Jan 30, 2013

ሒትለርና አይሁድ፤ መለስ ስብሀትና አማራ


የትግሬ እና የሻቢያ ምሁራን ቀጥፈዉ ዋሽተዉ በድፍረት የሌለ ታሪክ ታሪክ አድርገዉ ተከታዮቻቸዉን እያሳመኑ ነዉ። የእኛ ምሁራን ደግሞ ሲሞዳሞዱ ጥቅም አይቅርብን ብለዉ ሲልከሰከሱ ስለኢትዮጵያ ከሞላ ጎደለ የሚጽፈዉ ያዘነልን ነጭ ሁኗል።  ቢያስቡት ቢያስቡት መልስ የሌለዉ ነገር ነዉ። ነገር ግን ትግሬን ምን አደረግነዉ? ትግሬ ከሌሎች ወገኖች በላይ የደረሰበት በደል ምንድነዉ? ኢትዮጵያን ሊያጠፋ የተነሳበት ምክንያት ምንድነዉ? የሚለዉ ነገር ሁልጊዜ ጥያቄ ዉስጥ ይከተኛል።
የሚገርመዉ በኢትዮጵያ አንድነት ከምንም በላይ ተጠቃሚ የነበረዉ ትግሬ እና ጉራጌ ነበር። ምክንያቱም ካካባቢያቸዉ ወደሌላዉ የኢትዮጵያ ክፍል እየተዘዋወሩ ይጠቀሙ ነበር። ታድያ እነዚህ ከተንኮል ድርና ማግ የተሰሩ ዘወትር ቢላ እየሳሉብን እኛ ስንገነባ እነሱ ሲያፈርሱን እዚህ ደርሰናል። በጽሁፍህ ያልተስማመሁበት የትግራይ ህዝብ ከፍተኛ በደል ላይ እንዳለ ጠቁመሀል።፡በዉነቱ ለእነሱ የዚህ አይነት አባባል ከማሳቅ አልፎ ሌላዉን ሽንታም እያሉ ያላግጡበታል። ከእዉነታዉ ጋር ስለማይዛመድላቸዉ አያምኑትም። የትግራይ ህዝብ በጣም ደስተኛ ነዉ። በፖሊሲ ደረጃ አቦይ ስብሀት አላማችን ለሚቀጥለዉ 10 አመት የትግራይን ህዝብ ወደ መካከለኛ የኑሮ ደረጃ ማሸጋገር ነዉ ብሏል። መቀሌ ዛሬ ደረጃዋ ከአዉሮፓ እኩል ነዉ። ለግንዛቤ እንዲረዳህ ተከታታይ እዛ የሚሰራ የአገር ቤት ትያትር ስላለ እሱን መመልከት ነዉ። የነጻ ትምህርት እድል 100% የሚሰጠዉ ለትግሬ ነዉ ይህም በስዉር አይደለም መለስ ዜናዊ አማራዉ ቀደም ባለዉ ጊዜ ስለተጠቀመ ነዉ ብሎ መልሷል። እዉነትነቱን እንድትመረምር ላንተ ትቸዋለሁ። ወደ አሜሪካ እና አዉሮፓ እየተዘዋወሩ የሚነግዱት ትግሬዎች ናቸዉ። ከትግራይ መጥተዉ ቦታ ተስጥቷቸዉ ሽጠዉ እንዲጠቀሙ የተደረጉት ትግሬዎች ናቸዉ። ብዙ ብዙ ብዙ ማለት ይቻላል። ትግሬ ተጠቃሚ ነዉ ያለዉንም መንግስት በጣም ይደግፋል። ተበድለናል ካሉም እነሱ እራሳቸዉን ለመከላከል ብቃቱ ስላላቸዉ እነሱዉ ይንገሩን እንጅ እኛ የሌለ በደል ባንፈጥርላቸዉ ጥሩ ነዉ። ያለበለዚያ ምንም አልበደልንም ማለት ነዉ በማለት ልጓሙን ያጠብቁብናል። አንዳንድ የዋሆች አዲስ አበባ ደርሰዉ ሲመለሱ ለማኙ ሁሉ ትግሬ ነዉ ይላሉ። እንዴት ያስቃል ያ በትግርኛ የሚለምነዉ ሰዉ ሚስቱን ተቀምቶ የተባረረ የወልቃይት እና ጠገዴ ህዝብ እንጂ ትግሬ አይደለም።
በተረፈ ጽሁፍህ አንጀት ያርሳል። ጽሁፍህም የደረሰኝ በትግሬዎች አማካኝነት ነዉ። የዛን አይነት ድረ ገጽ እንኳን ለማዘጋጀት አልታደለንም። አብረሀ በላይ የፈለገዉን ያወጣል የፈለገዉን ይጥለዋል። ለምሳሌ ፐሮፌሰር ጌታቸዉ ስለ ምንሊክ እና ዮሀንስ የጻፉት በግማሽ ቀን ዉስጥ  ተሰርዟል። የዮሀንስን ክፉነት ስላመላከቱ።
ውድ እንባቢያን ለደብዳቤዎቻችሁ ሉላችሁንም አመሰግናለሁ። ዛሬ ለመንገር ወደፈለኩት ጉዳይ እንሂድ፤ እነሆ…
እንደ አውሮፓውያኑ ዘመን አቆጣጠር ጃንዋሪ 30 1939 ዓም አዶልፍ ሒትለር ሬግታንግ ጀርመን ውስጥ ንግግር ሲያደርግ “ከንግዲህ ጦርነት የሚነሳ ከሆነ ከጀርመን ውስጥ አይሁዳውያንን ነው የማጸዳው። አይሁዳውያን ናቸው ከምድርገጽ የሚጠፉት” ብሎ ተናግሮ  ነበር።
እነመለስ ስብሀት ትግል ሲጀምሩ በፕሮግራማቸው ጽፈው ካስቀመጡት ነገር አንዱ “አማራው ካልተመታ.. የትግራይ ነጻነት የማይታሰብ ነው። መጀመሪያ አማራው መመታት አለበት.. መንበርከክ አለበት” ብለው ነበር።”..አማራ..አማራ.አማራ..አማራ.. አማራ…” ሆነ ህልምና ቅዠታቸው ከውልደት እስከ እለተሞቻቸው።
“”Holocaust History” በሚል ፕሮጀክት አይሁዶች ያለቁበትን ሁኔታ የሚያጠና የታሪክ ተቋም  www.holocaust-history.org “ለምንድነው ያሁሉ እልቂት በአይሁዶች ላይ የተፈጸመው?” የሚል ጥያቁ ባቀረቡለት ቁጥር የሚሰጠው መልስ “ሒትለር አጥብቆ ስለሚጠላቸው ብቻ ነበር” የሚል ነው። ቀጥሎ አንግዲህ የሚነሳው ጥያቄ “ለምን ነበር ሂትለር አይሁዶችን የጠላቸው” የሚለው ሆነ።
በተመሳሳይ ሁኔታ መለስ ስብሀት ወደስልጣን አንደመጡ ባይሳካም(ለምን እንዳልተሳካላቸው ወደፊት እናወጋለን)  ፍጅቱን ባማሮች ላይ ጀምረውት ነበር፤ “ለምንድነው አማራውን ሕዝብ ሊጨርሱ የተነሱት?” የሚል ጥያቄ ይህ ድርጅት ቢገጥመው “ መለስ ስብሀት አማራዎችን ስለሚጠሉአቸው ስለሚፈሩአቸው ብቻ ነው።” የሚል መልስ እንደሚሰጥ እኔ አልጠራጠርም። “ለምን አማራን ጠሉት?..ፈሩት?”  ሁላችሁም የሚመስላችሁን ተናገሩ።
ሂትለር አይሁዶችን የጠላበት የፈራበት ሁኔታ ሲነገር፤ ያንን ያክል ጥፋት የሚያስደርስ ነው ባይባልም፤ የታሪክ ተመራማሪዎቹ አንዲህ ይላሉ። በመጀመሪያ ደረጃ በ1930 ዎቹ ውስጥ በጀርመንም ሆነ በአውሮፓ ጸረ አይሁድነት አስተሳሰብ የተንሰራፋ ችግር ነበር።ለዚያም መሰረቱ በመጽሀፍ ቅዱስ ታሪከ ክርስቶስን የሰቀሉ ናቸው የሚለው መንፈሳዊ ትምህርት ዋናው ያስተሳሰብ ዘዋሪ እምነት ነበር። ሁዋላ ላይ ግን ያን ሀይማኖታዊ ጥላቻ አንዳንዶች ወደ ፖለቲካ አጀንዳ ለውጠውት ለእኩይ የፖለቲካ አላማ ህዝብን በስራቸው ማሰባሰቢያ ፕሮፓጋንዳ አደረጉት። (አሁን ባገራችን የጎሳ ባህላዊ ግጭቶችን ወያኔዎች የፖለቲካ ልዩነት ቅርፅ ለመስጠት እንደሚሞክሩት አይነት) አይሁዳውንያን በጀርመንም ሆነ ባውሮፓ የላቁ ምሁራን፤ የላቁ ሀኪሞች፤ ፕሮፌሰሮች ፖለቲከኞች በሁሉም መስክ የተዋጣላቸው ሰዎች ስለነበሩ፤ ብዙ ፖለቲከኞች ይፈሯቸው፤ ይቀኑባቸው፤ ይጠሏቸውም ነበር።ሂትለርም አንዱ እንደነበር ታሪኩ ያወሳል። ጀርመን በአንደኛው የአለም ጦርነት የተጠቃችው በነሱ ምክንያት እንደሆነ ያምን ነበር።”በስለላና በመረጃ ጠላትን እያገለገሉ..” ይላል። እናም አንዳንዶች ይህን በመላው አውሮፓ የነበረ ጸረ-ሴማዊነት ወረርሽኝ አንደ መሰረት አድርገው ሂትለር ያንኑ ነው ያጠናከረው የሚሉ አሉ።
ሌላው ወገን ደግሞ ሂትለር አይሁዶችን የጠላበት ምክንያቱ ቪየና ውስጥ አንድ የስነጠበብ ትምህርት ቤት ለመማር ፈልጎ፤ተቋሙ፤ “ትምህርቱን መከታተል የሚያስችልህ ተሰጥኦና ችሎታ የለህም” ብሎ ማመልከቻውን ውድቅ አደረገበት። የኮሌጁ መምህራንና አስተዳዳሪዎች ባብዛኛው አይሁዳውያን ስለነበሩ በዚያው ቂምና ጥላቻ ቋጠረ።
ገሚሱ ደግሞ እንደሚለው ከሁለተኛው  የዓለም ጦርነት ቀድሞ ሂትለር ከመነሳቱ በፊት በነበረችው ጀርመን ህብረተሰብ ውስጥ፤ አይሁዳውያን በማናቸውም መስክ የተዋጣላቸው (አሁን በአሜሪካ እንዳሉት ማለት ነው) የተሳካላቸው ስለነበሩ፤ ከቁጥራቸው ማነስ አንጻር ከሌላው የጀርመን ዜጋ ጋር ሲያስተያዩዋቸው፤ በትምህርት፤ በንግድ፤ በማናቸውም የስራ መስክ የላቀውን ስፍራ ይዘው ሰለነበር፤ በሂትለር አስተሳሰብ በተንኮልና በሻጥር መላውን የጀርመን ዜጋ ቁልቁል ይዘው እነሱ የበላይ ሆኑ ብሎ ያምን በዚያም ምክንያት ይጠላቸው አንደነበር ተጽፏል።አሁን በኢትዮጵያ መለስ ስብሀት ከልት ስለ አማሮች  እንደሚያስበው ማለት ነው።
እርግጥ የአማራውን ሕዝብ ከሌላው የኢትዮጵያ ህዝብ የተለየ ተጠቃሚም ሆነ ተጎጂ የሚያደርገው ምንም ነገር የለም። ድህነትና ጭቆና የዘጠና ሚሊዮን ሕዝብ የጋራ እሴት ናቸው።
ናዚ ሂትለር ወደ ስድስት ሚሊዮን የሚሆኑ አይሁዳውያንን የፈጀበት ድርጊት ትምህርትነቱ ይላል ይኸው ፍጅቱን የሚያጠናው ተቋም፤ “በተወሰነ የህብረተሰብ ክፍል ጥላቻ የተመረዙ ግለሰቦች ወደ ስልጣን ሲመጡ፤ ሀገር የመምራት እድል ካገኙና አንድ ችግር ከተፈጠረባቸው፤ ለዚያ ችግር ምክንያቱ ነው ብለው የሚያምኑት ያ የሚጠሉት የህብረተሰብ ከፍል ስለሚሆን ሂትለር ባይሁዶች ላይ እንዳደረገው ተመሳሳይ እልቂት ሊፈጽሙ አንደሚችሉ ይታመናል” ይላል ሰነዱ።
“ያንድ ህብረተሰብ ክፍል ጥላቻ ይዘው ወደ ስልጣን የመጡ…” የሚለው ነገር በቀጥታ ወደ እኛው ጉዶች ያመጣናል። መለስ ስብሀት የሚመሩት የወያኔ መሪዎች ቡድን አማራውን ከዘጠና ሚሊዮን ሕዝብ ነጥለው ለምን ይጠሉታል? ለምን ይፈሩታል? ያኔ በረሀ የነበሩ ጊዜ እንኳ “መላ ኢትዮጵያን ተቆጣጥረን ይህን እድል እናገኛለን” ብለው የሚያስቡ ስላልነበረ ያሻቸውን ይበሉ። ባለፉት ሀያሁለት አመታት  ወደደም ጠላም የኢትዮጵያ ሕዝብ እጃቸው ላይ የወደቀ ህዝብ ነው። ሐገር አስተዳድራለሁ የሚል መንግስት የሚያስተዳድረውን ህዝብ አንዱን እያሞገሰ አንዱን ባደባባይ እየሰደበ የሚኖር ያለው ኢትዮጵያ ውስጥ ብቻ ነው።
“.. ገድለን የቀበርነውን አማራ አታንሱብኝ…..” ጀነራል ሳሞራ ዮኒስ።
“.. ለትምክተኛ አማራ ስልጣኑን አንለቅም….” መለስ ዜናዊ።
“…ስልጣኑን ካማራና ከኦርቶዶክስ እጅ አውጥተነዋል…..”  ስብሀት ነጋ።
“..ሱማሌ የከብት ጭራ መከተል እንጂ ራሱን ማስተዳደር አይችልም ይሏችሁ ነበር።…  ዛሬ እራሳችሁን ማስተዳደር እንደምትችሉ አሳዩአቸው…ነፍጠኞችን..” ታምራት ላይኔ ጂጂጋ 1983። (አሁን እራሳቸው ጌቶቹ የጁን ሰተውታል፤..አያሳስብም)
ልብ ይሏል፤ መለስ ዜናዊ አማራውን አንዴት ይጠላ እንደነበር። የወያኔ መሪዎች ስብሀት ነጋና ሌሎቹም ሁሉ፤.. ዋና ዋና የጦሩን አዛዦች ጨምሮ.. በዚህ ህዝብ ላይ ያላቸው ጥላቻና ፍራቻ ከቁጥጥራቸው ውጭ የወጣ በመሆኑ በያጋጣሚው በአንደበታቸው ሲገልጹት መስማት እንግዳ ነገር አይደለም። ሀያ ሁለተኛ አመታቸው። ለምን?.. መቼ ነው የሚማሩት? ..መቼ ነው የሚታረሙትስ? የኢትዮጵያ ህዝብ እነሱን ትምህርት ቤት ለመጨመር፡ ይህን የደንቆሮ ጡንቻቸውን ለማምከን እንደገና ጦርነት መክፈት ሊኖርበት ነው?
ለምሆኑ የጥላቻቸው መሰረት ምንድነው?
ሂትለር ሁለተኛው የአለም ጦርነት አካባቢ፤ “ጦርነት ከእንግዲህ በሗላ ከተቀሰቀሰ” አለ “አይሁዶችን አያድርገኝ”… እንዳለውም መጀመሪያ እራሱ ፖላንድን በመውረር ጦርነቱን ሲባርከው ሶስት ሚሊዮን የሚሆኑ አይሁዳውያን በቁጥጥሩ ስር ወደቁ። ከዚያ ወደ ሶቬት ሲዘምት ያንኑ ያህል ህዝብ እጁ ገባ። እነሱን እየመነጠረ ወደ መቀቀያ ካንብ ይሰበስባቸው ጀመር። ገድሎ ገድሎ መጨረስ ሲያቅተው።
እነመለስ ስብሀት በጦርነቱ ወቅት፤ ጦርነቱ ሰልችቶት የኢትዮጵያ ጦር ሰራዊት በገፍ እየሄደ ሲማረክላቸው፤ “አማራ ነን” ያሉትን የዋሀን እየመረጡ በመርዝም በጥይትም ይፈጇቸው ነበር። ከባድ የጉልበት ስራ እያሰሯቸው ጉርጓድ እስር ቤት እያጎሯቸው ሰውነታቸው እስኪተላ እየደበደቧቸው ይገሏቸው ነበር።
ሂትለር ስልጣኑን ከተቆጣጠረበት ጃንዋሪ 1933 ዓም ጀምሮ በአይሁዳውያን ላይ ባደባባይና በሀገሪቱ መገናኛ ብዙሀን ሽብር መንዛት ጀመረ።ባይሁዳውያንና በሌሎች የጀርመን ዜጎች መካከል የልዩነት ግንብ መገንባት ጀመረ።
በተመሳሳይ ሁኔታ እነመለስ ስብሀት መላ አገሪቱን ተቆጣጥረው የሽግግር መንግስት መሰረትን ብለው አዲስ አበባ ምክር ቤት ገብተው፤ መለስ ዜናዊ ምክር ቤት ውስጥ ለተሰበሰቡት የዘር ድርጅቶች በሙሉ፤ ለነባሮቹም ወዲያው አዳዲስ ለተፈለፈሉትም ሁሉ ወንበር ሲያድል፤ አማራውን አላስጠጉትም ነበር። ሁሉም መንግስት ናችሁ ሲባሉ ዘለሉ፤ ጨፈሩ፤ ያለወያኔ በአለም ላይ ሰው አልተፈጠረም አሉ።የብሄር ብሄረሰብ ተወካዮች። አንዳንዶቹ “በቃ ከንግዲህ እንደብርቅየ አራዊተ ታየን” አሉ። ኖርናት ።ሗላ ላይ ወያኔ እንደ አራዊቱ እያደነ ሊበላቸው። በገሀድ ግንቡ ያኔ መገንባት ተጀመረ።
ሂትለር ስልጣኑን እንደተቆጣጠረ አይሁዳውያንን በገፍ ከስራ ከትምህርት ተቋማት ከማናቸውም መስክ ማፈናቀሉን ተያያዘው።
እነመለስ ስብሀትም በተመሳሳይ ሁኔታ አማሮችንና ያማሮቹን አስተሳሰብ ይጋራሉ ያሏቸውን አርባ የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ መምህራንና ፕሮፌሰሮችን በማባረር የሂትለርን ስራ ደገሙት።ጀመሩት።እስከመጨረሻው ተያይዘውታል።
ሂትለር ወደ ስልጣን እንደመጣ ሰፊ የፕሮፓጋንዳ ሽፋን የተሰጠው ስራ አይሁዳውያን በጀርመን ህዝብ ዘንድ እንዲጠሉ ለማድረግ ሀያ አራት ሰአት የፕሮፓጋንዳ ስራ መስራት ነበር።እኛ ቤትም ወያኔያዊው ፕሮፓጋንዳ ባጼ ሚኒሊክ ጀምሮ መላውን አማራ ነፍጠኛ እያለ ስድብና የውሸት ታሪክ ያዘንብበትና ወደ ታዋቂ ግለሰቦች ተራ በተራ በመሄድ የሚያታክት ፕሮፓጋንዳ ይሰራ እንደነበር አይዘነጋም። እነ ጥላሁን ገሰሰ፤ እነ ፐሮፌሰር አስራት ወልደየስ፤ ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማሪአም፤ ሚትር አርቲስት አፈወርቅ ተክሌ፤ ሁሉንም መዘርዘር አይቻልም፤ በሀገሪቱ ውድ ዜጎች ላይ ይነዛ የነበረው ስም የማጥፋትና የማጥላላት ፕሮፓጋንዳ በነጻው ፕሬስ ጀግኖች ከመመታቱ በፊት ምን ያህል አማራው ላይ ያነጣጠረ እንደነበረ ኢትዮጵያውያን የቅርብ ጊዜ ታሪካችን ስለሆነ መደጋገም አያሻም።
ሂትለር በአይሁዳውያን ላይ ያንን ሁሉ እልቂት ሲያደርስ ጀርመናውያን ባለመቃወማቸው ለድርጊቱ ተባባሪ መሆናቸውን አመልክተው ነበር። እርግጥ የኛ ህዝብ ከወያኔ ጋር አልተባበረም። የሂትለር ድርጊቱ የራሱ ብቻ የሆነ ግለሰባዊ እቅድ ከመሆን አልፎ የፓርቲው ማለትም የናዚ ሶሻሊስት ፓርቲ መርህ እንዲሆን በመደረጉ፤ በወቅቱ ጀርመናውያን ባብዛኛው የፓርቲው አባልና ደጋፊ እንዲሆኑ በመገደዳቸው፤ እናም ባንድ አንባገን ግለሰብ የሚመሩ በመሆናቸው የፓርቲያቸውን አቋምና ፍልስፍና ሊቃረኑ አልቻሉም። እንደ ሕውሀት ግንባር አባላት ደደብነት ማለት ነው።
ይህ የህውሀት ሶሻሊስት ግንባር አባላትን ከመምሰሉ ባሻገር አሽከሮቻቸውን ደርበንላቸው ኢህአደግ እንበላቸውና፤ ባለፉት ሀያ ሁለት አመታት ህውሀት ያን ሁሉ ግፍ ባማሮች ላይ ሲፈጽም የተቃውሞ ድምጽ ያሰሙበት ጊዜ ነበረ? ከጉራፈርዳ ከሀያ ሺህ በላይ አማሮች ንብረታቸውን ተቀምተው ሲባረሩ ድርጊቱ እንዲቆም ወይም ልክ አይደለም ሲል የተደመጠ የኢህአደግ አባል ድርጅት አለ? የናዚ ፓርቲ አባላትም በዚህ መልኩ ነበር በአይሁዳውያን ላይ የደረሰውን የደገፉት። ኢህአደጎችስ ለምን? የህውሀት ፍልስፍና አማራውን በማጥፋት ላይ የተመሰረተ ስለሆነ መቃወም ተግባራቸው አይደለም? ወይንስ ለራሳቸውም የህሊና ባሮች ሰለሆኑ በጌቶቻቸው ቡራኬና ይሁንታ የሚጣልላቸውን ትርፍራፊ እየበሉ መኖር ብቻ ነው።
በሂትለር እምነት አርያን የሚባለው የጀርመን ህዝብ ዝርያ በመላው ጀርመን ከሚገኙ ዘሮች ሁሉ የበላይነት አለው። ስለዚህ ሁሉም ዘሮች በስሩ ማደር አለባቸው። ሌሎቹ ዘሮች ስላቮችና ፖልስ የሚባሉት ዝቅ ያለ የሰውነት ደረጃ ስላላቸው ለአርያን ዘሮች ነው ማገልገል ያለባቸው። አይሁዶች ጭራሹኑ ጥገኛ ተውሳካት ስለሆኑ መጥፋት ነው ያለባቸው። ሂትለር ያኔ በሚፈልጋት የጀርመን አይነት እንደተመኘው ሁሉ በመለስ ስብሀት ሰራሿ ኢትዮጵያም እነሆ ሀያ ሁለት አመታት ወያኔ መላው ኢትዮጵያ በትግሬ ስር ነው ማደር ያለበት ብሎ እንዳመነና እንደተነሳ፤ ሁሉ በመንግስቱ ስራ ፈላጭ ቆራጭ ቀጣሪ አባራሪ፤ ትግሬ። በግሉ ክፍለ ኢኮኖሚ ፈላጭ ቆራጭ ተቆጣጣሪ ሰሪ ፈጣሪ፤ ትግሬ። በውትድርናው ዘርፍ ፈላጭ ቆራች ዘማች አዝማች መሪ ትግሬ፤ ሆንና አፈፍነው። እንደ ሂትለር ምኞት አርያኖች አልተሳካላቸውም። የመለስ ስብሀት ምኞት ግን በሚገባ ተሳክቷል።ለጊዜውም ቢሆን የኢትዮጵያ ህዝብ በነሱ ስር ወድቋል።
ዛሬ በህይወት የሚገኙ የናዚ ወንጀለኞች ለፍርድ በሚቀርቡበት የኑረንበርግ ችሎት ላይ ኤሪክ ቮን ዴም የተባሉ ባለ ሶስት ኮከብ ጀነራል፡ በአይሁዳውያን ላይ ስላደረሱት እልቂት የምስክርነት ቃላቸውን እንዲሰጡ ሲጠየቁ “….ያ ፍጅት ሊቀር የማይችል የናዚ ፓርቲ ፍልስፍና መርህ ነበር ወይ?” ሲባሉ እንዳሉት “…ለአመታት…ለአስርት አመታት ስላቮች ከሰው በታች የሆኑ ፍጡራን መሆናቸውን ሰው እንዲያምን ተደርጎ ከተሰበከ፤ አይሁዶችም ጭራሽ ሰውም አይደሉም ብሎ ሰው እንዲያምን ከተሰበከ ያ እልቂት ሊቀር የማይችል ክስተት ነበር” ብለው እራሳቸው የጭፍጨፋው ተሳታፊ መሰከሩ። ሕውሀት ስለ አማራው ክፉ ነገር የሰበከውን ያህል የሰማው ኢትዮጵያዊ አለመኖሩ መበጀቱ፤ የከፋ ነገር ማድረግ እንዳይችል አድርጎታል።
እርግጥ ህውሀቶች የሂትለርን ድርጊት ካሁን ቀደም ባርሲ አርባጉጉ፤ በበደኖ፤ ባሰቦት ደብረወገግ ገዳም ከኦነጎች ጋር በመተባበር በሚገባ ጀምረውት ሞክረውት ዳር አልደረሰላቸውም። አማራውን በመጥላት የኢትዮጵያ ህዝብ ሊያግዛቸው አልቻለም። በኢትዮጵያ የሚገኙት ሰማንያ አንዱም ብሄረሰቦች ተፋቅረው ተከባብረው የሚኖሩና የኖሩ በመሆናቸው። የነመለስ ስብሀት ፕሮጀክት አልሰራም። ወደፊትም አይሰራም። የራሳቸው መጥፊያ ግን ይሆናል። የኢትዮጵያ ህዝብ እንደ ሩዋንዳ ህዝብ ጎረቤት በጎረቤቱ ላይ አይነሳም። ተራ የጀርመን ዜጎች ሳይቀሩ አይሁዶችን በማሳደድ በመግደል ሂትለርን አግዘውታል። እኛ ፍቅር በፍቅር በመሆናችን ይህ በሽታ የለብንም። ይህ በሽታ ያለው በወያኔዎችና አንዳንድ በዘር ተደራጅተው ከሚገኙ ደደቦች ደም ውስጥ ነው። ነቀርሳ ነው።
ለምሆኑ የወያኔ ጥቂት መሪዎች የአማራውን ሕዝብ ሊጠሉ የቻሉበት ምክንያት ምንድነው? ወደ ዘመነ መሳፍንት መለስ ብለን እስቲ አንድ ተያይዞ ሊመጣ የሚችል ነገር እንመልከት። በነበረው የርስበርስ ጦርነት ባጼ ቶዎድሮስ የተጀመረው ያሸናፊነት እና የበላይነት በአጼ ሚኒሊክ ሁሉንም ድል ማድረግ ሲጠናቀቅ፤ የየአካባቢው ንጉሶችና መሳፍንት የአሮሞውም የትግሬውም የከንባታውም ሁሉም ተሸንፈው ግዛቶቻቸው በአንድ ንጉሰነገስት ስር ሲወድቁ፤ አጼ ሚኒሊክ አገር የማቅናቱን ግዛት የማስፋቱን እርምጃ ቀጥለውበት ነበር። እናም በደቡብም በምስራቅም በየትም አቅጣጫ የሚልኩት ሰራዊት አብዛኛው አማርኛ ተናጋሪ ስለነበረ ተሸናፊዎቹ ቢገብሩም አማራውን አንደ ወራሪ መቁጠራቸውና መጥላታቸው አልቀረም ነበር።ያንኑ ጥላቻቸውን በህዝቡ ውስጥ ማሰራጨታቸውም አልቀረም።
ወደ ትግራይ በሽተኞች የመጣን እንደሆነ ዛሬ ያሉት አንጋፋ የህውሀት መሪዎች የሞተውን ጨምሮ አያቶቻቸውና አባቶቻቸው ወገናቸውንና ሀገራቸውን ከድተው ለጣሊያን ያደሩ አሽከሮችና ባንዳዎች ነበሩ። አባቶቻቸው እንዳወረሷቸው የጥላቻ ወሬና የፈጠራ ታሪክ፤ የአድዋው ድል የሚኒሊክ ድል፤ በነሱ አስተሳሰብ ሚኒሊክ አማራ ስለሆኑ ያማራ ድል ነው። በሁለተኛው የአለም ጦርነትም ባምስት አመቱ የወረራ ዘመን የነመለስ ስብሀት ወላጆችና ቤተሰቦች የጣሊያን ተላላኪዎችና አሽከሮች ሆነው፤ በሰላም እነዚህን ዛሬ የሚያቃጥሉንን ከሀዲዎች ለማሳደግ ጎንበስ ቀና ሲሉ፤ አርበኞች (በነሱ እምነት አማሮች) ጌቶቻቸውንም እነሱንም በዱር በገደል አናስወጣ አናስገባ ብለው ጣሊያንን አባረው የኢትዮጵያን ነጻነት ስላስመለሱ፤ ባንዳነቱ የቀረባቸው ወገኖች በአማራው ላይ የመረረ ጥላቻ ይዘው፤ በዚያው ጥላቻ ልጆቻቸውን ኮትኩተው አሳደጉ። ጣሊያንን ያባረረው ግን መላው የኢትዮጵያ ጀግና ነው። ኦሮሞ፤ አማራ፤ ትግሬ ወላይታ ወዘተ….ቢሆንም የእነመለስ ስብሀት ወላጆች ጌቶቻቸውን ያባረሩባቸው አማሮች እንደሆኑ አድርገው፤ ልጆቻቸው በአማራ ጥላቻ ተኮትኩተው እንዲያድጉ አደጉ። አሳሳቢው ነገር እነዚህ ሰዎች ካባቶቻው የወረሱትን ጥላቻ እነሱም ላልታደሉት ልጆቻቸው ማውረሳቸው ነው። ያም አልበቃ ብሎ የትግራይን ህዝብ ለመመረዝ ባለመታከት ስለ አማራ ህዝብ ክፉ ሲናገሩ መደመጣቸው ነው። መልካሙ ነገር ህዝቡ ከነሱ የቀደመ በመሆኑ ሊሰማቸው አይችልም። ምክንያቱም አማራ የሚባለው ሁሉ እንደ ትግሬ ደሀ ነው። እንደ ኦሮሞ ድህ ነው። እንደሶማሌ ድሀ ነው። እንደ አፋር፡ እንደ ከምባታ፡ እንደሁሉም የኢትዮጵያ ህዝብ ድሀ ነው። ምን አይነት አማራ ነው ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብ ሁሉ ጠላት ነው ብለው የሚያስተምሩት? አማርኛው ቋንቋ የመንግስት የስራ ቋንቋ ስለሆነ ይሆን? ለልጆቻቸው አዝናለሁ። ገንዘብና ጥላቻን ለሚያወርሷቸው። አእምሮአቸው ተጋርዶ ለሚያመልኳቸው አዝናለሁ። ጥላቻን ለሚወርሷቸው፤ እናም በሰብአዊ ፍጡር ጥላቻ ታውረው ሕይወታቸውን ለሚያጨልሙ። በኢትዮጵያ ውስጥ የሚጠላ ዘር የለም። የሚጠላ እና መጥፋት የሚገባው ገዢ ቡድን እንጂ።
እርግጥ የወያኔ መሪዎች የሚወዱት ወይም የቆሙለት የህብረተሰብ ክፍል አለ ማለት አይደለም። የሚወዱትም ራሳቸውን ነው። የቆሙትም ለጥቅማቸው ነው። አማራውን ብቻ ሳይሆን ኦሮሞውንም ጉራጌውንም ከንባታውንም አፋሩንም ሁሉንም በየጊዜው ይጨፈጭፉታል። እራሱን የትግራይን ህዝብም አይወዱትም። ሁለት ቀላል ማስረጃ እነሆ።
በጦርነቱ ዘመን የትግራይ ህዝብ እጅግ የከፋ ድርቅና ረሀብ ሲፈራረቅበት፤ ከመሀል አገር   የእርዳታ እህል እንዳይደርሰው መንገድ በመዝጋት፤ እነሱ በተቆጣጠሩት አካባቢና ባልተቆጣጠሩትም አካባቢ “እኛ ነን ለህዝባችን ረድኤት ድርጅቶች የሚያቀርቡትን እርዳታ ማደል ያለብን” ብለው የተባበሩት መንግስታትን አስጨንቀው ለረሀብተኛው እንዲያከፋፍሉ መድሀኒትና ምግብ ይሰጣቸው ጀመር። ያንን በብዙ ሚሊዮን የሚገመት የእርዳታ እህልና ቁሳቁስ ከአረብ ነጋዴዎች ጋር በመመሳጠር በቀጥታ ባህር እያሻገሩ በመሸጥ፤ በኩንታሎች አሸዋ እየሞሉ ለጋሾችን በማታለል እንዲገዙአቸው በማድረግ፤ በሚሊዮን ዶላር ሲንበሸበሹ፤ የጦር መሳሪያ ሲሸምቱ፤ የትግራይ ህዝብ እንደቅጠል ይረግፍ ነበር። እነሱ በየጫካው ከሰራዊቱ እየተሸሸጉ አረቄ ጠግበው ከውሽሞቻቸው ጋር ከረቦ እየደለቁ እየጨፈሩ ይዳሩ ነበር። ሱዳን እየሄዱ ውድ ሆቴሎች ውስጥ ይዝናኑ ነበር።
ሕጻናት፤ እናቶች፤ አባቶች፤ በረሀብ ሲረግፉ፤…ለመዋጋት አቅም የነበራቸውን ልጆችና አዋቂዎች በእርዳታው ምግብ እያማለሉ ወደውጊያ ሲያስገቡአቸው፤ የቀሩት ሕጻናት፤ድኩም እናቶችና አባቶች በሙሉ፤… እንዲያልቁ አደረጉ። ይህ በሆነበት አካባቢ እነመለስ ስብሀት በዚያን ጊዜ አንድም ተቆጣጣሪ አካል ወይም የውጭም ሆነ የውስጥ ጋዜጠኛ እንዳይደርስ አድርገው የትግራይ ወገናችንን አስፈጁት። ይህንን አላደረግንም ካሉ በቀጥታ የዚህን ጽሁፍ አቅራቢ መሞገት ይችላሉ። እኔም ያደረጉትን በማስረጃ ማመላከት እችላለሁ።
ሁለተኛው፤ የአውዚንን ጭፍጨፋ እንዴት አንዳቀነባበሩት ማየት ነው። በተባለው ቀን አውዚን ከተማ ገብተው ጉባኤ አንደሚያካሂዱ ወሬው በቅድሚያ እንዲሰራጭና ደርግ ጆሮ እንዲደርስ አደረጉ። አስራ ሁለት ሰዎች ሱዳን ሄደው በቪዲዮ ካሜራ ቀረጻ እንዲሰለጥኑ ተደረገ። ሁሉም ዝግጅት ከተጠናቀቀ በሗላ አንድ ቀን በጠራራ ጸሀይ በአውዚን ሞቅ ያለ የገበያ ቀን፤ በተለያየ አቅጣጫ የህውሀት ሰራዊት ተሰልፎ እየተኮሰ ከተማ እንዲገባና ወደገበያው እንዲያመራ ተደረገ። ወዲያውም የኢትጵያ አየር ሀይል በነሱ ላይ ጥቃት መሰንዘር ሲጀምር፤ ታጋዮቹ በያቅጣጫው እየተሯሯጡና እየተኮሱ ገበያተኛውን እንዲቀላቀሉ ተደረገ። ሕዝቡንም ተቀላቀሉ ። ያ ሁሉ ትርምስና እልቂት ሲፈጸም እነዚያ በቪዲዮ ቀረጻ የሰለጠኑት ተዋጊዎች ዶኩመንታሪ ፊልማቸውን ያነሱ ነበር።በዚያው እለት ነበር ወደ ሱዳን ልከው ድርጊቱ ለአለም መገናኛ ብዙሀን እንዲዳረስ ያደረጉት። ያ እንግዲህ በነሱ ተንኮል ላይ የደርግ ደደብነት ተጨምሮበት በህዝባችን ላይ የደረሰ መከራ ነበር። ታዲያ አነዚህ ለማን ነው የቆሙት? እና እነዚህ አማራውን ብቻ ነው የሚጠሉት? መልሱን ለአንባብያን እተወዋለሁ።

No comments:

Post a Comment