ሕውሃት ከጥንስሱ ጀምሮ የተለያየ ቋንቋ ተናጋሪዎችን የዘር ታርጋ እየለጠፈ አንተ አማራ ነህ፤ ኦሮሞ እንዳያጠፋህ ቀድመህ አጥፋው፡ አንተ ስልጤ ነህ ጉራጌ እንዳያንሰራራ ቀጥቅጠው፡ አንተ ትግሬ ነህ አማራ ጠላትህ ስለሆነ ዘሩን አጥፋው በሚል አስተምሮት የተቃኘ እና ህዝብን በህዝብ ላይ በማነሳሳት፤ በማጋጨት እስካሁን ስልጣን ላይ መቆየቱን የማይረዳ ኢትዮጵያዊ ባሁኑ ሰዓት ሊኖር እንደማይችል አፌን ሞልቼ መናገር እችላለሁ።
የትግሬ ነጻ አውጭ ድርጅት ፕሮግራም እንዳሰቀመጠው መጀመሪያ ጠላት አርጎ የወሰደው አማራን ነው፡ ከዚህም በመነሳት በሚሊየን የሚቆጠሩ አማርኛ ተናጋሪዎችን መፍጀቱ ይታወቃል። ከዘር ቀጥሎ የወያኔ የመከፋፈያ ስልት ሓይማኖት መሆኑን እና ለዚህም እንዲጠቅመው የኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያንን በነታጋይ ጻውሎስ ተቆጣጥሮት እንደነበረና አሁንም ሌላ ካድሬ በመመልመል ላይ መሆኑን የማናውቅ የለንም። የክርስትና ሃይማኖትን እንደተቆጣጠረው ሁሉ የእስልምና ሃይማኖት ተከታዮችንም ለመቆጣጠር ባዘጋጀው ሰፊ ዝግጅት የእስልምና እምነት ምን መሆን እንዳለበት እስልምና ተከታይ ወገኖቻችን ላይ ሊጭን ሲሞክር ሓይማኖቴን አንተ አትጭንብኝም በማለታቸው፤ ተገለዋል፤ ታስረዋል፤ ተሰደዋል፤ ተደብድበዋል፡ ይህ በግልጽ የምናውቀው ጸሃይ የሞቀው ሃቅ ነው፡:
አሁን የኢትዮጵያ ህዝብ በገሃድ የሚያወቀውን ሃቅ ወያኔ ከምን ተነስቶ ነው እስልምና ተከታዮች ክርስቲያኖችን ሊያጠፉ ነው የሚለውን ድራማ ይቀበሉኛል ብሎ ያሰበው?አማራንና ኦርቶዶክስ እስከወዲያኛው እንዳያንሰራሩ አጥፍተናቸዋል እያሉ በእብሪት የሚያናፉት እነ ሳሞራ ዩኑስ፤ ስበሃት ነጋ እና ሌሎችም ወያኔዎች አደሉም እንዴ? አሁን ከየት መተው ነው ለክርስትና እምነት ተከታዮች ጠበቃ ነን ለማለት የሚቃጣቸው? ነው ወይስ የኢትዮጵያ ህዝብ ያልነውን ሁሉ የመቀበል ግዴታ አለበት ከሚል ግልብ እብሪት የተነሳ ነው?
መላ የኢትዮጵያ ህዝብ ሆይ አገር ውስጥም ሆነ ውጭ ያለኸው፡ ወያኔ በበረከት ስምኦን ተደርሶ ማክሰኞ ባፈ ወያኔ ቴሌቪዥን ጣቢያው ሊያሰተላልፈው ያሰበውን “ጂሃዳዊ ሃረካት” የሚለውን ሰቆቃዊ ተውኔት ተከታተሉት ቀርጻችሁም አስቀምጡት፡ ለነገሩ ሚሰጥሩ ቀድሞ ህዝብ ጆሮ ስለደረስ ላያስተላልፈው ይችላል። ወያኔን ሰምታችሁ የሚለውን እንደማትቀበሉ በጣም እርግጠኛ ነኝ፡ ግን ከዚያች ቀን ጀምሮ የእስልምና ተከታይ ወገኖቻችሁ የሚያደርጉት ትግል እንድትቀላቀሉ አደራ እላለሁ።
እስልምናና ክርስትና እምነት ተከታዮች አትዮጵያ ውስጥ አብረው የኖሩት ከአመስት ሽህ ዘመን በላይ ነው፡ በነዚህ ዘመናት እስልምናና ክርስትና ባላቸው የመቻቻል እና የመከባበር ባህል ለአለም አርአያ ሲሆኑ እንጂ እርስ በርስ ሲተራረዱ አላየንም አልሰማንም፤ ታሪክም አልዘገበውም። ትናነት የመጣ ወያኔ ያውም የባንዳ ወንጀለኞች ጥርቅም ነው እስልምና ተከታዮች ክርስቲያኖችን ሊያርዱ ነው የሚለን? የወያኔ ፌዝ እዚህ ላይ ይቁምና ሁላችንም እጅ ለእጅ ተያይዘን ይህንን ያገር ነቀርሳ ማሰወገድ
መቻል አለብን፡
መቻል አለብን፡
እግዚአብሄር ኢትዮጵያን ይጠብቅ
እስከ ነጻነት
No comments:
Post a Comment