Feb 8, 2013

ሊነበብ የሚገባ !!!!!ፕሮፌስር ተስፋጽዮን መድኅኔ ስለኤርትራ በጻፉት ላይ የተሰጠ አስተያየት


ፕሮፌሰር ተስፋጽዮን የኢትዮ-ኤርትራ ችግር ከጠባብ ብሔርተኝነት ሳይሆን ሰፋ ባለ
የአስተሳሰብ አድማስ አንፃር በሰላማዊ መንገድ አንዲፈታ ከሚሹ ኤርትራውያን ምሁራን
መካከል ሲሆኑ፣ ቀደም ሲል ለውይይት አቅርበው ሰሞኑን በኢትዮሚዲያ ላይ የወጣው
ጽሑፋቸው  “የኤርትራ እናት አገር” የሚለው አስተሳሰብ ከኢጣሊያ ቅኝ ግዛትነት ጀምሮ
የመነጨና የቅኝ አገዛዝ ዓላማን ለማራመድ የተፈጠረ አስተሳሰብ መሆኑን ጥናታቸው
ያመለክታል። ከዚያ በተወረሰ ችግር አሁንም ኤርትራን ይበልጥ ሊበታትን የሚችል አደጋ
መኖሩን በማሳየት ኤርትራውያን ተባብረው እንዲታገሉ አሳስበዋል። ሸአቢያ ከ“ነፃነት” ወይም
ከ“ባርነት” አንዱን ምረጡ በሚል አስገዳጅነት ባለው መንፈስ የኤርትራ ሕዝብ በድምፅ
እንዲያፀድቅላቸው መገንጠልን ተግባራዊ ካደረጉ በኋላ በአቶ ኢሳይያስ አፈወርቂና በአቶ
መለስ ዜናዊ የተመሩት ሸአቢያና ወያኔ የተጓዙበት መንገድ ጠቃሚ ባለመሆኑ ምሁራን
የእርምት እርምጃ አንዲወሰድ ቢጠቁሙም መረዎቹ ሊያረሙት ባለመፈለጋቸው ውጤቱ የኸው
ሕዝቦቻችንን በተለየም የኤርትራን ሕዝብ እንደጎዳው የሚገልፀው ይህ ሰነድ ማስተዋል
ለሚፈልጉ የሕዝብ ወገኖች መማሪያ ሰነድ ነው።
የኃያላን ቅኝ ገዥዎች ዓላማቸውን ለማሳካት ሲሉ በኢትዮጵያ ጉዳይ ውስጥ እጃቸውን
አስገብተው የኤርትራን ነፃ መውጣት ለራሳቸው ዓላማ የተለያዩ ሸሮች በመሥራት የፖሊቲካ
ፓርቲዎች በኤርትራ አንዲቋቋሙ መገፋፋታቸውና የትግራይ ትግርኝ አራማጆችን ስሜት
በማዳበር ኤርትራን በመከፋፈል ቆላማው ክፍል በእንግሊዝ ቅኝ ሥር ወደነበረው ሱዳን፣
ደጋማው ከትግራይ ጋር ትግራይ ትግሪኝን አንዲፈጥርና ምሥራቁ ክፍል አሰብን ጨምሮ ወደ
ኢትዮጵያ አንዲመደብ አቅደው አንደነበር በጽሑፋቸው ገልፀዋል። አንዲሁም ያ ተፅዕኖ
አሁንም ለኤርትራ ችግር ይዞ እንደቆየ የገለጹት ሐቅ ነው። ሌላው ትልቁ ችግር በ1941 ዓ. ም
ኢጣሊያ በጦርነት ከተሸነፈች በኋላ እስከ 1950 ዓም ኤርትራ በእንግሊዝ ሞግዚትነት ከቆየች
በኋላ በብዙ ዲፕሎማሲያዊና ፖሊቲካዊ ጥረት በ1950 ዓም በፌዴሬሽን ከኢትዮጵያ ጋር
እንድትቀላቀል ተደርጎ ሳለ በአፄ ኃይለ-ሥላሴ መንግሥት ግፊት በተለይ ፌዴራላዊ
አስተዳደርን ፈርሶ በ1962 ዓ.ም. ከኢትዮጵያ ጋር እንድተዋኻድ የኤርትራ ፓርላማ እንዲወስን
ተደረገ፤ በዚህ የተደከመው ሁሉ ፈራርሶ ተበላሸ። ከዚያ ወዲህ ኤርትራ የሉአላዊነት ትግል
ስታደርግ ቆይታ በግንቦት 1992 ዓም መገንጠሏ የታሪክ እውነታ ነው። በንጉሠነገሥቱ
አመራር የተፈጸመውን ጭቆናዊ አገዛዝ የኤርትራ ታጋዮች ብቻ ሳይሆኑ ብዙ ተራማጅ
ኢትዮጵያውያን ይጋሩት የነበረው ሐቅ ሲሆን ያ በቅንነት ለእውነተኛ የሕዝብ ሉአላዊነት
የተደረገ ትግል ግን ደርግም አያያዙን አጥቶበት ዛሬ ደግሞ የደሞክራሲና ነፃነት ካባ ለብሰው
ነገር ግን ፀረ-ሕዝብ አቋም የያዙት የሻአቢያና የወያኔ አምባገነኖች የሕዝቦቹን የትግል ውጤት
ቀምተውና ቀልብሰው በሕዝብ መብቶች ላይ ብልግናና ውንብድና መፈጸማቸው ሁላችንንም
አሳዝኖናል። አሁን ኤርትራ ያለባትን ችግር ለማስወገድ ኤርትራውያን በአንድነት መታገል
እንዳለባቸውና ከኢትዮጵያውያን ዲሞክራቶች ጋርም ትብብር ማድረግ እንደሚያስፈልጋቸው
ፕሮፌሰር ተስፋጽዮን ያነሡት ሐሳብ የሚታመንበት ነው።

No comments:

Post a Comment