይጠራል፤ ያንን ኃይል እንኳን የኢትዮጵያ የጦር ኃይልና የአሜሪካውም አይችለውም፤ ዓይን ያለው ያያል፤ ጆሮ ያለው ይሰማል፤ ልብ ያለው ያስተውላል፤ ዶላር ነፍስን አይገዛም፤ ክብርን አይገዛም፤ ወዳጅንም አይገዛም፡፡
ፕ/ር መስፍን ወልደ ማርያም፤ የካቲት 2005

ሕገ መንግስቱን የሚጥስ መንግስት ባለበት አገር ሕገ መንግስቱን ለማስከበር መነሳት በራሱ ወንጀል ሆኖ እስር ቤት ሊያስወርድ እንደሚችል...



እስከ አሁን ድረስ ሙስሊሙ ያሳየዉ ጽናት አንድነት አስተዋይነት ለሁላችን ትምህርት ነዉ ይህ ሰላማዊ፣ አመፅ-አልቦ ትግል ጄን ሻርፕ “ከአምባገነንነት ወደ ዴሞክራሲ” በሚለው መፅሐፉ ላይ እንዳስቀመጠው 198 ደረጃዎች አሉት። አሁን በምርጫው ላለመሳተፍ ስንወስን፣ አንዱን ብቻ ነው በተወሰነ መልኩ የተጠቀምነው። ገና 197 ደረጃዎች ይቀራሉ ማለት ነው። እንግዲህ ተግቶ ደረጃ በደረጃ አንድ በአንድ መተግበር ያስፈልጋል።ይህ ትግል ጥብቅ ዲሲፒሊን የሚጠይቅ፣ ነገሮች ባልታሰበ ሁኔታ ወደ አመፅና ብጥብጥ እንዳያመሩ ጥንቃቄ ማድረግ ግድ የሚል፣ ሐላፊነት የሚሰማቸው ሰዎች ብቻ ሊያደርጉት የሚችሉት ነገር ነው። እንደ ማህተመ ጋንዲ ያለ የሞራል ልዕልና ያለው መሪ፣ እንደ ህንዶች ያለ ስርዓት ያለውና በአንድ ላይ ያለልዩነት መሰለፍ የሚችል ህዝብ መኖር የሚጠይቅ ነው። ስለዚህ ይህ እንዲሆን ከተፈለገ በመጀመሪያ እንደ ህዝብ ያሉብንን ልዩነቶች ለማጥበብና ለማመቻመች ጠንክሮ መስራት ያስፈልጋል። ቀጥሎ መስራት የሚኖርበት ስለሰለማዊ፣ አመፅ-አልቦ ትግል በስፋትና በጥልቀት ማስተማር፣ በተግበር ለዚህ መርህ መገዛት እንዲቻል ደረጃ በደረጃ ማለማመድ ያስፈልጋል። በዚህ ዙሪያ ሞስሊም ወንድሞቻችን እስካሁን እያሳዩት ያለው ሰላማዊ ተቃውሞ የሚደነቅ ነው። አገር በቀል የሰላማዊ ትግል ስልት በመሆኑ ለእኛ ጥሩ ትምህርትና ሞዴል ሊሆን የሚችል ነው። ይህ በራሱ የሚያሳየው ነገር አለ። ህዝባችን በአግባቡ የሚመራውና አምኖ ሊከተለው የሚችል መሪ ድርጅት ካገኘ ሰላማዊ ትግል
ለማካሄድ አያዳግተውም።

አምባገነኖችን እንዴት እንታገል?


ከበትረ ያዕቆብ
ፍኖተ ነፃነት 2ኛ ዓመት ቅጽ 2 ቁ 63 -ከምርጫው በፊት የምርጫ መደላድሉ ይስተካከ
የጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊን ሞት ተከትሎ በኢህአዴግ ውስጥ የተፈጠረው ትልቅ የአመራር ክፍተትና አሁንም ድረስ ውስጥ ውስጡን የቀጠለው የስልጣን ሽኩቻ አምባገነኑን ስርአት ክፉኛ አዳክሞታል፡፡ በኢህአዴግ ቤት ውስጥ የተፈጠረው መጠላለፍ እና በጥርጣሬ አይን መተያየት ከውጫዊው ጫና ጋር ተዳምሮ ዛሬ የ21 ዓመታት ዕድሜ ያስቆጠረውን አንባገነናዊ ስርዓት ለማስወገድ ከምን ግዜውም በላይ አመቺ ሁኔታ ፈጥሯል፡፡ ይህንንም ከግምት ውስጥ በማስገባት የተለያዩ ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች ህዝቡ አገዛዙን ለማስወገድ ለትግል መነሳት እንዳለበት ደግመው ደጋግመው ጥሪ እያስተላልፉ ይገኛሉ፡፡ ምንም እንኳን ብዙዎቹ እንዲሁ በደፈናዉ “ለሰላማዊ ትግል ተነሱ” ከማለት በስተቀር ብዙም በታቀደ እና ዘርዘር ባለመልኩ እንዴት መታገል እንዳለበት ለህዝቡ ሲናገሩ እና አቅጣጫ ሲሰጡ ባይደመጥ፡፡
ባለፈው አመት አጋማሽ “መንግስት በሐይማኖታችን ጣልቃ መግባት ያቁም!” በሚል በሙስሊሙ ህብረተሰብ የተጀመረው ሰላማዊ ትግል አሁንም እንደቀጠለ ነው፡፡ ትግሉ እስካሁን በሙስሊሙ ህብረተሰብ ዙሪያ ብቻ የተወሰነ ቢሆንም ህዝባዊ መሰረቱ በፍጥነት እየሰፋ እና ሙስሊም ካልሆነው ህብረተሰብም የሞራል ድጋፍ በማግኘት የበለጠ እየተጠናከረ ይገኛል፡፡ እንዲያውም በቅርቡ መንግስት ህገ-መንግስታዊ ጥያቄያችንን ለመመለስ ዝግጁ ሆኖ ባለመገኘቱ ከዚህ በኋላ ትግላችንን የምናካሂደው የስርዓት ለውጥ ለማምጣት ጭምር ይሆናል በማለት ማስጠንቀቂያ ያሉትን ቢጫ ካርድ ለመንግስት በአደባባይ እስከ ማሳየት ደርሰው ነበር፡፡
እንግዲህ እነዚህን እና ሌላም መሰል በሀገራችን እየታዩ ያሉ ወቅታዊ የፖለቲካ እንቅስቃሴዎችን ስንመለከት በእርግጥም አሁን ላይ ስለ ሰላማዊ ትግል በዝርዝር መነጋገር እና መወያየቱ ተገቢ ሆኖ እናገኘዋለን፡፡ ለመሆኑ ሰላማዊ ትግል ምን ማለት ነው? ከኢትዮጵያ ነባራዊ ሁኔታ አንፃርስ ምን ያህል አዋጪ ነው? ቀጣዩ ጽሁፍ በሰላማዊ ትግል ዙሪያ ግንዛቤ ለማስጨበጥ ይሞክራል፡፡
የሰላማዊ ትግል ምንነት
ሰላማዊ ትግል ትልልቅ የአለማችን የፖለቲካ ምሁራን ጭምር “ትክክለኛው አንባገነኖችን የማስወገጃ መሳሪያ ነው” ሲሉ የሚመሰክሩለት ትልቅ ህዝባዊ መሰረት ያለው የትግል ስልት ነው፡፡ ስልቱ ከትጥቅ ትግል በተለየ ሁኔታ ብዙ የህይወት መስዋትነት ሳያስከፍል ፣ ዜጎችን ለስደት ሳይዳርግ ፣ በንብረት ላይ ውድመት ሳያስከትል አንባገነኖችን ማስወገድ በማስቻሉ ተመራጭ ለመሆን በቅቷል፡፡
ከሰላማዊ ትግል ጋር በተያያዘ በፃፋቸው መፅሐፎቹ ዓለም አቀፍ እውቅናን ማትረፍ የቻለው የፖለቲካ ሳይንስ ተመራማሪው ጅን ሻርፕ “From Dictatorship to Democracy” በተሰኘው መፅሐፍ ላይ በግልፅ እንዳብራራው ፤ሰላማዊ ትግል በዋናነት ስነ-ልቦናዊ፣ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ ስልቶችን አጣምሮ በመጠቀም ሰላማዊ በሆነ መንገድ የሚካሄድ ትግል ነው፡፡ ጅን ሻርፕ አፅኖት በመስጠት አንደገለፀው፤ በራሱ የሚተማመን ህዝብ፣ ብልህነት የተሞላበት ስትራቴጅ፣ ስነ-ስርዓታዊ እና ደፋር እርምጃ በጥምረት ካሉ ከላይ የተጠቀሱት ስልቶች ማንኛውንም ዓይነት አንባገነን ስርዓትን በቀላሉ ማፈራረስ የሚችሉ ናቸው፡፡
ጅን ሻርፕን ጨምሮ ብዙ የፖለቲካ ምሑራን እንደሚስማሙበት ሰላማዊ ትግል ከሌሎች የትጥቅና የአመፃ የትግል ስልቶች በተሻለና አንድን ህዝብ ወደ ዲሞክራሲያዊ ስርዓት ማሸጋገር የሚያስችሉ ናቸው የትግል ስልት ነው ፡፡ ፕሮፌሰር መስፍን ወልደ ማርያም “ስልጣን ፣ ባህልና አገዛዝ…” በሚለው መፅሐፋቸው “በእኔ አስተሳሰብ የትጥቅትግል ለብዙ ዓመታት ስንተላለቅ የኖርንበትና የምናውቀው ነው ፤ ሰላማዊ የፖለቲካ ትግል ግን በጭራሽ አዲስ ነው ፤በትጥቅ ትግል አንዱን ጨቋኝ በሌላው እየለወጥን የአገዛዝን ባህል አጠነከርነው እንጂ ስልጣንን ለመግራትአልቻልንም…” በማለት የኢትዮጵያውያንን ያልተሳካ የትግል ታሪክ በመጥቀስ ሰላማዊ ትግል ለዲሞክራሲ ግንባታ የተሻለ አማራጭ መሆኑን ያስረዳሉ፡፡
በሰላማዊ ትግል ውስጥ ዜጎች የስልጣን ምንጭ የመሆናቸውን ታላቅ ሚስጥር ከመረዳት ባሻገር በተግባር ስለሚተገብሩት በቀጣይነት ስልጣን ላይ የሚወጣው አካል አንባገነን የመሆን እድል አይኖረውም ፤ ልሁን ቢል እንኳን ህዝቡ ፍፁም ያን የሚሸከም ትከሻ ስለማይኖረው ውጤቱ ፈጣን ውድቀት መሆኑ አያጠራጥርም፡፡
እንደሚታወቀው ግብፃውያን የጦር መሳሪያ ታጥቀው ግዙፉን አንባገነናዊ የሙባረክ አገዛዝ ለመታገል አልሞከሩም፡፡ ይልቁንም በመላ ሀገሪቱ የስራ ማቆም አድማ በማድረግ ሰላማዊ የተቃውሞ ድምፃቸውን እያሰሙ እጅ ለእጅ ተያይዘው አደባባይ መውጣትን ነበር የመረጡት፡፡ ይህንም በማድረጋቸው ግዙፉን አገዛዝ በትንሽ መስዋዕትነት ማስወገድ የቻሉ ሲሆን ፤ በምትኩም በዲሞክራሲያዊ መንገድ የመረጡትን አካል ስልጣን ላይ ማውጣት ችለዋል፡፡ እዚህ ላይ የግብፃውያን ትግል የቅርቡ ጊዜ ክስተት በመሆኑ ለሁሉም ሰው በቀላሉ ሊታወስ ይችላል በሚል እሳቤ እንደምሳሌ ይጠቀስ እንጂ በዓለማችን የበርካታ ሀገራትም ይህን መሰሉ ህዝባዊ ድል ብዙዎችን አስፈንጥዟል፡፡ ይህንን የትግል ስልት በመጠቀም በወቅቱ እንኳን ለማስወገድ ለመነቅነቅ ይከብዳሉ የተባሉ ሃያላን አንባገነኖችን በትንሽ መስዋትነት አንኮታኩተው በማስወገድ ዲሞክራሲያዊ ስርዓት ገንብተዋል፡፡ ምሳሌ ከሚሆኑን መካከል ጥቂቶቹን ለመጥቀስ ያክል፡- ህንዳውያን በጋንዲ መሪነት በወቅቱ የነበረውን የእንግሊዝ አንባገነናዊ ቅኝ አገዛዝ ማስወገድ የቻሉ ሲሆን ፤ ፊሊፒንሶችም በአውሮፓውያን አቆጣጠር በ1986 የፈርዲናንድ ማርኮን አገዛዝ አፈራርሰውበታል፡፡ በተመሳሳይም በሰርቢያ ፣ በጆርጅያ እና በዩክሬን ዜጎች ይህን የትግል ስልት በመጠቀም ስኬታማ የሚባል የስርዓት ለውጥ አካሂደዋል፡፡
በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ ስለ ሰላማዊ ትግል ሲሰበክ በርካታ አመታት ቢነጉዱም፣ በትግል ስልቱ ታግለው ለማታገል በተነሱት ዘንድ እናኳን የጠራ ግንዛቤ እንደሌለ ለማስተዋል አይከብድም፡፡ 21 ዓመታት ያስቆጠረው የኢህአዴግ ጨቋኝ አገዛዝ በሰላማዊ ትግል ሊወገድ እንደሚችል መገንዘብ የግድ ይላል፡፡ ስለ ሰላማዊ ትግል ምሉዕ ግንዛቤ መያዝ ብቻ ግን አንባገነኑን ስርአት ሊያስወግደው አይችልም፤ በመሆኑም ከኢትዮጵያ ህዝብ ጋር በቀላሉ ሊዋሀድ የሚችል የሰላማዊ ትግል ዘዴ በጥናት መምረጥ አስፈላጊ ነው፡፡
የሰላማዊ ትግል ዘዴዎች
ብዙ ጊዜ ስለ ሰላማዊ ትግል ሲነሳ ብዙ ሰዎች ወደ አዕምሯቸዉ ቶሎ የሚመጣላቸው ሰላማዊ ሰልፍ ፣ የስራ ማቆም አድማ እና የመሳሰሉ በጣም ጥቂት በተለምዶ የሚታወቁ የትግሉ ዘዴዎች ብቻ ናቸው፡፡ ሆኖም ግን ሰላማዊ ትግል በርካታ የትግል ዘዴዎችን በስሩ አቅፎ የያዘና በጥናት የሚመራ የትግል ስልት ነው፡፡ በአሁኑ ወቅት የተለያዩ መረጃዎች እንደሚጠቁሙት በዓለማችን ከ250 በላይ ሰላማዊ የትግል ዘዴዎች በግልፅ ተለይተው ታውቀዋል፡፡ እነዚህ ዘዴዎች ጠቅለል ባለ መልኩ በሶስት ዋና ዋና ክፍሎች የሚመደቡ ሲሆን ፤እነርሱንም ሰላማዊ ተቃውሞናማግባባት (Nonviolent protest and persuasion) ፣ ትብብር መንፈግ (Noncooperation) እና ሰላማዊ ጣልቃመግባት (Nonviolent intervention) በመባል ይታወቃሉ፡፡
ተቃውሞና ማግባባት፡- ይህ የሰላማዊ ትግል ዘዴ 53 ዓይነት ዝርዝር ዘዴዎችን በስሩ ይዟል፡፡ ለምሳሌ፡- የተቃውሞ ጉዞ እና ሰልፍ ማካሄድ፣ የስራ ማቆም አድማ ፣ የተቃውሞ ፊርማ ማሰባሰብ ፣ የመማፀኛ ፊርማ ማሰባሰብ ፣ የአንባገነኖችን ኢ-ፍትሀዊ እርምጃ በተለያዩ የመገናኛ ዘዴዎች ማውገዝ ፣ የተቃውሞ አርማዎች እና ምልክቶች የታተሙባቸውን ልብሶች መልበስ ፣ የተቃውሞ ተምሳሌታዊ ቁሳቁሶችን ማሳየት ፣ በየሀይማኖቱ ሕዝባዊ የፀሎተ ምህላ ፕሮግራሞችን ማዘጋጀት ፣ ወካይ ተምሳሌታዊ የተቃውሞ ድምፆችን ማውጣትና መጠቀም ፣ በተለያየ መልኩ የባለስልጣናትን መጥፎ ተግባር ማጋለጥ ፣ ባለስልጣናትን መንቀፍ፣ ማሽሟጠጥ፣ መዝለፍ፣ በአንባገነኖች የተገደሉ ሰዎችን በማሰብ ፕሮግራሞችን ማዘጋጀት ፣ መንግስታዊ ስብሰባዎችን ረግጦ መውጣት እና የመሳሰሉት ናቸው፡፡ ቶማስ ዌበር “Nonviolence: An Introduction” በሚለው ፅሑፉ እንዳብራራው እነዚህ ዘዴዎች የአገዛዙን ወንጀልና በደል አጉልተው የሚያሳዩ እና ለውጥ መፈለጋችንን ለዓለም ህብረተሰብ መልዕክት የሚያስተላልፉ እንዲሁም አገዛዙ ከወዲሁ የተጠየቀውን እንዲፈፅም የሚያግባቡ ዘዴዎች ናቸው፡፡
ጅን ሻርፕ ከዚህ ጋር በተያያዘ እንደገለፀው ዘዴዎቹ ግልፅ የተቃውሞ መልዕክት ማስተላለፋ ከማስቻላቸው ባሻገር ምልዓተ ህዝቡን ያሳተፈ ከባድ ትብርር ነፈጋን ለማካሄድ እንዲሁም ቀጣይ ተቃውሞዎችን ለማድረግ በእጅጉ ይረዳሉ፡፡
ትብብርን መንፈግ፡- ይህ ዘዴ ለአገዛዙ ፣ በአገዛዙ ስር ላሉ ማንኛውም ተቋማት ፣ ለባለስልጣናቱ ፣ ለአፋኝ ህጎቻቸው ፣ ለተግባራቸው… የሚደረግን ማንኛውም አይነት ትብብር የመንፈግ ተግባርንን የሚመለከት ነው፡፡ ይህን ዘዴ ጅን ሻርፕ ማህበራዊ ትብብር መንፈግ ፣ ኢኮኖሚያዊ ትብብር መንፈግ እና የፖለቲካ ትብብር መንፈግ በሚሉ ሶስት ንዑሳን ክፍሎች የከፍሎ ተንትኖታል፡፡ ማህበራዊ ትብብር መንፈግ በሚለው ስር የመንግስት ባለስልጣናትን እና ደጋፊዎቻቸውን ማግለል፣ ማውገዝ፣ ከማህበራዊ ግንኙነት መነጠል፣ ማኩረፍ እና ግላዊ ትብብርን ለባለስልጣናት እና ደጋፊዎቻቸው መንፈግና የመሳሰሉት ይገኙበታል፡፡ ኢኮኖሚያዊ ትብብርን ከመንፈግ ጋር በተያያዘ ማንኛውንም መዋጮዎችን ማቆም ፣የስርአቱ ባለሟሎችና አጋፋሪዎች ንብረት በሆኑ የንግድ ድርጅቶችና ምርቶች ያለመገልገል፣ የገንዘብ ተቀማጭን ከመንግስትና ከመንግስት ደጋፊዎች ባንክ ማውጣት እና የመሳሰሉት ይጠቀሳሉ፡፡ የፖለቲካ ትብብር ከመንፈግ ጋር በተያያዘ ደግሞ ለወጉ የሚደረጉ ምርጫዎችን መቃወም፣ የመንግስት ተቋማትን መተው ፣ በመንግስት የሚደገፉ የተለያዩ ድርጅቶችን መተው/የንግድ ወይም ሌላ ሊሆን ይችላል/ ያጠቃልላል፡፡ በአጠቃላይ ህዝቡን ያሳተፈ ትብብር መንፈግ በአንባገነኖች ላይ ትልቅ የሚባል ተፅዕኖ ማድረስ የሚችል የትግል ዘዴ ነው ፡፡ ይህ ዘዴ አንባገነኖች ያላቸውን የኢኮኖሚ ፣ የማህበራዊና የፖለቲካዊ የበላይነት እንዲያጡ በማድረግ ለማንበርከክ ይረዳል፡፡
ጣልቃ መግባት፡- ጅን ሻርፕ “The Politics of Nonviolent Action, Boston, Porter Sergeant” በሚለው መፅሐፉ እንዳብራራው ዘዴው የአገዛዙን ተቋማት ፣ ፖሊሲዎች ፣ አሰራሮች ፣ መርሆች ፣ ግንኙነቶች… ፋይዳ በማሳጣት አንባገነናዊውን አገዛዝ እንዲንኮታኮት የሚያደርግ ነው፡፡ ይህ ዘዴ በስሩ ተከታታይ ሁሉን አቀፍ አድማ (የሰራተኞች ፣ የተማሪዎች ፣ የመምህራን ፣ የነጋዴዎች ፣ የላባደሮች…)፣ህጋዊነት ለሌላቸው ሕጎች ሙሉ በሙሉ አለመገዛት፣ ህገወጥ ፍርድን አለመቀበል ፣ አማራጭ ተቋማትን ማቋቋም…የሚሉ በርካታ ዝርዝር ዘዴዎችን ይዟል፡፡
የሰላማዊ ትግል ዘዴዎች አመራረጥ እና አተገባበር
የተለያዩ የፖለቲካ ምሁራን እንደሚናገሩት በማንኛውም መልኩ አንድ ህብረተሰብ ወደ ሰላማዊ ትግል ከመግባቱ በፊት በአካል በመገናኘት ወይም ደግሞ የተለያዩ የመገናኛ ዘዴዎችን በመጠቀም ምን አይነት የትግል ዘዴዎችን እንዴት መጠቀም እንዳለበት በሰፊው በመወያየት፣ ወጥ አቋም መያዝ እና ጥሩ እቅድ ማቀድ አለበት፡፡ እዚህ ላይ ይህን ውይይት በማስተባበር እና በመምራት ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች እና/ወይም የሲቪክ ማህበራት እና ልዩ ልዩ የህዝብ አደረጃጀቶች የአንበሳውን ሚና ሊጫወቱ ይገባል፡፡
የሰላማዊ ትግል ዘዴዎች የአንባገነኖችን ድክመት ከግምት ውስጥ በማስገባት እና በሀገሪቱ ውስጥ ያለውን የፖለቲካ ምህዳር ባገናዘ በመልኩ ሲተገበሩ ይበልጥ በተሳካ መልኩ አንባገነኖችን በፍጥነት ማስወገድ ያስችላሉ፡፡ በተመሳሳይ ክርስቶፐር ኤ.ሚለር “STRATEGIC NONVIOLENT STRUGGLE” በሚል ርዕስ ባዘጋጀው የስልጠና መመሪያ ላይ ይህን ሐሳብ ሙሉ በሙሉ በመደገፍ አፅኖት ሰጥቶ ፅፏል፡፡ እዚህ ላይ በሀገሪቱ ውስጥ ያለውን የፖለቲካ ምህዳር ባገናዘበ መልኩ ሲል ምን ለማለት ፈልጎ እንደሆነ ግልፅ ለማድረግ የሀገራችንን የፖለቲካ ምህዳር መገለጫ የሚሆን አንድ ምሳሌ በማንሳት መመልከት እንችላለን፡፡
እንደሚታወቀው በሀገራችን ኢትዮጵያ በቀላሉ አደባባይ በመውጣት ተቃውሞን ማሰማት ወይም የተቃውሞ ሰልፍ ማካሄድ አስቸጋሪ ነው፡፡ እዚህ ላይ በ97 የታየው ዘግናኝ የመንግስት የሐይል እርምጃ ለዚህ ዓይነተኛ ማሳያ ነው፡፡ እንዲህ አይነት ጠባብ የፖለቲካ ምህዳር ባለበት ሀገር የትግል ዘዴዎችን እንዲሁ በጅምላ ሳይሆን ሁኔታውን ባገናዘበ መልኩ መምረጥ እንዲሁም አጠቃላይ ትግሉን ስልታዊ በሆነ መንገድ ማካሄድ ያስፈልጋል፡፡ አለበለዚያ አንባገነኖች የሚወስዱት የአፀፋ እርምጃ ብዙ መስዋትነት ሊያስከፍለን ይችላል፡፡ ክርስቶፐር ኤ.ሚለር እንደሚጠቁመው እንዲህ አይነት ጠባብ የፖለቲካ ምህዳር ባለበት ሁኔታ እንደ ፀሎተምህላ፣ ባንዲራን እና ወካይነት ያላቸው የተቃውሞ ምልክቶችን ማሳየት ፣ የስራ ማቆም አድማ….. ያሉ ብዙም ለአደጋ የማያጋልጡ ዘዴዎችን መርጦ በእነርሱ ተቃውሞን መጀመር ብልህነት ነው፡፡ በመቀጠልም ማንኛውንም ማህበራዊ ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ ትብብሮችን ሙሉ በሙሉ በመንፈግ ስርዓቱ በሂደት ሲዳከም ጠንከር ወዳሉት ሰላማዊ ሰልፍ እና የመሳሰሉ የትግል ዘዴዎች መግባት ይቻላል፡፡ እንደ ክርስቶፐር ኤ.ሚለር ማብራሪያ ከዚህ በተጨማሪም ብዙ ህዝብን በአንድ ላይ የሚያሰባስቡ የተለመዱ ባህላዊ እና ሐይማኖታዊ ስነ ስርዓቶችን በመጠቀም ተቃውሞን በአደባባይ መጀመር ይቻላል፡፡
ከላይ ካነሳነው ሀሳብ ጋር በተያያዘ ደቡብ አፍሪካውያን የአፓርታይድ ስርዓትን ሲታገሉ የተቃውሞ ድምፃቸውን በአደባባይ ለማሰማት የተጠቀሙበትን ዘዴ እንደ ምሳሌ እንመልከት፡፡ በወቅቱ በደቡብ አፍሪካ የነበረው መንግስት ሰላማዊ ሰልፍ ማካሄድን በጥብቅ ከልክሎ ነበር፡፡ ስለሆነም ደቡብ አፍሪካውያን የተቃውሞ ድምፃቸውን በአደባባይ ለማሰማት ከሰላማዊ ሰልፍ የተለየ ሌላ ዘዴ መፈለግ ነበረባቸው፡፡ በመጨረሻ ጥሩ “ ዘዴ አገኙ፡፡ ዘዴውም የቀብር ስነስርዓት ለመፈፀም በሚሰባሰቡበት ጊዜ ተቃውሞን ማሰማት ነበር፡፡ ከዚያም ደቡብ አፍሪካውያን የወዳጃቸውን አስከሬን በክብር ተሸክመው በትልልቅ ጎዳናዎች ላይ እየተንጎራደዱ የተቃውሞ ድምፃቻን ማሰማት ጀመሩ ፤መንግስትም አትቅበሩ ብሎ መከልከል ስለማይቻል ዝም ብሎ ለመመልከት ተገደደ፡፡
በተመሳሳይ ብዙም ሳንርቅ እዚሁ በሀገራችን የመንግስትን በሐይማኖት ጣልቃ መግባት የተቃወሙ ሙስሊም ኢትዮጵያውያን የተቃውሞ ድምፃቸውን በአደባባይ ለማሰማት እየተጠቀሙት ያለው ዘዴ ሌላው በምሳሌነት ሊጠቀስ የሚችል ነው፡፡ ኢትዮጵያውያኑ ሙስሊሞች ፍፁም ሰላማዊ ሆነው በእጅ ምልክት፣አፍን በመሸፈን፣ ታላቅ የተቃውሞ ድምፅ በማሰማት እንዲሁም የተለያ የትርጉም ያላቸውን ቀለሞች በማሳየት ከአምልኮ ስፍራቸው ብዙም ሳይርቁ(በርግጥ ሐይማኖታዊ በአሎቻቸውን ሲያከብሩ በከተማዋ ዋና ዋና ክፍሎች ተቃውሟቸውን አሰምተዋል) ያሳዩት ተቃውሞ ብዙ ትምህርት ሊቀሰምበት የሚገባ ነው፡፡ በተለይም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ወደ ቃሊቲ የታሰሩ መሪዎቻቸውን በነቂስ ወጥተው በመጠየቅ መንግስትን የሚቃወሙበት መንገድ የተቃውሞ ሂደታቸውን በሳልነትና እያደገና እየሰፋ መምጣት፣ በተጨማሪም ከአምልኮ ስፍራዎች ባሻገር መተግበር መጀመሩን የሚያመላክት ነው፡፡ በአጠቃላይ የኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ሰላማዊ የትግል ዘዴ በጠባብ የፖለቲካ ምህዳርን መሰረት በማድረግ የትግል ዘዴዎችን በስልት በመምረጥ እራስን ከአንባገነኖች ጨካኝ የአፀፋ እርምጃ መከላከል እንደሚቻል እና እንዴት የተለመዱ ባህላዊ እና ሐይማኖታዊ ስነስርዓቶችን በመጠቀም ጠንካራ ተቃውሞ በአደባባይ ማሰማት እንደሚቻል ትልቅ ትምህርት የሚሰጥ ነው፡፡
ጅን ሻርፕ እንደሚያስረዳው የሀገርን የፖለቲካ ምህዳር መሰረት ባደረገ መልኩ የትግል ዘዴዎችን መምረጥ እና የትግል ስልትን መንደፍ ብቸኛ ከአምባገነኖች የሚሰነዘርን ዘግናኝ የአፀፋ እርምጃ መከላከያ ስልት አይደለም፡፡ ከዚህም ባሻገር ለፖሊስ እና መከላከያ ሰራዊት አባላት በግልፅ የትግሉን አላማ በማስረዳት፣ ለትግሉ ቀና እይታ እንዲኖራቸውና ሰላማዊነቱን እንዲረዱ የተለያዩ ስልቶችን ቀይሶ በመስራት የአንባገነኖችን እርምጃ በጉልህ መቀነስ ይቻላል፡፡ ያም ሆኖ ግን ልብ ሊባል የሚገባው ነገር ለነፃነት እና ለዲሞክራሲ በሚደረግ ሰላማዊ ትግል ውስጥ ከአንባገነኖች የሚሰነዘርን ጥቃት ሙሉ በሙሉ ማስወገድ የሚቻል አለመሆኑን ነው፡፡ አንባገነኖች የትግሉን እንቅስቃሴ ለማፈን ሲሉ እርምጃ ከመውሰድ ወደ ኋላ ላይሉ ይችላሉ፡፡ ሆኖም ግን እንደ ጅን ሻርፕ ማብራሪያ መሰል እርምጃዎች አንባገነኖች በአለም አቀፍ ደረጃ ፍፁም እንዲጠሉ ያደርጋቸዋል ፣ ትልቅ የዲፕሎማሲ ክስረት ይፈጥርባቸዋል፣ በሚታገለው ህብረተሰቡ ውስጥም እልህን እየፈጠረ ትግሉን የበለጠ ያቀጣጥለዋል፡፡ እነዚህ ያልታሰቡ ውጤቶችም የኋላ ኋላ በእኩይ እርምጃቸው እንዳይቀጥሉበት ያደርጋቸዋል፡፡
ጅን ሻርፕ እንደሚመክረው የህብረተሰቡ ቆራጥነት እና ስነ-ስርዓት የታከለባቸው ተቃውሞዎች እየተጋጋሉ በሚሄዱበት ወቅት በተመሳሳይ ሁሉን አቀፍ ትብብር የመንፈግ እርምጃዎች እየጨመሩ እና እየተጠናከሩ መሄድ አለባቸው፡፡ ይህ ሲሆን የአንባገነናዊው አገዛዝ ውስጣዊ ድክመቶች እየጎሉ እና አገዛዙ እየተሽመደመደ ይሄዳል፡፡ በዚህ ወቅት ግን ሊሰሩ የሚገባቸዉ ወሳኝ ጉዳዮች አሉ፡፡ እነርሱም ነፃ ማህበራዊ ፣ ኢኮኖሚያዊ ፣ ባህላዊ እና ፖለቲካዊ ተቋማትን ማቋቋም እና ያሉትንም ማጠናከርን የሚጨምሩ ናቸው፡፡ እንደ ምሁሩ ማብራሪያ የእነዚህ ተቋማት ማቆጥቆጥ ለትግሉ አለም አቀፋዊ ተቀባይነትን የሚያስገኝለት ሲሆን ፤ በተጓዳኝ አንባገነናዊው አገዛዝ የሚደርስበት አለምአቀፋዊ ውግዘት እንዲጠናከር ያደርጋል፡፡
በሰላማዊ ትግል ውስጥ
ያሉ ቁልፍ ነገሮች
በሰላማዊ ትግል ላይ ጥናት ያደረጉ ምሑራን አፅኖት ሰጥተው እንደሚናገሩት አንድ ሰላማዊ ትግል የታቀደለትን ግብ ይመታ ዘንድ ብልህና ቆራጥ አመራር የሚያስፈልግ ቢሆንም በዋናነት በራሱ የሚተማመን ህዝብ ፣ ብልህነት የተሞላበት የትግል ስትራቴጂ እና ደፋር እርምጃ በጥምረት ሊኖሩት ይገባል፡፡ እነዚህ ሦስት መሰረታዊ ነገሮች በጥምረት ባሉበት ሁኔታ ማንኛውም ሰላማዊ ትግል መጨረሻው ደማቅ ድል ነው፡፡ አንባገነኖች ወደዱም ጠሉም አይናቸው እያየ የገነቡት እኩይ ስርዓታቸው መፈራረሱ እና እነርሱም በህዝብ እጅ ላይ መውደቃቸው የማያጠያይቅ ጉዳይ ይሆናል፡፡ ሆኖም እነዚህ የተጠቀሱት ሦስት ነገሮች እንዳሉ ሆኖ ከእነርሱ ባሻገር ሌላ ተጨማሪ ለሰላማዊ ትግል ስኬታማነት ቁልፍ ናቸው ተብለው የሚጠቀሱ እና በማንኛውም ሰላማዊ ትግል ውስጥ ሊሟሉ የሚገባቸው መሰረታዊ ነገሮች አሉ፡፡
ከእነዚህ በሰላማዊ ትግል ውስጥ ቁልፍ ከሚባሉ ነገሮች ውስጥ አንዱ እና ግንባር ቀደሙ አንድነት ነው፡፡ “ድር ቢያብር አንበሳ ያስር” እንደሚባለው ሁሉ በሰላማዊ ትግል ወቅት የሁሉም ህብረተሰብ ክፍል በአንድነት መቆም አንባገነኖችን በፍጥነት ብዙ ጉዳት ሳያደርሱ እንዲንኮታኮቱ ያደርጋል፡፡ ይህንን በተመለከተ ዶ/ር ሲንቲያ ቦአዝ “Nonviolent Revolution Clarified: Five Myths and Realities Behind Egypt’s Uprising” በሚለዉ ፅሑፋቸው እንዳስነበቡት ከግብፃዊያን የሰላማዊ ትግል የስኬት ሚስጥሮች መካከል አንድነት አንዱ እና ዋናው ነበር፡፡ ይህንን ቁልፍ የሰላማዊ ትግል ቁልፍ ነጥብ ከኢትዮጵያ ነባራዊ ሁኔታ ጋር አያይዘን እንመልከት፡፡ ኢህአዴግ የኢትዮጵያውያን አንድነት የስልጣን እድሜውን እንደሚያሳጥረው አስቀድሞ በመረዳቱ ህዝቡን በክልል፣በብሄር፣በሐይማኖት እና በተለያዩ መደቦች በመከፋፈል የልዩነትና የጥላቻ ዘርን ዘርቷል፡፡ በተለያዩ ወቅቶችም የተደራጁ የለውጥ እንቅስቃሴዎችን ለማክሰም ከሚጠቀምበት የሃይል እርምጃ ጎን ለጎን አንዱን በአንዱ ላይ በጠላትነት በማስነሳት አንድነትን በማጥፋት የስልጣን እድሜውን ሲያራዝም ቆይቷል፡፡ ስለዚህም ኢህአዴግን ለመጣል የሚደረግ ትግል በተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ውስጥ የአንድት መንፈስን ማኖርና ልዩነቶችን ማቻቻል አስፈላጊ ነው፡፡
ከአንድነት ቀጥሎ ለአንድ የሰላማዊ ትግሉ መሳካት ቁልፍ ተደርጎ የሚጠቀሰው ስነ-ስርዓት (Discipline) ነው፡፡ ብዙ ምሑራን አንድ ሰላማዊት ትግል የአንባገነኖች ትንኮሳ ቢፈታተነውም እንኳን ሰላማዊ ስነ-ስርዓቱን በጠበቀ መልኩ መካሄድ ይገባዋል በማለት ያሳስባሉ፡፡ እንደ እነርሱ ማብራሪያ አንድ ትግል ፍፁም ስርዓቱን በጠበቀ መልኩ ሰላማዊ በሆነ መንገድ ከተካሄድ አንባገነኖች በሐይል ጣልቃ ለመግባት ይቸገራሉ፡፡ ይህም የሚከፈለውን የህይወት መስዋዕትነት በከፍተኛ ደረጃ ዝቅተኛ እንዲሆን ያደርጋል፡፡ ይህ ሳይሆን ቀርቶ ሰላማዊው ተቃውሞ ወደ ሐይል አመፅ ከተለወጠ ግን ለአንባገነኖች የሀይል በትራቸውን እንዲያነሱ በር ይከፍትላቸዋል፡፡
ከስነስርአት ጋር በተያያዘ አንድ የኢትዮጵያውያን ታጋዮችን የቅርብ ጊዜ ተሞክሮ መጥቀስ ይቻላል፡፡ ባለፈው አመት አጋማሽ ላይ የጋመውን የሙስሊም ምዕመናን ተቃውሞ ወደ ግጭት እንዲለወጥ መንግስት የተለያዩ ያልተሳኩ ጥረቶችን አድርጓል፡፡ ከዚህ ጥረት ውስጥ የሚጠቀሰው ምዕመናኑ ተቃውሟቸውን በሚያሰሙበት ወቅት የከተማ አውቶብሶችን ከፊታቸው በመደርደር ለጥቃት ማመቻቸቱ ነው፤ ምዕመናኑ ግን ይህን ተንኮል አስቀድመው በመረዳታቸው “አንሰብርም…አንሰብርም” በማለት ስነስርአታቸውን አሳይተዋል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም መንግስት አስርጎ ያስገባቸውን በጥባጮች በመገሰፅ፣በማጋለጥና በካሜራ በማንሳት ፍፁም ስነስርአት የተላበሰ ሰላማዊ ትግል በማድረግ ላጥ ናቸው፡፡ ዲሲፕሊን ከዚህ ባሻገር ጥቅም እንዳለው ጅን ሻርፕ እንዲህ ሲል ይገልፃል፡- “Nonviolent discipline is extremely important… the stark brutality of the regime against the clearly nonviolent actionists politically rebounds against the dictators’ position, causing dissention in their own ranks as well as fomenting support for the resisters among the general population, the regime’s usual supporters, and third parties.” ይህን ቃል በቃል ስንተረጉመው እንዲህ ይላል፤ “የሰላማዊ ትግል ዲስፕሊን እጅግ ጠቃሚ ነው… አንባገነኑ አገዛዝ ፍፁም ሰላማዊ በሆኑ ተቃዋሚዎች ላይ የሚወስደው የሀይል እርምጃ በራሱ የስልጣን ተዋረድ ውስጥ አለመግባባት በመፍጠር በራሱ ላይ ችግር ከማስከተሉ ባሻገር ለተቃዋሚዎች ከብዙኃኑ ህዝብ ፣ ከራሱ ከአገዛዙ ደጋፊዎች እና ከሌላ ሦስተኛ ወገን የፖለቲካ ድጋፍ ያስገኛል፡፡”

Feb 22, 2013

The power of non violence!!!

አንድ ነገር ፍርድ ቤት ሲቀርብ ፈረንጆቹ በሕግ ቋንቋ አንድ ሰው ጥፋተኛ ነው ለማለት ከመጠራጠር ባለፈ ወይም ምንም ዓይነት መጠራጠር በሌለበት ሁኔታ አሳማኝ መሆን አለበት ይላሉ፡፡ በእኛ እምነት በአባሎቻችን ላይ የቀረቡት ማስረጃዎች የሰነድ፣ የድምፅ ወይም የምስል ማስረጃዎች ከመጠራጠር ባለፈ ሊያሳምኑ የሚችሉ ናቸው ብለን አናስብም፡፡ አናምንምም፡፡ ግን መንግሥት መንግሥት ነው፤ ለጊዜው አቅም አለው፡፡ ስለዚህ አንድን ነገር እሱ በፈለገው ሊተረጉመውና ትርጉም ሊሰጠው ይችላል ከተባለ እኛ ሕግ እናከብራለን፤ ፍርድ ቤት የሰጠውንም ውሳኔ እንቀበላለን፡፡ ነገር ግን አምነንበታል ማለት አይደለም፡፡ ከጥርጣሬ ባለፈ አምነንበታል ማለት አይደለም፡፡ እኛም ብቻ ሳንሆን ዓለም አቀፍ ታዛቢዎችም የሚሉት ነገር ነው፡፡ ብዙ ሰዎች የፍርድ ቤቱን ሒደት ተከታትለዋል፡፡ ብዙ ጊዜ የምንሰማው ከጥርጣሬ ባለፈ የሚያሳምን አይደለም የሚል አስተሳሰብ አላቸው፡፡ እኛ እውነተኛና በትክክል ከጥርጥር ባለፈ የሚያሳምን ነገር ቢገኝባቸው፣ ሕግ እንዲከበር እንፈልጋለን፡፡ መንግሥትም ተዓማኒ እንዲሆን እንፈልጋለን፡፡ ተግባሩና ድርጊቱ አዎ ትክክል ነው፤ የተሰጠው ፍርድም ትክክል ነው ብለን እንቀበላለን፡፡ ምክንያቱም ሕግ እንዲከበር ስለምንፈልግ፡፡ በአገራችን በእውነት ላይ የተመሠረተ ፍርድ ቅዱስ ነው፡፡ ከሰማይ በታች የተከበረ ነገር ነው፡፡ ስለዚህ ትክክለኛ ይሁን ነው ጥያቄያችን፡፡ ካልሆነ ግን የግዴታ ሥራ ነው ማለት ነው፡፡ አለቃ አዟል፣ መንግሥት አዟል በሚል ትክክል ያልሆነውን ፍርድ ተቀበሉ ከተባለ ፍርዱን እንቀበላለን፤ ልባችን፣ ነፍሳችን፣ ሕይወታችንና ኅሊናችን ግን አይቀበለውም፡፡  

The power of non-violence!!! must watch!!! Sobukwe

ESAT Kignit OSLO Norway Artist Tamagn Beyene Part II 22 February 2013 ...

ከቫንኮቨር ፀደንያ ቅድስት ማሪያም ቤተክርስትያን የተሰጠ የአቋም መግለጫ



በስመ አብ በወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ አሜን!!
Ethiopian-Orthodox-Church-Holy-Synod

በሕጋዊውና በብፁእ አቡነ መርቆሪዮስ የሚመራው የኢትዮዽያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ያስተላለፈዉን የአቋም መግለጫ ስለመደገፍ፡፡

ለአምላካቸዉ ለእግዚአብሄር አምላክነት በግልፅ ስለመሰከሩና ስለተጋደሉ አባቶቻችን በቅዱሳን መጻህፍት እንደተፃፈው በብሉይ ኪዳን ነቢያት አባቶቻችን ፣ በአዲስ ኪዳን ሐዋሪያትአባቶቻችን ፣ ባደረጉት ተጋድሎዎች ተጠብቆ የኖረዉን ስርዓት እኛም በዚህ ዘመን የምንገኝ በክርስቶስ ደም የቆመችዉን የኢትዮዽያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያናችንን ዶግማና ቀኖናዋን ሳይፋረስ የመጠበቅና የማስጠበቅ ብሎም ለትውልድ የማስተላልፈ ክርስቲያናዊ አደራ አለብን፡፡
በመሰረቱ ወደ ኋላ ዞር ብልን ስንመለከት የትኛውም ነብይ ወይንም ሐዋሪያ ምንም አይነት ፈተና ሳያገኝ ቅድስናን ወይንም ነብይነትን የተቀበለ የለም፡፡ አንገታቸውን ለሰይፍ ፣ ቆዳቸውን ለስለት፣ ሰውነታቸውን በድንጋይ ተወግረው ስለ እግዚሃቢሄር አመላክነት ለመመስከር ሕይወታቸውን መስዋእት በማድረግ ይህንን ሃይማኖታችንን ለቀጣዩ ትውልድ አቆይተውልናል፡፡
ታዲያ እኛም ዛሬ እንደ አባቶቻችን የቤተ ክርስቲያናችን ጉዳይ ያገባናል እንላለን፡፡ ለመላው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን አማኞች አወዛጋቢ የነበረው የሁለቱ ሲኖዶሶች ጉዳይ በእርቅና በሰላም መንገድ እንዲፈታ ከቤተክርስቲያንዋ አብራክ የወጡት ወገኖቻችን ላለፉት ሶስት አመታት የእርቁን ሂድት ሲያካሂዱ እንደነበር በዜና ማሰራጫዎች በስፋት ሲነገርበትና ስንከታተለው ሰንብተናል፡፡
ከጅምሩ በቅንነትና ለአንድንት ያልትንሳውና የመንግስት እጅ ያለበት የአዲስ አበባው ሲኖዶስ በአባ ዻውሎስ እልፈት የተፈጠረውን አጋጣሚ ተጠቅሞ ያለ አግባብ በቀድሞው የወያኔው ጠቅላይ ሚኒስተር በነብሩት በአቶ ታምራት ላይኔ ትእዛዝ የተናደውን የቤተክርስትያንዋን ቀኖና እንደማስትካከል ዛሬም እነ አባይ ፀሀይ በሃይማኖታችን ጣልቃ በመግባት የእርቁን ሂደት ሳይቋጭ አዲስ ፓትሪያርክ ለመሾም እየትዘጋጁ ይገኛሉ፡፡ የዛሬ ዋና መልእክታችን በገሀድ እየተፈፀመና እየተነገረ ያለዉን ለኦርቶዶክስ ምእመናን በድጋሚ ለማሰማት ሳይሆን በስደት የሚገኘው ሕጋዊው ሲኖዶስ ያወጣውን መግልጫ ሙሉ በሙሉ እንደምንደግፍ ለማሳወቅ እና ዛሬም እንደትላንትናዉ ከአባቶቻችን ጎን በፅናት እንደምንቆም እኛ የፀደንያ ቅድስት ማሪያም ልጆቻቸው በአንድ ድምፅ እንገልፃለን፡፡
ልማት ማለት የነበረዉን እየናዱ ታሪክን እየደመሰሱ ከሆነ ጥፋት እንጂ ልማት አንለዉም፡፡ ለዘመናት የቆየዉንና እንደ ሀገር ቅርስ የሚታየዉን ቤተክርስቲያናችንን እያፈራረሱ የሸንኮራ ተክል መትከል ማለት የሀገርን ሀዉልትና የታሪክ አሻራን ከምጥፋት ለይተን አናየውም፡፡ እንደዋልድባ ከመሳሰሉት ገዳማት ሙሁሮችና ሊቆች የሚፈልቁበት ስፍራ በልማት ስም ማፈራረስ ማለት ጅረቱን ለማቆም ምንጩን ማድረቅ እንደሚሉት ሁሉ ይህ የሀይማኖት፣የባህልና የአገር ማጥፋት ሴራ ክርስትያን ወገኖች ልናስተዉልና በጋራ ልንቋቋመው የሚገባ ጉዳይ ነው፡፡
ዛሬም ለዚህች አገር በውጪው አለም ተሰደው ወያኔ በቤተክርስቲያናችን ዉስጥ የሚያደርገውን ጣልቃ ገብነት እያጋለጡና እየተፋለሙ ኢትዮጵያዊነትን እንደ ችቦ አቀጣጥለው ለቀጣዩ ተውልድ እያስትላልፉ ያሉት አባቶቻችን ትላንትም የጣሊያንን የጠላት ሀይል ታቦትና ካህናትን ጭምር በመያዝ መስዋዕትነትን ከፍለው አኛ ልጆቻቸው በነፃነትና በክብር እንድንኖር ያደረጉት እነኚሁ አባቶቻችን ናቸው፡፡ ታዲያ ከዚህ አብራክ የወጣው ትውልድ ግን አገርና ሀይማኖት ሲጠፋ በየምክንያቱ ተከፋፍሎ አንገቱን ደፍቶ በባይተዋርነት መኖርን የመረጠ ይመስላል፡፡
ከፊታችን ለተጋረጠው ችግር ዝምታና አንገት መድፋቱ መፍተሄ አንደማይሆን አውቀን እውነተኞች ኢትዮጵያውያንና የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ልጆች እርስ በእርስ ያለውን ንትርክ ትተን ለአገራችንና ለቤተክርስቲያናችን ቅድሚያ በመስጠት እጅ ለእጅ ተያይዘን አጥፊውን በአንድነት እንቋቋም ብለን ጥሪያችንን እናቀርባልን፡፡
እግዚአብሄር አምላካችን ቤተክርስቲያናችንን እና አገራችንን ኢትዮጵያን ይጠብቅልን፡፡
ከፀደንያ ቅድስት ማሪያም ቤተክርስቲያን
ቫንኮቨር, ብሪቲሽ ኮሎምብያ

Feb 21, 2013

ዴንማርካዊው ወያላ


ዴንማርካዊው ሳይስ ፌልቦርግ ግሬገሰን የ19 ዓመት ወጣት ነው፡፡ ወጣቱ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን አጠናቆ ዩኒቨርስቲ ለመግባት በዝግጅት ላይ ነው፡፡
ሳይስ ዩኒቨርሲቲ ገብቶ የጋዜጠኝነት ትምህርትን መማር ስለመረጠ፣ ለትምህርቱ የሚረዳውን ልምድ ለማግኘት ወደ ኢትዮጵያ መጥቷል፡፡ ሳይስ ኢትዮጵያ ከመጣ ሁለት ወር ከግማሽ ሲሆነው፣ በቆይታውም በዝግጅት ክፍላችን በተለማማጅ ጋዜጠኝነት የተለያዩ ማህበራዊ ጉዳዮችን (በእንግሊዝኛው ጋዜጣ ላይ) በጽሑፍ ሲዳስስ ቆይቷል፡፡ ወጣቱ ኢትዮጵያ ሲገባ ቀልቡን ስለሳቡት የታክሲ ረዳቶች ለመጻፍ በማሰብ ከአስራ ሦስት ቀናት በፊት (ዕለተ ዓርብ)  እነሱ የሠሩትን ሠርቶ ስለወያልነት ቀኑ የጻፈውን ተርጉመን እንደሚከተለው አቅርበናል፡፡     

 ዕለቱ ልክ እንደአብዛኛዎቹ ቀናት ሞቃታማ፤ ፀሐዩም ሃሩር ነበር፡፡ የታክሲ ተሳፋሪዎች ከምታቃጥለው ፀሐይ ለማምለጥ፣ መጠለያ ለማግኘትና ወዳሰቡበት ቦታ ለመድረስ ታክሲ ውስጥ ለመግባት ይጣደፋሉ፡፡ አዲስ አበባ ውስጥ በፍጥነት የሚነጉዱ ሚኒባሶችን በፍጥነት ማውራት ከሚችሉ ወያላዎቻቸው ጋር መመልከት የዘወትር ክስተት ነው፡፡ ይህን ክስተት ለመጀመርያ ጊዜ ለተመለከተ ሁኔታውን ለመቀበል ይከብደዋል፡፡

በከተማዋ የፈረንጅ ወያላ ማየት የተለመደ ነገር ባይሆንም፣ በእለቱ ግን ከወሎ ሰፈር ቄራና ከቄራ ወሎ ሰፈር የሚጓዙ ተሳፋሪዎች የተመለከቱት ለየት ያለ ክስተት ነው፡፡ በእለቱ ለተከታታይ ዘጠኝ ሰዓታት በወያልነት ሥሰራ ሥራው ምን ያህል አስቸጋሪ እንደሆነ ተረድቻለሁ፡፡ ከሁለት ወራት በፊት ኢትዮጵያ ስመጣ፣ እዚህ ተወልጄ ባድግ ኖሮ የወያልነትን ሥራ እሠራ ነበር ብዬ አስቤ ነበር፡፡ የወያላዎቹ ወርሃዊ ክፍያ በጣም ትንሽ እንደሆነ ግን ተረድቻለሁ፡፡ ቢሆንም ግን ታክሲው የሚሄድበትን ቦታ በመስኮት ብቅ ብዬ እየጮህኩ መዳረሻ ቦታዎችን በመጣራት የወያልነቱን ሥራ ለመሥራት አስቤ ነበር፡፡

ሥራውን ለመሥራት ወስኜም ስለሥራው ጥልቅ መረጃዎችን ከሰጠኝ ከይድነቃቸው ንጋቱ ጋር በመሆን ካረፍኩበት ቤት ቅርብ ወደ ሆነ ታክሲ ማቆሚያ ሄድኩ፡፡ በመጀመሪያ ያነጋገርነው የታክሲ ሾፌር አብሬው እንድሠራ ካለመፈለጉም በላይ እብድ መስዬው ነበር፡፡ አሁንም ተስፋ ሳንቆርጥ ወደሌላኛው የታክሲ ሾፌር ስንሄድ እድላቸን ቀንቶ እሺታውን ገለጸልን፡፡ የሹፌሩ ዕድሜ 35 ሲሆን ስሙም ደረጄ ንጋቱ ይባላል፡፡ ይድነቃቸውም ለቀኑ እንደወያልነት ለምን መሥራት እንደፈለኩ ለደረጄ አስረድቶት ከጥቂት ድርድር በኋላ ተቀጠርኩ፡፡ ከቄራ ወሎ ሰፈር የሚሄደው መንገድ ቀጥ ያለ በመሆኑ ቦታውን ለማጥናትና በቦታው ለመሥራት ቀላል ነበር፡፡

ነገር ግን የታክሲውን በር መክፈትና መዝጋት እንዲሁም ገንዘብ መቀበልና መመለስ መለማመድ ነበረብኝ፡፡ ሥራው ከጠበኩት በላይ ከባድ ነበር፡፡ በመጀመርያ ላይ በር ለመዝጋት ስሞክር በእጄ ይዤያቸው የነበሩትን ሳንቲሞች መሬት ላይ በተንኳቸው፡፡ ለሥራው ዝግጁ ያልነበርኩ ቢሆንም ከአምስት ደቂቃ በኋላ ግን መንገዱ ላይ እየተዟዟርኩ ‹‹ወሎ ሰፈር ወሎ ሰፈር›› እያልኩ መጥራት ጀመርኩ፡፡

ከወሎ ሰፈር ቄራ ደርሶ መልሶችን ስናደርግ ከመኪናው ሳንቲምና ብር ይዤ ስወርድና መዳረሻውን ስጣራ አብዛኛው ሰው ይስቅብኝ ነበር፡፡ አብዛኛዎቹም ተግባብተውኝ ለመቁጠር በሚያዳግት ሁኔታ ለምን ይህንን ሥራ እንደምሠራ ሲጠይቁኝ ነበር፡፡ 

ሳንቲሞችን በእጄ በአግባቡ መያዝ ተቸግሬ ስለነበር መሬት ላይ ሲበተኑብኝ ለቅመው ይሰጡኝ ነበር፡፡ መልሳቸውም ስንት እንደሆነ ለማወቅ ግራ ሲገባኝ ስንት እንደምመልስላቸው ትክክለኛውን መጠን ይነግሩኝ ነበር፡፡ ደረጄም ተሳፋሪዎቹ በሥራዬ እንደተደሰቱ ሲነግረኝ ሥራውን የመሥራት ፍላጎቴ ያይል ነበር፡፡ ተሳፋሪዎቹ ሲወርዱ ‹‹አመሰግናለሁ›› እንዲሁም ‹‹መልካም ቀን›› ይሉኝ ነበር፡፡ እኔም ከ ሁለት ቢያጆ በኋላ ሳንቲሞችን ከእጄ አለማንጠባጠብ፣ ሂሳብ በትክክል መቀበልና መመለስ ቻልኩበት፡፡

የታክሲ ሹፌሩ ጥሩ እንግሊዝኛ ይናገር ስለነበር ጉዞ ላይም ሆነን እንዲመቸኝ አድርጎኛል፡፡ በየጉዞው መጨረሻ ላይ ተራ ጠብቀን ጉዞ እስክንጀምር ብዙ የዕረፍት ሰዓታት ነበሩን፡፡ በእነዚያ የዕረፍት ጊዜያትም በየታክሲ ማቆሚያው የሚያገኙኝ የታክሲ ሾፌሮች፣ ወያላዎችና መንገደኞች ሰላምታና ለዕለቱ ለምን ወያላ መሆንን እንደመረጥኩ በሚያቀርቡልኝ ጥያቄ ተጠምጄ ነበር፡፡ ይህ ሂደት የኢትዮጵያውያንን የተግባቢነትና የጓደኝነት መንፈስን እንድረዳ ስላደረገኝ ሁኔታው አስደንቆኛል፡፡ 

ከአምስት ቢያጆ በኋላ ሥራውን በደንብ እየተረዳሁ መጣሁ፡፡ ከዛ በኋላ ስድስተኛውን ቢያጆ ደረጄ በደረስንበት የታክሲ መዳረሻ ላይ ሳይቆም መንዳቱን ቀጠለ፡፡ ታክሲው ውስጥ ማንም ተሳፋሪ ባለመኖሩ በደረጄ ድርጊት ግራ ተጋባሁ፡፡ ከዚያም ደረጄ ሁኔታውን ሲያስረዳኝ በመስኮት ወጥቼ መዳረሻችንን እየጠራሁ ተሳፋሪዎችን እየለቀምን መሄድ እንዳለብን ነገረኝ፡፡ በዚህ ሁኔታም ተደናገጥኩ፡፡ ቀድሞ በነበሩን ቢያጆዎች ሒሳብ በመሰብሰብ ተጠምጄ ስለነበር በመስኮት ወጥቼ መዳረሻችንን አልተጣራሁም ነበር፡፡ ይልቁንም ደረጄ ሰዎችን ማየቱን ተያይዞ እናሳፍር ነበር፡፡ እየተጣራሁ የሚገቡት ተሳፋሪዎች የት እንደሚሄዱ ማወቅም ግራ ገብቶኝ ነበር፡፡ ቢሆንም ግን በሚሰጡኝ ሒሳብ የት እንደሚሄዱ ይገባኛል ብዬ ተስፋ አደረኩ፡፡  በታክሲው መዳረሻ ስንደርስ አንዳንድ ሰዎች ምንም ዓይነት ገንዘብ እንዳልከፈሉ አውቅ ነበር፡፡ ነገር ግን ያልከፈሉት ሰዎች የትኞቹ እንደነበሩ መለየት አልቻልኩም፡፡ ስለዚህ ተሳፋሪዎቹ ከታክሲው ሲወርዱ እየከፈሉ እንደሚሄዱ ተስፋ ባደረኩት መሠረት ያልከፈሉኝ በሙሉ እየከፈሉኝ ወረዱ፡፡ ከዚያ ያደረግነው ነገር ቢኖር ተሳፋሪዎችን በየመንገዱ እየለቀምን ከመሄድ ይልቅ ተራችንን ጠብቀን እየሞላን መሄድ ስለነበር በሁኔታው ተደስቼ ነበር፡፡

ምሳ ሰዓት ሲደርስ እጅግ ተርቤና በር የምከፍትበትና የምዘጋባቸው ክንዶቼ ዝለው ነበር፡፡ በሰፊው የምሳ ሰዓት እረፍታችን በርገር በላን ቡናም ጠጣን፡፡ ይህን ጊዜ ድካሜ ጠፍቶ ጉልበቴ ሁሉ ተመለሰ፡፡ ከምሳ ሰዓት በፊት በነበረው ቢያጆ በጣም ደስተኛ ነበርኩ፡፡ ምክንያቱም ሂሳቤን ቶሎ ሰብስቤና መልስ ሰጥቼ ስለነበር ከተሳፋሪዎች ጋር የማወራበትና መንገድ ላይ ያሉ ተሳፋሪዎችን የማስገባበት ጊዜ ነበረኝ፡፡ በዚህን ጊዜ በሥራዬ ጥሩ እንደሆንኩ ሲሰማኝ፤ ደረጀም በወያልነት መሥራት ስፈልግ አንድ ቀን ቀደም ብዬ ብነግረው አብረን ልንሠራ እንደምንችል ነገረኝ፡፡ ቢሆንም ግን ወያልነቱን ለዕለቱ የሠራሁት ለልምድ ብቻ ብዬ በመሆኑ መሥራት እንደማልፈልግ ብገልጽለትም፣ ከእሱ ጋር በነበረኝ ቆይታ ሥራዬን ስላደነቀና ኢትዮጵያ ስለነበረኝ ቆይታ ለረዥም ጊዜ በማውራታችን በጣም ደስተኛ ነበርኩ፡፡ 

የከሰዓት በኋላው ሥራ ከጠዋቱ ይልቅ የተጣደፈ ቢሆንም ሥራውን ስለተለማመድኩት ቀለል ብሎኝ ነበር፡፡ ቢሆንም ግን ክንዶቼ ይበልጥ እየዛሉ ነበር፡፡ ከመኪናው መውረድና ወደ መኪናው መግባት እግሮቼን ቢያደክሙትም መሄድ የነበረብንን ብዙ ቢያጆዎች ፈጽመናል፡፡ ጊዜው ሄዶ ፀሐይዋ መጥለቅ ስትጀምር የመጨረሻውን ቢያጆ ለመሥራት ተንቀሳቀስን፡፡ ክንዶቼ ሊቀነጠሱ የደረሱ እስኪመስለኝ ድረስ ቢደክመኝም ምኞቴን ስላሳካሁ ተደስቼ ፊቴ ላይ ከሚታየው ፈገግታ ጋር ደረጀን አመስግኜና ተሰናብቼ ከመኪናው ወረድኩ፡፡ በዕለቱ በእኔ ምክንያት ለሚደርስበት ኪሳራ 400 ብር ከፍዬዋለሁ፡፡ በውሎዬም የታክሲ ረዳቶች ሥራ ምን ያህል ጥረት እንደሚያስፈልገውና እንዴት ከባድ እንደሆነ ተረድቻለሁ፡፡ ሁኔታው ግን በጣም አስደንቆኛል፡፡

Feb 19, 2013

ክርስቲያኑ ኢትዮጵያዊ መብቱን ለማስከበር ያልቻለባቸውና የማይችልባቸው ምክንያቶች




  • ይህ ጽሑፍ የአቅማቸውን ጥቂት ነገር ለማድረግ የሚተጉትን ላይመለከት ይችላል።
(ደጀ ሰላም የካቲት 8/2005፤ ፌብሩዋሪ 15/2012/ PDF)፦ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በአገራችን በኢትዮጵያ እየተስፋፋ በመጣው እምነትን በነጻ የማራመድ መብት ገፈፋ ዋነኛ ተጠቂ ከሆኑት ኢትዮጵያውያን መካከል ኦርቶዶክሱ ክፍል ዋነኛ ተጠቃሽ ነው። በወታደራዊው የደርግ ዘመን የነበረውን ግፍና መከራ እንኳን ለጊዜው ብናቆየው “የሕዝብ ብሶት ወለደኝ” ያለው የኢሕአዴግ መንግሥት ከተመሠረተ ወዲህ ቤተ ክርስቲያናችን በዓይነ ቁራኛ ከመታየት እስከ የ“ነፍጠኛ ጎሬ” እስከመባል ድረስ ብዙ ዘለፋ አስተናግዳለች። ከዚያም ገፋ ሲል በአንዳንድ አክራሪዎች ምእመናኗ ታርደዋል፣ አብያተ ክርስቲያናት ተቃጥለዋል፣ ከየአካባቢው እንዲፈናቀሉ ተደርገዋል። ለዚህም በስልጣን ላይ ያለው ፓርቲ የሚያራምደው ፖሊሲ ሁነኛ ምክንያት ነው።

ከዚህ በፊት የተቻኮለ የፓትርያርክ ምርጫ፣ ‘የገበያ ግርግር …’ ይሆናል በሚል ርዕስ ነሐሴ 11/2004 ዓ.ም፤ ኦገስት 17/ 2012/ባቀረብነው ጽሑፍ ላይ እንዳተትነው ኢሕአዴግ ገና በትግል ላይ ከነበረበት ዘመን ጀምሮ ቤተ ክርስቲያናችንን በተመለከተ የያዘው አቋም “ቤተ ክርስቲያኒቱ የጠላት ወገን” እንደሆነች ያስቀመጠ፣ ሌሎች እምነቶችን በተለይም እስልምናን “በተጨቋኝነት” የፈረጀ ስለዚህም ይህንን የተጨቆነ እምነት “በማነቃቃትና ኃይል በመስጠት” ከኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ጋር እንዲገዳደር ያለመ፣ በመጨረሻም ቤተ ክርስቲያኒቱን ቀስ በቀስ በማዳከም የእርሱ አሽከር እንድትሆን በማድረግ ላይ ያተኮረ ነበር። ይህንን ዓላማውን ለማስፈጸምም ከዋናው የቤተ ክህነቱ አስተዳደር የተለየና የፓርቲውን ዓላማ የሚያራምድ ቤተ ክህነት ለመመስረት በመወሰን የረዥም ጊዜ ዓላማና ግብ ይዞ ሲንቀሳቀስ ቆይቷል። (አዲስ አበባን ከመቆጣጠሩ በፊት በትግራይ ፓርቲውን በፓርቲው የሚመራ ሁለተኛ ቤተ ክህነት አቋቁሞ እንደነበር ይታወሳል)።፡የራሱን አባላትም ወደ ታላላቅ ገዳማት በማስገባት በመነኮሳት ስም ዓላማውን እንዲያስፋፉ ሲያደርግ እንደቆየ የፓርቲው መሥራች ዶ/ር አረጋዊ በርሄ በመጽሐፋቸው አስፋፍተው ገልጸዋል።

ይህ መጽሐፍ ያተታቸው ብዙ ሐሳቦች አሁን በተግባር ላይ መዋላቸው በተግባር እየታየ ያለ እውነታ እንጂ መላምታዊ ሐቲት ወይም በአንድ ወቅት ብቅ ብሎ የጠፋ የፓርቲው ሐሳብ እንዳልሆነ ግልጽ ነው። በመነኮሳት ስም ያደራጃቸው አባላቱም በቤተ ክህነቱ የተለያዩ እርከኖች ላይ በመቀመጥ ቤተ ክርስቲያናችን የክርስቶስ ሳይሆን የአንድ የፖለቲካ ፓርቲ ዓላማ ማስፈጸሚያ እንድትሆን አስገድደዋታል። ወታደራዊው መንግሥት እንኳን ያላደረገውን የቤተ ክህነቱን መዋቅር ከዋናው እስከ አጥቢያው ካባ በለበሱ ካድሬዎች በማደራጀት ቤተ ክርስቲያኒቱ የክርስቶስ መንግሥት ሳይሆን የኢሕአዴግ መንግሥት አገልጋይ እንድትሆን አድርገዋታል።

ይህም ሳያንስ በልማትና በዕድገት ስም የቤተ ክርስቲያኒቱ ይዞታ ከመደፈሩም ባሻገር የገዳማት ርዕስ የሆነውን የዋልድባን ድንበር በመጋፋት እና የቅድስና ኑሮውን በመግሰስ አበው ገዳማውያን የመከራ ኑሮ እንዲኖሩ በማስገደድ ላይ ይገኛል። ታዲያ እዚህ ላይ ተያይዞ አብሮ የሚነሣው ነገር “ሃይማኖቱን የሚወደው፣ ለእምነቱና ለማተቡ ሟች የሆነው ክርስቲያን ሕዝብ እንዴት ዝም አለ? መንግሥትስ እንዴት የሕዝቡን ስሜት ከቁብ ሳይቆጥረው ቀረ? ሕዝቡንስ እንዴት እንዲህ ሊንቀው ቻለ? ሙስሊም ኢትዮጵያውያን ‘ድምጻችን ይሰማ’ ሲሉ የክርስቲያኑ ዝምታ ከምን የመነጨ ነው?” ወዘተ የሚለው ጥያቄ ነው።

እንደ እኛ እምነት ከዚህ የበለጠ መከራና ችግር በቤተ ክርስቲያኒቱ ላይ ቢወርድም አብዛኛው ክርስቲያኑ ሕዝብ፣ ካህናቱ እና ሲኖዶሱ ምንም ዓይነት የተቃውሞ ድምጽ ሊያሰሙ አይችሉም። የሚቃወሙ ጥቂት ድምጾች ከተገኙም በርግጠኝነት በውጪ አገር ካለው ክርስቲያን፣ ካህን ወይም ጳጳስ ብቻ ሊሆን ይችላል። እነርሱም ምንም ችግር እንደማይገጥማቸው እርግጠኛ ከሆኑ ብቻ ነው። የሩቁን ጊዜ ብንተወውና አሁን በመደረግ ላይ ያሉትን ሁለት የመብት ጥሰቶች ማለትም የዋልድባን ገዳም ማረስ እና ከሕዝቡ ይሁንታ ውጪ 6ኛ ፓትርያርክ ለመሾም (ለማስቀመጥ) የሚደረገውን ሩጫ እንኳን ለመቃወም ክርስቲያኑ ለምን እንዳልቻለ መጠየቅ እንችላለን። (የተቃወሙና የሚቃወሙ ጥቂት ድምጾች ቢኖሩም እነርሱም ከውጪ አገር የሚሰሙ ብቻ መሆናቸውን ሳንዘነጋ ነው ታዲያ)። ስለዚህም የዚህ ዝምታ ምንጩ የተለያየ ቢሆንም ለመወያያ እንዲሆኑ የሚከተሉትን ሐሳቦች እናቀርባለን።


  1. መብት የሚለውን ቁምነገር በትክክል አለመረዳት፤
  2.  

    ክርስቲያኑ ክፍል እንደማንኛውም ኢትዮጵያዊ ሁሉ “መብት” የሚለውን ቁምነገር በቅጡ ገና አልተረዳም። መብት ጠመንጃ በያዙ ሰዎች ችሮታ የሚታደለው እንደሆነ እንጂ ከእግዚአብሔር ያገኘው ነጻ ሥጦታ መሆኑን አይገነዘብም። ፊደል ያልቆጠረው ማይም ሕዝብ ብቻ ሳይሆን ኮሌጅ የበጠሰው ምሩቅም ቢሆን ተመሳሳይ ሐሳብ የሚያራምድ ሕዝብ ነው። ስለዚህም መንግሥት የሚያደርስበትን የመብት ገፈፋ ሲችል በመለመን፣ ሳይችል ደግሞ ጀርባውን አጉብጦ በመታገስ ወደመቃብር ይወርዳል እንጂ “መብቴ” ብሎ አይጠይቅም።


    አንድነት የለውም፤

      ከሌላ እምነት ተከታይ ኢትዮጵያውያን በተለየ ክርስቲያኑ ክፍል የተጎዳው አንድነት በማጣቱ ነው። ከሊቃነ ጳጳሳት ጀምሮ እስከ ጥቃቅን ማኅበራት ድረስ አንድነት የሚባል ነገር የለም። ጳጳሳቱ ተከፋፍለው ሁለት ሲኖዶስ አቋቁመናል ብለው ከሚነታረኩ ባሻገር ከእነርሱ በታች ያለውም እዚህ ግባ በማይባል በተለያየ ምክንያት የተከፋፈለ ነው። ይህንን ክፍፍል አንድ ሊያደርግ የሚችል ተአምር ካልተፈጠረ በስተቀር ሊያሰጋው የሚችል ተቃውሞ ሊመጣ እንደማይችል ኢሕአዴግም ጠንቅቆ ያውቃል። ስለዚህ ሕዝቡ ብዙ ቢሆንም፣ ምእመኑን ለእምነቱ ሟች ቢሆንም አንድነት እስከሌለው ድረስ ኃይሉ ከንቱ ይሆናል። ሆኗልም። ሙስሊሙ ሕብረተሰብ ከዚህ የተሻለ አንድነት አለው፤ ይህንንም አንድነቱን በዚህ አንድ ዓመት ባሳየው እልህ አስቆጨራሽ የመብት ትግል በገሃድ አሳይቷል። ፕሮቴስታንቱ ክፍል ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ የመንግሥት ቀኝ እጅ በመሆን በማገልገል ላይ በመገኘቱ የሥርዓቱ ዋነኛ ተጠቃሚና የሥርዓቱ ዋነኛ ደጋፊ ሆኗል።


      ትክክለኛ መረጃ የለውም፣

        ክርስቲያኑ ብቻ ሳይሆን አጠቃላይ ኢትዮጵያዊው ትልቅ የመረጃ እጥረት አለበት። መንግሥት የመገናኛ ብዙኃንን በሙሉ በግል አፍኖ በመያዙ ሕዝቡ የሚያየውም የሚሰማው ነገር የለም። ጋዜጦችና መጽሔቶች አሉ ከሚባሉ ጠፍተዋል የሚለው ይገልጻቸዋል። ያሉትም ቢሆን ውኃ ውኃ የማይል ጽሑፍ ከማንሸራሸር ውጪ መረጃ በመፈንጠቅ ሕዝቡን ከጨለማ ወደ ብርሃን ሊያመጡ የሚችሉ አይደሉም። አገልግሎት እንዲሰጡ የተፈቀደላቸው ሬዲዮኖች “ስፖርት፣ ሙዚቃ፣ ቫለንታይንስ ዴይ አደጋገስ” ወዘተ ካልሆነ ጠለቅ ያለ ሐሳብ ማቅረብ አይችሉም። አይፈረድባቸውም። የተለየ መረጃ ሊገኝበት የሚችለው ነጻ መስኮት (ኢንተርኔቱ) ደግሞ ተቆልፏል። ስለዚህ ይህ መረጃ በማጣት የታወረ ኅብረተሰብ ምኑን ከምኑ ሊያደርገው ይችላል?


        “እግዚአብሔር ያውቃል፣ የእግዚአብሔር ፈቃድ” በሚሉ ርዕሶች ዙሪያ ያለው የተሳሳተ የጽድቅ እና የኃጢአት ትምህርት፣

          አብዛኛው ክርስቲያን  እምነቱን አፍቃሪና አክባሪ ነው። መምህራኑን ይሰማል፣ ቃላቸውንም ይፈጽማል። ነገር ግን ከሚሰጡት ትምህርቶች አብዛኛዎቹ ሆን ተብሎም ይሁን በሌላ ምክንያት ሕዝቡን የሚያደነዝዙ፣ የጥንት ኦርቶዶክስ አባቶቹ እንዳደረጉት ለአገሩ፣ ለእምነቱና ለቤተሰቡ ከመሞት ይልቅ በቅኝ ግዛት እንደተያዙት ሌሎች አፍሪካውያን መጽሐፍ ቅዱሱን ገልጦ ሰማይ ሰማይ ብቻ የሚያይ ደካማ አድርገውታል። አባቶቹ አድዋ ላይ ታቦቱን ይዘው እንዳልውጡ፣ ሰማዕቱ አቡነ ጴጥሮስ ሰዉንም ምድሪቱንም ለፋሺስቶች እንዳይገዙ ገዝተው እንዳልተሰዉ፣ ብዙዎቹ አበው ለአገራቸውና ለእምነታቸው ደማቸውን እንዳላፈሰሱ አይነገረውም። ስለዚህም በስመ ኦርቶዶክስ የሚመራው ክርስትና ከጥንቱ “አትንኩኝ ባይ” ኦርቶዶክስ ጋር ምንም ግንኙነት ያለው አይደለም።

          የተሳሳተ ትርጉም እየተሰጣቸው ሕዝቡ እንዲደነዝዝባቸው ከሚያደርጉት ትምህርቶች መካከል “ሁሉንም ለእግዚአብሔር እንስጠው፣ “እግዚአብሔር ያውቃል፣ እኛ የእርሱን ጊዜ እንጠብቅ” የምትል የራስን ኃላፊነት ሳይወጡ በስንፍና የመቀመጥ አደንዛዥ ትምህርት አንዷ ናት። እግዚአብሔርማ ሁሉን ያውቃል። ምን ጥርጥር አለው። ነገር ግን አዋቂነቱ በዓለም ላይ የሚፈጸመውን ግፍና መከራ ሁሉ እንዲከወን እንደፈቀደ መቁጠር ኑፋቄ ነው።

          በዓለም ላይ በየሰከንዱ ብዙ ወንጀሎች ይፈጸማሉ። ያ ሁሉ ወንጀልና ሰቆቃ የእግዚአብሔር ፈቃድ ነውን? በርግጠኝነት አይደለም!!! እግዚአብሔር ያውቀዋል ግን? እንዴታ!! እግዚአብሔር የማያውቀው ምን ነገር አለ? የሰው ልጅ ግን በነጻ ፈቃዱ የሚፈጽመው ወንጀል ነው። ለዚህ ጥፋቱ ደግሞ በእግዚአብሔር ፊት ሲቆም ቅጣቱን ያገኝበታል።

          ከዚሁ አያይዘን ስንመለከተው በቤተ ክርስቲያናችን እና በአገራችን ላይ የሚፈጸመውን ግፍ እግዚአብሔር ያውቀዋል። ታዲያ ለምን ዝም አለ ለሚል ግብዝ መልሱ ሰዎች በነጻ ፈቃዳቸው ተጠቅመው ያደረጉት ነገር ነው የሚል ነው። ክፉዎቹ በክፋታቸው ተገፋፍተው ይህንን ሲያደርጉ እኛስ በመልካምነታችን ተጠቅመን የአቅማችንን ለማድረግ ያልቻልነው ለምንድር ነው?

          ከመጽሐፍ አንድ ምሳሌ እናንሣ። ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አልአዛርን ከሞት ሊያሥነሣው በሄደ ጊዜ የተፈጸመውን ማወቃችን ከላይ ለመግለጽ የፈለግነውን ሐሳብ ግልጽ ያደርገዋል። ታሪኩ በዮሐንስ ወንጌል ምዕራፍ 11 ላይ ይገኛል። አልአዛር ታመመ፣ ሞተ፣ ተቀበረ። ከተቀበረ ከአራት ቀን በኋላ ጌታ ወደዚያ ሥፍራ ሄደ። ከዚያም ከመቃብሩ ላይ ድንጋዩን አንሱ ብሎ ቤተሰቦቹን አዘዘ። ከዚያም አልአዛርን ከመቃብር አልጋ ከሞት ሸለብታ ቀስቅሶ ሕያው አደረገው። ከሞት ማሥነሣቱ ካልቀረ ድንጋዩን እንዲያነሱ ለምን አዘዛቸው? ለምን ሁሉንም ነገር ራሱ አልፈጸመውም? በዚህ የአልአዛር ድኅነት ውስጥ የሰው ድርሻ በቤተሰቦቹ ተሰርቷል፣ የእግዚአብሔር ድርሻ ደግሞ በራሱ በባለቤቱ ተሠርቷል። የሰው ድርሻ መቃብሩን መክፈት፣ የእግዚአብሐር ድርሻ ሙቱን ሕያው ማድረግ ነው። በዘመናችን ግን እያልን ያለነው “ሁሉንም ነገር አንተ ሥራው!!!” ነው። መቃብሩን አንተው ቆፍር፣ ሙቱንም አንተው አስነሳው፤ እኛ ዝም ብለን እንመለከትሃለን።  


          ሥር የሰደደ አድርባይነት መሰልጠኑ፤

            ቤተ ክርስቲያን ለረዥም ዘመን ከቤተ መንግሥቱ ጋር ተቀራርባ የኖረች እንደመሆኗ ሥልጣን ላላቸው ሰዎች ማጎብደድ፣ አድርባይነት እና እታይ-እታይ ባይነት ከጥንቱም ሰልጥኖብናል። በዘመናችን ደግሞ ገዝፎና ተስፋፍቶ ቀጥሏል። የጥንቶቹ መሪዎች ፓርቲ ስላልነበራቸው አባላትም አልነበሯቸውም። የአሁኖቹ መሪዎች ባለ ፓርቲ ስለሆኑ አድርባዮቹ የፓርቲዎቻቸው አባላት በመሆን መስቀልና ሽጉጥ ታጣቂ ካህናት አፍርተናል። በደርጉ ዘመን የኢሰፓ፣ በአሁኑ ደግሞ የኢሕአዴግ አባል ደባትር፣ ካህናትና መነኮሳት አያሌ ናቸው። ይህ አባልነትና አድርባይነት ከተራ ካህናት፣ ደባትርና መነኮሳት አልፎ (በዘመነ ኢሕአዴግ) ከጳጳሳቱ ደርሷል። አባል ያልሆኑትም ቢሆኑ ከዝምታ ውጪ ምንም ምርጫ የላቸውም። ስለዚህ አድርባይነቱ በቅርብ መፍትሔ ስለማያገኝ መከራችንም በቅርብ መፍትሔ ይገኝለታል ብሎ ለማሰብ ይከብዳል።


            መንግሥታት በፈቃደ እግዚአብሔር ሥልጣን ይይዛል የሚለው ትምህርት፣

              ከፍ ብለን ከጠቀስነው ጋር አብሮ የሚሄደው ጉዳይ መንግሥት የሆነ ሁሉ በእግዚአብሔር ፈቃድ ነው ሥልጣኑን ያዘው የሚል ሐሳብና ትምህርት ነው። ቤተ ክርስቲያንን የሚሰቅላትን “እግዚአብሔር ወዶ ፈቅዶ አስቀመጠው” ማለት ድንቁርና ካልሆነ ምን ይሆናል?


              ኃላፊነትን ለመቀበል መፍራት፣ ኃላፊነትን አለማወቅ፣ ኃላፊነትን ሁሉንም ለእግዚአብሔር መስጠት፣

                እንደተጠቀሰው ከርስቲያኑ ራሱን አቅም እያለው አቅም እንደሌለው፣ ዕውቀት እያለው እንደሌለው ስለቆጠረ ያለበትን ኃላፊነት ለእግዚአብሔር ሰጥቶ “እርሱ ያውቃል” እያለ ተቀምጧል። ኃላፊነቱን አለመወጣቱ ስሕተት መሆኑን የሚገነዘበው ራሱ በጣም ጥቂቱ ነው። ዋልድባ ሲፈርስ፣ አበው አልታረቅ ሲሉ፣ በቆረጣ አዲስ 6ኛ ፓትርያርክ ለማስቀመጥ ሲሯሯጡ “እኔ ምን አቅም አለኝ” ብቻ ነው መልሱ። ይህም ኃላፊነትን ካለማወቅና ኃላፊነትን ለመረከብ ከመስጋት የሚመነጭ ክፉ ደዌ ነው።

                ማጠቃለያ፦

                በአጠቃላይ ስንመለከተው ክርስቲያኑ ክፍል አሁን ያለበት ይህ እና ሌሎች ምክንያቶችም ተጨማምረውበት ለመብቱ ለመቆም፣ ቤተ ክርስቲያኑን ለመታደግና እምነቱን ለማስከበር የሚችልበት ሁኔታ ላይ እንዳልሆነ እንገነዘባለን። በቅርብ ዓመታትም ይሻሻላል ብሎ መጠበቁ ከባድ ነው። በተአምር ካልሆነ በስተቀር አሁን ባለው የክርስቲያኑ አያያዝ ዋልድባንም ያርሱታል፣ አበውንም እንደጀመሩት በማሰር በማንገላታትና በማሰደድ ይገፉበታል፣ የራሳቸው መጠቀሚያ የሆነ 6ኛ ፓትርያርክ በመሾም ሌላ የመከራ ዘመን ያጸናሉ።

                መፍትሔውስ?
                መፍትሔው አጭር ነው። ከአሁኑ መሰባሰብ፣ መደራጀት፣ የችግሮቹን ትክክለኛ ምንጭ መረዳት፤ ለማያውቁት ማሳወቅ፣ ለአጭር ጊዜ ሳይሆን ለረዥም ጊዜ መፍትሔ መሥራት። ‘እዛው ሞላ እዛው ፈላ’ እንደሚባለው ተረት ቶሎ መፍትሔ በመፈለግና ለአጭር ጊዜ ሆይ ሆይ በማለት ችግሩ አይፈታም። የቤተ ክርስቲያን የሆኑትን ከአድርባዮቹ፣ ከአስመሳዮቹና ከጥቅመኞቹ ለይቶ በመረዳት የራስን ኃላፊነት መወጣት። የቀደሙት አበው ከመቃብር ተነሥተው ቢመለከቱን እንዳያፍሩብን እኛም በትውልዳችን የራሳችንን ኃላፊነት መወጣት።

                ይቀጥላል!!!!

                ቸር ወሬ ያሰማን፤ አሜን።

                የቀድሟ ቀዳማዊ እመቤት ወ/ሮ አዜብ መስፍን በቂርቆስ ክፍለ ከተማ በምርጫ እንደምትወዳደር ሲገለጽ የቀድሞ የሥራ ኃላፊዎች እስከ 24 ዓመት በሚደርስ ፅኑ እስራት ተፈረደባቸዉ


                B. Tsegaye Norway ( ፈብ 17)

                የቀድሟ ቀዳማዊ እመቤት ወ/ሮ አዜብ መስፍን ከዚህ ቀደም በምርጫ ትወዳድርበት የነበረውን የትግራይ ክልል በመተው በአዲስ አበባ ከተማ ለምርጫ እንደምትቀርብ ከወደ አዲስ አበባ የመጡ ዜናዎች አመለከቱ። 
                “የአቶ መለስ ዜናዊን ሌጋሲ እኔ አስፈጽመዋለሁ” በሚል በአቶ መለስ የቀብር መታሰቢያ ፕሮግራም ላይ በድፍረት የተናገረችው ወ/ሮ አዜብ በአሁኑ ወቅት የፌደራሉ ፓርላማ አባል ብትሆንም ኢሕአዴግን ወክላ በመጪው የቀበሌና የወረዳ ምርጫ ላይ ኢሕ አዴግን በመወከል በበቂርቆስ ክፍለከተማ እንደምትወዳደር የዘ-ሐበሻ የአዲስ አበባ ዘጋቢዎች አስታውቀዋል።

                በተለይ “አፍቃሬ ኢሕአዴግ” በመባል የሚታወቀው የአቶ ልደቱ አያሌው ኤዲፓ በዚህ ምርጫ ላይ ሙሉ በሙሉ ሳይሆን በከፊል ብቻ እንደሚሳተፍ ባሳወቀበት በዘንድሮው ምርጫ ከወ/ሮ አዜብ ጋር ይወዳደራል ተብሎ የሚጠበቀው የኢዴፓው ወንድወሰን ተሾመ ነው። አቶ ወንደሰን ተሾመ ኢዴፓ ብቸኛው ያቀረበው እጩ ሲሆን ይህም እጩ ከወ/ሮ አዜብ በሚወዳደሩበት የምርጫ ጣቢያ እንዲወዳደር የተደረገው የፖለቲካ ትርፍ ኢሕአዴግ ለማግኘት አስቦ ነው ሲሉ አስተያየት ሰጪዎች ትዝብታቸውን ለዘ-ሐበሻ ይገልጻሉ።
                ባልተለመደ መልኩ ከትግራይ ክልል ተነስታ በአዲስ አበባ ከተማ ለምርጫ የምትወዳደረው ወ/ሮ አዜብ ምርጫው የተበላ እቁብ በመሆኑ በቀጥታ አሸንፋ የአዲስ አበባ ካቢኔ ውስጥ በመግባት የኦሕዴዱን ኩማ ደመቅሳ ቦታ በመቀበል የከተማዋ ከንቲባ እርሷን ለማድረግ የታቀደ ነገር እንዳለ ያስታውቃል ያሉት ታዛቢዎች በተለይም ከሰሞኑ ከወ/ሮ አዜብ ጋር ቅርርብ አላቸው የተባሉ አንዳንድ የአዲስ አበባ መጽሔቶች “የሴት ጠ/ሚ/ር ማየት ናፈቀን” የሚል ጽሁፍ ሁሉ መጻፉን ከወ/ሮ አዜብ ወደ አዲስ አበባ ከንቲባ መምጣት ጋር አያይዘውታል – ታዛቢዎቹ።
                አቶ አርከበ እቁባይ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ በነበሩበት ወቅት በአዲስ አበባ የታዩ ለውጦችን ቢያደርጉም የአዲስ አበባ ሕዝብ በምርጫ 97 ወቅት “አርከበ ለከተማዋ እድገት ብትጥርም፤ ኢሕአዴግን ወክለህ ብቻ ስለመጣህ አንመርጥህም” የሚል ምላሽ ከህዝቡ አግኝቶ ኢሕአዴግ በምርጫው በ0 በተሸነፈበት ወቅት ከወ/ሮ አዜብ ጋር እንደማይዋደዱ የሚነገርላቸው አቶ አርከበ በባልየው በአቶ መለስ ዜናዊ “በአዲስ አበባ ላይ ቀለም ከመቀባት በስተቀር ያመጣኸው ለውጥ የለም” በሚል በስብሰባ ላይ በግልጽ ተሰድበው ነበር።
                በአሁኑ ወቅት ሕወሃት በክፍፍል ላይ እንዳለ እየተዘገበ መሆኑ ይታወቃል። የአቶ ስብሃት እና የወ/ሮ አዜብ ግሩፕ በየፊናው ተፋጧል። አሁን ወ/ሮ አዜብን በአዲስ አበባ ከንቲባነት አማሎ ድርጅቱን የማዳን ሥራ እየተሰራ ነው የሚሉ የፖለቲካ ተንታኞች አሉ። ይህ በዚህ እንዳለ 
                የፌዴራል የሥነ ምግባርና የፀረ ሙስና ኮሚሽን ክስ የመሠረተባቸው የቂርቆስ ክፍለ ከተማ የቀድሞ የሥራ ኃላፊዎች በመንግሥት ላይ ከአራት ሚሊዮን ብር በላይ ጉዳት አድርሰዋል በማለት እስከ 24 ዓመት በሚደርስ ፅኑ እስራትና በገንዘብ እንዲቀጡ የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የካቲት 6 ቀን 2005 ዓ.ም. በዋለው አንደኛ ወንጀል ችሎት ውሳኔ አስተላለፈ፡፡


                የኮሚሽኑ ዓቃቤ ሕግ ክስ መዝገብ እንደሚያስረዳው፣ 1ኛ ተከሳሽ ማዘንጊያ ካሳ በቂርቆስ ክፍለ ከተማ የፋይናንስና ኢኮኖሚ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ፣ 2ኛ ተከሳሽ ሲሳይ አያሌው ዋና ሥራ አስፈጻሚ፣ 3ኛ ተከሳሽ ገብረ እግዚአብሔር ገብረ ማርያም ምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚ፣ 4ኛ ተከሳሽ ደስታ ሎሬንሶ የንግድና ኢንዱስትሪ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ፣ 5ኛ ተከሳሽ ተስፋዬ ነጋሽ የትምህርት ጽሕፈት ቤት ኃላፊ፣ 9ኛ ተከሳሽ ጌታሰው ጋሻው የሥራና የከተማ ልማት ጽሕፈት ቤት ኃላፊ፣ 10ኛ ተከሳሽ ራሔል ሙሉጌታ የሴቶች ጉዳይ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ፣ 11ኛ ተከሳሽ ሊዲያ ሳንቴ የባህልና ቱሪዝም ጽሕፈት ቤት ኃላፊ፣ 12ኛ ተከሳሽ ንጉሴ ፈንቴ የንብረት አስተዳደርና ጠቅላላ አገልግሎት ክፍል ኃላፊ የነበሩ ተከሳሾች፣ ዘለዓለም ክንፈ ከተባለ 15ኛ ተከሳሽ ጋር በመተባበር በሥልጣን ያለአግባብ መገልገል የሙስና ወንጀል ፈጽመዋል፡፡ 

                በተከሳሾቹ ላይ በአንድ የክስ መዝገብ አሥር ክሶች የተመሠረቱ ሲሆን፣ በ1ኛ ክስ 2ኛ፣ 3ኛ፣ 4ኛ፣ 5ኛ፣ 9ኛ፣ 10ኛ እና 11ኛ ተከሳሾች የመንግሥት ግዥ ከ250 ሺሕ ብር በላይ በግልጽ ጨረታ መከናወን እንዳለበት እያወቁ በተቃራኒው የመንግሥትን የግዥ አዋጅ፣ መመርያና አሠራር በመተላለፍ ግዥው በንግድና ኢንዱስትሪ ተመዝግቦ ከማይታወቅ ከአንድ ሕገወጥ ድርጅት እንዲፈጸም መወሰናቸውን ክሱ ያስረዳል፡፡ በ2ኛ ክስ 1ኛ፣ 12ኛ እና 15ኛ ተከሳሾች የመንግሥት ግዥ በቁጠባና ውጤታማ መንገድ እንዲፈጸም ከማድረግ ይልቅ ከሕገወጥ ግለሰቦችና ድርጅቶች ጋር ሕገወጥ የጥቅም ግንኙነትን በመፍጠርና ትዕዛዞችን በመስጠት መንግሥት ያለአግባብ ወጪ እንዲያወጣ አድርገዋል፡፡ 

                በ4ኛ እና በ8ኛ ክሶች 15ኛ ተከሳሽ የሕዝብና የመንግሥትን ጥቅም ለመጉዳት ከክፍለ ከተማው የሥራ ኃላፊዎች ጋር ተመሳጥሮ በንግድና ኢንዱስትሪ ጽሕፈት ቤት የማይታወቁ ድርጅቶችን በመፍጠር እንዲሁም ሐሰተኛ ሰነዶችን በማዘጋጀትና በመገልገል በሕገወጥ ግዥ የተገኘው ገንዘብ ወደ ሕገወጥ ድርጅቶች እንዲገባ አድርጓል፡፡ በ5ኛ እና በ5ኛ ክሶች 1ኛ እና 2ኛ ተከሳሾች ደግሞ በደመወዛቸው ከሚያገኙት ገንዘብ በላይ አካብቶ በመገኘታቸው በፈጸሙት ምንጩ ያልታወቀ ገንዘብ አካብቶ መገኘት የሙስና ወንጀል ተከሰዋል፡፡ በ9ኛ እና በ10ኛ ክሶችም እነዚሁ ተከሳሾች የሥራ ኃላፊነታቸውን ወደ ጎን በመተው ከሌሎች ግብረ አበሮቻቸው ጋር በመሆን ሕገወጥ ግለሰብና ድርጅቶችን ለመጥቀም በማሰብ በመንግሥት ላይ ከፍተኛ ጉዳት እንዳደረሱ ታውቋል፡፡ 

                በአጠቃላይ ተከሳሾቹ በ2001 ዓ.ም. በተለያዩ ጊዜያት ባካሄዱዋቸው ስብሰባዎች ባሳለፏቸው የግዥ ውሳኔዎች በድምሩ ከ18.4 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ ሆኖ የተለያዩ የቢሮ መገልገያ ዕቃዎችና የዕድሳት ግዥዎችን ከአሠራርና ከመመርያ ውጪ እንዲፈጸሙ አድርገዋል፡፡ በዚህም ምክንያት ጥራታቸውን ያልጠበቁ ዕቃዎችን በተጋነነ ዋጋ እንዲቀርቡ በማድረግ በመንግሥት ላይ ከ4.4 ሚሊዮን ብር በላይ ጉዳት በማድረስ ሕገወጥ ግለሰቦችና ድርጅቶች እንዲጠቀሙ ማድረጋቸውን የክስ መዝገቡ ያስረዳል፡፡ 

                በመሆኑም 1ኛ ተከሳሽ ማዘንጊያ ካሳ በሦስት ክሶች በድምሩ በ24 ዓመት ከሦስት ወራት ፅኑ እሥራትና 20 ሺሕ ብር፣ 2ኛ ተከሳሽ ሲሳይ አያሌው በሦስት ዓመት ፅኑ እስራትና 2,500 ብር፣ 3ኛ፣ 4ኛ፣ 5ኛ፣ 9ኛ፣ 10ኛ እና 11ኛ ተከሳሾች እያንዳንዳቸው በአንድ ዓመት እስራት፣ 12ኛ ተከሳሽ ንጉሴ ፈንቴ በስድስት ዓመት ፅኑ እስራትና አራት ሺሕ ብር፣ 15ኛ ተከሳሽ ዘለዓለም ክንፈ በ18 ዓመት ከአምስት ወራት ፅኑ እስራትና 20 ሺሕ ብር እንዲቀጡ ፍርድ ቤቱ የካቲት 6 ቀን 2005 ዓ.ም. በዋለው 1ኛ ወንጀል ችሎት ውሳኔውን ያስተላለፈ ሲሆን፣ ከወንጀሉ ጋር ተያይዞ ለመንግሥት የሚመለስ የገንዘብና ንብረት ጉዳይም በፍርድ ቤት ተይዞ በሒደት ላይ የሚገኝ መሆኑ ታውቋል፡፡ 

                በሰሜን ጎንደር የተለያዩ ፖለቲካዊና ማኀበራዊይዘት ያላቸው መፅሔቶችና መፅሐፎችእንዳይሸጡ ታገደ::

                በሰሜን ጎንደር የተለያዩ ፖለቲካዊና ማኀበራዊይዘት ያላቸው መፅሔቶችና መፅሐፎችእንዳይሸጡ ታገደ፤ አዙረው የሚሸጡወጣቶችም ከየካቲት 2 ቀን 2005 ዓ.ም. ጀምሮየያዙዋቸው እንደተወረሰባቸውም ታውቋል፡፡
                በተለይ በጎንደር ከተማ ቀበሌ 11 ልዩስሙ አባጃሌ በሚባል አካባቢ ያሉ የደንብአስከባሪዎች እዚህ ጎንደር ውስጥ ምንምዓይነት ፖለቲካዊ ይዘት ያላቸውንመፅሔቶች፣ ጋዜጦችና መፅሐፎችመሸጥ አትችሉም በሚል በተደጋጋሚጊዜ ከአዙአሪዎች እየወረሱ ቅጣት እያሉያስከፍሏቸው እንደነበር ቢታወቅምየካቲት 2 ቀን 2005 ዓ.ም. ግን ሙሉበሙሉ እንደወረሱባቸው ተጠቁሟል፡፡
                በአካባቢው ጋዜጣ፣ መፅሔትና መፅሐፍእያዞሩ ከሚሸጡት ወጣቶች መካከልአብዛኞቹ ከተለያዩ ዩኒቨርስቲዎችና ኮሌጆችተመርቀው ስራ አጥ የሆኑ እንደሆነምምንጮቻችን በተለይ ለፍኖተ ነፃነት ገልፀዋል፡፡
                ወጣቶቹ የተወረሱባቸውን ንብረቶችለማስመለስ ወደ አካባቢው መስተዳደርስራ አስኪያጅ ቢያመሩም ሥራ አስኪያጁ“የተወረሰባቸው የወጣቶቹ ንብረትሊመለስ ይገባል ፣ ወንጀል እስካልፈፀሙድረስም አዙረው መሸጥ ይችላሉ” ቢሉምየደንብ አስከባሪዎቹ ለመመለስ ፈቃደኛአለመሆነቸውን ማስታወቃቸው ተጠቁሟል፡
                ፡ የደንብ አስከባሪዎችም የአካባቢውንየብአዴን/ኢህአዴግ የድርጅት ጉዳይኃላፊ የሆኑት አቶ አያና ካልፈቀዱ
                ይመለስላቸውም ያሉ ሲሆን አቶ አያናምየተወረሱት መሔቶችና መፅሐፎችእንዲወረሱ ትዕዛዝ መስጠታቸው ታውቋል፡፡
                ወጣቶቹም በሁኔታው እጅግ ከማዘናቸውበተጨማሪ “ጋዜጦች፣ መፅሔቶችናመፅሐፎቹ የሚታተሙት አዲስ አበባየመንግስት ኃላፊዎች በሚያውቁት ህጋዊመንገድ ሆኖ ሳለ ጎንደር እየመረጡ አትሽጡመባላችን ምክንያቱ አልገባንም፣ የጎንደርህዝብ ከሌላው ኢትዮጵያ ህዝብ ተለይቶየሚታተሙ ህጋዊ ፅሑፎችን አታንብቡ፣መረጃም አታግኙ እንደማለት ይቆጠራል፤እኛንም ሰርታችሁ አትብሉ እንደማልት ነው”
                ሲሉ ያላቸውን ቅሬታ ለፍኖተ ነፃነት ገልፀዋል፡፡
                በከተማው ያነጋገርናቸው እንዳንድአንባቢዎች በበኩላቸው “በተለይ በጎንደርየኢህአዴግ ባለሥልጣናት በሚፈፅሙትሙስና እና ብልሹ አሰራር በህዝቡ ላይ ከፍተኛጫና ፈጥሯል፡፡ ህዝቡ መረጃ እንዳያገኝማድረጋቸውም አዲስ አይደለም፤ ይህም ህዝቡላይ ከፍተኛ ቁጣን እየቀሰቀሰ መሆኑ ግልፅ
                neው” ሲሉ በተለይ ለፍኖተ ነፃነት ገልፀዋል፡፡
                ጉዳዩ የሚመለከታቸው የአካባቢው የፀጥታዘርፍ ኃላፊ የሆኑት አቶ አዶዬ እንየውንስለሁኔታው ጠይቀናቸው ወጣቶቹ መንገድሳይዘጉ እንደፈለጉ ተንቀሳቅሰው መሸጥእንደሚችሉና ማንም ሊወርስባቸው
                እንደማይችል በመግለፅ ስለመወረሱምየሚያውቁት መረጃ እንደሌለ አስታውቀዋል፡፡
                የአካባቢው የብአዴን/ኢህአዴግ ድርጅትጉዳይ ኃላፊ የሆኑት አቶ አያናንየወጣቶቹን ንብረት እንዲወረስ እንዳደረጉብንጠይቃቸውም ለፍኖተ ነፃነት ምላሽለመስጠት ፈቃደኛ ሳይሆኑ ቀርተዋል፡:

                መልስ ከተሰጠን እናኮርፋለን፤ ከመሳፍንት አገዛዝ የወረስነው ባህል ነው


                በፍትሕ ጋዜጣ ላይ ለምንጽፍ ሁሉ እየተናገሩ አለማነጋገር፣ እያሰቡ አለማሳሰብ
                ፕሮፌሰር መስፍን ወ/ማርያም
                ይህ ጽሑፍ ለእኔም የተጻፈ በመሆኑ አንድ ቀልድ እንደመግቢያ ልናገር፤ አማኑኤል ሆስፒታል ሕመምተኛው ውጭ ይጽፋል፤ ሀኪሙ ይመጣና ‹‹ከበደ፣ እንደምናደርህ?›› ብሎት ሰላምታ ከተለዋወጡ በኋላ፣ ሀኪሙ ምን እየጻፍክ ነው? ይልና ይጠይቃል፤ ህመምተኛው ‹‹ደብዳቤ›› ይላል፤ ሀኪሙ ‹‹ለማን ነው?›› ብሎ ሲጠይቅ፣ ሕመምተኛው ‹‹ለራሴ›› ይላል፤ ሀኪሙ የሕመምተኛውን የውስጥ ስሜት ለማወቅ ጓጉቶ ‹‹ምን ይላል?›› ብሎ ይጠይቃል፤ ሕመምተኛው በመደነቅ ዓይኑን በልጠጥ አድርጎ ‹‹ዶክተር መቼ ተላከና፣ መቼ ደረሰኝና!›› አለው፤ እኔም…
                በኢትዮጵያ ውስጥ እያሰቡ ለወደፊት ማቀድ አያዋጣም፤ ለሁሉም ሰው የወደፊቱን የሚወስኑት ወንበሩ ላይ ተቀምጠው ሰይፉን የጨበጡት ብቻ ናቸው፤ ከአንድ ዓመት በኋላ ይህንን አድርጌ፣ ከሁለት ዓመት በኋላ ደግሞ ከዚህ ደረጃ ደርሼ… እያለ በራሱ ሀብት፣ በራሱ ጉልበትና በራሱ እውቀት ሥራውን እያቀነባበረ ከዓመት ወደ ዓመት በእቅድ የሚሄድ የተፈቀደለት ብቻ ነው፤ ፈቃዱም ቢሆን ለአንድ ዓመት የተሰጠው በሌላው ዓመት ይሰረዝ ይሆናል፤ ለባል የተፈቀደው ለሚስት አይሠራም ይሆናል፤ ምክንያቱ ግልጽ ነው፤ አንድ ሰውም ሆነ አንድ ድርጅት እቅድ እያወጣ እየተሳካለት ከአደገ በራሱ የሚተማመንና በራሱ ኃይል እየተራመደ የሚያድግ ሲሆን ላልተደላደለው ሥልጣን አስፈሪ ይሆናል፤ በቋፍ እንዲኖር የሚገደደው ደካማ ሆኖ በልመናና በመለማመጥ እንዲጎብጥ ስለሚፈለግ ነው፤ አንድ ሰው ራሱን ችሎ ብቅ ሲል በኩርኩም አናቱን እያሉ ማኮማተር ባህል ነው፤ አልፎ አልፎ እንዲህ በኩርኩም ልኩን እንዲያውቅ ካላደረጉት ጎበዙ ጎበዝ እየሆነ ጎበዝ ያፈራል፤ ከርሞ ጥጃ ከመሆን ይወጣል! ከርሞ ጥጃነት በሚፈለግበት ሥርዓት እድገት እንዴት ይመጣል?
                ሀሳብን በጋዜጣ ማውጣት አደባባይ መውጣት ነው፤ አደባባይ የሚወጡበት ጉዳይ የግል ሳይሆን የአገርና የሕዝብ ነው፤ መሆን አለበት፤ አደባባይ በወጣው ጉዳይ ላይ በአገርና በህዝብ ጉዳይ ያገባኛል የሚል ዜጋ ሁሉ ባለቤት ሊሆንበት ይችላል፤ በባለቤትነት ሊተችበት ይችላል፤ በጉዳዩ ላይ የሞቀ ክርክር ቢደረግበት ሁላችንም በብዙ መንገድ ተጠቃሚዎች ልንሆን እንችላለን፤ ነገር ግን እስከዛሬ የሚታየው አዲሱ ልምድ ከላይ ባለስልጣኖች እንደልባቸው ይናገራሉ፤ በግድም ይሁን በውድ አብዛኛው ሰው ይሰማቸዋል፤ ባለሥልጣኖቹን በማስተጋባት ቴሌቪዥኑና ራዲዮው ደጋግመው እስቲሰለች ድረስ ያሰማሉ፤ በግድም ይሁን በውድ የባለሥልጣኖቹ ንግግር ለብዙ ሰዎች ጆሮ ይደርሳል፤ ግን ጆሮ የደረሰ ሁሉ ወደልብ መተላለፉን እርግጠኛ መሆን አይቻልም፤ በአንጻሩ በግል ጋዜጦች ላይ የሚወጡት የተለዩና የተለያዩ ሀሳቦች በተለያዩ ጉዳዮች ላይ አመራሩን የሚተቹ ናቸው፤ እነዚህን ጋዜጦች የሚያነብቡ በጣም ጥቂቶች ናቸው፣ ጋዜጦቹን የሚያገኙዋቸው በገንዘባቸው እየገዙ በመሆኑ የሰዎችን ቀልብ መሳባቸው ይታወቃል፤ እነዚህን ትችቶች ባለሥልጣኖቹ ጉዳያቸው አድርገው የሚያነቡዋቸው አይመስለኝም፤ የእነሱ ንቀት ሚስትህ አረገዘች ወይ ቢሉት፣ ማንን ወንድ ብላ! እንዳለው ነው መሰለኝ፤ ባለሥልጣኖቹ ሁለት ጥቅሞችን ያጣሉ፤ አንደኛ የተቺዎቹን ሀሳብ መረዳትና ከራሳቸው ሀሳብ ጋር የማመዛዘን ዕድሉ ያመልጣቸዋል፤ ሁለተኛው ሕዝቡ በነፃነትና ያለምንም ግዴታ ትችቱን በማንበቡ ብቻ የሚያስተላልፈውን መልእክት ሳያውቁት ይቀራሉ፤ የዚህ ውጤት የአገር ጉዳት ነው፤ እንግዲህ እነሱ የሚናገሩትን ይናገራሉ፤ ሌላውም የሚናገረውን ይናገራል፤ በሁለቱም ወገን የሚነገረው ስለአንድ አገርና ስለአንድ ሕዝብ ነው፤ በሁለቱም በኩል የተያዘው ፈሊጥ ሳያነጋገሩ መናገር ነው፤ ክፉ ሕመም ነው።
                የሳያነጋገሩ መናገሩ ፈሊጥ የሚታየው በባለስልጣኖችና በተቺዎቻቸው መሀከል ብቻ አይደለም፤ በተቺዎቹም መሀከል ያው ነው፤ ተቺዎቹም መናገሩን እንጂ እርስበርሳቸው መነጋገሩን ገና የለመዱት አይመስልም፤ እንደታዘብሁት እስካሁን ድረስ በፍትሕ ጋዜጣ ላይ በየሳምንቱ የሚናገሩት ሁሉ እርስበርሳቸው እምብዛም አይነጋገሩም፤ ይህ ሊሆን የሚችለው እያንዳንዱ በሚናገረው ሁሉም ፍጹም ስምምነት ካላቸው ብቻ ነው፤ ወያኔ/ኢህአዴግም እንደዚህ ያለ ፍፁም ስምምነት ያለው አይመስለኝም፤ ወይም በጋዜጣው ላይ የሚናገሩት ሁሉ ይፈራራሉ ማለት ይሆናል፤ ለመፈራራታቸው ብዙ ምክንያቶችን መጥቀስ ይቻላል፤ ነገር ግን አንዱም ምክንያት ለአገርም፣ ለወገንም፣ ለራስም ጠቃሚ አይመስለኝም፤ እንዲያውም የባለስልጣኖቹን ባሕርይ ወደመውረሱ የሚያስጠጋ ይመስለኛል፤ ይህ እውነት ከሆነ፣ ማለት በእኩልነት መነጋገር የማንችል ከሆነ መጀመሪያ ማድረግ ያለብን እያንዳንዳችን ለየራሳችን ተገንዝበን ካረጋገጥን ራሳችንን የምናስተካክልበትን መንገድ መከተል ግዴታ ይሆንብናል።
                የፍትሕ ጋዜጣ የተሟላና የተዋጣለት ነው ባይባልም፣ በጣም ተፈላጊና ብዙ ሰውም የሚያነብበው ነው፤ ሆኖም በማስፈራራት የተካኑ ሎሌዎች አቤ ቶኪቾን ለስደት ከዳረጉት ወዲህ ፍትሕ ትንሽ ደረቅ ብሏል! በሀሳብ፣ በአስተያየትና እውቀትን በማስፋት የሚቀርቡት መጣጥፎች አብዛኛውን ጊዜ ፀሐፊው ከራሱ ጋር ብቻ የሚያወራባቸው መስለው ይታያሉ፤ የአንባቢን አእምሮ የመኮርኮር፣ ክርክር እንዲከፍት የማድረግ ኃይል ያላቸው አይመስሉም፤ ይህ የመጣጥፎቹ ጉድለት አይመስለኝም፤ ጠጥቶ ዝም፣ የጋን ወንድም! የሚባለው ዓይነት አንባቢና ፀሐፊ ነው፤ በጋዜጣው ላይ ብዙ ሰዎች መጣጥፎችን ቢያቀርቡም እርስበርሳቸው ሲነጋገሩ ወይም ሲከራከሩ አይታዩም፤ ይህ የሕመም ምልክት ይመስለኛል፤ አንድ ሰሞን ከአቶ ስብሐት ነጋ ጋር፣ አንድ ሰሞን ከፕሮፌሰር ገብሩ ታረቀኝ ጋር ክርክር ቢጤ ተጀመረና ሁሉም እየሮጠ በየምሽጉ ገብቶ ተቋረጠ፤ በዚያን ጊዜም ቢሆን ክርክሩን ከመሩት ሰዎች ውጭ የገባ አንድ ወይም ሁለት ሰው ብቻ ይመስለኛል።
                በተለያዩ መንገዶች ደጋግሜ እንደገለጥሁት በእኩልነት ደረጃ ሆነን ለመነጋገርና ለመከራከር ያቅተናል፤ በየፊናችን ስንናገር ራሳችንን ላይ አውጥተን ሰሚውን ከታች አድርገን መደመጥን እንጂ እኛ በተራችን ሌሎችን ማድመጥ እንዳለብን አናውቅም፤ እኛ ለመናገር የምንደፍረውን ያህል ለተናገርነው መልስ የሚሰጠው ድፍረት እንዲያገኝ አንፈልግም፤ እንዲያውም መልስ ከተሰጠን እናኮርፋለን፤ ከመሳፍንት አገዛዝ የወረስነው ባህል ነው፤ ለዚህ ነው ክርክር የማንጀምረው፣ ቢጀመርም የማይቀጣጠለው።
                አሁን ደግሞ ስለኢትዮጵያና ጃፓን፣ ስለአጼ ቴዎድሮስና ስለአንድ የጃፓን ንጉሥ ክርክር እየተካሄደ ነው፤ አዝማሚያው የተለመደውን ባሕርያችንን የያዘ ይመስለኛል፤ አንዱ ስለሁነት ሲናገር አንዱ ስለዓላማ ሉዓላዊነት እየተናገረ፣ አንዱ ስለአጼ ቴዎድሮስ ተግባር ሲናገር፣ ሌላው ስለአጼ ቴዎድሮስ ዓላማ መልስ ቢሰጥ መግባባት አይኖርም፤ ክርክሩን እያሻከረው ነው፤ በበኩሌ ሁለቱ ሰዎች የከፈቱት ክርክር ብዙ ቁም-ነገሮችን የያዘ በመሆኑ ብዙ ሰዎችን ይስባል የሚል እምነት ነበረኝ፤ አሁን እንደሚታየው ግን ሁለቱ ሰዎች እንደተለመደው እየተናገሩ ነው እንጂ እየተነጋገሩ አይደለም፤ ስለዚህም አንዳንዶቻችን ክርክር ውስጥ ገብተን የታሪክን አስተሳሰብና ታሪክን የማጥናትና የማጽዳት ኃላፊነታችንን ብንወጣ ጠቃሚ ይመስለኛል።
                በክርክሩ ውስጥ ብዙ ሰዎች የሚያውቁትን እየያዙ ቢገቡበት ስለቴዎድሮስና ስለዚያ ዘመን ከፍተኛ ትምህርት እናገኝበት ነበር።