Apr 22, 2013

የአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ብሔራዊ ምክር ቤት በፖሊስ ተከቦ ስብሰባውን አከናወነ


የአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ብሔራዊ ምክር ቤት ዋና ጸሀፊ አቶ ትግስቱ አወሉ በተለይ ለፍኖተ ነፃነት እንደተናገሩት የፓርቲው ብሔራዊ ምክር ቤት በተለያዩ አጀንዳዎች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳልፏል፡፡

UDJበፓርቲው ስትራቴጂክ እቅድ መሰረትየአንድነት ፓርቲ ጠቅላላ ጉባኤ በመጪው አመት መስከረም ወር የመጨረሻ ሳምንት ላይ እንደሚያካሂድ አስረድተዋል፡፡ በፓርቲው ደንብ ለሊቀመንበሩ በተሰጠው ስልጣን መሰረት ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ የድርጅት ጉዳይ ኃላፊ የነበሩትን ኢ/ር ዘለቀ ረዲን በስራ አፈፃፀም ብቃት ማነስ ምክንያት አንስተው በቦታው አቶ ስዩም መንገሻን መተካታቸውን ለምክር ቤቱ አሳውቀዋል፡፡ ምክር ቤቱም ሹመቱን አፅድቋል፡፡
አቶ ትግስቱ ጨምረውም ባለፈው ረቡዕ በሰንደቅ ጋዜጣ ለአንድነት ፓርቲ አሉታዊ አመለካካት ባለቸው አካላት የወጣውን መሰረተ ቢስ ውንጀላና በፓርቲው ስራ አስፈፃሚ አባል በነበሩት ኢንጅነር ዘለቀ ረዲ በተሰጠው የሀሰት መረጃ ዙሪያ ኢንጅነር ዘለቀ በተገኙበትና ሀሳባቸውን በነፃነት በገለፁበት ሁኔታ ሰፊውይይት መደረጉን አብራርተዋል፡፡
ምክር ቤቱ በሰጠው ውሳኔ መሰረትም ነገ ሰኞ ሰንደቅ ጋዜጣ ያወጣውን ሀሰተኛ መረጃ የሚያስተካክል መግለጫ እንዲሰጥ ኢ/ር ዘለቀን በሚመለከትም ጉዳዩ ለብሔራዊ ዲሲፕሊን ኮሚቴ እንዲመራ መወሰኑን የምክር ቤቱ ጸሀፊ ገልፀዋል፡፡ የአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ብሔራዊ ምክር ቤት ቅዳሜ ሚያዝያ 12 ቀን 2005 ዓ.ም ስብሰባ ባደረገበት ወቅት ከአስር የበለጡ የፌደራል እና የአዲስ አበባ ፖሊስ አባላት በፓርቲው ዋና ጽ/ቤት ዙሪያ ከበባና ቅኝት ሲያደርጉ እንደነበር የፍኖተ ነፃነት ጋዜጠኞች ዘግበዋል፡፡
ፍኖተ ነፃነት

No comments:

Post a Comment