Feb 22, 2013

The power of non violence!!!

አንድ ነገር ፍርድ ቤት ሲቀርብ ፈረንጆቹ በሕግ ቋንቋ አንድ ሰው ጥፋተኛ ነው ለማለት ከመጠራጠር ባለፈ ወይም ምንም ዓይነት መጠራጠር በሌለበት ሁኔታ አሳማኝ መሆን አለበት ይላሉ፡፡ በእኛ እምነት በአባሎቻችን ላይ የቀረቡት ማስረጃዎች የሰነድ፣ የድምፅ ወይም የምስል ማስረጃዎች ከመጠራጠር ባለፈ ሊያሳምኑ የሚችሉ ናቸው ብለን አናስብም፡፡ አናምንምም፡፡ ግን መንግሥት መንግሥት ነው፤ ለጊዜው አቅም አለው፡፡ ስለዚህ አንድን ነገር እሱ በፈለገው ሊተረጉመውና ትርጉም ሊሰጠው ይችላል ከተባለ እኛ ሕግ እናከብራለን፤ ፍርድ ቤት የሰጠውንም ውሳኔ እንቀበላለን፡፡ ነገር ግን አምነንበታል ማለት አይደለም፡፡ ከጥርጣሬ ባለፈ አምነንበታል ማለት አይደለም፡፡ እኛም ብቻ ሳንሆን ዓለም አቀፍ ታዛቢዎችም የሚሉት ነገር ነው፡፡ ብዙ ሰዎች የፍርድ ቤቱን ሒደት ተከታትለዋል፡፡ ብዙ ጊዜ የምንሰማው ከጥርጣሬ ባለፈ የሚያሳምን አይደለም የሚል አስተሳሰብ አላቸው፡፡ እኛ እውነተኛና በትክክል ከጥርጥር ባለፈ የሚያሳምን ነገር ቢገኝባቸው፣ ሕግ እንዲከበር እንፈልጋለን፡፡ መንግሥትም ተዓማኒ እንዲሆን እንፈልጋለን፡፡ ተግባሩና ድርጊቱ አዎ ትክክል ነው፤ የተሰጠው ፍርድም ትክክል ነው ብለን እንቀበላለን፡፡ ምክንያቱም ሕግ እንዲከበር ስለምንፈልግ፡፡ በአገራችን በእውነት ላይ የተመሠረተ ፍርድ ቅዱስ ነው፡፡ ከሰማይ በታች የተከበረ ነገር ነው፡፡ ስለዚህ ትክክለኛ ይሁን ነው ጥያቄያችን፡፡ ካልሆነ ግን የግዴታ ሥራ ነው ማለት ነው፡፡ አለቃ አዟል፣ መንግሥት አዟል በሚል ትክክል ያልሆነውን ፍርድ ተቀበሉ ከተባለ ፍርዱን እንቀበላለን፤ ልባችን፣ ነፍሳችን፣ ሕይወታችንና ኅሊናችን ግን አይቀበለውም፡፡  

No comments:

Post a Comment