Feb 9, 2013

የኢኦተቤ ፓትሪያርክ ምርጫ


የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ስድስተኛዉን ፓትሪያርክ ለመምረጥ ቀን መቆረጡን አስመራጭ ኮሚቴዉ አስታወቀ። በዚሁ መሠረትም በየካቲት 24ቀን የአዲሱ ፓትሪያርክ ሲመት እንደሚከናወን የአስመራጭ ኮሚቴዉ ሰብሳቢ ይፋ አድርገዋል።
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን አንድ ፓትሪያርክ ከዚህ ዓለም በሞት ሲለይ ቀጣዩን ፓትሪያርክ ከ40 እስከ 80 ቀናት ባለዉ ጊዜ እንደምትመርጥ ህገ ቤተክርስቲያኗ ያመለክታል። አምስተኛዉ የቤተክርስቲያኒቱ ፓትሪያርክ ካረፉ መንፈቅ ሞልቶ ትናንት የቤተክርስቲያኒቱ ፓትሪያርክ አስመራጭ ኮሚቴ ስድስተኛዉ ፓትሪያርክ የካቲት ወር መገባደጃ ላይ እንደሚመረጡ ይፋ አድርጓል። የአስመራጭ ኮሚቴዉ ሰብሳቢና የጅማ ሀገረ ስብከት ሊቀጳጳስ አባ እስጢፋኖስ ትናንት በንባብ ባሰሙት መግለጫ ኮሚቴዉ በተቋቋመ አንድ ወር ጊዜ ዉስጥ እቅዱን ለቋሚ ሲኖዶስ አቅርቦ ማፀደቁን አመልክተዋል። በመግለጫቸዉም የመራጮች ቁጥር ስምንት መቶ እንደሚሆን፤ በአስመራጭ ኮሚቴዉ ለፓትሪያርክነት የታጩ አምስት እጩ ፓትሪያርኮች ስም ዝርዝርም የካቲት 18 ቀን 2005ዓ,ም ይፋ እንደሚደረግ ገልፀዋል።
ጌታቸዉ ተድላ ኃይለጊዮርጊስ
ሸዋዬ ለገሠ
ተክሌ የኋላ

No comments:

Post a Comment