አቶ ሰዉነት ቢሻዉ እንዳሉት በዉስጥ ቲሸርት 5 ተጫወች የያዙአቸዉን የመለስ ዜናዊን ፎቶወች ባለማሳየታቸዉ ቢያዝኑም በቡርኪናፋሶ የገቡብንን ፬ ግቦች መታሰቢያነታቸዉ በየመንደሩ የነበሩንን ኳስ ሜዳወች ወደቤት መስሪያነት ለቸበቸቡአቸዉ ባለራእይ መሪ መለስ ዜናዊ እንዲሆን ጠይቀዋል ᎓᎓
የብስጭቱ ዝርዝር ቀጥሎ ይቀርባል፤
ጨዋታው እንደተጀመረ በጥቂት ደቂቃዎች ውስጥ ቁጭ ብድግ የሚያሰኝ ማራኪ ጨዋታዎችን አድርጎ የነበረው ብሄራዊ ቡድናችን በሽመልስ አማካይነት የተሞከረችው የጎል አጋጣሚ ለጥቂት በጣም ለጥቂት በግቡ ቋሚ አማካይነት መከነች። እንዴት ነው ነገሩ የግቡ ቋሚ የቡርኪናፋሶ ረዳት በረኛ ነው እንዴ ብለን በጣም ተበሳጨን! እርርር..ም አልን።
እያለ እያለ አንድ ጎል ገባብን አንድ የቡርኪናፋሶ ተጫዋች ኦፍሳይት ክልል ውስጥ ነበር። ምናልባት እርሱ አዘናግቷቸው ይሆን…? ብለን አሁንም ተበሳጨን። ትንሽ ቆይቶ አሉን ከምንላቸው ተጨዋቾች ውስጥ አዳነ ግርማ ከአንዱ የቡርኪናፋሶ ተጫዋች ጋር ተጋጭቶ ሲወድቅ አየነው። ሲገጭ ያየነው እግሩ አካባቢ ነው። አዳነ ግን የያዘው ብሽሽቱን ነበር። እንዴት ነው ነገሩ ሰዎቹ እግር ገጭተው ብሽሽት የሚያሳምሙት…? የአዴ ስልት ነው… ወይስ ህመም በእግር “ሜሴጅ” ያደርጋሉ። ብለን እየተጨነቅን ሳለ አዴ ህመሙ በረታበትና ከሜዳ ወጣ። ኤርሚ እንደዘገበልን፤ አዳነ የታመመው እግሩን ከተገቢው በላይ ከፍ በማድረጉ አማካይነት የሚመጣ የጡንቻ መሳሳብ ነው። ይህ ህመም ለሚቀጥሉት አስር ቀናት ከሜዳ ያርቃል። ተበሳጨን አይገልፀውም፤ “ኦ…. ብስጭት ሆይ እንዲህ ደጋግመሽ የምትጎበኝን አንቺ የቤተሰባችን አባል ነሽን!?” አልን።
ከዛ በኋላማ አዳነ አለቀሰ ተመልካቹ አለቀሰ ጎሉም አልቀነሰ። እየወሰዱ ብቻ ጎል…! አረ የከልካይ ያለ። አረ የተከላካይ ያለ! ያ “አጭበርባሪ” በረኛቸው በቀይ ሲወጣ “ችርስ” ብለን እጃችንን አጋጭተን የነበርን ሁላ ዝም ብሎ ብቻ ጎል ሲቆጠርብን፤ መቁጠሩ ደከመንና “የወጣው በረኛ የእኛ ነው እንዴ!” ብለን አሁንም ተበሳጨን ተበሳጨን ተበሳጨን።
እንሆ ብዙ ተስፋ ያደረግነው ጨዋታ አራት ለምንም በሆነ በጣም የሚያበሳጭ ውጤት ተደመደመ። ያለቀሰ ሰውም በረከተ።
መልካም ጨዋታ!!!
No comments:
Post a Comment