ኃላፊነትና ግደታ አለብህ
ከቀመሩ ደሳለኝ
በማንኛውም አገር፣ ጊዜና ዘመን እያንዳንዱ ተተኪ ትውልድ የአገሩ ወራሽ፣ ተተኪና ተረካቢ፣ ጠባቂና
ለሚቀጥለውም ትውልድ የሚያወርስ፣ የማስተላልፍና የማስረከብ ኃላፊነትና ግደታ በፅኑ አለበት።
በየትውልዱ ሁሉ የሚጠበቅና የሚከናወን ግደታ ነው። አገር የአንድና የሁለት ወይንም ጥቂት ትውልድ
ብቻ የሚጠቀምባትና የሚያልፍ ሳይሆን ማያቋርጥ ቀጣይነት ያለው ትውልድ ሁሉ የሚቀባበለው፣
የሚጠብቀው ያለፈውንና የሚመጣውን ትውልድ ሁሉ የያዘና ያቀፈ የአገርና ሕዝብ የታሪክ ሂደት ነው።
በእያንዳንዱ ትውልድ ታሪካዊ መልካም ተግባር ይጠበቃል። በዚህም ታሪካዊ የተፈጥሮ ሕግና ሥርዓት
አገርን በደንብ ያገናዘቡ የእኛ ቀደምት ትውልዶች ኢትዮጵያን ለዚህ ትውልድ ያደረሷት በብሔራዊ
አንድነት፣ በማይበገርና በማይገሰስ በሕዝብ ቁርጠኛ ትግል የአገርን ሕልውና ጠብቀው ነበር።የአገርን
ሉዓላዊነት፣ የሕዝቧን ደህንነት፣ዳርድንበርን ለማስከበርና ለመጠበቅ ውድ ሕይዎታቸውን በመክፈል
በደምና አጥንት ገንብተው ነው።
ለአገር ነፃነት መልካም ምግባር፣በጎነት፣ቆራጥና ደፋር ልብን ይፈልጋል።አገር ያለነፃነት አገር አይሆንም።
ነፃነት ሕያው የሕይውት ዋስትና መሰረትና አብይ ጉዳይ፣ የአገር ፍቅርና የክብር እሴት ሃብት ነው።ነፃነት
ዋጋ አለው። ይህውም ውድ የሆነ የሕይወት መሰዋዕትነት ደም ነው።ኢትዮጵያ ለብዙ ሺህ ዘመናት በነፃነት
ተጠብቃ የቆየችው የኛ ቀደምት ትውልድ በከፈሉት ቆራጥነት የደም ዋጋ ኃይል የአንድነት መሳሪያነት
ነው።በዚህም የኢትዮጵያ ሕዝብ ቆራጥነትና ፅናት አገርን በነፃነት መጠበቅ በዓለም ፊት ትልቅ ምሳሌነትን
ያተረፈ፣ ዛሬ ለአለነውና ለመጭውም ትውልድ የሚኰራበት ሕያው የታሪክ አለኝታ መመኪና ክብር፣
የዘላለም አገር ወራሽነት ሃብታችን በመሆኑ ጠብቀንና አስከብረን ለተተኪው ትውልድ ለማስረከብ
ኃላፊነቱ ከእጅግ ብርቱ ግደታ ጋር ነው።ለዚህም ነው “አገር አትሞትም ምንጊዜም ጠባቂ ትውልድ አላት”
የሚባለው። ይህን አምኖና ተቀብሎ አገርን በነፃነት የማይጠብቅ፣ወራሽ ትውልድ በኢትዮጵያ ሊኖር ከቶ
አይችልም። ከዚህ ያነሰ መስዋዕትነት ሆነ ኢትዮጵያዊነት የጐደለው ትውልድ፣ ከንቱ ትውልድ፣አገር
አልባነት፣ እፍረት፣ወራዳነት የቁም ሞት ነው። ሰው መሆን ይጠበቅብሃል።
ኢትዮጵያዊ ወጣት ትውልድ ሆይ !
አገርህ በባንዳዎች ወያኔ/ኢህአድግ ሸፍጥና ተንኰል ተተብትቦ ከደደቢት ጀምሮ እስከ አሁኑ ወቅት ድረስ
በአሀዳዊት እናት አገር ኢትዮጵያ ላይ የማጥፋት ዘመቻ እተካሄደና እየተፈጸመባት ትገኛለች።ሉዓላዊነቷ
በክህደት ተንቆና ተደፍሮ አገር ለሁለት ተከፍላ፣ የቀረው በጎጥ ወንጀል በቋንቋ ክፍፍል ተመድቦ፣ የአገር
ሕልውና የውሃ፣የአየር፣ የየብስ ዳር ድንበር ክልሏ ተደፍሮ፣ ተጥሶና ተዋርዳ አለች።በአምባገነንነት
በጠበንጃ ኃይል፣ በሕገ_ ወጥ ሕግ፣በሃሰት ሕገ_ መንግሥት፣በማጭበርበሪያ ዴሞክራሲ፣ በውሸት ሽፍጥና
ተንኰል ሕዝብ ሰብዓዊ መብቱን ተነጥቆ፣ዜግነቱን አጥቶ፣ ብሔራዊ ሃብትና ንብረቱን እየተዘረፈ፣ የአገሩ
ለም መሬት እየተሸጠ፣እተነጠቀና እየተባረረ፣ የሽብርተኛ ሕገ ወጥ ሕግ ወጥቶለት እየታሰረ፣እየተገረፈ ፣
ቶርች እተደረገ፣እየተገደለና እየሞተ፣ እየተፈናቀለና እየተሰደደ፣እንድሁም እየተሸጠ የአረብ አገር ባሪያእየሆነ በግፍና በጭቆና ማነቆ ተጠፍሮ በጥፋት ላይ በመሆኑ አንተ የኢትዮጵያ ወጣት ይህን በጽኑ ኅሌና
ተገንዝበህ በአስቸኳይ የምትታገለውና የምታጠፋው የባንዳ ሥርዓት ነው።
ወጣት ትውልድ !
ኢትዮጵያዊ ብሔራዊ ነፃነት ያነሰውና የጐደለው፣ዜግነትና አገራዊ ስሜትህን ተነፍገህ፣ በአደባባይ
ተዋርደህና ዝቅ ተደርገህ፣ ስብዕናና መብት ተነፍጐህ፣ኅብረተሰባዊ አንድነትህ፣ክብርና ኩራትህ ተንቆ
የአገሪቱ አጽመ _ርስት ባለቤትነትህ ተነጥቆ፣ በባንዳ ወያኔ በአጉል ጠባብ ጎጠኛ አቀንቃኝነት በቋንቋ
ልዩነት ክፍፍል ኢትዮጵያዊ አንድነትህ ከታሪክ ምዕራፍ አውጥቶ ሲያስትህ በውሸት ፕሮፓጋንዳ
ሳታውቀው እየቆሰልህና እየደማህ፣ እየነሆለልህ፣ እየጠፋህና እየሞትህ እንደሆነ ልብ በል ። ዳሩግን ልብ
ከአጣህ ቆየህ ።አንተ ዛሬ ወጣት በትምህርት ገበታ ላይ ነገ ደግሞ በሥራ ለአገር እድገት የምትሰለፍ
የመጭው ትውልድ መሰረት የሚጣልብህ ኃላፊነቱ እጅግ የላቀ ከፍተኛ የኅብረተሰብ ክፍል ነህ ብዬ
እገምታለሁ።ይህ ከዚህ በላይ የተዘረዘሩት ግፍና ጭቆና በአገርና ሕዝብ በአንተ በዛሬው አበባ በነገው
ፍሬና ዘር ላይ የተተበተበና የታሰረ ማንነትን፣ጥቅምና ደህነትን፣ አለኝታን የነጠቀና ያሳጣ በባንዳ ወያኔና
በሆዳም አድርባይ ባንዳዎች የማያባራ ፀረ_ኢትዮጵያ፣ ኢትዮጵያዊነትና ሰንደቅ ዓላማችን ላይ ያነጻጸር
የጥፋት ሴራ አጀንዳ ነው።ይህን የጠላት አመጣጥና አረማመድ በዓይነ_ኅሌና ልታይና ልትገነዘብ በተገባህ
ነበር። ነገር ግን ዘንግተሃል እያንቀላፋህ ነው።
“ባለቤቱን ካልናቁ አህያውን አይጭኑም፣ወይም አይመቱም” እንደተባለው አበው አነጋገር ቤተሰብህ እጅ
በመስጠቱ በአንተ በታዳጊው ላይ ብዙ ጥፋትና በደል እየተሰራብህ ነው።የትምህርት መጠን ውስንና
ጥራት ያነሰው፣አእምሮ ያልበሰለና አስተሳሰብ ያልሰፋ፣ የማይረዳ፣ማወቅ የተሳነውና ማንነትህን ያላገናዘበ፣
ለአገር ነፃነትና መብት የማታውቅ፣ደካማና የተናቀ፣ወራዳና የበታች በማድረግ ረግጦና አዞ ሊገዛህ፣
ሊመራህና ሎሌ ባርያ ሊያደርግህ ወያኔ በፈለገው አቅጣጫ በጠባብ ጎጠኝነት በቋንቋ ልዩነት ላይ ብቻ
ተመስርተህ ፣ ወያኔ የፈቀደልህን ባንዲራ በየመንደሩ እያውለበለብህ በውስን ግብዛዊ ስሜት
እንድትዋዥቅና እንድትቆራቆስ ሆኖ ኢትዮጵያዊ ዜግነትህን ዘንግተህ፣ ማንነትህን በሚያሳጣና በሚያስት ፣
በአልሆነ ጠማማ መንገድ ፣እየመራህና እንድትሄድ፣ጉድጓድም ውስጥ እንድትገባ የታቀደልህ ቦዘኔ ብኩን
ታዳጊ ትውልድ እንድትሆን ነው።
ወያኔ የአንተን አእምሮ አደንዝዞና ሰልቦ፣በማደንቆር ማንነትህን አሳጥቶ ቅል እራስ ሆነህ ወያኔ/ኢህአድግ
በአጠመደልህ ወጥመድ ዓይንህን ጨፍነህ፣ ጆሮህን አደንቁረህ ሰተት ብለህ በመግባት እራስህን፣ አገርና
ኅብረተሰብን የምትጐዳና የምትገድል ተልካሻ ትውልድ ሆነሃል።አገር እየጠፋች አንተ ሞትህን ሳታውቅ፣
የምዕራብ ዓለምን ብልጭልጭና የሚያብረቀርቁ የግብዞች ሽቅርቅር ጌጣጌጥ አልባሳቶች እየዋዠቅህ የወያኔ
ካድሬ ነጋደዎች ገንዘብ እየሰሩብህና የአንተን ወጣት ኅሌና ለማነኋለል፣ ለማጃጃልና ለመግደል በታሰበ
ርካሽ የባዕድ ባህሎች ተዘፍቀህ ፣በደደቢት ጫካና ዋሻ የለመዱትን ጸያፍ ወሲባዊ ድርጊት ፊልሞችን ፣
የተለያዮ የመጥፎ ፀባይ ሱስ፣አእምሮ አደንዛዥ እጾች፣የጫት፣ የዝሙት ድርጊቶች ሁሉ ተፈጻሚነት
ለማድረግ በአገር ውስጥ በስፋት በማስገባትና በማቅረብ የብዙ ሺህ ታዳጊ ውጣት አእምሮህን በመመረዝ
ሰለባ ውስጥ አስገብተውል፣ገብተሃል።
በዚህም ክስተት ማንነትህን፣ የአገር ወገን የወደፊት ትውልድ ኃላፊነትና ግደታ ዘንግተህ ወያኔን አፍቃሪ፣
አክባሪ፣ እንድሁም ፈርተህና ተሸማቀህ አጐብድደህ ከመኖር በስተቀረ ወያኔ/ኢህአድግ ጠላትና አጥፊነቱ
ገዳይህም መሆኑን በፍጹም መረዳት አልቻልክም።ከዚህም ጋር በጎዳና ተዳዳሪነት፣ በአጣና ቆራጭናፈላጭነት፣በኩብል ድንጋይ ጠራቢነት በወራዳ ተራ ኑሮ ተደስትህ የምትመካና የምትኰራ ትውልድ ሆነህ
ወያኔዎች ሲሞቱ ታለቅሳለህ ፣ መሬት ትወግራለህ። ይህ እጅግ ወራዳነትና የሚያሳፍር፣ ተራና ዝቅ ያለ
እራስን በራስ የማጥፋት ከንቱ የኅብተሰብ ዝቃጭነት ነው።ይህ ሰው መሆንን ዘንግቶ የነገሩትን ብቻ
የሚያስተጋባ ወይም የውሻ ጩህት ነው። በዚህ ኅሊና ቢስነት ማንነትን ያላገናዘበ፣ያልተረዳና ያላወቀ
ተግባር ትውልድን ሁሉ ያሳፈረ፣ ታሪክን የዘነጋና ያራከሰ እጅግ የሚያሳፍርና የሚጐዳ የማይሽር የኅብረተሰ
ቁስል ነው።
ትውልድ ሆይ! ወያኔ እየጐራረደና ገርድፎም እየጣለህ እንደሆነ አልተረዳህም፡ ልብ ይስጥህ !
የታሪክ፣የትውልድ አገርህን ትተህ ስደትን እንደ አማራጭ ምርጫህ በማድረግ ለሰደት ዲቪ እየጠየቅህና
እየተማጠንህ ከአገር ትሰደዳለህ።ሌላው ችግሩና ሰቆቃው የበዛበት ወደ ውጭ መሰደድን መፍትሄው
አድርጐ ከአገር በመውጣት በየሰው አገር እየሄደህና አይሞቱ ሞት ፣በውሃ ሰምጠህ የቀረህ፣ለዱር አራዊት
ምግብ የሆንክ፣በየእስር ቤቱ ታስረህና ተደብድበህ፣ በቁም አካልህ እየተወሰደ እያለቅህ ትገኛለህ።ቀሪህም
በዝምታ፣ በእንዝላልነት በረሃብ፣በችግር፣ በኑሮ ውድነት እየተሰቃየህና በበሽታ ፣ህመም እየረገፍህ ነው።
አንተ ወጣት ዛሬ በየዪኒቭርሲትው፣ ኰሌጂ እንድሁም ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የምትሄደው
ትምህርትን በመቅሰም አውቀህና ተረድተህ፣መጥፎና ጥሩውን ለይተህ፣ ለራስህ፣ ለአገርና ወገን አለኝታና
ደጀን ሆነህ፣ከሚመጣው አደጋ ሁሉ ተከላክለህ፣ ለመጠበቅና ለብልጽግና እንጂ ፤ያስተማሩህን ሁሉ ሆነህ
ወዳጅ ጠላትህን የማትለይ፣ጥሩና መጥፎው የተቀላቀለብህ ፣ የምትይዝ የምትጨብጠውን ግራ የተጋባህ፣
ቀኝና ግራህን የማትለይ፣ጥፋትና ልማት የማትገናዘብ ለመሆን አይደለም።ሰው ትምህርት ቤት የሚሄደው
እውቀትን ለማግኘትና ጥበብን ቀስሞ ራስን በመሆን በራስ ማንነትና ምንነት አገር ወገን ትውልድን ማዳን፣
መጠበቅ፣ተከብሮና ታፍሮ፣ ኮርቶ በነፃነት ለመኖር ነው።
አንተ ታዳጊ ወጣት ትውልድ! በአገርና ሕዝብ ላይ የወያኔ አረመኔዊ ጭካኔና ክህደት ፣ጥፋት፣ሽፍጥና
ተንኰል የሚደርስውና እያደረሰ ያለው ከጣሊያን ፍሽስት ወረራ ጊዜ እጅግ የከፋና የመረረ ነው።ወያኔ
ፀጉረ_ልውጥ አይምሰልህ እንጂ፤ድሮም በአገር ክህደት ባንዳዎች የነበሩ እነዚህ የባንዳ ልጆች ወያኔዎች
የአገር ጠላት ወራሪ አንተን የማይመስሉ አጥፊዎች ናቸው። አገር ተደፍሮና ተዋርዶ፣ታሪክ እየተበወዘ፣
አንድነት እየተናጋ፣ሕዝብ እየታመስ፣የአንተ ዜግነትና መብት በሕገ ወጥ ሥርዓት ታፍኖና እተረገጥህ፣
እየታሰርህ ማንነትህ እየጠፋና እየሞትክ ሲሆን፤ የአገርህ ለም መሬት ደግሞ ከአንተ የአገሪቱ ተወላጅ፣ዜጋና
ባለታሪክ ባለቤት፣አያት፣ ቅድመ አያትህ የሞቱላትን አጽመ_ርስት ሃብትን ተነፍገህና እየተቀማህ ለውጭ
አገሮች ለቻይና፣ ለህንድ፣ለአረብና ሌሎችም በርካሽና ለረዥም ጊዜ እየተሸጠ፣ እየተቸረቸረ ወያኔዎች
እየበለጸጉ፣ የአገርን ሃብት እያወጡና እሸሹት አንተ እየተቸገርህና እየደኽየህ በረሃብ እየተሰቃየህና ከአገር
እተባረርክ እየተሰደድህ ትገኛለህ።ይህ ሊያስቆጣህ፣ሊያናድድህና ጥርስ ሊያስነክስ በቻለ ነበር።
አንተ የአገሪቱ ባለቤት አገርህን ትተህ ስደትን ምርጫህ ሰታደርግ፣የርካሽ ባህል ተገዥና የወያኔ ተደላይ
ተላላና አገልጋይ በገዛ አገርህ ባንዳ ስትሆን፤ አገር፣ ሕዝብና ታሪክ ተዋርደውና ተራክሰው የባዕዳን
መጤዎች መፈንጫና የወያኔዎች መፈንደቂያና መቧረቂያ፣አብረህ ባንዳና ቅሌታም ሆነህ የታሪክ
ወራሽነትህ ፣የአገር ባለቤትነትህን ተነጥቀህና አጥተህ ፣ኢትዮጵያ ወራሽ ያጣች ፣ታሪኳ የጠፋ ፣ትውልድ
ያልተፈጠረባት አገር ልትሆን ነው።ለልጆችህ ምን ዓይነት አገርና ታሪክ ልታወርስ ነው?አገር አልባነትን
ባርነትን? ቅሌትና ባዶነትን ነው ? በዝምታ፣ በምንቸገረኝ ፣ በመከፋፈልና በአድርባይነት ኢትዮጵያን ወራሽ
ያጣች አገር ልታደርጓት ነው? እነዚያ የእኛ ቀደምት አባትና እናት ጀግኖች በአንድነት ለዘመናት ደማቸውንእያፈሰሱ የጠበቋትን ዛሬ አገር ተረካቢ ፣ ወራሽና ኃላፊነት፣ ተቆርቋሪ፣የትውልድ ግደታ የሚሰማው
መታጣት የሚያሳዝንና የሚያሳፍር የትውልድ ትቢያነት ነው።ኢትዮጵያ ወራሽ ያጣች አገር ሆና የቻይናና
የህንድ ዲቃላዎች ወይም የሌሎች አገር ስትሆን ምን ይሰማህና ማነኝስ ብለህ ራስህን ትጠራለህ? ኅሌናህ
ምን ያህል ይቆስልና ህመሙስ ምን ያህል የበረታና የከፋ ይሆንብህ? አዝናለሁ፣እናደዳለሁ ፣እጸጸታለሁ
ከዚህ ሁሉ ቅሌትና ውርደት፣ ከትውልድ ትቢያነት ለመዳንና አገርን ጠብቆ ለማቆየት መንቃትና መነሳሳት
አሁን መሆኑን እያስገነዘብኩ በአገሪቱ ግዛት የምትገኙ ወጣቶች ሁሉ እርስበርሳችሁ የምስጥር ግንኙነት
አድርጋችሁ፣ ስልትና እቅድ አውጥታችሁ፣ ሕዝባችንን በመቀስቀስ በአመጽ ወያኔን በመደምሰስና ሥርዓቱን
በማፈራረስ አገሪቱን እንዲታድኑ፣ ሥልጣንና ሃብት የሕዝብ ሆኖ እንዲረጋገጥ በብሔራዊ ደረጃ
እንዲትታገሉ ይህን ጥሪ አቀርባለሁ ።
ወጣት ለአገርና ሕዝብ ኃላፊነት አለብህ !
በወጣቱ ትግል አገር ይድናል !
ተነስ ብድግ በል!
አምጽ አሸንፍ !
No comments:
Post a Comment