Feb 23, 2013

ሕገ መንግስቱን የሚጥስ መንግስት ባለበት አገር ሕገ መንግስቱን ለማስከበር መነሳት በራሱ ወንጀል ሆኖ እስር ቤት ሊያስወርድ እንደሚችል...



እስከ አሁን ድረስ ሙስሊሙ ያሳየዉ ጽናት አንድነት አስተዋይነት ለሁላችን ትምህርት ነዉ ይህ ሰላማዊ፣ አመፅ-አልቦ ትግል ጄን ሻርፕ “ከአምባገነንነት ወደ ዴሞክራሲ” በሚለው መፅሐፉ ላይ እንዳስቀመጠው 198 ደረጃዎች አሉት። አሁን በምርጫው ላለመሳተፍ ስንወስን፣ አንዱን ብቻ ነው በተወሰነ መልኩ የተጠቀምነው። ገና 197 ደረጃዎች ይቀራሉ ማለት ነው። እንግዲህ ተግቶ ደረጃ በደረጃ አንድ በአንድ መተግበር ያስፈልጋል።ይህ ትግል ጥብቅ ዲሲፒሊን የሚጠይቅ፣ ነገሮች ባልታሰበ ሁኔታ ወደ አመፅና ብጥብጥ እንዳያመሩ ጥንቃቄ ማድረግ ግድ የሚል፣ ሐላፊነት የሚሰማቸው ሰዎች ብቻ ሊያደርጉት የሚችሉት ነገር ነው። እንደ ማህተመ ጋንዲ ያለ የሞራል ልዕልና ያለው መሪ፣ እንደ ህንዶች ያለ ስርዓት ያለውና በአንድ ላይ ያለልዩነት መሰለፍ የሚችል ህዝብ መኖር የሚጠይቅ ነው። ስለዚህ ይህ እንዲሆን ከተፈለገ በመጀመሪያ እንደ ህዝብ ያሉብንን ልዩነቶች ለማጥበብና ለማመቻመች ጠንክሮ መስራት ያስፈልጋል። ቀጥሎ መስራት የሚኖርበት ስለሰለማዊ፣ አመፅ-አልቦ ትግል በስፋትና በጥልቀት ማስተማር፣ በተግበር ለዚህ መርህ መገዛት እንዲቻል ደረጃ በደረጃ ማለማመድ ያስፈልጋል። በዚህ ዙሪያ ሞስሊም ወንድሞቻችን እስካሁን እያሳዩት ያለው ሰላማዊ ተቃውሞ የሚደነቅ ነው። አገር በቀል የሰላማዊ ትግል ስልት በመሆኑ ለእኛ ጥሩ ትምህርትና ሞዴል ሊሆን የሚችል ነው። ይህ በራሱ የሚያሳየው ነገር አለ። ህዝባችን በአግባቡ የሚመራውና አምኖ ሊከተለው የሚችል መሪ ድርጅት ካገኘ ሰላማዊ ትግል
ለማካሄድ አያዳግተውም።

No comments:

Post a Comment