Apr 29, 2013

ወይዘሮ መብራት እንኩአንም የዘንባባ ዝንጣፊ ይዘዉ ተቀበሉኝ አላልሽ

Hei , Vi har flyttet dagens program til et trygg og trivelig sted Radisson Blu Hotell Adr. Holbergsgt 30. Bak slottet, trikk 11,17,18 var presis kl.15:00 Alle deltagere må ha gyldig legitimasjon og forhånd melde plikt på tel 96991387.Vi har kun en felles nasjonal interesse som er å bekjempe fattigdom ved kjøp av Millennium Dam bond, ellers ingen politiske motiv.
Velkommen



 English translation: Hi, We have moved the current program to a safe and pleasant place Radisson Blu Hotel Adr. Holbergsgt 30 Behind the castle, tram 11,17,18 was accurate kl.15: 00 All entrants must have valid identification and pre-notification duty at tel 96991387.Vi only has a national interest which is to reduce poverty by purchasing Millennium Dam bond, or no political motive.
Welcome  


ለአባይ ግድብ ቦንድ ሽያጭ ዝግጂቱ 1 ሰአት ሲቀረዉ SMS የደረሰን ነዉ እኔ የምለዉ ግን ነብር እንዳባረራት ሚዳቌ ነፍስ አዉጭኝ ከ5 STAR ሆቴል ሆቴል እየተሮጠ ነዉ እንዴ አባይን የሚገድቡት፣ድህነትን እንቀ ንሳለን የሚሉት ወጉም አልቀረባቸዉ᎓


 ወሃ ዉስጥ እንደገባች አይጥ ኮሰስ ብለዉ ሲወጡ እያየን 150 000 KR ሰበሰብን ይሉናል ለነገሩ ቀኑ ሆሳህና ነበረ እና እንኳንም የዘንባባ ዝንጣፊ ይዘዉ ተቀበሉን አላሉን እንዳይሉ ምን ይገድወት ነበር እድሜ ለአይጋ ፎረምእና ETV᎓᎓

Apr 27, 2013

የእኔ ጥያቄ የእስረኛ ቤተሰቦችን እንዴት መርዳት ይቻላል ነዉ


የተዘነጉት እስረኞች” እና የተዘነጋው የቤተሰቦቻቸው ስቃይ


ላለፉት አራትዓመታት ቃሊቲ ማረሚያ ቤት ቅዳሜ እና እሁድ የሄደ ሰው ወጣቷን ናርዶስን ሳያገኝ አይመለስም፡፡ ናርዶስ ገና የ20 ዓመት ወጣትእና በኪያሜድ የመጀመሪያ ዓመት የነርሲንግ ተማሪ ናት፡፡ ናርዶስ ዘሪሁን በየሳምንቱ ቃሊቲ ማረሚያ ቤት የምትመላለሰው በ‹‹አሸባሪነት›› ‹በእነብርጋዴር ጄኔራልተፈራ ማሞ መዝገብ› ከተከሰሱት 36 ሰዎች መካከል ዕድሜ ልክ የተፈረደባትን እናቷን ልትጎበኝ ነው፡፡ እነዚህ እስረኞች ሚያዝያ16/2001 አመሻሹ 12 ሰዓት አካባቢ ነበር ሁሉም በያሉበት በቁጥጥር ስር የዋሉት፡፡ እኛም 4ኛ ዓመታቸውን ለማሰብ ተሰባስበንወደቃሊቲ ማረሚያ ቤት በተለይ እማዋይሽ ዓለሙን ለመጠየቅ ሄደን ነበር፡፡ እንደተለመደው ናርዶስንም አገኘናት እና ብዙ ነገሮችንአጫወተችን፡፡

ናርዶስ ትረካዋን የጀመረችው እናቷን እና ሌሎችም በተመሳሳይ መዝገብ ተከሰው የተፈረደባቸውንሰዎች አያያዝ ነበር፡፡ ‹‹ሳስበው የተረሱ ያህል እየተሰማኝ ነው፤ ምክንያቱም ብዙ ጊዜ ሚዲያዎች ስለነሱ አይደለም እያነሱ ያሉት፡፡በእናቴ ክስ የታሰሩት ከ30 ሰዎች በላይ ናቸው፡፡ አንድ ሰሞን ከይቅርታ ጋር በተያያዘ ስማቸው እየተነሳ ነበር አሁን ግን ሁሉነገር የተረሳ ይመስለኛል›› በማለት የእስሩ ሕመም ለታሳሪዎቹ እና ለቤተሰቦቻቸው ግን የሚረሳ ዓይነት አለመሆኑን ነገረችን፡፡

‹‹ሚያዝያ16፣ አርብ ቀን ነበር ሁሉም የተያዙት›› በማለት ሲታሰሩ የነበረውን ጠቅላላ ሁኔታ በማስታወስ ትጀምራለች፡፡ ‹‹ለአንድ ሰው የመጡየማይመስሉ ብዙ ሲቪል የለበሱ እና የፌዴራል ፖሊስ ልብስ የለበሱ ፖሊሶች መሳሪያቸውን አቀባብለው ነበር ወደቤት የገቡት፡፡ ስልካችሁንአጥፉ ወደማንም እንዳትደውሉ አሉን፡፡ የብርበራ ማዘዣ ይዘው ነበር፤ ‹ቤት ልንፈትሽ ነው የመጣነው እማዋይሽ ዓለሙ በቁጥጥር ስርውለሻል› አሏት ቤት ፍተሻው እስከ ምሽቱ አራት ሰዓት ድረስ ቀጥሏል፡፡ ቀኑ አርብ ነበር፤ እናቴ ደግሞ እስከ 12 ሰዓት ትጾምስለነበር ከሥራ ወደቤት እንደገባች ‹ምግብ ስጡኝ› እያለች እያለ ነበር ፖሊሶች የገቡት ስለዚህ ምግብ ሳትበላ ውላ ነው ወደ እስርቤት የወሰዷት፡፡ ከዚያ በኋላ አራት ወራት ያክል ዓይኗን አላየነውም ነበር፤ ትሙት ትኑር የምናውቀው ነገር አልነበረም፡፡ ደግነቱ በሌላ ጉዳይ ታስራ በተፈታች ሴት አማካይነት መልዕክት ደረሰኝ፡፡ ‹አንቺደህና ከሆንሽ ሽሮ እና ጎመን ሰርተሸ አስገቢልኝ፤ እኔ ደግሞ ደኅንነቴነን የባናና ማስቲካ ወረቀት እልክልሻለሁ፡፡ ደኅና ካልሆንኩኝግን ያ ነገር ይቀራል› ብላ ላከችብኝ፡፡ ከዚያ እኔም ሽሮ እና ጎመን ሠርቼ በመላክ፣ እሷም የባናና ወረቀት በመላክ ደኅንነታችንንየሚገልፅ መልዕክት እንለዋወጥ ነበር፡፡ ይህ ሁሉ እየሆነ ባለበት ሰዓት እኛ በሌለንበት ጉዳያቸው ፍርድቤት ይታይ ነበር፡፡›› በማለትጉዳያቸው በኢፍትሐዊ መንገድ በመንግሥት እንደተያዘ አጫውታናለች፡፡

‹‹እናቴ ስዕልመሳል ትወዳለች፡፡ እናም በየጊዜው የጀመረቻቸው ስዕሎች የተበላሹ ሲመስሏት ቅርጫት ውስጥ ትጥላቸዋለች፡፡ ይመስለኛል፤ የቤት ሠራተኛችን እጅ አለበት፡፡ ስትታሰር የቀረበባት መረጃ እነዚህ የተጣሉወረቀቶች ተሰብስበው ‹የድርጅቱን አርማ ስታዘጋጅ ነው› የሚል ነው፡፡ ሌላው ቀርቶ ፈቃድ የነበረው፣ ያውም የማይሠራ ሽጉጥም እንዲሁበማስረጃነት የቀረበባት መሆኑ ነው፡፡›› በማለት ለእርሷ ፍርዱ ፍትሐዊ አለመሆኑን እና እናቷም ነጻ መሆኗን እንደምታምን ነግራናለች፡፡

‹‹የሚያሳዝነውነገር ደግሞ ሲታሰሩ በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን የተላለፈው ዜና ነው፤ እንኳን አገር ወዳዷ እናቴ ማንም ባገሩ ላይ የሚያደርገውን ነገርነው አደረጉ ያለው፤›› የዜናውን ፖለቲካዊ ወገንተኝነት ወቅሳለች፡፡ እናቷ ሕዝብና አገር የማሸበር ፍላጎት ሊኖራት ለአገር ፍቅርሕይወቷን የሰጠች መሆኗን ስታጫውተን ‹‹እናቴ ሁልጊዜ የምትነግረኝ ነገር አለ፤ ሕይወቴ ማለፍ ካለበት አገሬን በሚጠቅም ነገር መሆንአለበት ትለኝ ነበር፤›› ብላናለች፡፡ ነገር ግን መንግሥት በአንድ በኩል ‹‹ሕገ መንግሥቱን ለመናድ በመሞከር ነው ያሰርኳችሁ እያለበሌላ በኩል ደግሞ የፖለቲካ እስረኞች የሉኝም ይላል፤›› ካለች በኋላ ‹‹ተቃዋሚ መባላቸው ካልቀረ የኢሕአዴግ መንግሥት የፖለቲካእስረኞች እንደሆኑ ቢያምን እንኳ ጥሩ ነው፤›› ብላናለች፡፡ ‹‹እናቴለአገሯ ከማንም በላይ ሠርታለች ብዬ አምናለሁ፡፡ ነገር ግን አገራችንለእናቴ ውለታዋን እየከፈለቻት ነው ብዬ አላምንም፡፡ ያለሃጢያታቸው ሃጢያት ተሰጥቷቸው ነው ያሉት›› በማለት ፍርዱ አገር ወዳድእናቷን የሚያዋርድ እንደሆነ በሐዘን ተርካልናለች፡፡

የእናቷ በአሸባሪነትመፈረጅ ለናርዶስ ማኅበራዊ እና ስነልቦናዊ ቀውስ እያደረሰባት መሆኑንም አጫውታናለች፡፡ ‹‹ለትምህርቴ መስጠት የሚገባኝ ጊዜ ያህልመስጠት አልቻልኩም፤ እናቴ የታሰረችው እኔ ስምንተኛ ክፍል እያለሁ ነበር፡፡ ዩንቨርስቲ መግባት ሲኖርብኝ አሁን ግን ‹ነርሲንግ›እየተማርኩ ያለሁት በዚሁ ተፅዕኖ ነው፡፡ ሌላው ቀርቶ የእነርሱን የእስር ዜና ኢቲቪ ከአቀረበበት መንገድ አኳያ ትምህርት ቤት ውስጥራሱ እኔን መቅረብ የሚፈሩ ሰዎች አሉ፤› በማለት የእናቷ እስር በእርሷ ማኅበራዊ ሕይወቷ ላይ ያጠላበትን ጥላ አጫውታናለች፡፡

‹‹እስጢፋኖስአካባቢ የሚገኘው እና በእናቴ ስም ተይዞ የነበረው የቀበሌ ቤታችንበልማት ስም ሲፈርስ እንኳን ለጎረቤቶቻችን በምትኩ ሲሰጣቸው ለእኛ ግን አልተሰጠንም፡፡ ሌላው ቀርቶ መታወቂያ እንኳን ለኛ ለመስጠትፈቃደኞች አይደሉም›› ቤታቸውን ካፈረሱባቸው በኋላ አክስቷ ጋር እየኖረች እንደሆነ ስትነግረን በየመሐሉ እየገታችው ታወራልን የነበረውእምባዋ ከቁጥጥር ውጪ ሆኖ ሲወርድ ማድረግ የቻልነው ነገር ቢኖር በዝምታ ማጀብ ነበር፡፡

‹‹ያለአባትያሳደገችኝን የእናቴን ፍቅሯን አልጠገብኩትም›› የምትለን ናርዶስ ‹‹በዚህ ዕድሜዬ ለኔ የሚገባኝ ቦታ ቃሊቲ አልነበረም፡፡›› በማለትብዙ ነገር መሥራት በነበረባት ጊዜ ቃሊቲ በመመላለስ እንዲባክን መንግሥት እንደፈረደባት እንደሚሰማት ነግራናለች፡፡ ‹‹አራት ዓመቱን በአሰቃቂ ሁኔታ ነው ያሳለፍኩት፤ ከ16 ዓመታት በኋላ ከእስር የተፈታው አባቴየራሱን ሁሉ ነገር ትቶ ሕይወቱን ለኔ መስዋዕት ባያደርግ ኖሮ አልወጣውም ነበር›› በማለት እንደዕድል እናቷ ከመታሰሯ ሁለት ወርያክል ቀድሞ በተፈታው አባቷ ድጋፍ ከብዙ ቀውስ እንደተረፈች እየነገረችን ከናቷ ጋር የነበራትን ፍቅር ‹‹እናቴ ሁለ ነገሬ ነች!››ብላለች፡፡

‹‹እናቴንሊጎዳ የሚያስብ ሰው እኔን አንድ ነገር ሊያደርግ ይችላል በሚል ተሳቅቄነው የምኖረው›› በማለት በዙሪያዋ ያለውን ወዳጅ እና ጠላት እንኳን ማመን እየቸገራት እሷ ራሷም ቢሆን ከማኅበረሰብ የመነጠል እናየመስጋት ስነልቦናዊ ችግር ውስጥ እንደሆነች አስረድታናለች፡፡

‹‹የርዕዮትዓለሙእህት እስከዳር ዓለሙ ‹የቤታችን ሰላም እና ፍቅር ከርዕዮት ዓለሙ ጋር ታስሯል› ያለችው በጣም ትክክል ነው›› በማለት በታሰሩት ሰዎች ቁጥር እኩል የሚሆኑ ቤተሰቦች በከፍተኛ ፈተናውስጥ እያለፉ መሆኑን አበክራ ነግራናለች፡፡

የናርዶስ ታሪክ የብቻዋ ታሪክ አይደለም፡፡ የሌሎች የብዙ ቤተሰቦቻቸው የታሰሩባቸውቤተሰቦች ታሪክ ነው፡፡ ናርዶስም ‹‹እንደኔ ሁሉ ችግር ላይ ያሉ፣ አባቶቻቸው የታሰሩባቸው ብዙ ልጆች አሉ›› ብላናለች፡፡ በዚሁመዝገብ ተከሰው የሞት ፍርድ የተፈረደባቸው አቶ መላኩ ተፈራ ቤተሰቦችም ከሰኞ እስከ እሁድ ቃሊቲ ደጃፍ ላይ ከማይጠፉት ሰዎች ውስጥይመደባሉ፡፡ በሥራ ጉዳይ ከአገር ውጪ ያለችው ልጃቸው ፅዮንም አባቷን ለመጎብኘት ሲባል ቶሎ፣ ቶሎ እንድትመላለስ ተገድዳለች፡፡እነጄኔራል ተፈራ ማሞ፣ እነአሳምነው ፅጌ እና ሌሎችም ደግሞ በእስረኞችመሐል ‹‹ተነስቷል በሚል ፀብ›› ሰበብ ከቃሊቲ ማረሚያ ቤት ወደዝዋይ እንዲዛወሩ ተደርገዋል፡፡ ይህ ከቤተሰቦቻቸው ጋር እንዳይገናኙሌላ ተጨማሪ ጫና አሳድሮባቸዋል ብላናለች፡፡ እዚህ የቀሩት ታሳሪዎችም አጋሮቻቸውን በማጣት ለብቸኝነት ስሜት ተዳርገዋል፡፡

ከነርሱ መዝገብውጪ ያሉ ሌሎችም እስረኞች እና ቤተሰቦቻቸው በተመሳሳይ ፈተና ውስጥ መሆናቸውን እስረኞችን ለመጎብኘት በሄድንባቸው ጊዜያት ተረድተናል፡፡መንግሥት ለፖለቲካ ግብአቱ የይቅርታ ደብዳቤ ካስፈረማቸው በኋላ እንኳን ለመፍታት ፍላጎት አያሳይም፡፡ ይልቁንም፤ ከቦታ ቦታ እያዘዋወረስቃያቸውን ያበዛል፡፡ ለዚህ እንደምሳሌ ባለፈው አርብ (ሚያዝያ 11/2005) ወደዝዋይ እንዲዘዋወር የተደረገው ጋዜጠኛ ውብሸትታዬ ተጠቃሽ ነው፡፡ በእርሱ የጋዜጠኝነት ደሞዝ ላይ ጥገኛ የነበሩት ባለቤቱ እና ልጁ (ፍትሕ ውብሸት) በእናትዬው መፍጨርጨር ሕይወታቸውንእንዲመሩ ከመገደዳቸውም በላይ አሁን የቤቱን አባውራ ለመጠየቅ ዝዋይ ድረስ እንዲመላለሱ ተፈርዶባቸዋል፡፡ ለዚህም ነው መንግሥት የፖለቲካ አይደሉም የሚላቸውን የፖለቲካ እስረኞችን ከነቤተሰቦቻቸው ከሚቀጣበት መንገድ ይታረም ዘንድ ሊጠየቅ ይገባዋል በማለት የምንመክረው፡፡
----
ይህ ጽሑፍ ዕንቁ መጽሔት ላይ ታትሟል!

Apr 23, 2013

በህወሓት የጉባኤ ኣጀንዳ ዙርያ ስብሰባ ሊጠራ ነው …!


 አብራሃ ደስታ 
ከኢህኣዴግ ጉባኤ በኋላ መሪዎቻችን (ከበፊቱ ብሶባቸው) መግባባት ኣቅቷቸዋል። በፌደራል ደረጃ የሚደረጉ ስብሰባዎች ያለ ዉጤት ይጠናቀቃሉ። ለምን ኣይግባቡም? (‘ቀሽም ጥያቄ’) የሚያግባባ ነጥብ የላቸውማ። ድሮ (ባለራእዩ መሪዕረፍት በፊት) ሁሉም ነገር እሳቸው ይሰሩት ስለነበር) በመሪያቸው ነበርየሚግባቡት’ (አብረው የሚጓዙ) በሰውይግባባሉ’ (ሌላ ሊያግባባቸው የሚችል ሓሳብ ወይ መርህ አልነበራቸውም፣ የላቸውም) አሁን ታድያ እንዴት ይግባቡ?

ባለራእዩሰውዬ መመርያ ይሰጣል፣ፖሊሲ ነው ተግብሩትይላቸዋል፣ እነሱም እሱ የተናገረውንቃልእየደገሙ (ከላይ እስከ ታች) ይዘምራሉ። ስሕተት መሆኑ (ሊተገበር የማይችል መሆኑ) ሲረዱስሕተቱ ያለው አፈፃፀም ላይ ነውብለው ራሳቸው ያፅናናሉ። ህዝቡ በማይፈፀሙ ፖሊሲዎች ተስፋ እንዳይቆርጥ መሪዎቻችን ሁሌ ስለ አዲስ ፖሊሲ ወይ አሰራር ይሰብካሉ። ሁሌ ስለአዲስ ኣሰራርወይ ዕቅድ ሲወራልን ለውጥ የመጣ ያህል እንዲሰማን ለማድረግ ያህል ነው።

አሁን ሰውየውአርፈዋል ለተከታዮቻቸው የተውት መርህ መሰረት ያደረገ የፖለቲካ አቅጣጫ የለም። የኢህኣዴግ ካድሬዎች ታድያ አሁን የሚግባቡበት ቋንቋ የላቸውም። የኣምስት አመቱየዕድገትና የትራንስፎርሜሽን አቅድይዘት ወይ መሰረታዊ ፅንሰ ሓሳብ ምን እንደሆነ የሚያውቀው የለም። በዚህ ጉዳይ ተደጋጋሚ ውይይት ተደርጎ ያለ ዉጤት ተበትነዋል። (ዕቅዱ ግን ድሮውም ቢሆን ምንም የሚጨበጥ ሓሳብ አልነበረውም ….. የሚሰማን አጣን እንጂ) ዕቅዱ ‘Ambitious’ ብለን በተደጋጋሚ አሳስበን ነበር (‘ሊተገበር የሚችል ዕቅድ አሳዩንብለን ተማፅነን ነበር) አሁን ግን ካድሬዎቹ ራሳቸው (በተለያዩ ስብሰባዎች) ‘የተለጠጠው (ዝተለጠጠ)’ ዕቅድ ማለት ጀምረዋል።

በኢህኣዴግ ደረጃ ያለው ችግር የስልጣን ሽኩቻ ነው (የባለስልጣናቱ ዓላማ ስልጣን ነው) ህወሓቶች በኢህኣዴግ የነበራቸው ሚና ማጣት አይፈልጉም። ግን ይህንን ሚና ሊጫወት የሚችል ደህና ሰው የላቸውም። (ዓቅም የነበራቸው የፓርቲው ሰዎች በተለያየ ምክንያት እንዲጠፉ ተደርገዋል ) ራሳቸው በራሳቸው ችግር ፈጥረው (በሁለት ተከፍለው፣ ጓደኞቻቸው ኣባረው) ተዳክመዋል (አሁን ትግራይ እንኳ መቆጣጠር በሚችሉበት ሁኔታ ኣይገኙም) 

በኣሁኑ ግዜ በኢህኣዴግ ዉስጥ የተሻለ የስልጣን ተፎካካሪ ብአዴን ነው። ግን ብአዴን ከሌሎች ሦስቴ የኢህኣዴግ አባል ድርጅቶች ተቀባይነት የለውም። የህዝብ ድጋፍም በሰፊው የለውም። የሚጠበቀው ያህል (ኢህኣዴግ ለመቆጣጠር የሚያስችል) ጠንካራ አባላትም የሉትም። ግን በኢህኣዴግ ስርወ መንግስት የህወሓት አልጋ ወራሽ ብአዴን ይመስላል። በህወሓትና ብኣዴን ከፍተኛ ውዝግብ አለ።

ኦህዴድ በኢህኣዴግ ዉስጥ በጣም ያኮረፈ ቡድን ነው። የተለያዩ ምክንያቶች እየደረደረ ስልጣን ለኦህዴድ መሰጠት እንዳለበት ይወተውታል። ግን ኦህዴድ ሁለት ችግሮች ተደቅነውታል። (አንድ) በኦህዴድ ውስጥ መግባባት ብሎ ነገር የለም። (ሁለት) በሌሎቹ የኢህኣዴግ አባል ድርጅቶች እምነት ባለፈው የኦህዴድ ጉባኤ ወደ ሓላፊነት የወጡ ሰዎች ከኦነግ ጋር ግንኙነት አላቸው። በነሱ እምነት ኦነግ የኦህዴድ መዋቅር ተቆጣጥሮታል። ስለዚ ለኦህዴድ ስልጣን መስጠት እጅግ ያስፈራቸዋል።

ሌላው ደኢህዴን ነው። ደኢህዴን ጠንካራ ኣይደለም። በሁለት ቡድኖች ተከፍሎ ትርምስ ላይ ነው። ከቡድኖቹ አንዱ ከህወሓት ጎን መሰለፍ ይፈልጋል። ብቻውን (ህወሓት ከዚህ በፊት እንዳደረገው) የኢህኣዴግ ስልጣን መቆጣጠር የሚችልበት ዕድል የለውም። ህወሓትም ቢሆን ደካማ ሁነዋል። ዶር ደብረፅዮን ገብረሚካኤል በኢህኣዴግ ጉባኤ ሲናገርበቃ ወድቀናልብሎ ነበር። ይሄ ከህወሓት ጋር መጠጋት ለሚፈልግ ቡድን ራስ ምታት ነው።

ህወሓቶች ጉዳዩ ኣስጨንቋቸዋል። የነ አባይ ወልዱ ቡድን የነ አርከበ ዕቁባይ ቡድን ካባረሩ ወዲህ የባሰ ንትርክ ዉስጥ ገብተዋል። እርስበርሳቸው አይግባቡም፣ ይናናቃሉ። የኣሁኑ መሪዎች ማንም አያከብራቸውም። በህወሓት ጉባኤ የተሳተፉ አባላት በነ ኣባይ ወልዱ የተመለመሉ ቢሆኑም በጉባኤው ወቅት በነኣርከበ የተወሰደው እርምጃ ግራ አጋብታቸዋል። ጉባኤተኞቹእነ ኣርከበ ከውጡ ህወሓት ከማን ትቀራለች?’ የሚል ጥያቄ ነበራቸው። 

የፓርቲው ሊቀመንበር የሚመረጠው (በፓርቲው ደንብ መሰረት) በጠቅላላ ጉባኤ ነው (በቀጥታ ግን አይደለም) እንዲህ ነው። ጉባኤተኞቹ አርባ አምስት የፓርቲው የማእከላዊ ኮሚቴ አባላት ይመርጣሉ። በውጤቱ (ባገኙት ድምፅ) መሰረት በቅደም ተከተል (የተመረጡት ሰዎች) ስማቸው ይገለፃል። የማእከላዊ ኮሚቴ አባላት የፓርቲው ስራ ኣስፈፃሚ (ፖሊት ቢሮ) ይመርጣል። ፖሊት ቢሮ አባላት ደግሞ የፓርቲው ሊቀመንበርና ምክትል ይመርጣሉ።

በምርጫው ከፍተኛ ስልጣን ያለው (በመርህ ደረጃ) ጉባኤተኛው ስለሆነ ከፍተኛ ድምፅ ያለው (By Default) የፓርቲው ሊቀመንበር ይሆናል። የማእከላዊ ኮሚቴ አባላት ይሄንን አውቀው ባገኙት ድምፅ መሰረት ዘጠኙ (Top Nine) ለፖሊት ቢሮ ይመርጣሉ። ፖሊት ቢሮ አባላትም በተሰጠው ድምፅ መሰረት ከፍተኛውን ያገኘ የፓርቲው ሊቀመንበር አድርገው ይመርጣሉ።

በጉባኤው የተሳተፉ አባላት ሊቀመንበር (ከተሰጣቸው አማራጭ) አድርገው የመረጡት ዶር ደብረፅዮን ነበር። ዶር ደብረትፅዮን የኣንደኛነት ድምፅ ሲያገኝ አባይ ወልዱ ሁለተኛ ነበር። (ደብረፅዮን ለኣባይ 23 ድምፅ ይበልጠዋል) ውጤቱ ግን ጉባኤተኞቹ እንደጠበቁት ኣልሆነም። የፖሊት ቢሮ አባላት ሁነው የተመረጡት (top nine) ዘጠኙ ኣልነበሩም። በውጤቱ መሰረት የህወሓት ሊቀመንበር መሆን የነበረት ዶር ደብረፅዮን ሲሆን ዉጤቱ ተገልብጦ አቶ ኣባይ ተመረጠ። ይሄ የሆነው የኣቶ አባይ ቡድን አብዛኛው የማእከላዊ ኮሚቴ ወንበር መያዝ በመቻሉ ነበር። (ጉባኤተኞቹ የነኣባይ ቡድን ደጋፊዎች ሲሆኑ አባይ ፓርቲው ይመረዋል ብለው ግን አያምኑም። ስለዚህ ጉባኤተኞቹ ደብረፅዮን ሊቀመንበር አድረገው መርጠው እንደሄዱ ነው የሚያውቁ)

ይሄን ዉሳኔያቸው ታድያ በጉባኤተኞቹ ጥሩ ስሜት አልፈጠረም። የኣሁኑ መሪዎች የህዝብ አመኔታም የላቸውም። ይሄን ችግር ለመፍታት ሲሉ ከነገ እሮብ (ሚያዝያ 16, 2005 ዓም) ጀምሮ ጉባኤው በተመለከተ በመላው ትግራይ (በየደረጃው ከከፍተኛ የክልል ቢሮዎች ጀምሮ እስከ ቀበሌ አስተዳደር ድረስ) ስብሰባ እንደሚደረግ ታውቋል። ለስብሰባው ማስኬጃ ብዙ ሚልዮን ብር ተመድበዋል (ከመንግስት ካዝና መሆኑ ነው) 

ኣየ ህወሓት! በቃ ስብሰባ ነው። እኔ ደግሞ ስብሰባ ስጠላ! (እንኳን የህወሓት አባል አልሆንኩ)

It is so!!!