የኢሳት የኦህዴድ ምንጮች እንደገለጡት በአብዛኛው የኦሮሚያ ዞኖች በተለይም በምስራቅ ኦሮሚያና በአርሲ ዞኖች የሚገኙ የድርጅቱ አባላት ለ3 ተከፍለው እርስ በርስ እየተካሰሱ ነው።
የክፍፍሉ መንስኤዎች በድርጅቱ እምነት ማጣት፣ ሙስናና የግል ጥቅምን ማሳደድ መሆናቸውን ለማወቅ ተችሎአል።
አመራሮቹ እርስ በርስ እየተባሉ ይገኛሉ ያሉት ምንጮች፣ ሁኔታው በዚህ ከቀጠለ የድርጅቱ ህልውና ሊያከትም እንደሚችል ጠቁመዋል።
በዞን ደረጃ የሚታየው መከፋፋል ዋናዎቹን የኦህዴድ አመራሮችን መጨመሩንም ለማወቅ ተችሎአል። ሰሞኑን በዝግ በከፍተኛ አመራሮች ዙሪያ እየተካሄደ ያለው ግምገማ የዚህ አካል መሆኑን ለማወቅ ተችሎአል።
ድርጅቱ ከመቼውም ጊዜ በላይ መዳከሙን የገለጡት ምንጮች ክፍፍሉ እስከ ወረዳ መዝለቁንም ጠቁመዋል።
No comments:
Post a Comment