አዲስ አበባ ጥር 9 2005 (ኤፍ ቢ ሲ ) የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመለስ ፋውንዴሽንን ማቋቋሚያ አዋጅ መርምሮ አጸደቀ
ምክር ቤቱ ዛሬ ያጸደቀው አዋጅ አቶ መለስ ዜናዊ በሕይወት ዘመናቸው ሲታገሉላቸው የነበሩትን የልማታዊና ዴሞክራሲያዊ መንግሥት ፣የሰዎች ዴሞክራሲያዊ ግንኙነት ፣ እኩልነት ፣ ክብርና ብልጽግና እንዲረጋገጥ ብሎም የሰላም ፈለጋቸውን ማስቀጠል እንዲቻል ነው ፡፡
የምክር ቤቱ አባላት በአዋጁ አስፈላጊነትና ዝርዝር ጉዳዮች ዙሪያ ሰፋ ያለ ማብራሪያ እንዲሰጣቸው ጥያቄዎችን አንስተው ምላሽተሰጥቶባቸዋል፡፡
የህግ፣ ፍትህና አስተዳደር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ አስመላሽ ወልደስላሴ አቶ መለስ ዜናዊ የኢትዮጵያ ብሔሮች ፣ ብሔረሰቦችናሕዝቦች በእኩልነት በመከባበርና በአንድነት የሚኖሩባት አገር እንድትሆን ከልጅነት እስከ ህልፈተ ህይወታቸው የከፈሉትን መስዕዋትነት መዘከርአስፈላጊ ነው ብለዋል በሰጡት ማብራሪያ ፡፡
በአገሪቱ ሰላም ፣ ልማት ፣ መልካም አስተዳደርና ዴሞክራሲ እንዲሰፍን ለማድረግ የሰጡትን አመራር ለማስታወስና በአፍሪካ አስተማማኝ ሰላምእንዲረጋገጥ ከፍተኛ አርአያነት ያለው ተግባር የፈጸሙ በመሆናቸው ፋውንዴሽኑን ማቋቋም ማስፈለጉንም አስረድተዋል፡፡
የልማታዊና ዴሞክራሲያዊ መንግስት አስተሳሰብ በማመንጨት ፣ በመተንተን ፣ በማስረጽና በመተግበር ግንባር ቀደም ሚና የተጫወቱበመሆናቸው ይህንኑ ለቀጣዩ ትውልድ ማስተላለፍ ተገቢ መሆኑንም አቶ አስመላሽ ገልጸዋል፡፡
ፋውንዴሽኑ በአዋጅ ከተቋቋመ በኋላ በሚያከናውናቸው ተግባራት የአቶ መለስ ዜናዊ አስክሬን የሚያርፍበትና በሕዝብ የሚጎበኝ መናፈሻመገንባትና ማስተዳደር ፣ ዓለም ዓቀፍ ደረጃውን የጠበቀ ቤተ መጽሐፍት በመገንባት እርሳቸው የጻፏቸውን የተለያዩ መጽሐፍትና የተሰሩጥናታዊ ፊልሞች እንዲገኙበት ይደረጋል፡፡
በህዝቦችና በአገራት መካከል የመግባባት የመተባበር መንፈስ እንዲዳብር በተለያዩ መንገዶች ትምህርት መስጠትና በኢኮኖሚያዊ ፣ ማህበራዊ ፣ዴሞክራሲያዊ እና በሰላም አስተሳሰብ ምርምር ለሚያደርጉ ሁሉ አስፈላጊ ሁኔታዎቸን ማመቻቸት ሌላው የፋውንዴሽኑ ተግባር እንደሚሆንይጠበቃል፡፡
በችግር ምክንያት ትምህርታቸውን መከታተል ለማይችሉ ዜጎች በተለይም ለሴቶች የነጻ ትምህርት ዕድል ለመስጠትና የአረንጓዴ ልማትአስተሳሰብ ማስፋፋት መተግበርና መደገፍ የፋውንዴሽኑ ዋና ዋና ተግባራት እንደሚሆኑ በውይይቱ ላይ መገለፁን ኢዜአ ዘግቧል
No comments:
Post a Comment