Apr 2, 2013

ኢህአዴግ 3 ሚሊዮን 245 ሺህ ኢዴፓ ደግሞ በ1 እጩ ተፋጠዋል!


መጪው ሚያዚያ በመላ ሀገሪቱ በሚካሄደው የወረዳና የክልል ምክር ቤቶች ምርጫ ዙሪያ የከተማው ህዝብ ሁሉ መነጋገሪያ መሆኑን የሞቃዲሾ ከተማ አንዳንድ ነዋሪዎች መናገራቸውን ሶዜአ (ኢዜአ አላልኩም) ዘገበ፡፡የሰሞኑን የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ በመ
ከታተል ተጠምደው ያሉት የጩርጩራ ወረዳ ነዋሪዎች አርሴናል ምንም እንኳ ከሻምፒዮንስ ሊግ ቢሰናበትም የሚያዚያው የኢህአዴግና የኢዴፓ የምርጫ ፉክክር የዋንጫ ጨዋታ ያህል እንደሚጠበቅ ናግረዋል፡፡የሚያዚያውን ምርጫ በጉጉት እንዲጠብቁ ካስቻላቸው ክስተት መካከል በየትኛውም አለም ተደርጎ በማያውቅ ሁኔታ ከሶስት ሚሊዮን በላይ እጩዎችን ያቀረበውን ገዥውን ፓርቲ በአንድ እጩ ለመ
ገታተር ቆርጦ የተነሳው የኢዴፓ ውሳኔ እንደሆነ የሚናገሩት የቦስኒያ የመልካም አስተዳደርና ህዝብ አደረጃጀት የስራ ሂደት መሪ ውጤቱ ምንም ይሁን ምን ኢዴፓ የህዝብን ውሳኔ በፀጋ መቀበል እንዳለበት አስጠንቅቀዋል፡፡ምርጫውንም ሆነ የምርጫውን ውጤት በናፍቆት እንደሚጠብቁት የሚናገሩት የሴራሊዮን የሴቶች ህጻናትና ወጣቶች ሊግ ተወካዮች በበኩላቸውም የሁለቱ ፓርቲዎች ፍልሚያ እጅግ አጓጊ መሆኑን ግምት ውስጥ በማስገባት ሂደቱ በጊነስ ቡክ ኦፍ ሪከርድስ መዝግ ላይ እንዲሰፍር የተቻላቸውን ሁሉ ጥረት እንደሚያደርጉ ቃል ገብተዋል፡፡አንድ እጩ ያቀረበው ኢዴፓ ባይመረጥ በመላ ሃገሪቱ ብጥብጥ እንዳይነሳ ስጋት አለን የሚሉ የባንግላዲሽ ከተማ አማካሪዎች ምክር ቤት አባላት በበኩላቸው ገዥው ፓርቲ እንደከዚህቀደሙ ፍትሃዊ ምርጫ ለማካሄድ የፈረመውን የስነ ምግባር ደንብ እንዲያከብር ጠይቀዋል፡፡ በሁለቱ ፓርቲዎች መካከል ክርክር በኢቲቪ ለመከታተል ቅድመ ዝግጅታቸውን የጠናቀቁት የአንጎላ ወጣቶች ሊግ አባላት ለሁለቱ ፓርቲዎች የተሰጠው የአየር ሰአት ድልድል ባቀረቡዋቸው እጩዎች ብዛት መደረጉ የምርጫውን ፍትሃዊነት ከወዲሁ እንደሚያሳይ ተናግረዋል፡፡የሚያዚያውን ምርጫ በተመለከተ የዚዚ ቲቪ ዘጋቢ ያነጋገረው በአዲስ አበባ መጽሃፍ በማዞር የሚተዳደር ወጣት ስለ ጉዳዩ ምንም አይነት ግንዛቤ እንደሌለው ከተናገረ በኋላ ስለሚያዚያው ምርጫ ከተሸከማቸው ቨየተለያ መጽሃፍት መካከል አንዱን መዞ ‹‹ ምርጫማ ጥሩ ነው ›› የተሰኘውን የገጣሚ ሰለሞን ሞገስን ግጥም ለዘጋቢው ጋብዞታል፡፡

No comments:

Post a Comment